No summary available.
ጥር 26 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው መንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ኤ.ሲ.ዱ.አይ/ቮካ- ኢትዮጵያ - ስራጅ ዓብደላ/ጠበቃ/ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የተነሣውን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት በአፊር ብ/ክ/መንግስት በደብቲ ወረዲ ፍ/ቤት ከሣሾች የነበሩት ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱትም ሳይከፈል ቀርቶአል ያለትን የበረሃ አበል እንዱከፈላቸው ነው። የወረዲው ፍ/ቤት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ፣ተጠሪዎች በጠየቁት መሰረት የበረሃ አበል እንዱከፈላቸው ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለክልለ የዞን አንድ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶአል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በወረዲው ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ ሽሮአል። ከመዝገቡ እንደሚታየው የከፍተኛው ፍ/ቤት በወረዲው ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ የሚሽር ውሳኔ የሰጠው ጥር 20 ቀን 2000 ዓ.ም በነበረው ችልት ሲሆን፣በልላ በኩል ደግሞ መጋቢት 15 ቀን 2000 ዓ.ም መዝገቡን በማስቀረብ ላላ ትእዛዝ ሰጥቶአል። ትእዛዙም እንዲየነው “….ቀደም ሲል የተሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ የቀድሞ ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ግ ቁ. 208 አስተካክለናል። ተጠሪዎች ጉዲያቸውን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 142/1/ መሰረት ለአስማሚ እንዱያቀርቡ ብለናል። የሚል ይዘት ያለው ነው። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሚያዝያ 17 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የከፍተኛው ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት የተደረገ እርማት ነው፤ በሚል የሰጠውን ትእዛዝ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት በሕጉ መሰረት ሉከፈለን ሲገባ ሳይከፈለን ቀርቶአል ያለትን የበረሐ አበል እንዱከፈላቸው ሲሆን፣የወረዲው ፍ/ቤትም ሉከፈል አይገባም በማለት ከአመልካች የቀረበውን የመከላከያ ክርክር ባለመቀበል የተጠየቀው የበረሐ አበል መጠኑን ጭምር በመግለጽ እንዱከፈል ወስኖአል። አመልካች ለከፍተኛው ፍ/ቤት በይግባኝ ያቀረበውም አበለ እንዱከፈል መወሰኑ ትክክል አይደለም በማለት ነው። ከዚህ የተነሣም የከፍተኛው ፍ/ቤት አበለ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የተጠየቀው አበል አይከፈልም በማለት ግልጽ የሆነ ውሳኔ ሰጥቶአል። በወረዲው ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔም ሙለ በሙለ ሽሮአል።
የክርክሩ መነሻ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይ የስራ ክርክር ሲሆን፣የሚመራውም በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕጉ እና አግባብ ባላቸው የአዋጁ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። በአዋጅ አንቀጽ 138 እንደተመለከተው በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የስራ ክርክር ችልት የተጀመረ የስራ ክርክር ውሳኔ ካገኘ በኋላ በይግባኝ የሚታየው በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የስራ ክርክር ችልት ነው(የአዋጁ አንቀጽ 139) በመደበኛው የስራ ክርክር ሂደትም ይግባኝ ሰሚው የስራ ክርክር ችልት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው የሚሆነው። ይህ ችልት በሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ያለው ተከራካሪ ወገን ከዚህ በኋላ አቤቱታውን ሉያቀርብ የሚችለው ለሰበር ችልት ነው። ከዚህ ውጪ በሆነ ሁኔታም ውሳኔው ሉለወጥ ወይም ሉሻሻል አይችልም። ይህ እንግዱህ አጠቃላይ ሂደቱ(ስርአቱ) ሲሆን፣ውሳኔውን በመቃወም ወደ በላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ለማለት ወይም አቤቱታ ለማቅረብ የሚፈልግ ተከራካራ ወገን ውሳኔውን በሰጠው ፍ/ቤት ሉታረም የሚገባ ወይም የሚችል ስህተት አለ ብል ካመነ ወደ በላይ ፍ/ቤት አቤት ከማለቱ በፉት ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት አቤቱታ የሚያቀርብበት ስርአት እንዲለም ይታወቃል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 ጥያቄ የሚነሳውም እዚህ ላይ ነው።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 208 ርእሱ እንደሚያመለክተው “ስህተትን ስለማረም” በሚል የተደነገገ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አቤቱታ የቀረበለት ፍ/ቤት (ውሳኔውን የሰጠው) ሉያርም ወይም ሉያስተካከል የሚችለው በሰጠው ውሳኔና ትእዛዝ ላይ የአፃፃፍ ስህተት፣የቁጥር አፃፃፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት መኖሩን ካረጋገጠ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ግልጽ ነው። በክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ ላይ አከራክሮ የሰጠውን ውሳኔ ስህተትን ማረም በሚል ሉያሻሽል ወይም ሉለውጥ አይችልም። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠበት ክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ ተጠሪዎች የጠየቁት የአበል ክፍያ ተገቢነት ያለው ነው ወይስ አይደለም የሚል ነው።
ይህም ፍ/ቤቱ ከመረመረው በኋላ ጥያቄው ተገቢነት የለውም የሚል ውሳኔ ሰጥቶበታል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 የተመለተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ በኋላ የሰጠው ትእዛዝ ግን ከጉዲዩ ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም።
ከተጠቀሰው ቁ. 208 ድንጋጌም ጋር የሚገናኝ አይደለም። ፍ/ቤቱ ከመጀመሪያውኑ ሉያስተናግደው የሚገባ አልነበረም።
ስለዚህም በዚህ ረገድ የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ እግኝተነዋል።
No topics extracted.