No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 14 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደል ቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ህጽአት ፍስሐጽዬን - ከጠበቃ ይርጉ ሰንበቱ ጋር ቀረቡ።
ተጠሪ፡- 1ኛ ወ/ሮ አልማዝ ተረፈ - አልቀረቡም 2ኛ በአ.አ ከተማ መስተዲደር ዞን 04 ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ሣሙኤል ድጉማ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት የቀረበው በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ሐምል 12 ቀን 1998 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ የካቲት 02 ቀን 1999 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኗ አመልካች ከሣሽ የአሁኑ ተጠሪዎች ደግሞ እንደቅደምተከተላቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሽ ነበሩ የስር ከሣሽ ግንቦት 22 ቀን 1994 ዓ.ም አሻሽለው ባቀረቡት ክስ በአ.አ ከተማ ወረዲ 16 ቀበላ 03 ክልል ውስጥ ቁጥሩ 314 የሆነውን ቤት ለአንደኛ ተጠሪ ከታህሳስ 23 ቀን 1991 ዓ.ም ጀምሮ ማከራየታቸውን ገልፀው ተጠሪ ያለባቸውን የቤት ኪራይ ከፍለው ቤቱን እንደነበረ አድርገው ለአመልካች እንዱያስረክቡ ሁለተኛ ተከሣሽም ቤቱን ያላግባብ አንደኛ ተከሣሽ በብር 355,000.00 /ሦስት መቶ አምሣ አምስት ሺህ ብር/ ሽጦ በመገኘቱ ከነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን የሚሰጠውን የአገልግልት ኪራይ ከአንደኛ ተከሣሽ ጋር ባልተነጣጠለ ሁኔታ እንዱከፍልና ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቡ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል የአሁኑ አንደኛ ተጠሪም በክሡ ገንዘብ ሙለ በሙለ የዲኝነት ገንዘብ አለመከፈለን የቤት ኪራይ ገንዘብ በክፍያ ግምት የሚታገድ መሆኑንና አመልካች ኢትዩጵያዊ ስላልሆኑ የማይንቀሳቅስ ንብረት ባለቤት መሆን የማይችለና ክስ ለማቅረብም መብትና ጥቅም የላላቸው መሆኑን በመዘርዘር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አቅርበው በፍሬ ነገር ረገድም የቤት ኪራይ ውለ በውለ መሰረት እንዱራዘም አለመደረጉን ቤቱን ለመረከብ የቀረበ ሰው ካለመኖሩም በላይ የቤቱ ባለቤት የሆኑት ግለሰብ በሞት የተለዩ እና ባለቤት ነኝ የሚለት አመልካችም አሜሪካን ሀገር የሚኖሩ በመሆኑ የሚረከብ ሰው ያላገኙ መሆኑን ቀበላ መጥቶ የቤቱን ባለቤት እንዱናገሩ ጠይቋቸውም ከአገር እንደወጡ የተደረገ መሆኑን ገልፀውላቸው ቤቱ ለሽያጭ በጨረታ በመቅረቡ ተጫርተው ነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈ ውል ከአስተዲደር ጽ/ቤቱ መግዛታቸውን ጠቅሰው በግዥ ያገኙትን ቤት የሚመልሱበት ምክንያት የለም ሲለ ተከራክረዋል።
የአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ስም የሚታወቅና አመልካች መብት የላላቸው መሆኑን በመጥቀስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ቤቱን በመንግስት በወጣው መመሪያ መሰረት መሸጡን እና የሽያጭ ገንዘቡን በዝግ አካውንት ማስቀመጡን በመግለፅ ያላግባብ የተጠቀመው ነገር በላለበት ሁኔታ ተጠያቂነት የለም ሲል ተከራክሯል ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የሽያጭ ውለ ህገ ወጥ ነው በማለት ተከሣሾች ቤቱን እንዱያስረክቡ ከ28/12/93 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የቤቱን ኪራይ ባልተነጣጠለ ኃላፉነት እንዱከፍለ እና ወጭና ኪሣራን በተመለከተ የአመልካችን ዝርዝር የማቅረብ መብት በመጠበቅ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ ተጠሪዎች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን በተናጠል ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅረበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የይግባኝ መዝገቦችን አንድ ላይ አጣምሮ በመመርመር አመልካች በቤቱ ላይ መብት ያላቸው መሆኑን አላስረደም፣ የኪራይ ገንዘቡም በጊዜ ማለፍ እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው የሚለ ምክንያቶችን በመዘርዘር የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ከሻረ በኋላ ህጋዊ መብት አለኝ የሚል ሰው ካለ በህጉ አግባብ ክስ ከማቅረብ ውሣኔው የማያግደው መሆኑን በመግለፅ ወስኗል የአሁኑ የሰበር አቤቱታ አቅራቢውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሚያዚያ 02 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት 7 /ሰባት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ በፍ/ቤቶቹ ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ አመልካች የሟች ሚስት መሆኔን በመ/ቁ 79/83 አሣውቄና ማስረጃ ለፍ/ቤት ቀርቦ እያለ አለመታየቱ ያላግባብ መሆኑ ቤቱ በባል ስም ብቻ መመዝገቡም አመልካችን መብት የላቸውም ለማለት የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ የማያስችል መሆኑን የቤት ኪራዩን በተመለከተም ውሣኔው የፍ/ብ/ህ/ቁ 2968 ድንጋጌን መንፈስ አለማገናዘቡንና የኪራይ ገንዘቡ እንደተከፈለ ይቆጠራል መባለ ያላግባብ መሆኑን ዘርዝረው ውሣኔው እንዱሻርላቸው ዲኘነት መጠያቃቸውን የሚያሣይ ነው የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተጠሪዎች ቀርበው መልሣቸውን ሰጥተዋል። አንደኛ ተጠሪ ሰኔ 13 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ የአመልካች በመ/ቁ 79/83 ተሰጠ የሚለትን ማስረጃ በስር ፍርድ ቤት ያላቀረቡት መሆኑን ፣ ስለኤርትራዊ መሆንና አለመሆን ሲከራከሩም ኤርትራዊ አይደለሁም ሣይለ በትውልድ ኤርትራዊ ብሆንም የወጣሁት በፖለቲካ አይደለም ብለው መከራከራቸውን፣ የኪራይ ውለ ስላልተራዘመ ውል አለ ልባል እንደማይችልና የክፍያ ግዳታ አለመኖሩን፣ ቤቱን በግዥ ምክንያት በመያዛቸውም የኪራይ መክፈል ግዳታ እንዳላለባቸውና የሽያጭ ውለ ይፍረስልኝ ጥያቄ ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመዘርዘር የሰበር አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል ሁለተኛ ተጠሪ በበኩለ ሰኔ 12 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ ማመልከቻ አመልካች በስር ፍ/ቤት የሟች ብርጋዳ ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ሚስት ስለመሆናቸውም ሆነ ልጆቻቸውም ወራሽ ለመሆናቸው አረጋግጠው ማስረጃቸውን ከክስ አቤቱታቸው ጋር አያይዘው አለማቅረባቸውን፣ በቤቱ ላይ መብት ያላቸው መሆኑን ያላስረደ መሆኑን አመልካች በስር ፍርድ ቤት ኢትዩጵያዊ ለመሆናቸው ያቀረቡት አንዲችም ክርክር አለመኖሩ የኪራይ ውለ የውለ ጊዜ ካለቀ በኋላ የኪራይ ገንዘብን ተጠሪ የሚከፍልበት ምክንያት አለመኖሩን ዘርዝሮ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ ባግባቡ በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ተጠሪዎች በሰጡት መልስ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር ግራ ቀኙ ለማጣሪያ ጥያቄ የሰጡትን መልስ የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል እንደመረመረውም ለክርክሩ መነሻ በሆነው ቤት አመልካች ክስ ለማቅረብ ህጉን መሰረት ያደረገ ጥቅም ወይም መብት የላቸውም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኗ አመልካች በተወካያቸው አማካኝነት ክስ ሲመሰርቱ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ንብረታቸው መሆኑን መጥቀሣቸውን የአሁኑ ተጠሪዎች ባቀረቡት መከላከያ መልስ አመልካች በቤቱ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት መከራከራቸውን አመልካችም በተጠሪዎች በኩል ለቀረበው ለዚሁ ክርክር በሰጡት የመልስ መልስ አመልካች ከእነልጆቻቸው የብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ሚስትነትና የልጆቹን ወራሽነት በፍርድ ቤት በሥ/ፍ/መ/ቁ 79/83 ጥቅምት 10 ቀን 1984 ማስወሰናቸውንና ውሣኔው በእጃቸው የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው መከራከራቸውን የስር ፍ/ቤትም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የአመልካች መሆኑን አንደኛ ተጠሪ አምኖ በመቀበል መከራየታቸውን የኪራይ ውለና በሥ/ፍ/መ/ቁ 79/83 መወሰኑ በቀረበው ክስና ክርክር አመልካች ማስረዲታቸውን በመግለፅ አመልካች ባቀረቡት ክስ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን አስረድተዋል እንዱሁም ተጠሪዎች በቤቱ የተሻለ ማስረጃ አቅርበው አላስረደም በሚል ምክንያት አመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም የሚለውን የተጠሪዎችን መቃወሚያ ውድቅ ማድረጉን የአሁኑ ተጠሪዎች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ የቅሬታ ነጥቦች ከሆኑት ውስጥ በተጠሪዎች በኩል የቀረበው መቃወሚያ መታለፍ ያላግባብ መሆኑ አንደ እንደነበርና ይህንኑ ነጥብ በተመለከተም ከፍተኛው ፍ/ቤት በጭብጥነት ይዞ ከመረመረው በኋላ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ ያላግባብ መሆኑን ጠቅሶ አመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት መወሰኑን ነው ። የአሁኑ ተጠሪዎች አመልካች በሥ/ፍ/መ/ቁ 79/83 በፍ/ቤት የተረጋገጠ ማስረጃ አለ የሚለት በክርክሩ ሂደት ተያይዞ ያልቀረበ እና የማያውቁት መሆኑን ለዚህ ችልት በሰጡት መልስ ገልፀው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ሉፀና ይገባል በማለት የሚከራከሩ መሆኑንም ተረድተናል። በአጠቃላይ የክርክሩ ሂደት የሚያሣየው አመልካች የሟች ብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ሚስትነትን እና የልጆቻቸው ወራሽነት በፍ/ቤት ውሣኔ አረጋግጫለሁ የሚለት ሰነድ በስር ፍርድ ቤት ስለመኖሩ ከመጠቆሙ ውጪ የአመልካች ክስ አባሪ ሆኖ ቀርቦ ተጠሪዎች ይዘቱን በመመልከት ያልተከራከሩበት የስር ፍ/ቤትም ቢሆን አመልካች ባቀረቡት ክስና ክርክር አስረድተዋል ከማለት ውጪ ራሡ የሰነደን ይዘት በመመልከት ማረጋገጡን በውሣኔው ላይ ያልጠቀሰ መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል።
በመሰረቱ ከሣሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሰረት አዘጋጅቶ ከሚያቀረበው የክስ ማመልከቻ ጋር በክሱ መሰማት ወቅት ለጉዲዩ ማስረጃ ይሆኑኛል የሚሎቸውን የሰውም ሆነ የጽሁፍ ማስረጃዎችን ዝርዝርና ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጮቻቸውን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 ድንጋጌ ያሣያል በተለይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 137/3/ የሰነድ ማስረጃዎችን በተመለከተ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ከአቤቱታው ጋር በማያያዝ ወይም ከቀነ ቀጠሮ በፉት ወይም በመጀመሪያው ቀን ቀጠሮ ካልቀረበ በቀር ማስረጃው ላቀርብ ወይም ይቅረብልኝ ተብል ሉጠየቅ እንደማይችል ተመልክቷል። ይሄው ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኘው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 256 ስር በተመለከተው አኳኋን ማስረጃዎቹ ሣያቀርቡት የቀሩት ከባድና በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ፍ/ቤቱ ሲረዲ ብቻ ነው።
የማስረጃ አቀራረብን በተመለከተ በሥነ ሥርዓት ህጉ የተመለከተው ላላው ደንብ የይግባኝ ሰሚውን ፍ/ቤት ሥልጣን የሚመለከት ነው በዚህም መሰረት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 345 ድንጋጌ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በራሡ አስተያየት ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው ማናቸውም ዓይነት ሰነድ ወይም ምስክር ወይም ላላ ዓይነት ማስረጃ በተጨማሪነት እንዱቀርብለት የማዘዝ ህጋዊ ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ ያሣያል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 145 /1/ ድንጋጌም በልላ ፍ/ቤት የሚገኝ ሰነድ የፁሁፍ ማስረጃ ወይም ፍርድ የተሰጠበት መዝገብ ለውሣኔው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍ/ቤቱ በራሡ አነሣሽነትም ሆነ በተከራካሪዎቹ ጠያቂነት እንዱቀርብለት ማዘዝ የሚችል ስለመሆኑ ያስረዲል።
ከላይ እንደተገለፀው ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት ውሣኔ የሰጠው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ሚስትነታቸውን በሥ/ፍ/መ/ቁ 79/83 አረጋግጠዋል በማለት በውሣኔው ላይ የገለፀው ሁኔታ በውሣኔው ግልባጭ መኖሩን እየተመለከተ ነው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልትም በዚህ ረገድ ቅሬታው ቀርቦለታል። እንዱህ ከሆነ በአመልካች የተጠቀሰው የፍ/ቤት መዝገብ ከሚገኝበት ፍ/ቤት በየደረጃው ጉዲዩን ባዩት ፍ/ቤቶች አነሣሽነት ጭምር ላቀርብና ተጠሪዎች በሰነደ ይዘት የሚያቀርቡት ክርክር ከታየ በኋላ ውሣኔ መስጠት በተገባ ነበር ይሁን እንጂ የስር ፍርድ ቤት ሰነደ ሣይቀርብለት እና ለተጠሪዎች ሣይደርስ ሰነደ መኖሩን ማመኑ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶችም የአመልካችን መብትና ጥቅም ያረጋግጣል የተባለው የፍ/ቤት መዝገብ በስር ፍርድ ቤት የውሣኔው ግልባጭ ተገልጾ እያለ መዝገቡ ከሚገኝበት ፍ/ቤት በህጉ በተሰጣቸው ሥልጣን መሰረት እንዱቀረብ ሣያደርጉ የአመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት መወሰናቸው የክርክሩን አመራር ከላይ በተመለከቱት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ የማስረጃ አቀራረብ ደንቦች መሰረት አለመምራታቸውንና በውጤቱም በቤተሰብ ህጉ የተመለከቱትን የአመልካችን መብቶች የጎዲ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ ውሣኔ የሰጡት የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ድንጋጌዎች በማይደግፈትና የፍርድ አካሄደ ባልተሟላ ሁኔታ በመሆኑ በየርከኑ ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ እና ትዕዛዝ ሙለ በሙለ ሉሻሩ የሚገባና የስር ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ሁለንም መከራከሪያ ነጥቦችን እና ስለመኖሩ የተጠቆመውን የፍ/ቤት መዝገብ ሰነድ በማስቀረብ ተመልክቶ በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥ ማድረጉ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ የካቲት 02 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ሐምል 12 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ ታህሣስ 28 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
2/ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች በሥ/ፍ/መ/ቁ 79/83 አለ ያለትን የሚስትነትና የልጆቻቸውን ወራሽነት ማስረጃ በማስቀረብና ተገቢውን በመፈፀም እንዱሁም ተገቢነት አላቸው የሚሎቸውን ማስረጃዎችን ሁለ በማስቀረብ በግራ ቀኙ ሁለም የመከራከሪያ ነጥቦች እንደገና ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት ተመልሶለታል ይፃፍ።
3/ በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።