No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 375ዐ2 ታህሣሥ 2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ ከተማ አስተዲደር ፍትህና ሕግ ጉዲዮች ቢሮ - ነ/ፈጅ ታረቀኝ ሞላ ቀርበዋል።
ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ የኋላሸት ገመዲ ቤኛ - ቀርበዋል።
ወ/ሮ ጌጤ ገመዲ ቤኛ - ወኪል ቀርበዋል።
ጉዲዩን በመመርመር የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻው አመልካች ግንቦት ዐ1/2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ አቤቱታው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 4493ዐ መጋቢት 15/2ዐዐዐ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 66633 ሚያዝያ 3ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጡት ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው ናቸው በማለት እንዱሻሩለት በመጠየቁ ነው።
የአሁኑ አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት በክርክር ጣልቃ ለመግባት ተቃዋሚ የነበር፣ በከፍተኛ ፍ/ቤቱ ደግሞ ይግባኝ ባይ ሆኖ የተከራከረ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎችም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሾች በከፍተኛ ፍ/ቤቱ ደግሞ መልስ ሰጭዎች በመሆን ተከራክረዋል።
በስር ፍ/ቤት ለቀረበው ክርክር መነሻው የአሁኑ አመልካች ኀዲር ዐ9/2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ያቀረበው መቃወሚያ ሲሆን ይዘቱም የስር ፍ/ቤቱ ጥቅምት 29/1999 ዓ.ም. በሰጠው ፍርድ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12፣ የቤት ቁጥር 486 የሆነውን ቤት ስር ከሣሾች የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ከሥር ተከሣሾች ከነበሩት /የቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 12 አስ/ጽ/ቤት እና አቶ ለአዚም በደዊ/ እንዱረከቡት መወሰኑ ባለ ንብረት የሆንኩት በክርክሩ ባልተሳፍኩበት በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.
358፣ 36ዐ መሰረት ጣልቃ አስገብቶ በማከራከር ቀደም ብል የተሰጠውን ፍርድ ውድቅ ያደርግልኝ የሚል ነው።
ከላይ ለቀረበው ጥያቄ ስር ከሣሾች የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ታህሣሥ 24/2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጡት መልስ የመቃወም አመልካቹና ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ጽ/ቤት አንድ አካልና ተመሣሣይ ክርክር ያላቸው ስለሆኑ አመልካቹ በመጀመሪያው ክርክር እንደተሳተፈ ስለሚቆጠር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
358/36ዐ መሰረት ያቀረበው ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በኮ/መ/ቁ. 4493ዐ መጋቢት 15/2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ብይን የመቃወም አመልካቹና ቀደም ብል ማለትም ጥቅምት 29/1999 ዓ.ም. በተሰጠው ፍርድ ውስጥ አንደኛ ተከሣሽ የነበረው የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ጽ/ቤት አንድ አካልና ተመሣሣይ ክርክር ያላቸው በመሆናቸው የመቃወም አመልካቹ በመጀመሪያው ክርክር እንዲልተሳተፈ ስለማይቆጠር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358/36ዐ መሰረት ያቀረበው ጣልቃ የመግባት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብሎል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩ በይግባኝ ቀርቦለት በመ/ቁ. 66633 ሚያዝያ 3ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ትእዛዝ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
ከላይ የሰፈሩትን የስር ፍ/ቤቶቹ ብይኖች በመቃወም የአሁኑ አመልካች ግንቦት ዐ1/2ዐዐዐ ዓ.ም. የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት ያቀረበ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም አከራካሪው ቤት መንግሥት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ወርሶ የሚያስተዲድረው ሃብት ሲሆን ለተጠሪዎቹ የተወሰነላቸው አላግባብና አመልካች በክርክሩ ሳይሳተፍ ነው፤
አመልካችና ስር አንደኛ ተከሣሽ የነበረው የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ጽ/ቤት የየራሳቸውን ህጋዊ ሰውነት ያላቸው የተለያዩ አካላት እንጂ አንድ አይነት ባለመሆናቸው የስር ፍ/ቤቶቹ በክርክሩ ጣልቃ ገብቼ እንዲልከራከር ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ብሎል።
ተጠሪዎችም ሐምል 17/2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ መልስ የሰጡ ሲሆን ይዘቱም አመልካችና ቀደም ብል የሥር ፍ/ቤቱ አንደኛ ተከሣሽ የነበረው የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 361/1995 /የተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር/ አንቀጽ 2 መሰረት የከተማው አስተዲደር የተለያዩ እርከኖች ስለሆኑ ክርክራቸው ተመሣሣይ እንጂ የሚለያይ ባለመሆኑና የአመልካችና የቀበላው ስልጣን የሚመነጨው ከከተማው አስተዲደር ነው፤ አመልካች የከተማው አስተዲደር አንድ የሥራ ክፍል እንጂ ራሱን የቻለ አካል ባለመሆኑ ቀበላው ቀደም ብል ተከራክሮበት የተወሰነው ጉዲይም የከተማው አስተዲደር ክርክር ተደርጎ መወሰድ ስላለበት የአመልካች ጥያቄ ተገቢነት የለውም። የስር ፍ/ቤቶቹ የፈፀሙት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም የሚል ነው።
አመልካችም መስከረም 29/2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ የመልስ መልስ የሰጠ ሲሆን አጭር ይዘቱም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 2/1995 አንቀጽ 29 እና እንደገና በተሻሻለው የከተማው አዋጅ ቁጥር 4/2ዐዐዐ /የአዱስ አበባ አስተዲደር የአስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ/ መሰረት የተቋቋመ ሲሆን የቀበላ አስተዲደር አካላት የተቋቋሙት ደግሞ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ክፍለ ከተሞችና ቀበላዎች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1/1995 እንዱሁም የዚሁ አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 18/1997 መሰረት የተቋቋሙና የየራሳቸው ሕጋዊ ሰውነት፣ ስልጣንና ተግባር ያላቸው አካላት ናቸው የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ እንደሰፈረው ሆኖ ይህ ፍ/ቤትም አመልካችና የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ጽ/ቤት አንድ አካል ናቸው ወይስ አይደለም? የሁለቱ አካላት ክርክር ተመሣሣይ ላሆን ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለ ጭብጦችን በመመስረት ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት መረዲት እንደተቻለው አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲይከራከር በስር ፍርድ ቤቱ የተከላከለው ቀደም ብል በክርክሩ ተሳትፍ የተወሰነበት የተጠቀሰው ቀበላ ካቀረበው ክርክር ተመሳሳይ ክርክር የሚያቀርብና በመሰረቱ አንድ አካል ናቸው በሚል ነው። በርግጥ እነዚህ ሁለት አካላት በአንድ መንግስታዊ መዋቅር /በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር/ ስር የሚገኙ አካላት ናቸው። ይሁን እንጂ በአንድ የክልል ወይም የከተማ መንግሥታዊ መዋቅር ስር መገኘታቸው ብቻ አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ተመሣሣይ ጥቅምን የሚወክለ አካላት ናቸው ወደሚል መደምደሚያ የሚደርስ አይደለም፤ እነዚህ ሁለት አካላት የከተማ መስተዲድሩ የተለያዩ እርከኖች ወይም አካላት ሆነው የየራሳቸው ሕጋዊ ሰውነት፣ ስልጣንና ተግባር እንዲላቸው በአዱስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከወጡት አዋጅ ቁጥሮች 2/1995፣ 4/2ዐዐዐ፣ 1/1995 እና 18/1997 መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ቀበላውና አመልካች አንድ አካል ናቸው በመባል በሥር ፍ/ቤቶቹ የተሰጠው ብይን ተገቢነት የላለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው።
ቀበላው በክርክሩ ቀደም ብል ከቀረበው ክርክር አመልካቹ የተለየ ላላ ክርክር ሉያቀረብ አይችልም የተባለውም ቢሆን ክርክራቸው ተመሣሣይና አንድ አይነት ጥቅም የሚወክል መሆኑና አለመሆኑ የሚታወቀው አመልካቹ በክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ የሚያቀርበውን የክርክር አይነትና የሚወክለውን ጥቅም ቀበላው አቅርቦት ከነበረው በማነፃፀር የሚታወቅ እንጂ አስቀድሞ ተመሣሣይ ክርክር አለው የሚል ግምት በመያዝ አይደለም፤ ከዚህ ትንታኔ አኳያም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 4493ዐ መጋቢት 15/2ዐዐዐ ዓ.ም. እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 66633 ሚያዝያ 3ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጡት ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል፤ ይፃፍ።
አመልካችና የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 29/1999 ዓ.ም. በሰጠው ፍርድ አንደኛ ተከሣሽ የነበረው የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ጽ/ቤት በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ስር የሚገኙ የየራሳቸው ሕጋዊ ሰውነት፣ ስልጣንና ተግባር ያላቸው የተለያዩ አካላት በመሆናቸው አመልካቹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ ይከራከር፤ ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ፤ ክርክሩ ያለቀ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ት እ ዛ ዝ ግንቦት ዐ4/2ዐዐዐ ዓ.ም. በዚህ ችልት የተሰጠው እግድ ተነስቷል፤ ይፃፍ።
No topics extracted.