No summary available.
ታህሣሥ 7 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ጏንፊ ኦሪቲ ቀርቧል ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፀሐይ ሉበን የሺጥላ አለሙ ጠበቃ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ተወስኗል።
ጉዲዩ የተመረመው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የስር ጣልቃገብ አመልካች ሲሆኑ ተጠሪ የስር ከሳሽ ነበሩ። ጣልቃ ገብ አመልካች በአሁን ተጠሪ ላይ ባቀረቡት መቃወሚያ ተጠሪ ከሟች ጋር አብሬ ያፈራሁትን ቁጥሩ 373 የሆነውን ቤት ተከሣሾች ያካፍለኝ ሲለ ክስ ያቀረቡት እኔ በጣልቃ ገብ አመልካች (የአሁን አመልካች) ከሟች ባለቤቴ ከነበሩት አቶ ታምሩ አሸናፉ ጋር በባልና ሚስት የጋራ ንብረት በመሆኑና በመሐከላችን በተነሳው ያለመግባባት በፍ/ቤት ውሣኔ ስንለያይ ንብረቱ የጋራችን በመባለ እኔ ለልጆቼ ስል ሳልካፈል ትቻለው(አልወሰድኩም) ነበር። ስለዚህ በመብቴ ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ጣልቃ እንድገባ በማለት እንዱፈቀድላቸው ጠይቋል።
የመጀመሪያ ደ/ፍ/ቤትም መዝገቡን በመመርመር በሰጠው ብይን የአሁን አመልካች የጣልቃ ልግባ አቤቱታቸው ላይ መሰረት ያደረጉት የሟች አቶ ታምሩ አሸናፉ ሚስት መሆናቸውን እና ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ክስ ያነሱበት ቤት ከሟች ጋር አብረን ሰርተናል በማለት ነው። ይህ የጣልቃ ልግባ ምክንያት ደግሞ አመልካችን ጨምሮ(የስር ጣልቃ ልግባ ባይን) የአሁን ተጠሪና የሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ክርክር ባነሱበት የመ/ቁ. 0057 ላይ የውርስ ንብረት አጣሪ ተሹሞ ሪፖርቱ የፀደቀበት ክርክር ነው ጣልቃ ልግባ ባይ በዚህ የጣልቃ ልግባ አቤቱታቸው በውርስ ንብረት አጣሪ ሪፖርት መሰረት ክርክር በተነሳበት የቤት ቁ. 373 ላይ ድርሻ አለኝ የሚል የጣልቃ ልግባ ምክንያት አላቀረቡም ይህ ከሆነ ደግሞ ከሣሽ ተጠሪ በውርስ አጣሪው ሪፖርት መሰረት በቤት ቁጥር 373 ላይ ክፍፍል ተደርጏ ድርሻዬ ይሰጠኝ ሲለ ክስ ባቀረቡበት መዝገብ ላይ ጣልቃ ልግባ ባይ (አሁን አመልካች) በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 41/2/ መሰረት የጣልቃ ገብነታቸውን ማመልከቻ በክሱ ውስጥ ይገባኛል የሚለበትን ምክንያት ሳይዘረዝሩና ሳይገልጹ ጣልቃ ልግባ ያለት ጥያቄ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም ሲል ወስኗል።
ይግባኝ ባይ(የአሁን አመልካች) በፍ/ቤቱ በተሰጠው ብይን ባለመስማማት ለፋደራል ከ/ፍ/ቤት ይግባኛቸውን አቅርቧል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የተሰጠውን ብይን ጉድለት የለበትም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው።
አመልካች ግንቦት 4 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ በፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ እና በፋ/ከ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አቤቱታ አቅርቧል።
ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል ጉዲዩ በሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ የተወሰነው አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 መሰረት ያቀረበችው የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ውድቅ የተደረገበትን እግባብነት ለመመርመር ሲባል ነው። በዚሁ መሰረት ይህን ነጥብ ግራ ቀኙ ወገኖች ከሰሙት ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እኛም የዚህን ክርክር አመጣጥ በአጭሩ ስናየው ለአመልካች የጣልቃ ልግባ ምክንያት ከሟች ባለቤታቸው (አቶ ታምሩ አሸናፉ) ጋር በሚስትነት አብረው ያፈሩአቸው የጋራ ንብረት እንደነበረና ከሟች ጋር ያለመግባባት በመፈጠሩ ምክንያት በፍ/ቤት ተፊተው ንብረቱን በተመለከተ ለልጆቻቸው ጥቅም ሲለ ሳይካፈለት እንደቆየ እና የአሁን ተጠሪ በንብረቴ ላይ ውሳኔ እንዲያሰጡብኝ በማለት ነው።
እንግዱህ ከዚህ መገንዘብ እንደቻልነው የአመልካች ጥያቄ ክርክር በተነሳበት ባለው ቤት ላይ መብት አለኝ የጋራ ንብረቴን እንደሚስትነቴ አልተካፈለም እያለ ነው አመልካች ከሟች ጋር ባልና ሚስት እንደነበሩ በፍ/ቤት እንደተፊቱ የተካደ ነገር የለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 41 መሰረት ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር ከጉዲዩ (ከክርክሩ) ጋር ተያያዝነት ባለው ጉዲይ መብትና ጥቅም እንዲለ ከተገለፀ ጣልቃ ለመግባት በቂ ምክንያት ነው በያዝነው ጉዲይም አመልካች የሟች ሚስት የነበሩ መሆናቸው ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል። ላላው የሥር ፍ/ቤት አመልካች በውርስ አጣሪው ሪፖርት ላይ ይህን ጥያቄ አላቀረቡም ብሎል ይህ ደግሞ የአመልካች በውርስ አጣሪው ሪፖርት ላይ ጥያቄ የለማቅረብ የጋራዬ ነው ባለት ንብረት ላይ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር የሚከለክላቸው አይሆንም። ምክንያቱም ባለመብትነት የሚወሰነው ወደ ክርክር ከተገባና ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት በኋላ ስለሆነ ነው።
No topics extracted.
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት አመልካች በክሱ ውስጥ ያገባኛል የሚለትን ምክንያት አልዘረዘሩም መብታቸውን አልገለፁም በማለት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉንና የከፍ/ቤቱም ይህን ማረም ሲገባው ማጽናቱ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16228 ጥቅምት 11 ቀን 2000 ዓ.የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 61828 በመጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 41 መሰረት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ጣልቃ ገብተው ይከራከሩ ብለናል። ይፃፍ።
በፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ የግራ ቀኙን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ በሕጉ መሰረት እንዱወሰን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 341 መሰረት መዝገቡን መልሰናል።
4.ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።