No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣሥ 14 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዩጵያ እህል ንግድ ድርጅት - ብርሃኑ አሻግሬ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ከድጃ ሳቢር ቀረበች ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረችው የአሁንዋ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተችው የአመልካች ሰራተኛ ለነበረው በሞት ለተለየው ባለቤትዋ ሉከፈል ይገባ ነበር ያለችውን ክፍያ እንዱከፈላት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የተጠሪ ባለቤት በሕይወት እያለ ክስ መስርቶ ከተከራከርን በኋላ በሕጉ መሰረት ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎች ሁለ ተከፍለዋል። ተጠሪ በአሁኑ ደረጃ ያቀረበችው ክስ የሚስተናገድበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክሮአል። ፍ/ቤቱም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ፣ ብዙዎች በክሱ የተመለከቱት ክፍያዎች ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ከዓመት ዔረፍት ፈቃድ ጋር ተያይዞ ያቀረበው የክፍያ ጥያቄ ግን በመቀጠል አመልካች እንዱከፈል ወስኖአል። ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም ብልአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሰኔ 17 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ ያቀረበው፤ተጠሪ ለባለቤቴ ሉከፈል ይገባው የነበር ነው በማለት ያቀረበችው የክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ነው ወይ? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ እንደተመለከተው የተጠሪ ባለቤት የነበረው መሐመድ ሁሴን ከአመልካች ጋር አድርጎት የነበረው የስራ ውል መቋረጥን መነሻ በማድረግ በአመልካች ላይ ክስ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ሞቶአል። ከዚህ የተነሣም ተጠሪ ክርክሩን ስትከታተል ቆይታለች። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር በመመርመር አመልካች የማስጠንቀቂያ እና የስራ ስንብት ክፍያዎች እንዱሁም ወጪና ኪሣራ ይከፈል ሲል ወስኖአል። ተጠሪ በስምዋ አዱስ ክስ የመሰረተችው ከዚህ በኋላ ነው። አመልካች የክሱን መቅረብ የተቃወመውም እነዚህን ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ነው ።
ከፍ ሲል እንደገለጽነው ተጠሪ በክስዋ ላይ ያመለከተችው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱሰጡአት ሲሆን፣ ከዚህም አንደ የዓመት ዔረፍት ፈቃድ የሚመለከት ነው። የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት የተቀበለውም በዚህ ረገድ የተጠየቀውን ክፍያ ብቻ ሲሆን፣ ለመቀበለ የሰጠው ምክንያትም አመልካች በማመንም ይሁን በመካድ መልስ አልሰጠበትም የሚል እንደሆነ ከውሳኔው ተመልክተናል። በበኩላችን እንደምናየው አመልካች የክሱን መቅረብ በአጠቃላይ ተቃውሞ ተከራክሮአል።
ለዚህ የሰጠው ምክንያትም የተጠሪ ባለቤት መስርቶት በነበረው ክስ ተጠቃል የተጠየቀ ወይም አንድ ላይ ሉጠየቅ ይገባው የነበረ ነው የሚል ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዚህ መልክ የቀረበውን የአመልካች ክርክር በመገንዘቡ በውሳኔው ላይ አመልክቶአል። ይህ መሰል መቃወሚያ ሲቀርብም አግባብነት ያለውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ ይሆናል።
ማንኛውም የፍትሐብሕር ክስ ሲቀርብ ስለ ክሱ አቀራረብ በተመለከተ የተቀመጡትን የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ድንጋጌዎች ሉከተል እንደሚገባ የሚያከራክር አይደለም። የተጠሪ ባለቤት አቅርቦት የነበረው ክስ ከአመልካች ላይ የሚፈለገውን መብት የሚዘረዝር እና ክሱን ለማቅረብ ምክንያት የሆኑትን ሁለ አጠቃል የያዘ እንደነበር ይገመታል። በልላ በኩል ደግሞ ክሱ የተወሰኑትን ክፍያዎች ሳያካትት ቀርቶ ነበር አልተባለም እንጂ ቢባልም ኖሮ ከፍ/ቤት የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር በልላ አዱስ ክስ ሉጠየቅ እንደማይችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.216 (4) ተመልክቷአል።ይህ ጉዲይ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 5 አንፃር ሲታይም በአዱሱ ክስ (ተጠሪ ባቀረበችው) እና ቀደም ሲል ክርክር ተደርጎበት የመጨረሻ ውሳኔ ባገኘው ክስ መካከል ልዩነት የለም። በመሆኑም ተጠሪ ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረባቸው ክስ በድጋሚ የሚታይበት የሕግ ምክንያት የለም። የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔም ከዚህ አኳያ ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ጥር 21 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 64777 ግንቦት 25 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348 (1) መሰረት ተሽሮአል።
ተጠሪ የጠየቀችው የዓመት እረፍት ፈቃድ ክፍያ እንደ ላልች ክፍያዎች ተቀባይነት የለውም። ሉከፈላት አይገባም ብለናል። መዝገቡ ይመለስ።