No summary available.
ታህሣሥ ዐ9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- ገዋኔ ኢንተርþራይዝ ኃላ.የተ.የግል ማህበር - ነ/ፈጅ ተስፊዬ ጎላ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዮሱፍ ይማም - ቀረበ - መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ውል ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰውን የጉዲት ኪሣራ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ጥር 24 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈ ውል ተጠሪ ለአመልካች የመጥረጊያ አለላ በማቅረብ ወደ ውጭ ለመላክ የገባውን ግዳታ ለመወጣት ያመቸው ዘንድ በተጠሪ እግር ተተክቶ በተጠሪ ሰራተኞች የልማቱን ስራ ለማካሄድ ብር 17ዐ,6ዐ9.14 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠኝ ብር ከአስራ አራት ሣንቲም/ ማውጣቱን፣ የተጠሪ የውሃ ንþና ትራክተሮች በዔዲ በመሬት ባለይዞታዎች በመያዛቸው ምክንያት ለዚህ ዔዲ አመልካች ብር 1ዐ3,445.8ዐ /አንድ መቶ ሦስት ሺህ አራት መቶ አርባ አምስት ብር ከሰማኒያ ሣንቲም/ ወጪ ማድረጉን፣ አመልካች ያጣው የገቢ ትርፍ ዝርዝር ድምሩ ብር 285,98ዐ.ዐዐ /ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ብር/ መሆኑን፣ ተጠሪ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ውለን በማፍረሱም የካቲት 27 ቀን 1993 ዓ.ም በተደረገው ውል መሰረት ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ አምስት ሺህ/ የገደብ መቀጫ የመክፈል ግዳታ ያለባቸው መሆኑን በመዘርዘር በአጠቃላይ ብር 471,589.14 /አራት መቶ ሰባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከአስራ አራት ሣንቲም/ ከወጪና ኪሣራ ጋር ተጠሪ እንዱከፈል ይወሰንለት ዘንድ በአፊር ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት በዞን ሦስት ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርበው ታኀሣሥ 17 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ በግራ ቀኙ ውል መኖሩን ሣይክደ በውለ አለመፈፀም ምክንያት አመልካች ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች፣ ለመሬቱ ባለይዞታዎች ተከፈለ ለተባለው ወጪም አላፉነት የላለባቸው መሆኑንና የአመልካች ማስረጃዎች አግባብነት እና ተቀባይነት የላቸውም የሚለባቸውን ምክንያቶች በመዘርዘር መልስ አቅርበዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተውን ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ተገቢ ናቸው ያላቸውን ሁለት ጭብጦችን መስርቶ የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች በኩል ወጡ ለተባለት የተለያዩ ወጪዎች አላፉነት የለባቸውም፣ የገደብ መቀጫውን ግን ተጠሪ ለውለ መፍረስ ምክንያት ነው ባይባለም ከአንዲንድ ሁኔታዎች አንፃር ሉከፍለ የሚገባ ሆኖ ተገኝተዋል በማለት ተጠሪ ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለአመልካች እንዱከፍለና የአመልካች የወጪና ኪሣራ ዝርዝር የማቅረብ መብት በመጠበቅ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኛቸውን አቅርበው ይኸው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የአሁኑ አመልካች ሕጉ ያስቀመጠውን መስፈርት ተጠቅሞ ውለን ማፍረስ ሲገባው በሕጉ መሰረት አልፈፀመም የሚል ምክንያት በመዘርዘር የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር የአሁኑ አመልካች ለአሁኑ ተጠሪ በውለ አንቀጽ 5.2 ስር የተመለከተውን የገደብ መቀጫ ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ሚያዝያ 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪ ክስ ባላቀረቡበት ጉዲይ ባለእዲ እንድንሆን የተወሰነው ያላግባብ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል በማለት ተከራክረው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ እንዱፀና ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪን ያስቀርባል ተብል በሰበር ችልቱ እንዱታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርበው ህዲር 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። በመልሣቸውም ላይ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የካቲት 27 ቀን 1993 ዓ.ም የተደረገውን ውል መሰረት በማድረግ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ መሻሩም ሆነ የገደብ መቀጫውን ለአመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑ ስህተት ባለመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ነ/ፈጅ በበኩላቸው የተጠሪን መልስ በመንቀፍ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሣቸውን ህዲር 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሯል። እንደመረመረውም አመልካች ለተጠሪ ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ አምስት ሺህ/ እንዱከፍል መወሰኑ ሥነሥርዓታዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
በክርክሩ ሂደት በአመልካችና በተጠሪ መካከል ውል መኖሩ መታመኑ፣ በተጠሪ በኩል በስር ፍ/ቤት የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አለመቅረቡ የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው። ለአመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ የመሰረተው የአሁኑ ተጠሪ የካቲት 27 ቀን 1993 ዓ.ም እና ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም ከአመልካች ጋር በተዋዋለት መሰረት የመጥረጊያ አለላ ምርት ለማቅረብ ግዳታ ገብተው የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ተቀብለው ምርቱን ሣይሰበስቡና ለአመልካች ሣያስረክቡ የመስኖ እርሻውን ጥለው በመጥፊታቸው በአመልካች ላይ የተለያዩ ወጪዎች መከሰታቸውን በመግለጽ የእነዚህ ወጪዎች ድምር እና የገደብ መቀጫ ለውለ አለመፈፀም በጉዲት ካሣነት እንዱከፈል ይወሰን ዘንድ ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ደረሱ ለተባለት ወጪዎች ተጠሪ አላፉነት የለበትም በማለት ከወሰነ በኋላ ለገደብ መቀጫው ግን ተጠሪን ተጠያቂ አድርጓቸዋል።
እንግዱህ የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ያልተስማሙበትና ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡበት ነጥብ የገደብ መቀጫውን በተመለከተ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል ከዚህ ውጪ ለውለ አለመፈፀም ምክንያት አመልካች በመሆኑ ልጠየቅ አይገባም ከማለት ውጪ የደረሰብኝ ጉዲት ስላለ አመልካች ሉከፍለኝ ይገባል በማለት በሥርዓቱ መሰረት የጠየቁት ዲኝነት አለመኖሩን የክርክሩ ሂደት ያሣያል።
በመሰረቱ በመጀመሪያ ደረጃ ጉዲዩን የተመለከተው ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ወገን ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኙን የሚያቀርበው የበታች ፍ/ቤትን ውሣኔ ለማስለወጥ፣ ለማሻሻል ወይም ሙለ በሙለ ውድቅ ለማድረግ ነው።
ይህም ላሆን የሚችለው ያቀረበው ክስ ኖሮት ያላግባብ ውድቅ ከሆነበት ወይም የተጠቀው ዲኝነት በአግባቡ ሣይታይ የታለፈ ከሆነ ነው ዲኝነት ደግሞ በከሣሽነት ወይም በተከሣሽነት ሉጠየቅ ይችላል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም በይግባኝ የቀረበለትን ጉዲይ የሚያስተናግደው በበታች ፍ/ቤት የተደረገውን የክርክር እና የተጠየቀውን ዲኝነት ይዘት እንዱሁም አግባብነቱን በመመልከት ነው። በበታች ፍ/ቤት ተከሣሽ የነበረ ወገን የተከሣሽ ከሣሽነት ሥርዓቱን አሟልቶ ሣይጠይቅ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ፍርደ ተለውጦ የፍርድ ባለመብት እንዱሆን ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት የሚጠይቅበት እና ተቀባይነት የሚያገኝበት ሥርዓት አለመኖሩን ስለይግባኝ ፍርድን ለመቃወምና ለፍርድ እንዱሻሻል ወይም እንዱጣራ ስለማመልከት የተደነገጉት ከቁጥር 32ዐ እስከ 37ዐ የተመለከቱት የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ያሣያለ።
ስለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሥልጣን የሚደነግገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ በተለይ ሲታይም ፍ/ቤቱ ማናቸውም ይግባኝ የቀረበለትን ፍርድ ወይም ውሣኔ ለማፅናት፣ ለማሻሻል ወይም ለመሻር የሚችል መሆኑን ከመደንገጉ ውጪ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያልተጠየቀ ዲኝነት የመስጠት ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ አያሣይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 182/2/ ስር የተመለከተው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ስልጣንም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አስተያየት መስጠት ወይም መወሰን ይገባው ነበር ብል በሚገምተው ጉዲይ ላይ ትእዛዝ ወይም ውሣኔ ለመስጠት የሚችል ስለመሆኑ፣ በተጨማሪም ተገቢ መስል የታየውንና ነገሩን ለማስፈፀም ተስማሚ ነው ብል የሚገመተውን ማናቸውንም ላላ ውሣኔ ወይም ብይን ወይም ትእዛዝ ወይም ፍርድ መስጠት ስለመሆኑ የተገለፀ ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ መሰረት የተሰጡት የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሥልጣንና ተግባራት የሚከናወኑት በበታች ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ሥርዓቱን የጠበቀ ክርክር ሲቀርብና የተጠየቀ ዲኝነት ሲኖር ነው። አንድ ተከራካሪ በሥነ-ሥርዓቱ መሰረት ክስ ባልቀረበበት ጉዲይ ባለዔዲ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
በመሆኑም ለውለ አለመፈፀም ምክንያት አመልካች በመሆኑ የገደብ መቀጫውን በውለ መሰረት ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ክስ ባላቀረበበት ሁኔታ ተጠሪ ለውለ አለመፈፀም ምክንያት አይደለም ወደሚለው ድምዲሜ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከደረሰ በኋላ ተጠሪ የገደብ መቀጫው ለአመልካች ሉከፍል አይገባም በሚል ውሣኔ መቆም እየተገባው በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያልተጠየቀ ዲኝነት መስጠቱ ሥነ-ሥርዓታዊ ካለመሆኑም በላይ ለውሣኔው መሰረት ያደረጋቸው የፍትሐብሕር ድንጋጌዎችም አግባብነት የላላቸው ናቸው። በዚህም መሰረት አመልካች ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ አምስት ሺህ/ ለተጠሪ እንዱከፈል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ሉፀና ይገባል በማለት የጠየቀውን ዲኝነት ስንመለከተው የአሁኑ ተጠሪ ለውለ አለመፈፀም ተጠያቂ ስለመሆናቸው እርግጠኛ ያልሆነ ስለመሆኑ ከውሣኔው ላይ "… ውል አፍራሽ ተከሣሽ ነው ባንልም …" በሚል ከገለፀው ሁኔታ መረዲት የሚቻል ከመሆኑም በላይ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ለውለ መፍረስ ምክንያት የሆነው የአሁኑ አመልካች ነው በማለት የወሰነው በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችን መዝኖ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሣኔ በዚህ ችልት የሚታይበትን አግባብ አላገኘንም። በይዘቱ የማስረጃ ምዘና ነውና።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1771/2/ በተመለከተው መሰረት ተጎጂው ወገን የጉዲት ኪሣራ የመጠየቅ መብት የሚኖረው የውለ አለመፈፀም በገንዘብ የሚተመን ኪሣራ የደረሰበት መሆኑ ሲታወቅ እንደሆነ ነው። በዚህ ረገድ የበታች ፍ/ቤት በማስረጃ ምዘና የተለያዩ ከመሆናቸው ውጪ በውለ ወይም በሕጉ አተረጓጎም ረገድ የተለያዩበት ሁኔታ ስለመኖሩ የክርክሩ ሂደት አያሣይም። በመሆኑም ተጠሪ ለገደብ መቀጫው ተጠያቂነት የለባቸውም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው የውሣኔ ክፍል የሚለወጥበትን ሕጋዊ ምክንያት ስላላገኘን በዚህ ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
ው ሣ ኔ 1/ የአፊር ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 968 የካቲት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ//ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
2/ ተጠሪ ለውለ መፍረስ ምክንያት አይደለም የተባለው የውሣኔ ክፍል እንዲለ ሆኖ የገደብ መቀጫውን በተመለከተ ግን አመልካች ለተጠሪ ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ አምስት ሺህ/ ሉከፍል አይገባም ብለናል።
3/ አመልካች የዞኑ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ያጽናልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ አልተቀበልነውም።
4/ ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
5/ መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ።