No summary available.
ኀዲር 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ድራጋድስ ጄ ኤንድ ፒ. ጆየንት ቬንቸር - ጠበቃ አቶ ደቸ ፈለቀ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሳባ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማኀበር ጠበቆች
ይህ ጉዲይ በግልግል ዲኝነት ጉባዓ ከተሰጠ ውሣኔ ጋር በተያያዘ የይግባኝ አቀራረብን የሚመለከት ነው።
የጉዲዩ አመጣጥን እንደተመለከትነው አመልካች ከኢትጵያ መንገድች ባለሥለጣን ጋር ከአዱስ አበባ እስከ ጅማ ድረስ ያለውን አውራ መንገድ የማሻሻያና መልሶ ጥገና ሥራ ለመሥራት ውል ተዋወል ከመንገድ ሥራ የተወሰነውን በንዐስ ሥራ ተቋራጭ /sub- contract/ ውል ለማሰራት በነበረው ፍላጎት ከተጠሪ ጋር የካቲት 25 ቀን 1996 ዓ.ም የንዐስ ሥራ ተቋራጭነት ውል እንደተዋዋለ በዚህም የንዐስ ሥራ ተቋራጭነት ውል አንቀጽ 17 ላይ በውለ አፈፃፀም ረገድ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር በአዱስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ሥር በተቋቋመው የግልግል ተቋም ታይቶ እንደሚወሰን በተስማሙት መሰረት በክፍያ አፈፃፀም ረገድ በመካከላቸው አለመግባባት በፈጠሩ ተጠሪ አቤቱታውን ግራ ቀኙ ለመረጡት የግልግል ተቋም አቅርቦ ተቋሙም በሚሰራበት የግልግል ደንብ /rules of procedure/ መሰረት ግራ ቀኙን አከራክሮ የካቲት 3 ቀን 1999 ዓ.ም ውሣኔ መስጠቱን ተገንዝበናል።
ከዚህ በኋላም የሥር ተከሣሽ የአሁን አመልካች የግልግል ጉባዓው በሰጠው ውሣኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ይግባኝ ባይ ይግባኝ ያቀረበው ይግባኝ ላቀርብበት በሚችል ምክንያት ነው ወይንስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ መሥርቶ ጉዲዩን በመመርመር አለመግባባቱ በግልግል ዲኝነት እንዱታይ አስቀድሞ ግራ ቀኙ እንደተስማሙ፣ጉዲዩን በግልግል ዲኝነት የተመለከተውም ተቋም በአዋጅ ቁጥር 341/95 መሰረት ሥልጣን በተሰጠው አካል እንደተቋቋመ፣ ይግባኝ ባይ ጉባዓው ጉዲዩን እንዱመለከት ከፈቀደ በኋላም በክርክሩ ሂደት ሙለ በሙለ እንደተካፈለ፣ የግልግል ጉባዓው የሚሰጠው ውሣኔ ይግባኝ እንደላለውም የግልግል ጉባዓው በሚመራበት ደንብ ላይ እንደተመለከተና ይግባኝ ባይ ይህ የደንቡ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የለውም በማለት ቢከራከርም ግራ ቀኙ ወገኖች ወደ ግልግል ተቋሙ ሲሄደ ተቋሙ ክርክሩን የሚመራበት የእራሱ ሥርዓት እንዲለው ስለሚታወቅ ይግባኝ ባይ በተቋሙ በመዲኘት እስከመረጠ ድረስ በተቋሙ አሰራር የማይገዛበት ምክንያት ስለላለ በዚሁ መሰረት በግልግል ውሣኔው ላይ ይግባኝ አይባልበትም ተብል በግልግል ደንቡ ላይ የተቀመጠውን እንደተቀበለው ስለሚቆጠር በዚህ ረገድ ያቀረበው የይግባኝ ቅሬታ የይግባኝ መብቱን ቀሪ ባደረገበት ሁኔታ ስለሆነ አግባብነት የለውም በማለት ይግባኙን ሣይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ሰበር ችልቱ የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ የግልግል ተቋሙ የሰጠው ውሣኔ ይግባኝ የማይበልበት ነው መባለ ተጠሪ ባለበት ለሰበር ቀርቦ ሉወሰን እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሁፍና በቃል አከራክሯል። ከዚህም በተጨማሪ የግልግል ተቋሙ የሚመራበትን የሥነሥርዓት ደንብ /rules of procedure/ እና እንደዚሁም በግራ ቀኙ ወገኖች የተደረጉ የተለያዩ መፃፃፍችን ለጉዲዩ አወሳሰን እንደሚረዲ በማመኑ ችልቱ አስቀርቦ ተመልክቷቸዋል።
የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን ይህ ሰበር ችልትም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
በዚህ ችልት ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥም አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ይግባኝ የሚባልበት ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው ነው።
አመልካችና ተጠሪ የካቲት 25 ቀን 1996 ዓ.ም የንዐስ ሥራ ተቋራጭነት ውል ሲዋዋለ በውለ አፈፃፀም ረገድ አለመግባባት ሲፈጠር ይሄው አለመግባባት በአዱስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ሥር በተቋቋመው የግልግል ተቋም ታይቶ እልባት እንደሚያገኝ መስማማታቸውን የተገነዘብን ሲሆን ይህን ተቋም /forum/ በመምረጥ ረገድ ስምምነት ስለመደረሱ ግራ ቀኙን አላከራከረም።
አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው የግልግል ተቋሙን በመምረጥ ረገድ በመካከላችን ስምምነት ቢኖርም የግልግል ተቋሙ በሚሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ የማይባልበት ስለመሆኑ ግራ ቀኛችን አልተስማማንም። የግልግል ተቋሙ የሚመራበት የግልግል ደንብ ላይ የጉባዓው ውሣኔ ይግባኝ እንደማይባልበት ቢጠቀስም ይህ የደንቡ ቃል በሕገ መንግሥት የተረጋገጠን የይግባኝ መብትን የሚፃረር ከመሆኑም በላይ የግልግል ዳኞች በሚሰጡት ውሣኔ ላይ ከፍ/ቤት ይግባኝ ለማቅረብ ይቻላል ተብል በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 35ዐ/1/ ላይ የተመለከተውንም የሚጋፊ ስለሆነ ተፈፃሚነት የለውም በማለት ነው።
ተጠሪም በበኩለ በንዐስ ሥራ ተቋራጭነት ውለ መሰረት የተፈጠረውን አለመግባባት በአዱስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ም/ቤት ሥር ለተቋቋመው የግልግል ዲኝነት ተቋም አቤቱታው ሲቀርብ ጉባዓው የተጠሪን ክስ እንደዚሁም የግልግል ተቋሙ የሚመራበትን ደንብ ለአመልካች በሸኚ ደብዲቤ እንዱላክና አመልካችም ስለ ደንቡ አንዲንድ ማከራከሪያ ከጠየቀ በኋላ ተቀብል የግልግል ጉባዓውን የተለያዩ ድንጋጌዎች በመጥቀስ የተከራከረ ሲሆን ይህም አመልካች ደንቡን ተቀብል ሙግቱን መቀጠለን የሚያሣይ ነው።
ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች በደንቡ ለመግዛት ሙለ ፈቃድን ስለሰጠ የጉባዓው ውሣኔ ይግባኝ አይባልበትም ተብልም በዚሁ ደንብ ላይ የተጠቀሰውንም እንደተቀበለው ይቆጠራል በማለት ይግባኙን ሣየቀበል መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት ስለሆነ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
አመልካችና ተጠሪ አለመግባባትን በግልግል ለመፈታት በውል የመረጡት የአዱስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የግልግል ተቋም የሚመራበት የግልግል ደንብ የውል ክርክርን ለግልግል ስለማቅረብ በሚደነግገው አንቀጽ 1/1/ ሥር ተዋዋይ ወገኖች ውላቸውን በሚመለከት ለሚነሱ ማናቸውም አለመግባባቶችና ክርክሮች በአዱስ አበባ ንግድ ም/ቤት የግልግል ተቋም የግልግል ደንብ ውሣኔ እንዱያገኝ በጽሁፊቸው ሲስማሙ በዚሁ መሰረት እነዚህ አለመግባባቶች በተቋሙ የግልግል ደንብ ውሣኔ እንደሚሰጣቸው መደንገጉን ተገንዝበናል።
በዚህ የግልግል ደንብ አንቀጽ 1/1/ ላይ እንደተመለከተው ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች ወደዚህ የግልግል ተቋም ሲሄደ የግልግል ተቋሙ ግራ ቀኙን ማከራከር ከመጀመሩ በፉት ተከራካሪ ወገኖች በዚህ የሥነ-ሥርዓት ደንብ የሚይዙ ስለመሆኑ የጽሁፍ ስምምነት መቀበል እንደሚገባው አከራካሪ አይሆንም።
በእርግጥ የግልግል ጉባዓው ተጠሪ ያቀረበውን ክስና የግልግል ተቋሙም የሚመራበትን ይህንኑ የግልግል ደንብ አያይዞ ለአመልካች እንደላከና አመልካችም ይህንኑ ደንብ መሰረት አድርጎ ክርክሩን መምራቱን መገንዘብ ቢቻልም ሁኔታው ደንቡን ካወጣው ተቋም ሃሣብ /intention/ አንፃር ሲታይ ደንቡን ጠቅላላ ድንጋጌ ተከራካሪ ወገኖች ተገንዝበው በዚሁ መሰረት ለመገዛት ወስነዋል ለማለት የሚቻለው በደንቡ አንቀጽ 1/1/ ላይ እንደተመለከተው ግልጽ የሆነ የጽሁፍ ስምምነት ሲኖር ነው።
በልላ በኩልም አመልካች ደንቡ ደርሶት የደንቡንም የተለያዩ ድንጋጌዎች በመጥቀስ ሙግቱን የቀጠለ ስለሆነ ደንቡን እንደተቀበለውና በዚሁ ደንብ አንቀጽ 2ዐ/2/ መሰረትም የይግባኝ መብቱን እንደተወ ይቆጠራል ቢባል እኳን ይግባኝ መሰረታዊ መብት እንደመሆኑ መጠን ይህንኑ መሰረታዊ መብት ተፊላሚ ወገኖች አስቀርተዋል ለማለት የሚቻለው የነገሩን አካባቢ ሁኔታ በሚገባ በተገነዘቡ ጊዜ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 35ዐ/2/ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ተከራካሪ ወገኖች የይግባኝ መብታቸውን አስቀርተዋል ወይንም ትተዋል ለማለት የሚቻለው የነገሩን አካባቢ ሁኔታ በሙለ በተረደበት ደረጃ እርስ በርሣቸው በሚያደርጉት ስምምነት ሲሆን ነገር ግን አለመግባባቱ በግልግል ተቋሙ ዓማካይነት እንዱታይ ጥያቄው በቀረበ ጊዜ /At the stage of submission/ የነገሩን አካባቢ ሁኔታ በሚገባ ተገንዝበዋል ለማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ ናቸው ስለማይባል በዚህ ሁኔታ ይግባኙን ለማስቀረት የሚሰጡት ፈቃድ በሕጉ ላይ እንደተቀመጠው የነገሩን አካባቢ ሁኔታ በሚገባ በመገንዘብ እንዲደረጉት የሚቆጠር አይሆንም።
በኢትዮጵያ የፍትሐብሕር ሕግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተመሥርተው ማብራሪያ የፃፈትም þሮፋሰር አለን ሴድለር ይህንኑ በማብራሪያቸው ላይ አንፀባርቀውታል።
አመልካች የይግባኝ መብቱን ለመተው አድርጎታል የተባለው ስምምነት የነገሮችን አካባቢ ሁኔታዎች በሚገባ ካለመገንዘብ ነው ከተባለ ደግሞ በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 35ዐ/2/ ድንጋጌ መሰረት ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው ማለት ነው።
ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች የይግባኝ መብቱን ያስቀረ ስለሆነ ያቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ተገቢነት የላለው ነው በማለት ሣይቀበለው መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች የይግባኝ መብቱን ቀሪ ያላደረገ ስለሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን መርምሮ የበኩለን እንዱወስን ጉዲዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.