No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 371ዐ5 ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር መላኩ መለሰ /ነገረ ፡ ፈጅ/ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ሰልሞን አበበ ኮከብ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ነው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተውም የስራ ውላ ከሕግ ውጪ ተቋርጦብኛል፤ ስለዚህ ውዝፍ ደመወዜ ተከፍልኝ እና ያልተሰጠኝ የዓመት ፈቃድ ተሰጥቶኝ ወደስራዬ እመለስ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ የስራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ በተደነገገው መሰረት የስራ ውል ሉያቋርጥ የሚችል ጥፊት በመፈፀሙ ነው፤ ለአምስት የስራ ቀናትም በስራው ላይ ሣይገኝ ቀርቶአል በማለት የተከራከረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም ክርክሩን ከሰማ በኋላ ተጠሪ የሦስት ወር ደመወዝ ተከፍልት ወደሥራው ይመለስ፤ ለመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት የሚገባውን የዓመት እረፍትም በማካካሻ እረፍት መልክ ይሰጠው በማለት ወስኗል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ውሣኔ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሚያዝያ 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተገለፀው ተጠሪ የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለት ቢከራከርም፤ አመልካች ግን የስራ ውለ የተቋረጠው ተጠሪ በፈፀመው የስራ ውልን የሚያቋርጥ ድርጊት ምክንያት ነው በማለት ተከራክሯል። በአመልካቹ ክርክር እንደተገለፀው ተጠሪ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል በሚል ተጠርጥሮ በፖሉስ ምርመራ ተደርጎበታል።
የተጠሪ ስራ የልደር ኦþሬተርነት ሲሆን፤ 12ዐ ሉትር ናፍጣ ወስድ ለግል ጥቅሙ አውሎል በሚል ነው በፖሉስ ተይዞ ምርመራ ሉጣራበት የቻለው። በዚህ ምክንያት ታስሮ በፖሉስ ቁጥጥር ሥር የቆየ ሲሆን፣ ከተለቀቀ በኋላም ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ሥራው ላይ ሣይገኝ እንደቀረ በአመልካች ክርክር ተገልጿል። የእምነት ማጉደልን በተመለከተ አመልካች የቆጠረው ማስረጃ የፖሉስ የምርመራ መዝገብ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ይህን የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ አልተመለከተም። የፖሉስ የምርመራ መዝገብ በራሱ በቂ አስረጂ ላሆን አይገባም በሚል ሣያስቀርበው እንደቀረ ከሰጠው ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በስራው ላይ አልተገኘም የሚለውን ክርክር በተመለከተም ፍ/ቤቱ በቂ የሆነ ማጣራት ሣያደርግ እንዲለፈው ነው ውሣኔው የሚያሣየው።
በግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች የተካደ ወይም ያልተማመኑበት የፍሬ ነገር ነጥብ የሚነጥረው በማስረጃ ነው። በግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች የተቆጠረው ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ በአግባቡ መሰማት አንደና ዋነኛው የፍርድ አመራር ስርዓት መሰረታዊ መርህ ነው። በእርግጥ በተከራካሪ ወገን የቀረበ ማስረጃ ሁለ ያለምንም ምክንያት መሰማት አለበት ማለት አይደለም። የተቆረጠው ማስረጃ ለተያዘው ክርክር አግባብነት የላለው ሆኖ ከተገኘ ውድቅ የሚደረገው እንዱሁ በደፈናው ሣይሆን፣ ምክንያቱን በግልጽ በጽሐፍ በማስፈር ነው /የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ.138/። በተያዘው ጉዲይ እንደምናየው የስር ፍ/ቤቶች ወደ ውሣኔ ያመሩት በአመልካች የተቆጠረውን ማስረጃ አስቀርበው ሣያዩ እና ሣይመረምሩ ነው። ማስረጃው በፖሉስ ምርመራ የተደረገበት የምርመራ መዝገብ ሲሆን፣ ይህም ቢያንስ ተጠርጣሪው /ተጠሪ/ የሰጠው ቃል፣ ተፈፀመ ስለተባለው ወንጀል በተመለከተ የተሰሙ ምስክሮች፣ የመርማሪውን አስተያየት ወይም ግኝት እንደሚይዝ ይገመታል። አመልካች የምርመራ መዝገቡን በአስረጂነት የቆጠረውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ መገመት የሚያስቸግር አይደለም። በመሆኑም ፈራጅ የሆነው አካል (ፍ/ቤቱ) ይህን መዝገብ አስቀርቦ ሣይመለከትና ከተያዘው ጭብጥ ጋር አገናዝቦ ሣይመረምር ብቃት ያለው ማስረጃ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ ሉደርስ አይችልም፤ አይገባምም።
በሁለተኛ ደረጃ ያየነው ከስራ መቅረትን በተመለከተ የተነሣውን ክርክር ነው። የስር ፍ/ቤት ይህን ነጥብ ያለፈው ተጠሪ የቀረው በፖሉስ ቁጥጥር ስር ስለነበር ነው በሚል ነው። እዚህ ድምዲሜ ላይ ሉደርስ የቻለበትን ምክንያት ግን በዝርዝር አልገለፀም። ተጠሪም በዚህ ድምዲሜ እንደማይስማማ ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረበው ክርክር ገልጿል። ከስራ ቀረሁ የሚለው በመታሰሩ ምክንያት ሣይሆን፣ ታሞ ሐኪም ቤት ሲመላለስ /ሲታከም/ ስለነበረ ነው። እነዚህን ሁኔታዎች ደምረን ስንመለከት ፍ/ቤቱ ወደ ውሣኔ ያመራው ምንም ዓይነት ማስረጃ ሣይሰማ እንደሆነ ነው። በግልጽ የቀረበን ክርክር በተቆጠረው ማስረጃ ወይም አግባብነት ባለው መንገድ ሣያጣሩ /ሣያነጥሩ/ መወሰን ደግሞ ዋነኛው መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀም ነው። ስለዚህም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 21629 ጥቅምት 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተሰጥቶ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 6ዐ83ዐ መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተከፈተው መዝገብ ቁ. 21629 ክርክሩ እንዱቀጥል በማድረግ እና በአመልካች የተቆጠሩትን ማስረጃዎች በመስማት ክርክሩን መርምሮ የመሰለውን ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 341/1/ መሰረት ይመለስለት ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻለ። ውሣኔው ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ይፃፍ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.