No summary available.
ጥቅምት 6 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
በቀለ ዱሪብሣ ቀረቡ።
ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ - ተወካይ ተስፊዬ በቀለ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የምክር በሪሁን - ጠበቃ አቶ ጌትነት የሻነህ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ. 10906 የሰጠው ትእዛዝና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጡት ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ በአመልካቾች እና በላልች ሁለት ሰዎች እንደዚሁም በአዱስ አበባ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ላይ ክስ መስርቶ ሕጋዊ ውሣኔ አሰጥቻለሁ በማለት ያቀረበው የአፈፃፀም ክስና ክርክር ነው።
የክርክሩም ፍሬ ጉዲይ ተጠሪ ያቀረበው የቤት ሽያጭ ውል ይፈፀምልኝ ጥያቄ ሲሆን የክርክሩ ይዘትም የአሁን አመልካቾች ለወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ መጋቢት 18 ቀን 1984 ዓ.ም በተፃፈ ውል በአዱስ አበባ ወረዲ 17 ቀበላ 12/13 ቁጥሩ 552 የሚገኘውን ቤት ሸጠው ይህንኑ ቤት ተጠሪ ከእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ግንቦት 21 ቀን 1989 ዓ.ም የገዛሁት ስለሆነ ቤቱን እንዱያስረክቡኝ በስሜ እንዱያዞሩ የሚል ክስ ሲያቀርብ እነ በላይነሽ ካሣዬም በአመልካቾች ላይ ክስ ያቀርባለ።
የአሁን አመልካቾች በሕግ በሚፀና አኳኋን ለወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ቤት አልተሸጠም፤ ተጠሪም ከእኛ ጋር የገባው ውል ስለላለ ክስ ሉያቀርብብን አይገባም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ጉዲዩ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚያም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ቀርቦ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ አመልካቾችን የሚጠይቅበት ምክንያት እንደላለ በመግለጽ እንደውለ ሉፈጽሙ አይገደደም በማለት በመዝገብ ኀዲር 13 ቀን 1999 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ክስ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ የሻረው በመዝገብ መጋቢት 29 ቀን 1998 የሰጠውን ውሣኔ ነው፤
ይፈፀም የተባለው መስከረም 2 ቀን 1999 ዓ.ም በመዝገብ የተሰጠ ውሣኔ ነው፤ ስለዚህ አፈጻጸሙ ይቀጥል የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በይግባኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን በፍታብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካቾች የከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደ ውለ ሉፈጸም ይገባል በማለት የሰጠው ፍርድ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሽሯል፤ ተጠሪ ቤት ሸጣልኛለች የሚላት ወ/ሮ በላይነሽ በቤቱ ላይ መብትና ይዞታ የላላት መሆኑና ውለም አስገዲጅነት እንደላለው ተረጋግጧል፤ ከዚህ በኋላ በአፈፃፀም ቤቱን ለተጠሪ እንድናስረክብ የተሰጠው ትእዛዝ በፍርድ የተሻረና የማይፀና ውሣኔን ለማስፈፀም የተሰጠና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት ሉሻር ይገባዋል በማለት አቤቱታ አቅርበዋል።
ተጠሪ በበኩለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሻረው አመልካቾች ከወ/ሮ በላይነሽ ጋር ተከሳሽ መሆን የለባቸውም በማለት ነው፤ ፍርድ ቤቱ እነ ወ/ሮ በላይነሽን አስመልክቶ የተሰጠውን ውሣኔ አልሻረም፤ እኔ የአፈፃፀም ፊይል የከፈትኩት በወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ እና በአቶ ጉልላት ሞላ ብቻ ላይ እንጅ በአመልካቾች ላይ አይደለም፤ ስለዚህ በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም፤ በማለት ተከራክሯል። አመልካቾች የአፈፃፀም ትእዛዝ የተሰጠበት ጉዲይ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በግልጽ የተሻረ ነው፤ ስለዚህ የተሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ መሰረታዊ ስህተት አለበት የሚል ክርክር አቅርበዋል።
በሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው ተጠሪ የአፈፃፀም ክስ ያቀረበበት ቤት የአመልካቾች ንብረት የሆነና፣አመልካቾች ለበላይነሽ ካሳዬና ለአቶ ጉልላት ሞላ ሸጠውት እነ ወ/ሮ በላይነሽ ለእኔ ሸጠውልኛል የሚለው ቤት ነው። አመልካቾች ከእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ጋር በሕግ የፀና የቤት ሽያጭ ውል የለንም የሚል ክርክር ያነሱ ሲሆን በአፈፃፀሙ ቤቱን እንዱለቁና ለተጠሪ እንዱያስረክቡ እየተገደደ ያለት እነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ሣይሆኑ አመልካቾች ናቸው።
No topics extracted.
ከዚህ አንፃር ስንመረምረው ተጠሪ በእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ላይ አስወስኛለሁ በሚል ፍርድ መነሻ አመልካቾችን በአፈፃፀም ለማስገደድ ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለው ነጥብ መመርመር ያስፈልጋል። ተጠሪ እነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ለእሱ ቤት የሸጡለት መሆኑን በፍርድ ቢያረጋግጥ እንኳን የቤቱ ስመ ንብረት እና ይዞታ በአመልካቾች ስም በመሆኑ በፍርድ ሉያስፈጽመው የሚችል ውሣኔ የለም። ምክንያቱም በእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ እና በተጠሪ መካከል የቤት ሽያጭ ውል አለ መባለ ብቻውን ተጠሪ ገዝቸዋለሁ የሚለውን ቤት ለመረከብ እና ስመ ንብረቱን ለማዛወር የሚያስችል መብት አያሰጠውም። ተጠሪ የቤቱ ስመ ንብረት እና ይዞታ እንዱዛወር ለማድረግ የሚችለው እነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ የሽጡለት የራሳቸው ንብረት የሆነ ቤት ከሆነ ብቻ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬና አቶ ጉልላት ሞላ ለእኔ ሸጠውልኛል የሚለው ቤት ስመ ንብረቱም ሆነ ይዞታው በአመልካቾች ስም ያለ ነው። ተጠሪ እነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ቤቱን የሸጡልኝ ከአመልካቾች ገዝተውት ነው የሚል ክርክር እና ክስ ቢያቀርብም በአመልካቾች እና በእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ መካከል በሕግ የፀና የቤት ሽያጭ ውል የለም በማለት አመልካቾች ክደው ተከራክረዋል። በዚህ ጭብጥ ላይ ቤቱን ገዝተዋል የተባለት በላይነሽ ካሣዬና አቶ ጉልላት ሞላ በአመልካቾች ላይ የውል ይፈፀምልን ክስ አቅርበው በፍርድ የተረጋገጠ መብት አላገኙም።
በመሆኑም በመጀመሪያ በአመልካቾችና በእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ መካከል በሕግ የሚፀናና አመልካቾች የባለቤትነትና የይዞታ መብታቸውን እንዱለቁ የሚያስገድድ ውል ያለ ስለመሆኑ ውሣኔ ባላገኘበት ሁኔታ ተጠሪ እነ በላይነሽ ካሣዬ ከአመልካቾች የገዙትን ቤት ለእኔ ስለሸጡልኝ በውለ መሰረት ይፈፀምልኝ የሚል ክርክር በማቅረቡ ብቻ አመልካቾች ንብረታቸውን ለተጠሪ ለቅቀው እንዱወጡ ትእዛዝ የሚሰጥበት ምክንያት የለም።
ይህንንም ነጥብ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍትሀብሕር ይግባኝ መዝገብ ሚያዝያ 25 ቀን 1999 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቶበታል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በውሣኔው አመልካቾች ከእነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ጋር አድርገውታል ስለተባለው የቤት ሽያጭ ውል በተመለከተ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ አግባብነት የላለው መሆኑን በግልጽ ካሰፈረ በኋላ አመልካቾች ተጠሪ ካቀረበባቸው ክስ ጋር ተያይዞ እንደውለ እንዱፈጽሙ አይገደደም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በይግባኝ እልባትና ውሣኔ ያገኘውን ጉዲይ የተሰጠው ውሣኔ ስህተት አለበት የሚል ከሆነ ለሰበር ሰሚ ችልት ከሚያቀርብ በስተቀር እነ በላይነሽ ካሣዬን ነጥል በመክሰስ በተዘዋዋሪ መንገድ የአመልካቾችን ቤት ለመረከብ የተከተለው የክርክር ስልት ተገቢ አይደለም። አፈፃፀሙን የያዘውም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ለተጠሪ ቤቱን እንዱያስረክቡ ሉገደደ የማይገባ መሆኑን በግልጽ በማስፈር የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጠበትን ጉዲይ ወደ ጏን በመተው በአፈፃፀም ተከሳሽ እነ ወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬ ናቸው የሚል ምክንያት በመስጠት አመልካቾች ቤታቸውን ለተጠሪ አስረክበውና ለቅቀው እንዱወጡ የሰጠው ትእዛዝ ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ግልጽ ውሣኔ ዋጋ የሚያሣጣና የሚሽር በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የዲኝነት አካሄድ ሥርአትን የሚጥስና የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ገዥነትና የበላይነትን የሚፃረር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ትእዛዝ ነው ብለናል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ይህንን ትእዛዝ የሕግና የፍሬ ጉዲይ ስህተት የለበትም በማለት የአመልካቾችን ይግባኝ መሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ተጠሪ በወ/ሮ በላይነሽ ካሣዬና አቶ ጉልላት ሞላ ላይ ያስወሰነው ውሣኔ አልተሻረም በሚል ሰበብ አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ ለቅቀውና አስረክበው እንዱወጡ በመዝገብ መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽረዋል። ይፃፍ።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዝያ 25 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በሰበር ሰሚ ችልት ያልተሻረ ወይም ያልተሻሻለ ውሣኔ በመሆኑ ህጋዊ አስገዲጅነትና ተፈፃሚነት ያለው ውሣኔ ነው። ስለሆነም አመልካቾች ቤታቸውን እንዱለቁና ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በአፈጻጸም መገደድ የለባቸውም ብለናል። ይፃፍ።
ተከራካሪዎች በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጥቅምት 6 ቀን 2001 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።