No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነገረፈጅ አቶ አደም ንጉሴ ቀረቡ መልስ ሰጭ፡- አቶ ታረቀኝ ገ/ፃዱቅ - ቀርበዋል።
መዝገቡ የተቀጠረው ለውሳኔ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በይግባኝ እያከራከረ እያለ ይግባኝ ባይ የነበረው የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ይግባኙን ለመስማት በተቀጠረበት እለት አልቀረበም። መልስ ሰጭ የነበረው አቶ ታረቀኝ ገ/ፃዱቅም ክድ ተከራክሯል። ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት መዝገቡ ተዘግቷል። በማለት የካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ. 60818 ላይ የሰጠው ትእዛዝ ነው።
የአሁን አመልካች የተዘጋው መዝገብ ተንቀሳቅሶ ጉዲዩ እንዱታይለት ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ በዚያው መዝገብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት መዝገቡ ይንቀሳቀስ ዘንድ ይግባኝ ባይ ያቀረበው ምክንያት በቂ ባለመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት ያለው አይደለም በማለት አሰናብቶታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መዝገቡን ለመዝጋትም ሆነ የተዘጋው መዝገብ እንደገና ሉንቀሳቀስ አይገባውም ሲል የሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይታረምልን በሚል ክርክሩን ዘርዝሮ በማቅረቡ ነው።
የአሁን መልስ ሰጭም በበኩለ መዝገቡ ለቃል ክርክር ተቀጥሮ በነበረበት እለት ይግባኝ ባይ ያለመቅረቡን በመገንዘብ የተሰጠው ትእዛዝ ተገቢ ነው፤መዝገቡን መልስ ለመቀበልና የቃል ክርክር ለመስማት በሚል መቀጠር የሚፃረረው የሥነ-ሥርአት ሕግ ባለመኖሩ የሥር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ይጽናልን ሲል ተከራክሯል።
እኛም ሁለቱም ወገኖች በሰበር ደረጃ ያቀረቡትን ክርክር ከይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የይግባኝ መዝገብ ግልባጭ ጋር አገናዘበን ተመልክተናል።
የአሁን አመልካች በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኝ ባይ በመሆን የአሁን መልስ ሰጭ ደግሞ በመልስ ሰጭነት ተሰይመው በሚከራከሩበት ጉዲይ መዝገቡ ለየካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ተቀጥሮ የነበረው የግራ ቀኙን ክርክር ለመስማት እና የመልስ ሰጭን የጽሐፍ መልስ ለመቀበል በሚል እንደነበረ በዚሁ እለት ፍ/ቤቱ በመዝገቡ ላይ ካሰፈረው ለመረዲት ተችሎል።
በዚሁ እለትም ግራ ቀኙ መቅረባቸውን ለማረጋገጥ ጥሪ በተደረገላቸው ጊዜ ይግባኝ ባይ ላቀርብ እንዲልቻለም የተካደ ጉዲይ አይደለም።
ይሁን እንጂ በተያዘ ቀጠሮ የቃል ክርክር ማድረግና የመልስ ሰጭን የጽሐፍ መልስ መቀበል በክርክር አካሄድ ሁለቱም እራሳቸውን የቻለ ሥርአቶች እንጂ አንደ ላላውን ሉተካ የሚችል ወይም ደግሞ ተመሳሳይ የክርክር ደረጃዎች አይደለም። የሁለቱም ሥርአት አለመፈፀም የሚያስከትለው ውጤት የተለያየ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በዚህ አኳኋን ከማዘዙ በፉት ግልጽ በሆነ አኳኋን መዝገቡ ለምን እንደተቀጠረ ለይቶ አለማዘዙ በጉዲዩ አመራር የተፈፀመ ስህተት ነው።
በተለይም የካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ከነበረው ቀጠሮ በፉት መዝገቡ ለቃል ክርክር በሚል ተቀጥሮ እያለ መልስ ሰጭ ጊዜ አጥሮኛል በማለት ባመለከቱት መሰረት ተለዋጭ ቀጠሮው ለየካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም እንዱሆን ተደርጓል በማለት አመልካች ላቀረበው ክርክር መልስ ሰጭ ይህንኑ አላስተባበለም። ይህም ከሆነ ከየካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በፉት በነበረው ቀጠሮ መልስ ሰጭ ቀርቦ የቃል ክርክር ማድረግ እየቻለ ቀጠሮ አጥሮብኛል ማለቱ በተከታዩ ቀጠሮ ክርክሩን በጽሐፍ ለማቅረብ እንደፈለገ ስለሚያመለክት መዝገቡ ለየካቲት 14 ቀን ተቀጥሮ የነበረው የቃል ክርክር ለማድረግ ነበር ወደሚለው መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም። በመሆኑም ከላይ እንደተገለፀው በአንድ ቀጠሮ የቃል ክርክር እና የጽሐፍ መልስ ፣መልስ ሰጭ እንዱያቀርብ ብል ማዘዙ ሥነ-ሥርአታዊ ካለመሆኑም በላይ መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው የቃል ክርክር ለማድረግ እንደሆነ በግልጽ ያልተመለከተ ስለሆነ ይግባኝ ባይ በቀጠሮው እለት አልቀረቡም እንኳ ቢባል ስለጉዲዩ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 ተፈፃሚነት ያለው አይደለም።
የይግባኝ ባይ በቀጠሮው የመቅረብና ያለመቅረብ ጉዲይ ፍ/ቤቱ እንደጀመረው የክርክሩ አቅጣጫ መልስ ሰጭ ላቀረበው የጽሐፍ ክርክር የበኩለን የመልስ መልስ ለማቅረብ መቻለ ወይንም ለማቅረብ ያለመቻለ ጉዲይ ነው።
የአሁን አመልካች መዝገቡ መታየት በጀመረበት እለት በመዝገብ መደራረብ ምክንያት በልላ ችልት በመጠራቱ እንጂ በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ይህንኑ ጉዲይ እየተከታተልኩ ነበር የሚለው ክርክሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ የመልስ መልሱን የማቅረብ መብቱን ለማስጠበቅ እንጂ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74 ጋር ሉገናኝ የሚችል አይደለም።
No topics extracted.
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 339 እንደተደነገገው የይግባኝ ክርክሩን ለመስማት ሉከተል ከሚችለው ሥርአት አንደን ለይቶ መከተል ሲገባው በአንድ ጊዜ ሉፈፀሙ የማይችለትን ሥርአቶች አቀላቅል እንዱፈፀም በማዘዙ ምክንያት እና ከሁለቱ ሥርአቶችም መዝገቡ የተቀጠረው መልስ ሰጭ የጽሐፍ መልሱን ለማቅረብ በሚል ነው የሚለውን ነጥብ የመዝገቡ ግልባጭ ስለሚያስረዲ መዝገቡ የተቀጠረው የቃል ክርክር ለማድረግ በሚል ነው፤ በዚሁ እለትም ይግባኝ ባይ አልቀረቡም፤መልስ ሰጭም ክድ ተከራክሯል የሚለውን መነሻ በማድረግ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
73 መሰረት ተዘግቷል ሲል የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሥነ- ስርአት ህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 60818 የካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም እና የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጣቸው ትእዛዞች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በነበረው ቀጠሮ በእራሴ ጉድለት ምክንያት ሳይሆን በቀጠሮ መደራረብ ነው የሚለው ክርክሩ ከቀረበው ማስረጃ አኳያ ታይቶ ተከታዩ ሥርአት (የመልስ መልስ የማቅረብ መብቱ) ይጠበቅለት እንደሆነ አስፈላጊው እንዱፈጸም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341 መሰረት መዝገቡን መልሰናል።