No summary available.
ጥቅምት 13 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ተስፊሁን ዋኘው - ቀረቡ ተጠሪ፡- በጅያክ አግሮ ኮሜርሻያል ኢንተርþራይዝ - ተወካይ ሙላት ታግል ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግን መሰረት ያደረገ ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካችና በልላ ግለሰብ ላይ መጋቢት 27 ቀን 1999 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር አስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረተው የንብረት ጉዲት ካሣ ክስ ነው። የክሱ ሂደት ቀጥልም አመልካች የፍ/ቤቱ መጥሪያ ደርሷቸው መልስ ይዘው አለመቅረባቸውና ክሱ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮም አለመቅረባቸው ተረጋግጧል ተብል ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ብይን ከተሰጠ በኋላ አመልካች በላለበት ክርክሩ እንዱታይ የተሰጠው ብይን ተነስቶ ወደ ክርክሩ ገብተው ለመከራከር እንዱፈቀድላቸው አለኝ ያለትን ምክንያት ገልፀው ጥያቄ ቢያቀርቡም የስር ፍ/ቤት ሣይቀበላቸው ቀርቶ በመጨረሻም በአሁኑ ተጠሪ የቀረበለትን ክስ እና ማስረጃ መርምሮና ተገቢ ነው ያለውን ማስረጃ ሁለ በማስቀረብና በመመልከት የአሁኑን አመልካችና አንድ ላይ ተከሦ የነበረውን ግለሰብ ለንብረት ጉዲቱ አላፉ በማድረግ የብር 7ዐ,500.00 /ሰባ ሺህ አምስት መቶ/ ካሣ በአንድነትና በነጠላ ሉከፍለ ይገባል በማለት ወስኗል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ያለበትን ምክንያት ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ የፍ/ቤቱ መጥሪያ ደርሶ ያልቀረቡት በውሃ ሙላት ምክንያት መሆኑን፣ በብይኑም ሆነ በዋናው ውሣኔ ላይ በአንድነት ይግባኝ የመጠየቅ መብት በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተጠበቀላቸው ሆኖ እያለ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በዋናው ውሣኔ ላይ ብቻ ይግባኝ እንደቀረበ በመቁጠር መወሰኑ ከጭብጡ ውጭ መሆኑን በመዘርዘር የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። ይህ ችልትም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካችን በብይኑ ላይ በይግባኝ ሣትመጣ በፍሬ ነገሩ ላይ ይግባኝ ማለት አትችልም ሲል ይግባኙን አለመቀበለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ተጠሪን ያስቀርባል ብል ተጠሪ ሐምል 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን አቅርቧል። የመልሱ ይዘትም በአጭሩ የሚሞላ ውሃ የተባለው ሐሰት መሆኑንና ይልቁንም የመኪና መንገድ ያለ መሆኑን ይግባኙ የቀረበውም በዋናው ጉዲይ ላይ መሆኑንና መጥሪያውም በጊዜው የደረሰ መሆኑን በመግለጽ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያሣይ ነው። አመልካች ጥቅምት ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ይህንኑ የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ትእዛዝ፣ ከግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሯል። እንደመረመረውም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ የቀረበውን የአመልካችን ይግባኝ ያለመመርመሩ አግባብነት የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
እንደሚታወቀው የፍትሐብሕር ክርክሮች የሚመሩት በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት ነው። ይኸው የሥነ-ሥርዓት ሕግ አካቶ ከያዛቸው ጉዲዮች ውስጥ አንደ የተከራካሪ ወገኖች በክርክሩ ወቅት ያለመቅረብና ውጤቱ ነው።
በዚህም መሰረት መጥሪያ ተልኮለት በተገቢው መንገድ የደረሰው መሆኑ በተረጋገጠበት ተከሣሽ ላይ ፍ/ቤቱ ሉከተለው የሚገባው ሥርዓት ጉዲዩ ተከሣሹ በላለበት የሚሰማበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 7ዐ/ሀ/ ስር ተመልክቷል። የዚህ የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ መንፈስ የሚያሣየውም በፍ/ቤቱ መጥሪያ መሰረት ያልቀረበ ተከሣሽ በክርክሩ ሂደት ለማንሣት የሚችላቸውን የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ክርክሮች እንዱሁም በማስረጃ አሰማም ሂደት የመስቀለኛ ጥያቄ የማንሣት መብቱን ሣይጠቀም የሚቀር መሆኑን ነው። ለተከሣሽ እነዚህ መብቶች የሚቀሩ ሆነው በከሣሽ በኩል የቀረበው ክስ ተያይዘው ከቀረቡት ማስረጃዎች ጋር ተመርምሮ እና በጉዲዩ ላይ መፈፀም ያለበት ላላ አስፈላጊ ሥርዓት ሁለ ከተፈፀመ በኋላ ተገቢ ውሣኔ መስጠቱ ፍ/ቤቱ ሉያከናውነው የሚገባው ተከታዩ ሂደት ነው። ላላው በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተመለከተው ሥርዓት ተከሣሹ ሉከተለው የሚገባው መፍትሕ ነው። ክርክሩ በላለበት እንዱቀጥል የተደረገበት ተከሣሽ በተከታዩ ቀነ ቀጠሮ ቀርቦ በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ያለመቅረቡን ካስረዲ መከላከያውን አቅርቦ የመከራከር መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.72 ያስገነዝባል። እንዱሁም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78/1/ አንድ ተከሣሽ በክርክሩ ላይ ቀርቦ መልስ ሣይሰጥ ወይም ተገቢውን መከራከሪያ ሣያቀርብ በመቅረቱ በላለበት አንድ ውሣኔ ወይም ትእዛዝ የተሰጠ ከሆነ ውሣኔው ወይም ትእዛዙ መሰጠቱን በተረዲው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ትእዛዙ ወይም ውሣኔው እንዱነሣለት የማመልከት መብት እንዲለው ተደንግጓል።
No topics extracted.
ይሁን እንጂ በእነዚህ የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች መሰረት አቤቱታ አቅርቦ ተቀባይነት ያጣ ተከሣሽ በተከታዩ ያለው የሥነ-ሥርዓት መፍትሕ ምንድነው ነው? ወደክርክሩ ልግባ ወይም በላለሁበት የተሰጠው ውሣኔ ይነሣልኝ የሚለው ጥያቄ ውድቅ ሲሆንበት በዚሁ ይግባኝ ማቅረብ ወይስ በዋናው ጉዲይ ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ በመጠበቅ በሁለም ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ? የሚለት ጥያቄዎች የሥነ-ሥርዓት ሕጉን በመመልከት ግልጽ ድንጋጌ ማግኘትና ምላሽ ለመስጠት የሚቻልባቸው ባይሆኑም የውሣኔ አሰጣጥና የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን በመፈተሽ ግን ምላሹን ለማግኘት አስቸጋሪ የሚሆን አይደለም።
በዚህም መሰረት ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትእዛዝ ወይም ውሣኔ የተሰጠበት ተከሣሽ ከላይ በተገለፁት የሥነሥርዓት ድንጋጌዎች አቤቱታውን አቅርቦ በፍ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ በዚሁ ብይን ላይ ቅሬታውን ለበላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ከማሣየት የሚከለክለው የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ አለመኖሩን የይግባኝ አቀራረብን በተመለከተ የሚደነግጉት ድንጋጌዎች ያሣያለ። በዋናው ጉዲይ ላይ ውሣኔ እስከሚሰጥ ድረስ ተከሣሹ ጠብቆ በዋናው ጉዲይ ላይ ከተሰጠው ውሣኔ ጋር አጠቃልል ይግባኝ ሉያቀርብ ይገባል ልባል የሚችል አይደለም። ምክንያቱም ከይግባኝ አቀራረብ የጊዜ ገደብ ሥርዓት ጋር ሉጣጣም የማይችልበት ሁኔታ ከመኖሩም በላይ በዋናው ጉዲይ ላይ ውሣኔ እስኪሰጥ ተጠብቀው በዋናው ጉዲይ ላይ ከተሰጠው ውሣኔ ጋር ተጠቃልለው ይግባኝ ላቀርብባቸው ይችላል ተብለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32ዐ ንዐስ ቁጥሮች ስር የተመለከቱት ምክንያቶች በባህርያቸው ጊዜያዊ አገልግልት ያላቸው ሆነው መሰረታዊውን መብት ሉያጣብቡ የማይችለ ከመሆናቸው ጋር ተዲምሮ ሲታይ የይግባኝ መብት የሚከለክል ሥርዓት የለም። አንድ ተከራካሪ ወደ ክርክሩ ገብቶ እንዱሣተፍ እድል መስጠት የሕግ ሥርዓት የግድ የሚለው ሲሆን ይህንን ዔድል መንፈግ መሰረታዊውን መብት ማጣበብ በመሆኑ ቅሬታ ያለው ወገን በይግባኝ ሥርዓት ጥያቄውን አቅርቦ ጉዲዩ እንዱታይለት ማድረግ መብቱ ነው።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትእዛዝ ተሰጥቶ ይኸው ትእዛዝ እንዱነሣላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ሲያጣ በዚሁ ነጥብ ብቻ ቀደም ብለው ይግባኛቸውን ለበላይ ፍ/ቤት ሣያቀርቡ በዋናው ጉዲይ ውሣኔ ሲሰጥ ግን ይግባኛቸውን አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም አመልካች ጉዲዩ ባለሁበት ይታይልኝ በሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ወደ ክርክሩ ሉገቡ አይገባም ተብል ብይን ሲሰጥ በዚሁ ብይን ላይ ይግባኝ ብለው መምጣት ሲገባቸው ውሣኔ ሲሰጥ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ይግባኝ ብለው መምጣታቸው ሥነ-ሥርዓታዊ አይደለም በሚል ምክንያት ፍሬ ጉዲዩን ሣይመረምር መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ የሰበር ችልት የሚከራከሩት ወደ ክርክሩ ሉገቡ አይገባም የተባለው ያላግባብ መሆኑንና በይግባኝም በዚሁ ነጥብና በዋናው ጉዲይ ወደ በላይ ፍ/ቤት ከመሄድ የሚከለክል ሥርዓት የለም በሚል ነው። ተጠሪ በበኩለ አመልካች ወደ ክርክሩ አይገቡም የተባለው ባግባቡ መሆኑንና ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡትም በዋናው ጉዲይ ላይ ብቻ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል።
የአመልካች ወደ ክርክሩ ልግባ ጥያቄ ውድቅ የተደረገው በቂ ምክንያት እያለኝ ነው በማለት ያቀረቡት ጥያቄ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ መመዘኛው ምን እንደሆነ በግልጽ ያልተመለከተ ሲሆን ባለው አሰራርም ፍ/ቤት የሚቀርብለትን ማስረጃ በመመርመርና የራሱን የህሉና ሚዛን መሰረት በማድረግ ሉያስተናግደው የሚችለው በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚደርሰው ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብል በሰበር ችልት ሉታረም የሚችል አይደለም።
በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክር የምንቀበለው ሆኖ አልተገኘም።
በዚህ ችልት ላታይና ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው ነጥብ አመልካች በፍሬ ጉዲዩ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚችለ መሆን ያለመሆኑ ነው።
አመልካች ወደ ክርክሩ ለመግባት ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ካጡ በኋላ ጉዲዩ በላለበት ታይቶ ውሣኔ ተሰጥቷል። ለጉዲዩ አግባብነት ሉኖረው የሚችለው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78/1/ ነው። የዚህ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌ የአማርኛና የእንግሉዝኛው ትርጓሜ ሙለ ይዘቱ ቀጥል የሰፈረው ነው። ይኸውም «ቁ.78 ተከሣሽ በላለበት የተሰጠውን ውሣኔ ስለማንሣት 1/ አንድ ተከሣሽ በክርክሩ ላይ ቀርቦ መልስ ሣይሰጥ ወይም ተገቢውን መከራከሪያ ሣያቀርብ በመቅረቱ በላለበት አንድ ውሣኔ ወይም ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ውሣኔው ወይም ትእዛዙ መሰጠቱን በተረዲው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ትእዛዙ ወይም ውሣኔው እንዱነሣለት ሉያመለክት ይችላል።» «Art. 78- Setting aside decree ex-parte against defendant
በልላ አገላለጽ ተከሣሹ ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት ወይም በላለሁበት የተሰጠው ትእዛዝ ወይም ውሣኔ ይነሣልኝ ብል ጥያቄ ማቅረብ ወይም ይህንኑ በመተው ለበላይ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ ምርጫው በሥነ-ሥርዓቱ የተተወለት መብት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጂ ለበላይ ፍ/ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ በተሰጠው ውሣኔ ይግባኝ ሲያቀርብ የይግባኝ አቀራረብ አድማሱ በተወሰኑት ነጥቦች ላይ ብቻ መሆን አንዲለበት የይግባኝ አቀራረብን በተመለከተ የተደነገጉት ድንጋጌዎች መንፈስ ያስረዲል። እንደሚታወቀው የፍትሐብሕር ሙግት አካሄድ ሥርዓታችን በተከራካሪ ወገኖች መነሣት ያለባቸው የክርክር ነጥቦች እንዲለ ያሣያል። በክርክሩ ሂደት ተነስተው በፍ/ቤቱ ተገቢ ያልሆነ ውሣኔ ተሰጠብኝ የሚለው ወገንም ነጥቡን ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል። የይግባኝ ቅሬታ ነጥብ መሆን ያለበት ግን በበታች ፍ/ቤት የተነሣ ነጥብ እንጂ አዱስ ላሆን እንደማይገባ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329/1/ ያሣያል። በመሆኑም ጉዲዩ በላለበት ታይቶ የተወሰነበት ተከሣሽ ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሲያቀርብ ሉኖር የሚችለው በስር ፍ/ቤት በተከራካሪነት ቀርቦ ያላነሣውን ነጥብ እንዲያነሣ ነው ከሚባል በስተቀር ሙለ በሙለ ይግባኝ ሉያቀርብ አይችልም የሚባልበት ሥርዓት የለም። እንደዚህ ዓይነት ተከራካሪ በፍ/ቤቱ የውሣኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ክሱን፣ የማስረጃዎችን አግባብነት፣ ተቀባይነት እና ጥንካሬ ባግባቡ ያላገናዘበ ሁኔታ አለ የሚል ከሆነ ይግባኝ ሉያቀርብ ይችላል። ፍ/ቤቱ የከሣሽ ክስ ተከሣሽ በላለበት ስለታየ ብቻ የተጠየቀው ዲኝነት ይሰጣል ተብል የማይጠበቅ ስለመሆኑ የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓት ያስገነዝባል። ፍ/ቤት ከሣሹ ያቀረበውን ክስ አባሪ ሆነው ከቀረቡት ማስረጃዎች አግባብነት፣ ተቀባይነትና ጥንካሬ አኳያ በመመርመር ተገቢውን ዲኝነት መስጠት የእለት ተዔለት የሥራ ድርሻው ነው። በዚህ አኳኋን ታይቶ የተሰጠ ውሣኔ አይደለም የሚል ተከሣሽ በክርክሩ ሂደት ተሣታፉ ያልነበረ ቢሆን አዱስ ክርክር ከማንሣት በመለስ የይግባኝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሲጠቃለልም አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ ያቀረቡት ይግባኝ ሣይመረመር የተዘጋው ጥያቄያቸውን የሚከለክል ግልጽ ሥርዓት በላለበት ሁኔታ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ 1/ የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16249 መጋቢት ዐ3 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
2/ አመልካች ወደ ክርክሩ ሉገቡ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ካጡ በኋላ በላለበት ጉዲዩ ታይቶ በተሰጠው ውሣኔ ፍ/ቤቱ በሕጉ መሰረት ውሣኔ አልሰጠም በሚለ ነጥቦች ተወስነው በፍሬ ጉዲዩ ላይ ይግባኝ ለበላይ ፍ/ቤት ከማቅረብ የሚከለክላቸው የሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ የለም ብለናል።
3/ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች ይግባኝ ማቅረብ የሚችለ መሆኑን ተገንዝቦ ፍሬ ጉዲዩን በመመርመር በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰንለታል።
ይፃፍ።
4/ በዚህ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
5/ መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ።