No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ጉደር አግሮ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ/- ጠ/አለም ወ/አረጋይ ተጠሪ፡- አቶ ኃይለ ወልደ - አልቀረቡም
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የተጠሪ የስራ ውል የተቋረጠው በሕገ ወጥ መንገድ ነው ተብል በተሰጠው ውሣኔ ላይ ሲሆን ለሰበር ችልት የቀረበው የሕግ ጥያቄም ለምስክሮች ስለሚሰጥ መጥሪያ አደራረስ የሚመለከት ነው።
ተጠሪ አመልካች ያለአግባብ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን ገልፀው ሕጉ የሚፈቅድላቸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ክስ መስርተዋል። አመልካች በሰጠው መልስ የስራ ውለ የተቋረጠው ተጠሪ ያሽከረክሩት የነበረው መኪና ለአቶ አገኘሁ የኔነህ በመሸጡና ከሣሽ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከገዢው ጋር አዱስ የስራ ውል በማድረግ በስራ ቦታ ላይ ያልተገኙ በመሆኑ እንደሆነ ተከራክሮ ስንብቱ ሕጋዊ ነው እንዱባልለት ጠይቋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት መዝገቡንና ማስረጃዎቹን መርምሮ የተጠሪ ምስክሮች ተጠሪ መኪናው ከተሸጠ በኋላም የድርጅቱን መኪና በመያዝ ያገለግለ እንደነበር አስረድተዋል፤ ተጠሪ መኪናው መሸጡ እንዲልተገለፀላቸው ያስረደ ሲሆን አመልካች ግን ተጠሪ መኪናው መሸጡን ማወቅ ነበረባቸው ወይም አሣውቄአለሁ የሚል ክርክር ስለላለው ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት ተጠሪ የኪሣራ እና የስንብት ክፍያዎች እንዱሁም የሐምል ወር 1998 ዓ.ም ደመወዛቸው እንዱከፈላቸው ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች በአቤቱታው ተጠሪ ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና በመሸጡ ተጠሪ መኪናዋን ከገዙት ግለሰብ ጋር ለመስራት ተስማምተው በስራ ቦታቸው ባለመገኘታቸው የሥራ ውለ መቋረጡን መኪናዋን የገዙትን ግለሰብ በምስክርነት ቆጥረናቸው ምስክሩ ሆነ ብለው በመሰወራቸው መጥሪያውን ልንሰጥ ስላልቻልን በሚኖሩበት አካባቢ ባለው ፖሉስ ጣቢያ አማካኝነት እንዱደርሣቸው በድጋሚ መጥሪያ እንዱታዘዝልን ያመለከትን ቢሆንም ፍ/ቤቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 116 እና 118/2/”ን” በተሣሣተ መንገድ በመተርጎም መጥሪያው በመሐላ ቃል በተደገፈ አቤቱታ ለፍ/ቤቱ ስላልተመለሰ በድጋሚ መጥሪያ አይታዘዝም ማለቱ ስህተት ነው ብለዋል።
የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ የታዘዘ ሲሆን ተጠሪም ቀርበው ሕጉ በሚፈቅደው ቃለ መሐላ አቅርበው ምክንያታቸውን መግለጽ ሲችለ ስላላቀረቡ የፍ/ቤቶቹ ውሣኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል። ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ መርምሯል።
ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ያላግባብ ተሰናብቻለሁ በማለት ክስ ሲያቀርቡ አመልካች ደግሞ ተጠሪ ሲያሽከረክሩ የነበሩት መኪና በመሸጡ ተጠሪ ንብረቱን ከገዙት ሰው ጋር ለመስራት በመዋዋል በስራ ቦታቸው ባለመገኘታቸው የስራ ውለ ተቋርጧል ሲል ተከራክሯል። አመልካች ይህንን አባባለን እንዱያስረደለት መኪናውን ገዙ የተባለትን ግለሰብ በመስክርነት ቆጥሯቸው የነበረ መሆኑንና ምስክሩን አግኝቶ መጥሪያ መስጠት ባለመቻለ ግን መጥሪያው ምስክሩ በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ ፖሉስ ጣቢያ አማካኝነት እንዱደርሣቸው ጠይቆ ፍ/ቤቱ ይህንን ሁኔታ በቃለ መሐላ አስደግፍ ባለማቅረቡ ድጋሚ መጥሪያ እንዱሰጥ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ስህተት መሆኑን ገልጿል። በእርግጥ ተያይዞ በቀረበው የሥር ፍ/ቤት የውሣኔ ግልባጭ ላይ ይህ ስለመሆኑ የተገለፀ ነገር ባይኖርም ተጠሪ በዚህ ሰበር ችልት በሰጡት መልስ ይህንኑ አረጋግጠዋል። ስለሆነም አመልካች ለምስክሩ የተላከውን መጥሪያ ምስክሩን አግኝቶ መስጠት አለመቻለን በቃለ መሐላ በማስደገፍ አለማረጋገጡ በድጋሜ መጥሪያ እንዲይታዘዝ ያስከለክለዋል ወይ? የሚለውን ይህ ችልት ተመልክቷል።
አመልካች ስንብቱ ሕገ-ወጥ አይደለም በማለት አጠብቆ የሚከራከረው ተጠሪ የሚነደት መኪና በመሸጡና ተጠሪም መኪናውን ከገዙት ሰው ጋር ለመስራት ተስማምተው ከስራ ቦታቸው ላይ ባለመገኘታቸው በበቂ ምክንያት ተሰናብተዋል በማለት ነው። ይህ ለመሆኑም መኪናውን የገዙት ግለሰብ ቀርበው እንዱመሰክሩ ጠይቋል። አንድ ተከሣሽ ለቀረበበት ክስ የሚያቀርበውን ማስተባበያ በማስረጃ እንዱያስረዲ መብት አለው። እኛም እንደተገነዘብነው አመልካች የቆጠራቸው መስክር መሰማት ለውሣኔ አሰጣጥ ጠቃሚ እና አስፈላጊ መሆናቸውን ነው። በእርግጥ የተከሣሽ መከላከያ ማስረጃዎች ልቅ በሆነ መንገድ የሚቀርቡ ሣይሆኑ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት መሆን ይገባዋል። ስነ - ስርዓቱን ተከትል የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ግን ያለ ሕጋዊ ምክንያት ውድቅ ማድረግ የተከሣሹን የመከላከል መሰረታዊ መብት የሚያጣብብ ነው።
No topics extracted.
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 116 ስለምስክሮች መጥሪያ አሰጣጥ ሲገለጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 118 ሥር የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ለምስክር የሚሰጥ መጥሪያ ሁለ ለተከሣሾች መጥሪያ ስለመስጠት በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት የሚፈፀም ቢሆንም ከቁጥር 1ዐ3 እስከ 1ዐ5 የተመለከቱት ድንጋጌዎች ግን ተፈፃሚ እንደማይሆኑ ያመለክታል። የሥር ፍ/ቤት አመልካች ለቆጠራቸው ምስክር የተላከው መጥሪያ ምስክሩ ባለመገኘታቸው ሲመለስ በቃለ መሐላ መረጋገጥ ነበረበት በማለት ለምስክሩ ድጋሚ መጥሪያ እንዲይላክ መከልከለን ተገንዝበናል።
በእርግጥ ለተከሣሹ መጥሪያ በሚላክበት ወቅት መጥሪያ ሰጪው ተገቢውን ፍለጋ አድርጎ ተከሣሹን ማግኘት ያልቻለ ከሆነ መጥሪያ መስጠት ያልቻለበትን ምክንያት በቃለ መሐላ አረጋግጦ መመለስ እንዲለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.1ዐ3 ያመለክታል። በመሆኑም መጥሪያ በድጋሚ ለተከሣሽ የሚላከው መጥሪያ ሰጪው የተከሣሹን አለመገኘት በቃለ መሐላ አረጋግጦ መጥሪያውን ሲመልስ ነው። ከፍ ሲል እንደተገለፀው ለምስክር የሚሰጥ መጥሪያ አደራረስ ለተከሣሽ በሚላክበት ዓይነት ቢሆንም ይህ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 1ዐ3 ግን በምስክር ጉዲይ ላይ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው በሥነ ሥርዓት ሕጉ በግልጽ የተመለከተ ስለሆነ ምስክሩን ማግኘት ባልተቻለ ጊዜ መጥሪያው በግድ በቃለ መሐላ በተደገፈ አቤቱታ ካልተመለሰ በቀር በድጋሚ መጥሪያ ሉላክ አይገባም የሚባልበት የሕግ መሰረት የለም።
በልላ በኩል ግን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 118/2/ሀ/ ሥር እንደተመለከተው እንዱቀርብ የተፈለገው ምስክር ለጉዲዩ አወሣሰን ጠቃሚ ከሆነ ፍ/ቤቱ የተላከው መጥሪያ ለባለአድራሻው በሚገባ ያልደረሰው መሆኑን አረጋግጦ ባለጉዲዩ ተገቢውን ኪሣራ ከፍል መጥሪያ እንዱወስድ ማድረግ አለበት። በተያዘው ጉዲይም አመልካች የሥራ ውለ ተቋረጠ የሚለው ተጠሪው መኪናውን ገዙ ከተባለት ግለሰብ ጋር ስራ በመጀመሩ በሥራ መደቡ ላይ ባለመገኘቱ ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ መረጋገጡ ለውሣኔው አስፈላጊ ነጥብ መሆኑ አያጠያይቅም። ስለሆነም ይህንን እውነታ ያስረዲለ የተባለት ምስክር መጥሪያ ያልደረሣቸው መሆኑ ከተረጋገጠ በድጋሚ እንዱደርሣቸው አስፈላጊ ይሆናል። በቀጠሮ መለወጥ ምክንያት በተጠሪ ላይ የሚደርስ መጉላላት ካለም ፍ/ቤቱ አመልካች ተገቢውን ኪሣራ እንዱከፍል ለማዘዝ ይችላል እንጂ ለምስክር ስለሚደረስ መጥሪያ ተፈፃሚነት በልላው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 1ዐ3 መሰረት መጥሪያው ያልደረሰበት ምክንያት በቃለ - መሐላ መደገፍ ነበረበት በሚል የአመልካች ጥያቄ ውድቅ መደረጉ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
ው ሣ ኔ 1/ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24475 በ23/5/2ዐዐዐ ውሣኔ እና በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 63168 በ21/ዐ6/2ዐዐዐ የተሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
2/ አመልካች የቆጠሯቸው መኪናዋን ገዝተዋል የተባለት ምስክር መጥሪያ ደርሷቸው ምስክርነታቸውን ከሰጡ በኋላ ተገቢ ነው ያለውን ውሣኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 መሰረት ጉዲዩ ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ተመልሷል።
3/ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።