No summary available.
ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ወ/ሮ ውዳ ወልደስላሴ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ነሐሴ 21 ቀን 1989 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፤ ሟች በሕይወት እያለ ነሐሴ 9 ቀን 1989 ዓ.ም እማኞች ባለበት ባደረጉት ኑዛዜ በድሬዲዋ ከተማ ከፍተኛ 1 ቀበላ 06 በአሁኑ አጠራር በቀበላ 04 የሚገኘውን የቤት ቁጥር 839 ለእኛ ለአመልካቾች አውርሰውናል፤ ሁለተኛ አመልካችም አካለመጠን ላልደረሰችው ተማሪ ኮከብ እሱባለው ሞግዚት አድርገው ሾመውኛል፤
ስለዚህ በምናቀርበው ማስረጃ ተረጋግጦ የወራሽነት ማረጋገጫና አካለመጠን ላልደረሰችው ተማሪ ኮከብ እሱባለው የሞግዚትነት ማስረጃ ይሰጠን በማለት ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም የአመልካቾችን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተቃዋሚ ካለ እንዱቀርብ ትእዛዝ በሰጠው መሰረት የአሁን አመልካቾች በተቃዋሚነት ቀርበው ቀደም ሲል አመልካቾች ተመሳሳይ አቤቱታ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበው ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገ ሲሆን በይግባኝም ጸንቷል። ስለሆነም አመልካቾች ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዲይ በድጋሜ ያቀረቡ ስለሆነ ፍ/ቤቱ ውድቅ ሉያደርገው ይገባል በማለት የተከራከሩ ሲሆን በአማራጭም ሟች ውዳ ወ/ስላሴ አድረገውታል የተባለው ኑዛዜ በእድሜም ሆነ በጤንነት ረገድ እራሳቸውን በማያውቁበት ጊዜ የአሁን አመልካቾች እራሳቸው ፈጥረው ያዘጋጁትና በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ከመሆኑም በላይ አመልካቾች የወ/ሮ ውዳ ልጅነትም ሆነ የሩቅ ዝምድና ስለላላቸው የኑዛዜ ወራሽነት ጥያቄው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የድሬዲዋ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ አቤቱታው አስቀድሞ በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ አግኝቷል የተባለውን በተመለከተ ፍ/ቤቱ አቤቱታውን ሳይቀበለው የቀረው አንድ ኑዛዜ ከተደረገ በኋላ በዚሁ ኑዛዜ መሰረት ወራሾች የንብረት ክፍፍል ከሚያደርጉ በስተቀር ኑዛዜ በፍ/ቤት እንዱጸድቅ ሕግ ስለማያስገድድ ኑዛዜ ይጽደቅልን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔ ጠበቃ ውብሸት ሥነ ጊዮርጊስ ቀረቡ ከመስጠቱ በስተቀር የኑዛዜ ወራሾች ናችሁ ወይንም አይደላችሁም የሚል የመጨረሻ ውሳኔ ስላልሰጠ ጉዲዩ አስቀድሞ እልባት አግኝቷል ተብል የቀረበው ክርክር አግባብነት የለውም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
የኑዛዜውን ሕጋዊነት አስመልክቶ የተነሳውን ክርክር በተመለከተም ሟች በጤነኛ አእምሮና በነጻ ፈቃዲቸው ኑዛዜውን ስለማድረጋቸው በአመልካቾች ምስክሮች የተረጋገጠ ስለሆነና ሟችም ንብረታቸውን ለፈለጉት ሰው በኑዛዜ የማስተላለፍ መብት ስላላቸው ተጠሪዎች የአመልካቾችን የኑዛዜ ወራሽነት በመቃወም ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ካለ በኋላ በልላ በኩልም ሟች ኑዛዜ ያደረጉበት ቤት ባለሐብትነቱ በከፉል የእራሳቸው በከፉል ደግሞ የሟች ባቤታቸው የነበረ ስለሆነ ከእራሳቸው ድርሻ አልፍ የሟች ባቤታቸውንም ድርሻ ጨምሮ ያደረጉት ኑዛዜ ሕገ ወጥ ስለሆነ በድርሻቸው ልክ የተደረገው ኑዛዜ ብቻ ትክክል ነው ብል በዚሁ ልክ አመልካቾች ወራሾች ናቸው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለድሬዲዋ ከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለሰበር ቀርቦ ሉወሰን እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የዚህን ችልት ምላሽ የሚሻው ነጥብ የተጠሪዎች የኑዛዜ ወራሽነት በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠው አግባብነት ባለው ሁኔታ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው ነው።
ከዚህም አኳያ ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪዎች የኑዛዜ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ ማስረጃ እንዱሰጣቸው አቤቱታቸውን ለድሬዲዋ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበዋል። አቤቱታው የቀረበለትም ይሄው ፍ/ቤት በቅድሚያ የአመልካቾችን/የአሁን ተጠሪዎችን/ ምስክር ከሰማ በኋላ ተቃዋሚ ካለ ይቅረብ በማለት የጋዜጣ ጥሪ አድርጓል። እዚህ ላይ ተቃዋሚ ቢኖር ይቅረብ ተብል የተሰጠው ትእዛዝ አግባብነት ነበረውን የሚለው ነጥብ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን ተቃዋሚ እንዱቀርብ ትእዛዝ መስጠት የነበረበት አመልካቾች አቤቱታቸውን እንዲቀረቡ ማስረጃ ከመስማቱ በፉት መሆን ይገባው ነበር። ተቃዋሚ የሚጠራበት አላማ የቀረበውን አቤቱታ ከማስረጃውና በአጠቃላይም ከሚቀርበው ክርክር አኳያ የበኩለን ማስረጃና ክርክር እንዱያቀርብ እድል ለመስጠት ነው። ነገር ግን በተያዘው ጉዲይ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ተቃዋሚ እንዱቀርብ ትእዛዝ መስጠቱ ተቃዋሚው በምስክሮች አመሰካከር ላይ የሚያነሳውን ክርክር/The right to confront witnesses/ የሚያጠብና ጉልህ የሆነ የሥነ- ሥርአት ጉድለት መፈጸሙን የሚያመለክት ነው።
No topics extracted.
ስለሆነም የድሬዲዋ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካቾችን /የአሁን ተጠሪዎችን/ ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተቃዋሚዎችን መጥራቱ እንደዚሁም ይ/ሰሚው ፍ/ቤት ይህንኑ ጉድለት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።