No summary available.
ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤ/ኃይል ኮርፖሬሽን ተጠሪዎች፡-
መኯንን ግርማይ - ቀረቡ።
በድ ዘለቀ - ቀረበ
ፈጠነ አያዩ - አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሾች የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት የኤላክትሪክ ምሰሶ ጉድጓድ ለመቆፈር ጊዜያዊ ሰራተኞች በመሆን ሰርተናል፤
በኋላም ወደ ረዲት የኤላክትሪክ መስመር መዘርጋት አሸጋግሮን ስንሰራ ከቆየን በኋላ ካለማስጠንቀቂያ ከስራ ስላሰናበተን ወደ ስራችን ተመልሰን ቋሚ ሰራተኞች እንድንሆን ይወሰንልን በማለት ነው። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎችም በስራ ላይ ደረሰብን ለሚለት ጉዲት ያወጡት ወጪ ይተካላቸው ዘንድ በተጨማሪ ጠይቀዋል። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ በእሱ እና በተጠሪዎች መካከል የተደረገ የስራ ውል እንደላለ በመግለጽ ተከራክሯል። ፍ/ቤቱ ከግራ ቀኝ ወገኖች የቀረበለትን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪዎች የአመልካች ሰራተኞች ናቸው፤ የስራ ውላቸው የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው፤ በመሆኑም አመልካች በሕጉ መሰረት የሚከፈለትን ክፍያዎች እንዱሁም በስራ ላይ ሣለ ለደረሰባቸው የአካል ጉዲት ይክፈል በማለት ወስኗል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ውሣኔ አጽንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች መጋቢት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪዎች የአመልካች ሰራተኞች ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው አከራካሪው ነጥብ በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የስራ ውልን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ነበር ወይስ አልነበረም? የሚለው ነው። ከስር ጀምሮ ከቀረበው የአመልካች ክርክር እንደሚታየው ተጠሪዎች በተባለው የምሰሶ ጉድጓድ ቁፊሮ ወይም የኤላክትሪክ መስመር መዘርጋት ስራ አልተሣተፈም አይልም። ክርክሩ ይህን ስራ የሰሩት ከኔ ጋር የስራ ውል አድርገው ሣይሆን፣ ስራውን እንዱሰራ ኮንትራት ከተሰጠው ግለሰብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ነው የሚል ነው። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ይህን ጭብጥ በመያዝ ማስረጃ እንደሰማና በዚህም አመልካች ስራውን በኮንትራት የሰጠው ግዛው ወንዲፍራሽ ለተባለ ሰው እንደሆነ፣ ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የቅጥር ግንኙነት እንደላላቸው፣ ግዛው ወንዲፍራሽ ክፍያውን ሲፈጽም እንደቆየ ማረጋገጡን በአንድ በኩል ሲገልጽ፤ በልላ በኩል ደግሞ ተከሣሽ /አመልካች/ ከሱ ጋር የቀን ስራ ሲሰሩ አለመቆየታቸውን ሙለ በሙለ አልካደም፤ ክፍያው ሲፈፀም የነበረው ከአመልካቹ በተገኘ ገንዘብ ነው የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ እንደሰጠ ለመገንዘብ ችለናል።
በበኩላችን እንደምናየው አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የተደረገ የሥራ ውል እንደላለው በግለጽ በማመልከት ተከራክሯል። ተጠሪዎች የተባለውን ስራ ሉሰሩ የቻለበትን ምክንያትም ከመግለፁም በላይ፣ በቆጠረው ማስረጃም እንደክርክሩ ጭብጥ አስረድቷል። የሥር ፍ/ቤቶች ይህንኑ ሁኔታ በውሣኔዎቻቸው ላይ በሚገባ አስፍረው ግንዛቤ አግኝተው ሣለ ተቃራኒ የሆነውን ውሣኔ መስጠታቸው ትክክል አይደለም። ማንኛውም ክርክር ሉወሰን የሚገባው በቀረበው ክርክር ማስረጃ እና በሕጉ መሰረት ብቻ ነው። እነዚህን መሰረታዊ ቁምነገሮች በማለፍ የሚሰጥ ውሣኔ በማንኛውም መለኪያ ሕጋዊ ላሆን አይችልም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔም ከቀረበው ክርክር፣ከተሰማው ማስረጃ እና ከሕጉ ውጭ የተሰጠ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
መዝገቡ ይመለስ።