No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- 1. ሐጂ ታጁ ለገሰ ቀረበ።
መዝገቡ የቀረበው የAማራ ብሕራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ መስከረም 6 ቀን 2AAA ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት Aመልካቾች ኀዳር 2 ቀን 2AAA ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር Aቤቱታ ስላቀረቡ ነው። የክርክሩ መነሻ በAፈፃፀም የባልና የሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
ከዚህ ክርክር Aንደኛ Aመልካች የሆኑት ሀጂ ታጁ ለገሰ በሁለተኛ መልስ ሰጭ Eና ወ/ሮ ሀዋ መሐመድ ጋር በጋብቻ ሲኖሩ የጋራ ንብረት Aፍርተዋል። Aንደኛው Aመልካች ከወ/ሮ ሀዋ መሐመድ ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍች ሲፈርስ የጋራ ንብረታቸውን Eንዲካፈሉ ከተሰማሙ ባልና ሚስት ከቀበል በተከራዩት ቤት ላይ ያላቸው የንግድ ድርጅት ተካፍለው ኑሯቸውን Eንዲመሩ ወስኗል። ይህንንና ልሎች የጋራ ንብረቶችን ለማካፈል ለወ/ሮ ሀዋ መሐመድ የAፈፃፀም ከሳሽነት የAፈፃፀም መዝገብ ተከፍቶ Aፈፃፀሙ በሂደት ላይ Eያለ ተጠሪው ቤቱ የቀበል A2 በመሆኑ ባልና ሚስቱ ንብረታቸው ያልሆነውን ላካፈሉ Aይገባም በማለት ለጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መቃወሚያ Aቅርቦ ፍርድ ቤቱ የንግድ ድርጅቱ የባልና የሚስት የጋራ ንብረት ነው። ቤቱን Aስመልክቶ የተከራይ መብት ነው ያላቸው ስለዚህ ተቃውሞው ተገቢ Aይደለም በማለት ብይን ሰጥቷል። ይህንን Aውቀውም ተጠሪው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ Aቅርቦ የወረዳውን ፍርድ ቤት ውሣኔ Aጽንቷል።
ተጠሪው ይህንን በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ Aቅርቦ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቤቱ የቀበል ስለሆነ የንግድ ድርጅቱን ሸቀጥና Eቃ ባልና ሚስቱ Eንዲካፈሉ በማለት የወረዳውና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሣኔዎች ሽሮAቸዋል። Aመልካች ይህንን ውሣኔ በመቃወም ባለቤቴ የነበረችው ወ/ሮ ሀዋ መሐመድ በEኔ ስም ከማዘጋጃ ቤት በተከራየሁት ቤት ላይ የነበራትን ድርጅት ከልላው ንብረት ጋር ተካክሶ የተካፈለች ሲሆን በEሷ ስም ከቀበል በተከራየነው ቤት ያለን የንግድ ድርጅት Eኔ ልትካፈል Aይገባም መባሉ ተገቢ Aለመሆኑና ቀበልውም በዚህ ጉዳይ ተከራካሪ የሚሆንበት ሁኔታ ስለልለ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ይሻርልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የተጠሪ ተወካይ በበኩሉ ቤቱ የቀበል ቤት ሆኖ Eያለ Eንደባልና Eንደ ሚስት የጋራ ንብረት ተቆጥሮ ይካፈሉ ቤቱን ለIንሸስትመንት ስለሚፈለግ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። Aመልካቾች የመልስ መልስ Aቅርበዋል።
የክርክሩ Aመጣጥና በመዝገቡ የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Aኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው የAንደኛው Aመልካች ሚስት በነበሩት በወ/ሮ ሀዋ መሐመድ ስም የነበረው የንግድ ድርጅት የሚካሄድበት ቤት የቀበል ንብረት Aንደሆነና የኪራይ ውል 394 395 ከቀበል A2 የተያያዘ መሆኑ ክርክር Aልተነሣበትም። የወረዳ ፍርድ ቤትም ሆነ የከፍተኛ ፍርድ ቤት Aመልካቾች Eና ወ/ሮ ሐዋ መሐመድ የቀበል የሆነውን ቤት ለሁለት ተካፍለው የባለቤትነት መብት ያግኙ የሚል ትEዛዝ Aልሰጡም።
በልላ በኩል የወረዳና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የጋራ የሆነውና የተጠሪው የሆነውን ቤት በኪራይ ይዘው Eየሰሩበት ያለው የንግድ ድርጅት Eንዲካፈሉ መወሰኑ ተጠሪውን መብትና ጥቅም የሚነካ Aይደለም። ተጠሪው ፍርድ ቤቶቹ በሰጡት ውሣኔ መሰረት የንግድ ድርጅቱ ሲከፈል የቤቱን መሰረታዊ ይዘትና ዋጋ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ያደርሣል የሚል ክርክር Aላቀረበም። ድርጅቱ መከፈል የማይቻል ሲሆን Aመልካቾችና ወ/ሮ ሃዋ መሐመድ የንግድ ድርጅቱን Eንዳለ በመሸጥ ዋጋውን Eንዲካፈሉ ለማድረግ የሚያበቃ ምክንያት ከመሆኑ ውጭ ተጠሪውን ከወረዳ ጀምሮ Eስከ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ክርክር Eንዲያቀርብ ምክንያት ላሆን የሚችል መሰረታዊ ጉዳይ Aይደለም።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የንግድ ድርጅቱ የሚከናወንበት ቤት የቀበል ስለሆነ ባልና ሚስቱ ንብረቱንና Eቃውን ነው የመካፈል መብት ያላቸው በማለት የሰጠውን ውሣኔ Aንድ የንግድ ድርጅት በንግድ መደብርነት በውስጡ Aካትቶ የሚይዛቸው ነገሮች በውስጡ ከተቀመጡት ሸቀጦችና Eቃዎች የማይወሰን Eንደሆነ በተለይ በንግድ ህጉ Aንቀጽ 127 ንUስ Aንቀጽ 2 በንግድ መደብር የንግድ ቤቱ ስም የሚነገድበት የተለያየ የንግድ ማስታወቂያ የንግድ ስራ የሚያከናውንባቸው ቤቶች የመከራየት መብት የሚያጠቃልል መሆኑን ሣያገናዝብ የተሰጠና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል። በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የንግድ ድርጅት ማካፈል ማለት የንግድ ድርጅቱን ካፒታል Eና በውስጡ ያሉ Eቃዎች ከመካፈል ውጭ የንግድ ድርጅቱ በሚከናወንበት ቤት ላይ ያላቸውን የኪራይ መብት Aይጨምርም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ መስከረም 6 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ግልባጩ ይተላለፍ።
የAማራ ክልል የጐንደር ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 10 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eና የስሜን ጐንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 22 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል። ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡት ወጭ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻሉ።
ይህ ፍርድ መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ነ/ዓ