No summary available.
ግንቦት 5 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ተገኔ ጌታነህ ሂሩት መለሰ መድህን ኪሮስ Aመልካች፡- ወ/ሮ ዝማም ህሉፍ ወኪል ቀረበ።
ተጠሪ፡- Aቶ መረሣ ገ/ዮሐንስ ጠበቃው ቀርቧል፣፣
ለሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በመቀል ዞን ማ/ፍርድ ቤት ነው። የAሁኗ Aመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46/96 በመስከረም 4 ቀን 1992 ዓ.ም በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የቦታ ሽያጭ ውል ፈርሶ ወደነበሩበት Eንዲመለሱ በሰጠው ውሣኔ መሰረት Eንዲፈፀምላቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ተጠሪ ቤት Eና ቦታውን ለAመልካች Eንዲያስረክቧቸው ትEዛዝ ሰጥቷል። ጉዳዩ በይግባኝ የተመለከቱት የመቀል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Eና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ትEዛዝ ስህተት የለውም በማለት የቀረበላቸውን የይግባኝ ቅሬታ ውድቅ Aድርገውታል።
የAሁኑ ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር Aቤቱታ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ችሎቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ በግራ ቀኙ የተደረገው የቦታ ሽያጭ ውል ሻጭ ባለቤት ሳይሆኑ የተፈፀመ ስለሆነ ውሉ ፈራሽ ሆኖ ተዋዋዮቹ ወደነበሩበት Eንዲመለሱ ተወስኗል። ይህም ማለት ገዢ ገንዘባቸው Eንዲመለስላቸው ቦታው ደግሞ ቦታውን ለማስተዳደር ስልጣን ላለው ማዘጋጃ ቤት Eንጂ 382 383 ለተጠሪ Aይደለም በማለት ተጠሪ ለAመልካች ቦታውን Eንዲያስረክቡ የተሰጠውን ትEዛዝ ነው።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችሎትም የተሰጠው የAፈፃፀም ውሣኔ ዋናውን ውሣኔ የተከተለ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ቀርቦ Eንዲታይ Aድርጓል።
ከመዝገቡ Eንደተረዳነው ከAመልካች ክርክር የሰበር ችሎቱ የሰጠው የAፈፃፀም ውሣኔ በዋናው ጉዳይ ላይ የተሰጠውን ፍርድ የሚለውጥ ነው፣ 3ኛ ወገኖች ክርክር ባላቀረቡበት ጉዳይ መብት Eንዲያገኙ የሚደረግበት ህጋዊ መሰረት የለም የሚሉ ይገኙበታል።
ይህ ችሎትም ጭብጥ የያዘው በAፈፃፀም የተሰጠው ውሣኔ ዋናውን ፍርድ መሰረት Aድርጐ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር ስለሆነ ዋናው ውሣኔ ምን ይላል የሚለውን ማየት ያስፈልጋል። ምክንያቱም Aንድ ውሣኔ የሚያስፈጽም ፍ/ቤት በውሣኔው መሰረት ከማስፈፀም ውጪ በAፈፃፀም ጊዜ ዋናውን ፍርድ ላለውጥ የሚችልበትን የህግ መሰረት የለውም ለAፈፃፀም ምክንያት ከሆነው ውሣኔ ላይ Eንደተገነዘብነውም Aመልካች ለከብት Eርባታ ተብሎ በጊዜያዊነት የተሰጣቸው የመሬት ሽያጭ ውል Eንዲፈርስላቸው ያቀረቡት ክስ Eስከ ትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ድረስ ከታየ በኋላ Aመልካች በቦታው ላይ የባለቤትነት መብት ሳይኖራቸው ያደረጉት የሽያጭ ውል ህግን የሚፃረር በመሆኑ ውሉ Eንዳልነበር ተቆጥሮ Eንዲፈርስና ተዋዋይ ወገኖች የሽያጭ ውል ከማድረጋቸው በፊት ወደነበሩበት ሁኔታዎች Eንዲመለሱ ተወስኗል። ከዚህ ውሣኔ Eንግዲህ መገንዘብ የሚቻለው የውሣኔው ውጤት ሻጭ የሸጠው መሬት Eንዲመለስለት ገዢ ደግሞ ለሻጩ የከፈለው ገንዘብ Eንዲመለስለት የሚያደርግ መሆኑን ነው። የሰበር ችሎቱ በዋናው ጉዳይ ላይ ከፍ ሲል የተመለከተውን ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ደግሞ በመቀጠል የመቀል ከተማ ቦታን የማስተዳደር ስልጣን የመቀል ማዘጋጃ ቤት Eሲሆን Eያከራከረ ያለው ቦታ ወደፊት Eንድት ይሁን የሚለውን ላወስንና Eርምጃ ላወስድ የሚችለው Eራሱ ስለሆነ ተከታትሎ Aንድ ነገር የማድረግ መብቱ ተጠብቆለታል ብሐል። በዚህም ጉዳይ Aከራካሪ የሆነው ግራ ቀኙ ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደነበሩበት ቦታ Eንዲመለሱ ከተወሰነ በኋላ የመቀል ማዘጋጃ ቤትን በተመለከተ ፍ/ቤቱ ያለው ነገር ነው።
ከፍ ሲል Eንደተመለከተው የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ዋናው ፍርድ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት Eንዲመለሱ ሲወሰን ገዢ የከፈሉት ገንዘብ Eንዲመለስላቸው Eና ቦታው ግን ማዘጋጃ ቤቱ Eንዲረከበው ከመወሰኑ በቀር Aመልካችን የፍርድ ባለመብት የሚያደርግ ውሣኔ Aልተሰጠም በማለት ለደረሰበት መደምደሚያ መሰረት ያደረገው ከውሣኔው በኋላ ማዘጋጃ ቤቱ ወደፊት ቦታውን በተመለከተ ተገቢ ነው ያለውን Eርምጃ Eንዲወስድ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ነው Eኛ Eንደተረዳነው ግን ሰበር ችሎቱ ማዘጋጃ ቤቱ ቦታውን Aስመልክቶ Eርምጃ Eንዲወስድ ማሳሰቢያ ከመስጠቱ በቀር ቦታው በክርክሩ ተካፋይ ላልነበረው Aካል Eንዲመለስ የተሰጠው ውሣኔ Aለመኖሩን ነው።
ስለሆነም የትግራይ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው የAፈፃፀም ውሣኔ ከዋናው ውሣኔ ያፈነገጠ መሆኑን ተገንዝበናል።
በልላ በኩል ግን ይህ ችሎት ግራ ቀኙን በቃል በAነጋገረበት ወቅት ቦታው ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በተጠሪዎች Eጅ መሆኑንና ማዘጋጃ ቤቱም ቦታውን ለተጠሪዎች ሰጥቶ ቦታውን የሚመለከቱ ሰነዶች ለመውሰድ በዝግጅት ላይ Eንዳሉ በዚህ ችሎት የEግድ ትEዛዝ ምክንያት መቆሙን ተገንዝበናል። ከዚህም የቦታው ባለቤት የሆነው ማዘጋጃ ቤት ቦታውን ለተጠሪዎች Aሳልፎ መስጠቱን ተረድተናል። የፍ/ባለEዳው በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ፍርድን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመፈፀም የማይችል መሆኑን ፍ/ቤቱ ከተረዳው ደግሞ ፍርድ Eንዲፈፀም ትEዛዝ Eንደማይሰጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 392/2/ ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም ምንም Eንኳን 384 385 በዋናው ውሣኔ ውሉ ፈርሶ ቦታው ለAመልካች Eንዲመለስ የተወሰነ ቢሆንም በAሁኑ ወቅት ማዘጋጃ ቤቱ ቦታውን ለተጠሪዎች የሰጠ በመሆኑ ፍርዱ ላፈፀም የሚችል Aይደለም።
No topics extracted.
በዚህም ምክንያት የትግራይ ክልል ሰበር ችሎት የሰጠውን ምክንያት በመቀየር ውሣኔውን Aጽንተናል።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ. 10962 በታህሳስ 5 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።