No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች ፡- Aቶ መሐመድ ኑር ጅብሪል ቀርቧል።
ተጠሪ፡- Eነ ወ/ሪት ውበት ላላሶ /3/ ሰዎች ቀርባለች።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ በፍርድ Aፈፃፀም ላይ የቀረበ Aቤቱታ ሲሆን በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ በAዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ በፍርድ ባለመብት 1ኛ Eና 2ኛ ተጠሪዎች Eንደዚሁም በፍርድ ባለEዳ 3ኛ ተጠሪ መካከል የነበረው የAፈፃፀም ክርክር ቀጥሎ በAዋሳ ከተማ በከፍተኛ 1 ቀበል 02 ክልል የሚገኝ ቤት በሐራጅ Eንዲሸጥ የAፈፃፀም ትEዛዝ ተሰጥቶ Eንዳለ የAሁን Aመልካች በፍርድ Aፈፃፀም በሐራጅ Eንዲሸጥ ትEዛዝ የተሰጠበትን ቤት የፍርድ ባለEዳ /3ኛ ተጠሪ/ በስማቸው ተመዝግቦ Eንደሚገኝ የሚያረጋግጥ የባለቤትነት የምስክር ወረቀት Aቅርበውልኝ ቤቱን ከEሳቸው ላይ የገዛሁ ከመሆኑም በላይ ባለቤትነቱ በስሜ ተዛውሮ የሚገኝ ስለሆነ ቤቱ በሐራጅ Eንዲሸጥ የተሰጠው ውሣኔ ያለAግባብ በመሆኑን ፍ/ቤቱ ይህንኑ ትEዛዝ ያንሳልኝ በማለት መቃወሚያ Aቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ በፍርድ Aፈፃፀም በሐራጅ Eንዲሸጥ ትEዛዝ የተሰጠበት ቤት Aቤቱታ Aቅራቢው ያልተከፋፈለ የውርስ ሀብት መሆኑን Eየተገነዘበ ከፍርድ ባለEዳ ላይ ስለመግዛቱ መገንዘብ የተቻለ ስለሆነ Aቤቱታው ተቀባይነት የልለው በመሆኑ Aፈፃፀሙ ላቀጥል ይገባል በማለት ብይን ሰጥቷል። Aመልካች በዚሁ ብይን ቅሬታ Aድሮባቸው 378 379 Aቤቱታቸውን Eስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ድረስ ያቀረቡ ቢሆንም Aቤቱታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ለዚህ ሰበር ችሎትም የቀረበው Aቤቱታ ይህንኑ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎት Aቤቱታው ለሰበር ይቅረብ ብሎ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሑፍና በቃል Aከራክሯል።
የዚህን ችሎት ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ Aፈፃፀም ላቀጥል Aይገባም በማለት Aመልካች ያቀረቡት Aቤቱታ በሥር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት Aለማግኘቱ በAግባቡ ነው ወይንስ Aይደለም የሚለው ነው። ከዚሁ ጭብጥ Aኳያም ጉዳዩን መርምረናል።
Eንደመረመርነውም 3ኛ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት በስማቸው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከሚመለከተው መንግስታዊ ተቋም ካገኙ በኋላ ሐምል 1 ቀን 1995 ዓ.ም በተፃፈ ውል ለAመልካች በሽያጭ ያስተላለፉ ስለመሆኑ የሽያጭ ውሉ ከተደረገ በኋላም Aመልካች Eንደውሉ ይፈፀምልን በማለት በ3ኛ ተጠሪ ላይ ክስ መስርተው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን Aከራክሮ በመ.ቁ. 340/96 በ2/4/96 ዓ.ም 3ኛ ተጠሪ በሽያጭ ውሉ መሰረት ቤቱን ለAመልካች Eንዲያስረክቡ በማለት ውሣኔ መስጠቱንና በዚሁ ውሣኔ መሰረትም Aፈፃፀሙ ቀጥሎ Eንዳለ 1ኛ ተጠሪ Aፈፃፀሙን በመቃወም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 418 መሰረት Aቤቱታ Aቅርበው ፍ/ቤቱም Aከራክሮ 1ኛ ተጠሪ Aቤቱታቸው በማስረጃ ያልተደገፈ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ብሎ Aፈፃፀሙ Eንዲቀጥል በማለት ትEዛዝ መስጠቱን ከመዝገቡ ተረድተናል።
Aመልካች በ3ኛ ተጠሪ ላይ ክስ መስርተው ከፍ ብሎ Eንደተጠቀሰው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት 3ኛ ተጠሪ ለAመልካች ላያስረክቡ ይገባል ተብሎ ውሣኔ ከተሰጠ ይሄው ቤት በፍርድ Aፈፃፀም በኩል በሐራጅ ተሸጦ ተጠሪዎች ገንዘቡን ላከፋፈሉ ይገባል ተብሎ የተሰጠውን ውሣኔ ተከትሎ Aፈፃፀም ሲቀጥል Aመልካች በዚሁ ቤት ላይ በፍ/ቤት ውሣኔ የፍርድ ባለመብት የሆኑ በመሆኑ Aፈፃፀሙ በዚህ ቤት ላይ ላቀጥል Aይገባም በማለት ያቀረቡት Aቤቱታ ግራ ቀኙ በቤቱ ላይ ካቋቋሙት መብት Aኳያ ታይቶ የAፈፃፀም ትEዛዝ መስጠት ሲገባው Aመልካች በዚህ ቤት ላይ መብት የላቸውም በማለት ያቀረቡትን Aቤቱታ ውድቅ በማድረግ Aፈፃፀሙ ይቀጥል ተብሎ በAዋሳ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት የተሰጠው የAፈፃፀም ትEዛዝና Eስከ ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስም ይህንኑ ትEዛዝ በማጽናት የተሰጠው ትEዛዝ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የAዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 147/98 ታህሣሥ 13 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ብይን Eንደዚሁም የAዋሳ ከተማ ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 01015 በ18/5/98 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ. 13987 ታህሣሥ 25 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
No topics extracted.
ለዚህ የሰበር Aቤቱታ ምክንያት የሆነው የፍርድ Aፈፃፀም Aመልካችና ተጠሪዎች በየበኩላቸው ያቀረቡትን ክርክር መርምሮ Eንዲወስን ለAዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።