No summary available.
ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ነ/ፈጅ Aለሙ Iብሳ ተጠሪ፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ነ/ፈጅ የምስራች ደሳለኝ መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዳይ የፍርድ Aፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን በፍርድ ባለመብት የAሁን ተጠሪና በፍርድ ባለEዳዎች Eና Aቶ ካላድ የሱፍ /2 ሰዎች/ መካከል የነበረው የፍርድ Aፈጻጸም ክርክር በሥር ፍ/ቤት ቀጥሎ በከፍተኛ 5 ቀበል 12 ክልል በ1ኛ የፍርድ ባለEዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቁጥር 1267 የሆነው መጋዘን ተሽጦ ሕዳር 3 ቀን 1969 ዓ.ም በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ለፍርድ ባለመብት Eንዲከፈል በማለት በቅድሚያ መጋቢት 30 ቀን 1979 ዓ.ም ከዚያም በ15/2/97 ዓ.ም የAፈጻጸም ትEዛዝ መስጠቱን ከመዝገቡ የተረዳን ሲሆን 2ኛው የAፈጻጸም ትEዛዝ ከተሰጠ በኋላ በፍርድ Aፈጻጸም Eንዲሸጥ ትEዛዝ የተሰጠበት መጋዘን ላይ መብት ያለኝ ስለሆነ Aፈጻጸሙ በዚህ መጋዝን ላይ ላቀጥል Aይገባም በማለት የAሁን Aመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት መቃወሚያ Aቅርቦ Aፈጻጸሙን በጊዜው ይዞት የነበረው የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መቃወሚያው ለፍርድ ባለመብት Eንዲደርስ በማድረግ Aከራክሮ መቃወሚያው በAግባቡ Aልቀረበም የሚልበትን ምክንያት በዝርዝር Aስፍሮ ተቀባይነት የለውም ብሎ Aስቀድሞ በተሰጠው የAፈጻጸም ትEዛዝ መሰረት ይሄው መጋዘን ተሽጦ በውሳኔው ከፍርድ ባለEዳዎች የሚፈለገው ገንዘብ ለፍርድ ባለመብት Eንዲከፈል በማለት ትEዛዝ ሰጥቷል።
Aመልካች በዚሁ ትEዛዝ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ትEዛዝ ጉድለት የልለው ነው በማለት ይግባኙን ባለመቀበል ይህንኑ የሥር ፍ/ቤትን ትEዛዝ Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎትም Aቤቱታውን መርምሮ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ይህም ችሎት በቅድሚያ የተመለከተው የAሁን Aመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aፈጻጸሙን በመቃወም ለፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረበው Aቤቱታ ለፍርድ ባለመብት ብቻ Eንዲደርስ ተደርጐ የፍርድ ባለEዳዎች በዚህ ላይ ክርክራቸውን ሳያቀርቡ ትEዛዝ መስጠቱን Aግባብነት በተመለከተ ነው።
በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ 3ኛ ወገኖች መብት ያቋቋምን ስለሆነ በዚህ ንብረት ላይ Aፈጻጸም ላቀጥል Aይገባም በማለት 3ኛ ወገኖች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 418/1/ መሰረት መቃወሚያ ሲያቀርቡ ተከራካሪ ወገኖች ይህንኑ መብት የሚቃወሙ ከሆነ ፍ/ቤቱ የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ ውሳኔ Eንደሚሰጥ ከተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 ከፍ ብሎ ከተመለከተውና ከቁጥር 419 ድንጋጌ በግልጽ መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ በፍርድ Aፈጻጸም Eንዲሸጥ የተባለው መጋዘን የ1ኛ የፍርድ ባለEዳ ንብረት ነው Eንደተባለ በትEዛዙ ላይ የተመለከተ ሲሆን በዚህ ንብረት ላይ ተቃዋሚው የAሁን Aመልካች Aፈጻጸሙን በመቃወም Aቤቱታ ሲያቀርብ ከላይ ከተጠቀሰው የሥነ ሥርAት ሕጉ ድንጋጌ Aኳያ Aቤቱታው ለፍርድ ባለመብቱና ለባለEዳዎች ደርሶ የሁሉንም ወገኖች ክርክር በመስማት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 419 መሰረት ፍ/ቤቱ ውሳኔ መስጠት ሲገባው Aቤቱታው ለፍርድ ባለመብት ብቻ Eንዲደርስ በማድረግ ለዚህ Aቤቱታ ምክንያት የሆነውን ትEዛዝ መስጠቱ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ጉድለት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 41092 በሰኔ 22 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ የፍድራል ከ/ፍ/ቤትም በመ/ቁ. 41120 በታህሣሥ 10 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት ያቀረበው Aቤቱታ ለፍርድ ባለEዳዎችም Eንዲደርስ ተደርጐ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ Eንዲሰጥበት ጉዳዩ ለፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተመልሷል።
በዚህ ችሎት ትEዛዝ የቀረበው መዝገብ በመጣበት Aኳኋን ይመለስ።
No topics extracted.
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።