No summary available.
ጥቅምት 26 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ Aለሚቱ ተረፈ ተጠሪ፡- የትግል ፍሬ ልብስ ስፍት ማህበር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ በAፈፃፀም የተያዘን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፍድራል መጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት Aመልካች የፍርድ ባለመብት፤ ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለEዳ ነበሩ። Aመልካች ለAፈፃፀም ያቀረበችው ውሣኔ በሰኔ 26 ቀን 1996 ዓ.ም በሽምግልና ጉባዔ ተሰጠ የተባለው ነው። የፍርድ ባለAዳው ለAፈፃፀም ክሱ በሰጠው መልስ ለAፈፃፀም የቀረበው ውሣኔ በAስታራቂ ሽማግልዎች የተሰጠ የድርድር ሃሣብ Eንጂ በፍ/ቤት የሚፈፀም ውሣኔ Aይደለም በማለት የተከራከረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ይህን ክርክር በመቀበል ለAፈፃፀም የቀረበው ውሣኔ ስልጣን ባልተሰጣቸው Aስታራቂ ሽማግልዎች የተሰጠ ነው። በግልግል ዳኞች Eንደተሰጠ ተቆጥሮ የሚፈፀም Aይደለም በማለት የAፈፃፀም ክሱን ዘግቶAል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ስህተት የለበትም በማለት ይግባኙን ውድቅ AድርጎAል። Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች ህዳር 17 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪውን Aስቀርበን ክርክሩን Aሰምተናል። በሰበር ችሎቱ Eንዲመረመር የተፈለገው ነጥብ የሥር ፍ/ቤቶች Aመልካች ለAፈፃፀም ያቀረበችው ውሣኔ በፍ/ቤት ላፈፀም Aይችልም ማለታቸው Aግባብ ነው ወይ? የሚለው ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ፣ ከቀረበው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል Eንደተመለከተው Aመልካች ለAፈፃፀም ያቀረበችው ውሣኔ በ26.1A.96 ዓ.ም የተሰጠው ነው። ይህ ውሣኔ ሦስት Aባላት ባሉት የሽምግልና ጉባዔ የተሰጠ ነው። የሽምግልና ጉባዔው ላቋቋም የቻለው ጉዳዩ ስለህበረት ስራ ማህበራት በወጣው Aዋጅ ቁ. 147/91 መሰረት መታየት ያለበት በሽምግልና ነው ተብሎ በፍ/ቤት ቀደም ሲል በመበየኑ ምክንያት Eንደሆነም ከመዝገቡ ተመልክተናል። በዚህ መሰረት የሽምግልና ጉባዔው ከተቋቋመ በኋላም Aመልካች በከሣሽነት፤ተጠሪ ደግሞ በተከሣሽነት ቀርበው ተከራክረዋል። በመጨረሻም ጉባዔው ውሣኔ ሰጥቶAል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ የሽምግልና ጉባዔው በሰጠው ውሣኔ ላይ ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ይግባኝ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶAል። ፍ/ቤቱም የሽምግልና ጉባዔውን ውሣኔ AጽንቶAል። Aመልካች የAፈፃፀም ክሱን ያቀረበችው ከዚህ በኋላ ነው።
Eንደምንመለከተው በፍ/ቤት ቀደም ሲል በተሰጠው ብይን መሰረት ሦስት Aባላት ያሉት የሽምግልና ጉባዔ ከመቋቋሙም በላይ፤ Aመልካች Eና ተጠሪም የጉባዔውን ስልጣን በመቀበል ቀርበው ተከራክረዋል። በመሆኑም ውሣኔውን የሰጠው የሽምግልና ጉባዔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 215(1) Eንደተመለከተው በፍ/ቤት ላፈፀም የሚችል ውሣኔ ላሰጥ የሚችል Aካል ነው ማለት ነው። በግልግል ወይም በቤተዘመድ ሽምግልና ዳኞች የተሰጠ ውሣኔ የሚፈፀመው በመደበኛ ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ በሚፈፀምበት Aይነትና ሁኔታ Eንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 319(2) በግልጽ ተመልክቶAል። የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ግን ይህን በግልጽ የተመለከተውን ሕግ የተከተለ 370 371 Aይደለም። ስለዚህም ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
በዚህ ጉደይ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 3A58 ግንቦት 5 ቀን 1997 ዓ.ም Eና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 39254 ጥቅምት 23 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻሉ። ውሣኔው ለሰበር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ። መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የሦስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ የሰ/መ/ቁ. 28A19 IXY 1 k” 2AAA ¯.U ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ብርሃኔ ገ/EግዚAብሕር - ጠበቃ መሰለ ገ/ጊዮርጊስ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ገርጊስ ናይዝጊ - ጠበቃ ወንድሙ ግዛው መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
No topics extracted.
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በAመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የጋራ ንብረት ክፍፍልም በተመለከተ ፍ/ቤቱ ውሣኔ ሲሰጥ Aሁን ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነው በወረዳ 19 ቀበል 55 ክልል የሚገኘው ቁጥር 1A8 የሆነውን ቤት የገበያ ዋጋ ግምት ግማሽ የAሁን ተጠሪ ለAሁን Aመልካች ሰጥተው ቤቱን Eንዲያስቀሩ ተጠሪ በዚህ መልኩ የቤቱን የገበያ ዋጋ ግማሽ ለAመልካች ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ ግራ ቀኙ ተስማምተው ቤቱን በገበያ ዋጋ ሸጠው የቤቱን ሽያጭ ዋጋ ገንዘብ ለሁለት Eንዲካፈሉ በዚህ መልኩም ቤቱም ለመሸጥ ካልቻሉም በፍርድ Aፈፃፀም መምሪያ በኩል በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡን Eኩል Eንዲካፈሉ የሚል ውሣኔ ሰጥቶ በዚሁ ውሣኔ መሰረት Aፈፃፀሙ ቀጥሎ ፍ/ቤቱ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት Aስተዳደር ቤቱን በመሐንዲስ Aማካይኝነት ገምቶ ውጤቱን Eንዲልክ ትEዛዝ ሰጥቶ የቤቱ ግምት ብር 83‚596.61 Eንደሆነ በመግለጽ ክፍለ ከተማው ለፍ/ቤቱ መልስ በመስጠቱ የዚህን ግምት ግማሹን ተጠሪ ለAመልካች ሰጥተው ቤቱን Eንዲያስቀሩ በማለት የAፈፃፀም ትEዛዝ ሰጥቶ በዚሁ ትEዛዝ Aመልካች ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ 372 373 ቅሬታቸውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ Aፈፃፀሙ የቀጠለው በፍርዱ መሰረት ስለመሆኑ ለሰበር ቀርቦ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ የሚሻውም የጉዳዩ ጭብጥ Aፈፃፀሙ የቀጠለው በፍርዱ መሰረት ነው ወይንስ Aይደለም የሚለው ሲሆን በዚሁ ነጥብ ላይ በመመስረት Aቤቱታው ተመርምሯል።
በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የጋራ ንብረት ክፍፍልን Aስመልክቶ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
1A32A መጋቢት 21 ቀን 1996 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሣኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ መሰረትም ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነው በወረዳ 19 ቀበል 55 ክልል የሚገኘው ቁጥር 1A8 የሆነው የጋራ ቤት ከላይ Eንደተመለከተው የገበያ ዋጋ ግምቱን ተጠሪ ለAመልካች በመስጠቱ ቤቱን Eንዲያስቀሩ ፈቃደኛ ካልሆኑም በሁለቱ የጋራ ስምምነት በገበያ ዋጋ ተሸጦ የሽያጩን ገንዘብ Eኩል Eንዲካፈሉ ይህም ካልተቻለ በፍርድ Aፈፃፀም መመሪያ Eኩል በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡን Eኩል Eንዲካፈሉ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ሆኖም ግን Aፈፃፀሙ ሲቀጥል በዚሁ ውሣኔ መሰረት መፈጸም ሲገባው የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት የሆነው ቤት በክፍለ ከተማው መሐንዲስ በኩል Eንዲገመት መደረጉ ከውሣኔ ያፈነገጠ ከመሆኑም በላይ በውጤት ደረጃም ቢሆን የመሐንዲስ ግምትና የገበያ ዋጋ ልዩነት Eንዳለው የሚታመን ስለሆነ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው የAፈፃፀም ትEዛዝ በመ/ቁ. 1A32A መጋቢት 21 ቀን 1996 ዓ.ም. ፍ/ቤቱ ከሰጠው ውሣኔ ጋር የተጣጣመ ሆኖ Aልተገኘም። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዳዩ በይግባኝ ሲቀርብለት ይህንኑ ስህተት ማረም ሲገባው ይግባኙን ሳይቀበል በመቅረቱ በAግባቡ ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 14724 በ23/9/98 ዓ.ም. የሰጠው የAፈፃፀም ትEዛዝ Eንደዚሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ19/3/99 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 1A32A መጋቢት 21 ቀን 1996 ዓ.ም. በተሰጠው ውሣኔ መሰረት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት በገበያ ዋጋ Aስገምቶ የግምቱን ግማሽ የAሁን ተጠሪ ወ/ሮ ገርጊስ ናይዝጊ ለAሁን Aመልካች ለAቶ ብርሃኔ ገ/EግዚAብሕር በመስጠት ቤቱን Eንዲያስቀሩ በዚህ መልኩ ተጠሪ ካልተስማሙ ቤቱን በጋራ በገበያ ዋጋ ሸጠው ገንዘቡን Eንዲከፋፈሉ ይህም ካልተቻለ ቤቱ በፍርድ Aፈፃፀም መመሪያ በኩል በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡን Eኩል Eንዲከፋፈሉ Eንዲያደርግ ጉዳዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።