No summary available.
ሐምል A3 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ሂ\ƒ መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የባህርዳር ልዩ ዞን ገንዘብ መምሪያ Aልቀረበም መልስ ሰጭዎች፡- 1. የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ነገረፈጅ Aቶ ደመቀ ተሾመ ቀረበ 2. ሙክታር መሐመድ Aልቀረበም መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው የA.ብ.ክ.መ.ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. A2A96 ግንቦት 3A ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ላይ ነው።
የነገሩም መነሻ Aመልካች የፍርድ ባለመብት ሆኖ በግብር Eዳ ምክንያት ያስወሰነውን ገንዘብ ለማስከፈል የሁለተኛ የፍርድ ባለAዳ ንብረት የሆነው በባህርዳር ከተማ ወረዳ A2 ቀበል 13 በካርታ ቁጥር 9333 ተመዝግቦ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት Eንዲሸጥ Aፈፃፀሙን ለያዘው ለምE/ጎጃም መስ/ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ጠይቋል።
ይህም ፍ/ቤት ይህ በAፈፃፀም የተመራው ንብረት በEርግጥም የሁለተኛው የፍርድ ባለመብት መሆኑ ከተረጋገጠ በሐራጅ ይሸጥ ዘንድ ተገምቶ Eንዲቀርብለት የባህርዳር ከተማን ማዘጋጃ ቤት Aዟል። ማዘጋጃ ቤቱም ይኸው ይገመት የተባለው ንብረት በ1ኛ መልስ ሰጭ Eና በIት/ያ ንግድ ባንክ የብድር ገንዘብ ምክንያት በዋስትና የተያዘ መሆኑን ገልፆ የግምቱን ሥራ ሰርቶ ውጤቱን Aስተላልፏል።
በግምቱም መነሻ ጨረታ ተደርጎ ገዢው Eንደታወቀ ከሽያጩ ገንዘብ የፍርድ ባለመብቱ የጠየቀው ይከፈል፤ ተራፊው ለፍርድ ባለEዳው ይመለስለት ሲል የከፍተኛው ፍ/ቤት ትEዛዝ ሰጥቷል። ይህ ትEዛዝ ከተሰጠ በኋላ የAሁን 2ኛ መልስ ሰጭ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ.ቁ. 418 መሰረት ጨረታው Eንዲፈርስ Aቤቱታ Aቅርቧል። የAቤቱታውም ፍሬ ቃል በሐራጅ ይሸጥ የተባለው ንብረት በEዳ ምክንያት በመያዣነት የተያዘ መሆኑ በማዘጋጃ ቤት መረጋገጡ ሲታወቅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 423/2//ለ/ መሰረት በወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ ላይ በመያዣ መያዙ መገለጽ ሲኖርበት ይኸው በሥርዓት ስላልተሟላ፤
Eንዲሁም ይሸጥ የተባለው ንብረት የማይንቀሣቀስ ሀብት Eንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ.ቁ. 426 መሰረት የጨረታ ማስታወቂያም ወጥቶ ለAንድ ወር ያህል መቆየት ሲገባው ይህ የቆይታ ጊዜ Aልተጠበቀም ስለሆነም በAሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ጉድለት የተፈፀመበት ስለሆነ የሐራጅ ሽያጩ በዚሁ ሕግ በቁጥር 445 - 447 በተመለከተው መሰረት ላሰረዝ፤ ላፈርስ ይገባል የሚል ነው።
Aፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤትም ጣልቃ ገብ የክርክሩ ተካፋይ ሆኖ መያዣ የተሰጠበትን የEዳ መጠን ባልገለፀበት ሁኔታ በቁጥር 423(2)(ለ)መሰረት የመያዣ ልኩን ማወቅ ስለማይቻል በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በመያዣ የተያዘ ንብረት መሆኑ Aልተገለፀም የሚለው መከራከሪያ ነጥብ ተቀባይነት የለውም።
የጨረታ ማስታወቂያው ማሟላት የሚገባውን Aላሟላም ከመባሉ በቀር የሽያጩ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ተከናውኗል። የማጭበርበር ተግባር ተፈጽሞበታል Aልተባለም ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 445 መሰረት የተደረገውን የጨረታ ሽያጭ ማፍረስ Aይቻልም Eንዲሁም የጨረታው ሽያጭ ከፀደቀ Eና ባለመብቱ በEዳ የሚፈልገውን ገንዘብ ከወሰደ Eና ተራፊው ደግሞ ለባለEዳው ከተመለሰ በኋላ ሽያጩ ይፍረስ ማለቱ የሐራጅ ገዥውን መብት የሚጎዳ በመሆኑ ጨረታው Eንዲሰረዝ የቀረበውን ጥያቄ Aልተቀበልነውም በማለት ወስኗል።
የይግባኝ Aቤቱታ የቀረበለት የክልሉ ጠ/ፍ/ቤትም በጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤት Aስቀድሞ በመያዣ በተያዘ ንብረት ላይ ለልላ Eዳ ማስፈፀሚያ Eንዲውል ጥያቄ ሲቀርብለት በሐራጅ ማስታወቂያው ላይ በመያዣ መያዙን ሣይገልጽና ጨረታውም በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ማስታወቂያው ለAንድ ወር መቆየቱን ሣያረጋግጥ ጨረታው መካሄዱን በተቃውሞ Aማካኝነት Eንደተረዳ ጨረታው Aንዲፈርስ ማድረግ ሲገባው ይህን ሣያደርግ ሽያጩ Eንዲከናወን Aድርጎ ገንዘቡ ለ1ኛ መልስ ሰጭ ለAሁን Aመልካች Eና ለAሁኑ ሁለተኛ መልስ ሰጭ Eንዲከፈል ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለ በመሆኑ ጨረታውን Aፍርሰን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 447(5) መሰረት ገንዘቡ ለገዥ ያለ ወለድ Eንዲመለስ በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮ ወስኗል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ይታረምልን በማለት ነው። በAቤቱታው የተጠየቀውም ዳኝነት፣
በዚህም መሰረት ቀርቦ የመያዣ ልኩን ሣይገልፅ በሐራጅ ማስታወቂያው ላይ ንብረቱ በመያዣ የተያዘ መሆኑ Aልተገለፀም በማለት ዘግይቶ ላከራከርበት ስለማይቻል፡-
No topics extracted.
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁ. 423(2) (ለ) Eና 426 ን መሰረት Aድርጎ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ይታረምልን የሚል ነው።
Aመልካችና 1ኛ መልስ ሰጭ በዚህ ሰበር ችሎት ባደረጉት የቃል ክርክር በሥር ፍ/ቤት ያደረጉትን ክርክር በማጠናከር ተከራክረዋል።
Eኛም ጉዳዩን Aግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
የAሁን መልስ ሰጭ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 415 መሰረት በAፈፃፀም ክሱ ጣልቃ ለመግባትና ጣልቃ ገብቶም የጨረታውን ሽያጭ በማስረከብ ያቀረባቸው የመከራከሪያ ነጥቦች ሁለት ናቸው Aንደኛው የAሁን Aመልካች ለEዳ ማስፈፀሚያነት Eንዲውል የመራው ንብረት በ1ኛ መልስ ሰጭ የብድር ገንዘብ ምክንያት በመያዣነት የተያዘ መሆኑን Eያወቀ Eንዲሸጥ ማድረጉ ተገቢ Aይደለም የሚል ሲሆን ልላውና ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የAሻሻጥ ሂደቱ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌውን የተከተለ Aይደለም የሚል ነው።
የመጀመሪያውን ነጥብ በሚመለከት ለጉዳዩ Aግባብነት ያለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3A59(1) የተመለከተን Eንደሆነ ፣ 1ኛ/ መልስ ሰጭ ተበዳሪ ለሆነው ለሁለተኛው መልስ ሰጭ በሰጠው የብድር ገንዘብ ምክንያት በሐራጅ ይሸጥ የተባለውን ንብረት በመያዣ የያዘው ስለመሆኑ የተካደ Aይደለም። ክርክር የተነሣውም መያዣ ሰጭው ይህንኑ በመያዣ የተያዘውን ንብረት ለልላ ሦስተኛ ወገን በማስተላለፉ ሣይሆን ልላ ገንዘብ ጠያቂ ለEዳ ማስፈፀሚያነት ተሸጦ Eንዲከፈለው በማስያዙ ክሱን Eንዲህም ያለ ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ የማይንቀሣቀስ ንብረት መያዣ መጠቀምን በሚመለከተው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3A59(1) መሰረት ለAመልካች በቅድሚያ የመያዣ መብት የተሰጠው በመሆኑ ልላ ገንዘብ ጠያቂ ከሆነው ከAሁኑ Aመልካች ቀድሞ በብድሩ ምክንያት የሚጠይቀውን ገንዘብ Eንዲከፈለው የመጠየቅ መብት የሚሰጠው ካልሆነ በቀር Aስቀድሜ በመያዣ ይዤዋለሁ በመያዣ የያዝኩት መሆኑን Aመልካች Eያወቀ Eንዲሸጥ መጠየቅ Aልበረበትም ሲል የጠየቀው ዳኝነት ሕጋዊ መሰረት ያለው Aይደለም ለምን ቢባል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3A84 Eንደተመለከተው ምንም Eንኳ Aንድ ንብረት በEዳ ምክንያት በመያዣነት ሲያዝም ባለEዳው የህንኑ ንብረት ለመሸጥ ለመለወጥ የሚችል በመሆኑ መያዣ የያዘው ገንዘብ ጠያቂ ያለው መብት ቢኖር ከላይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3A59(1) መሰረት ገንዘብ በቅድሚያ የማግኘት መብት ብቻ ነው ። ከዚህም የምንረዳው በመያዣ የተያዘ ንብረት ላሸጥ የሚችል መሆኑን ነው።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም በAንድ በኩል በAሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ጉድለት የተፈፀመበት ነው የሚለውን በውሣኔው መሰረት ካደረገ በኋላ በስተመጨረሻ ጨረታው ፈራሽ ነው የሽያጩ ገንዘብ ለገዢው ያለወለድ ይመለስለት በማለት መወሰኑ በውስጠ ታዋቂነት ይህንኑ ንብረት 1ኛ መልስ ሰጭ Aስቀድሞ በመያዣነት ቢያዝም መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ላሸጥ Aይገባውም የሚለውን መልEክት የያዘ ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም የተደረገው የሐራጅ ሽያጭ ተሰርዟል በሚለው ጉዳዩን ቋጭቶ መቆሙ ከላይ በተመለከተው ምክንያት የሕግ ስህተት ፈጽሟል።
በAሁን Aመልካች ጠያቂነት ይኸው ይሸጥ የተባለው ንብረት ለEዳ ማስከፈያ Eንዲውል ማሸጥ ይቻል ዘንድ ተገምቶ Eንዲቀርብ ሲታዘዝ በልላ የብድር ገንዘብ ምክንያት በመያዣነት የተያዘ መሆኑን ገልፆ Eንዲገምት የታዘዘው ማዘጋጃ ቤት Aፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት Aስታውቋል። Eንደ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 423(2)(ለ) መፈፀም ይቻል ዘንድ ፍርድ ቤቱ በEራሱ Aነሣሽነት የመያዣውን ልክ ምን ያህል Eንደሆነ ማዘጋጃ ቤቱን በትEዛዝ ጠይቆ መረዳት ሲቻል 1ኛ መልስ ሰጭ የክርክሩ ተካፋይ ሆኖ የመያዣ ልኩን ባላሣወቀበት ሁኔታ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ይህ Aልተገለፀም መባሉ ተገቢነት የለውም ሲል የሰጠው ምክንያት ተቀባይነት ያለው Aይደለም።
Eንዲሁም የማይንቀሣቀስ ንብረት በሐራጅ Eንዲሸጥ በማስታወቂያ በተገለፀ ጊዜ ማስታወቂያው ለ3A ቀናት ሣይቆይ በሐራጅ ላሸጥ Eንደማይችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 426 Aስገዳጅነት ባለው ሁኔታ ተደንግጎ Eያለ ይህ ጊዜ ሣይጠብቅ ለ16 ቀናት ብቻ ቆይቶ Eንዲሸጥ መደረጉ ሥነ ሥርዓታዊ ጉድለት የተፈፀመበት መሆኑን ስለሚያመለክት በEነዚህ ሁለት ምክንያቶች የሽያጩ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ መፈፀሙን ስለተረዳን ሽያጩ Eንዲፈርስ መደረጉ ተገቢ ሆኖ Aግኝተነዋል።
ይሁን Eንጂ የመጀመሪያው የሐራጅ ሽያጭ Aሻሻጥ ሥርዓት ጉድለት ተገኝቶበት Eንዲፈርስ ከተደረገ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለውን በሚመለከት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 447(5) መሰረት ገዥ ነው ተብሎ ለነበረው ወገን የንብረቱ ዋጋ ከEነ ወለዱ ወይም Eንደነገሩ Aካባቢ ሁኔታ ያለወለድ ገንዘብ የተቀበለው ሰው Eንዲመልስ ይደረጋል የሚለው ከመገለፁ በቀር ልላ የተቀመጠ ውጤት የለም ። ሆኖም የሸያጩ ሥርዓት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በማጭበርበር ምክንያት Eንዲፈርስ ከተደረገ የፍርድ ባለመብቱ የጠየቀውን ገንዘብ Eንዲያገኝ ባለEዳውም ግድታውን Eንዲወጣ ለማድረግ ሲባል ተገቢ በሆነ መንገድ Eና ከማጭበርበር ተግባር ነፃ በሆነ ሁኔታ በድጋሚ ሐራጅ ንብረቱ ላሸጥ Eንደሚችል የሚያከራክር ስላልሆነ ንብረቱ በድጋሚ ሐራጅ ላሸጥ ይገባል ብለናል።
ንብረቱ በድጋሚ ሐራጅ በሚሸጥበት ጊዜ በሽያጩ ገንዘብ ላይ የቀዳሚ መብት ያለው ማን ነው? የሚለውን በሚመለከት በAመልካችና በ1ኛ መልስ ሰጭ መካከል የሚነሣውን ክርክር Aግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ለAብነትም ያህል በAዋጅ ቁጥር 286/94 በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3A59 መሰረት ታይቶ ተገቢው ዳኝነት ላሰጥበት ይገባል።
ው ሣ ኔ
በምE/ጎጃ መስ/ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት Aማካኝነት የተደረገው የሐራጅ ሽያጭ ፈርሷል። ድጋሚ ጨረታ ይካሄድ በጨረታው ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ የቀዳሚ መብት ላለው ወገን ክፍያው ይፈፀም።
የሥር ፍ/ቤቶች በጉዳዩ ላይ የሰጡትን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ሽረናል። መዝገቡ ተዘግቷል።