No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 25A31 ታህሳስ 1 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ Aልታየወርቅ ኃ/ማርያም - ጠበቃ AርAያ ተጠሪ፡- Aቶ ዓለማየሁ ገለቱ - ጠበቃ ጌታቸው Eንግዳ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍርድ ባለመብት የAሁን ተጠሪና በፍርድ ባለEዳው መካከል Aፈፃፀም ቀጥሎ የAሁን AAመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aፈጻጸሙን በመቃወም ያቀረቡት Aቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለተውም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ውድቅ በማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የክርክሩ ሂትም ባጭሩ ሲታይ የAሁን Aመልካች በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት ባቀረቡት Aቤቱታ Aፈጻጸም Eየቀጠለበት ያለው በወረዳ 25 ቀበል A1 ክልል የሚገኘውና በሟች Aቶ Aበራ ገብረስላሴ ስም የተመዘገበውን የቤ/ቁ. 65A የሆነውን ቤት ሰኔ 21 ቀን 1995 ዓ.ም. በተፃፈ ውል ከሟች ወራሾች ሕጋዊ ወኪል ከሆኑት ከፍርድ ባለEዳ ከወ/ሮ Aልማዝ ከበደ ላይ በብር 14A ሺህ በመግዛት ቤቱን ተጨማሪ ገንዘብ በማውጣት ያሻሻልኩት ሲሆን የፍርድ ባመብት ከቤቱ ሽያጭ ገንዘብ ላይ ድርሻቸውን መጠየቅ ሲችሉ Aመልካች የገዙት ቤት በሐራጅ Eንዲሸጥ ያቀረቡት ጥያቄ Aግባብነት ስለልለው የሐራጅ ሽያጩ ቀሪ Eንዲሆን ይታዘዝልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤትም የፍርድ ባለመብትን ክርክር ከተቀበለ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ Aመልካችና የፍርድ ባለEዳ ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል የፍርድ ባለመብት Eስካልተስማሙ ድረስ ከሽያጩ ገንዘብ ላይ ድርሻውን Eንዲቀበሉ የማይገደዱ ከመሆኑም በላይ Aመልካች በሐራጅ Eንዲሸጥ በተባለው ቤት ላይ ቀዳሚ መብት የልላቸው በመሆኑ Aቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት Aፈጻጸሙ Eንዲቀጥል ትEዛዝ ሰጥቷል።
ይግባኝ የቀረበለትም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ትEዛዝ Aጽንቶቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ለሰበር ያስቀርባል ብሎ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ Aመልካች ገና ከመነሻው Aቤቱታቸውን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.418 መሰረት ማቅረባቸው Aግባብነት ነበረውን? የሚለው ሆኖ ስለተገኘ ከዚሁ Aኳያ ተመርምሯል።
በዚህ ሰበር ችሎት ግራ ቀኙ ክርክር ሲያደርጉ ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነውና በወረዳ 25 ቀበል A1 ክልል የሚገኘው ቁጥር 65A የሆነው ቤት የፍርድ ባለመብት በነበሩት በAሁን ተጠሪና የፍርድ ባለEዳ በነበሩት በወ/ሮ Aልማዝ ከበደ መካከል ዋናው ክርክር ሲደረግ በዚሁ ቤት ላይ ፍርድ ያረፈበት መሆኑን ግራ ቀኙ ተጠይቀው Aረጋግጠዋል። ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ ፍርድ Aርፎበታል ከተባለ ደግሞ ይሄው ፍርድ ላሰረዝልኝ ይገባል የሚለው ወገን Aቤቱታ ማቅረብ ያለበት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት Eንጂ በ418 መሰረት ላሆን Aይችልም።
ምክንያቱም ሁለቱ የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች የተለያየ ዓላማና ውጤት ያላቸው ስለሆነ ነው።
360 361 በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aቤቱታ Aቅራቢ በዋናው ፍርድ ላይ ምንም ዓይነት ክርክር የልላውና Aፈጻጸም Eንዲቀጥል ትEዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት Aለኝ የሚል ወገን መሆን Aለበት።
በተያዘውም ጉዳይ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ የፍርድ ውሣኔ Eስከተሰጠ ድረስ ከላይ በተጠቀሰው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት Aመልካች ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት መቃወሚያ ማቅረብ ሲገባቸው ፍርድ ባረፈበት ንብረት ላይ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aቤቱታ ማቅረባቸው ከሥነ ሥርዓት ውጭ የቀረበ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሐል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ከሥነ-ሥርዓት ውጪ የቀረበውን Aቤቱታ ከመነሻው መቀበል ያልነበረበት ቢሆንም ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሰጠው ትEዛዝ ግን Aቤቱታውን ባለመቀበል ስለሆነ ከውጤት Aኳያ የሚነቀፍ ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11745 የካቲት 3A ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ Eንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46A67 ግንቦት 9 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ ከውጤት Aኳያ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
Aመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aቤቱታ ለማቅረብ Aይችሉም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
No topics extracted.
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።