No summary available.
ታህሣሥ 17 ቀን 2AAA ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡- Aቶ ደስታ ሰርዳ ተጠሪ፡- የመተከል ዞን ፍትህ መምሪያ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ክርክር የተጀመረው በስር የAፈፃፀም ተከሣሽ በነበረው Aቶ Aምሣሉ ኤቢሣ ላይ ያስፈረደበትን ገንዘብ ለማስመለስ የመተከል ዞን ፍትህ መምሪያ የAፈ/መ/ቁ. A1378 Aስከፍቶ የዚሁ የፍ/ባለEዳ የሆኑትን ሁለት የመኖሪያ ቤቶችና Aንድ መጋዘን በመሐንዲስ Aስገምቶ ለመተከል ዞን ከ/ፍ/ቤት በማቅረቡ፣ የAሁኑ Aመልካች ከመኖሪያ ቤቶቹ መካከል በኤበች በር የሚገኘውን ግምቱ 6,34A ብር የሆነውን ቤት ቀድሞ ለEኔ በሽያጭ ስለተላለፈልኝ Aፈፃፀሙ በቤቱ ላይ ላቀጥል Aይገባም ሲሉ በመቃወም በመቅረባቸው ነው። ከማመልከቻውም ጋር ቤቱን ከAፈ/ተከሣሹ ላይ ለመግዛታቸው ያስረዱልኛል ያሐቸውን ለቤቱ ሽያጭ ለወንበራ ወረዳ ማዘጋጃ ቤት በ17/2/97 በካርኒ ንምራ የተከፈለ ብር 14A Eና የመተከል ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ የፀደቀ የቤት ሽያጭ ውል Aያይዘዋል።
የዞኑ ከ/ፍ/ቤትም የAፈ/ከሣሹ ንብረት ይጣራ ብሎ ከማመልከቱ Aስቀድሞ ቤቱ የተሸጠ በመሆኑ፣ለAፈፃፀም የተያዘው በኤበች በር Aካባቢ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የተቃዋሚው ሕጋዊ ንብረት በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ይለቀቅለት ሲል ወስኗል።
የAሁኑ ተጠሪም በፍ/ቤቱ ውሣኔ ቅር በመሰኘቱ ቅሬታውን ለቤ/ጉ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት በይግባኝ Aቅርቧል። የይግባኙም ፍሬ ሀሣብ በAጭሩ፣ በተጠቀሰው ንምራ ቁጥር የተደረገው ክፍያ የንግድ ትርፍ ግብርና የቴምብር ቀረጥ የተፈፀመበት Eንጂ የስም ማዛወር የተደረገበት Aይደለም፣ ውሉ በዞኑ ፍትህ መምሪያ ቢፀድቅም መፅደቁ የስም ማዛወር ተግባር Aይደለም፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1185 Eና 2878 መሰረት የቋሚ ንብረት ሽያጭ ውል ፀድቆ ስም ዝውውር Aልተፈፀመም የሚል ነው በዚሁ የይግባኝ መዝገብ ውስጥ የስር Aፈፃፀም ተከሣሽ 1ኛ መ/ሰጭ የነበረ ሲሆን በመልሱም የሽያጭ ውሉን በተዋዋይነት መፈረሙንና ውሉም በፍ/መምሪያው ፀድቆ መመዝገቡን ገልፆ የስም ዝውውሩን በተመለከተ በተለያዩ ምክንያቶች በቶሎ Aለመፈፀሙን Aስረድቷል። በይግባኝ መዝገቡ 2ኛ መ/ሰጭ የነበረው የAሁን Aመልካች በበኩሉ ቤቱን በሕጋዊ መንገድ ለመግዛቴ በበቂ ማስረጃ ያስረዳሁ በመሆኑ ይግባኙ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል መልስ ሰጥቷል።
የክልሉም ወ/ፍ/ቤት ለውሣኔው መንደርደሪያ ይሆነው ዘንድ፡ ∀የሽያጭ ውል ሰነድ መቅረቡ፣ይህም ውል በፍ/መምሪያው የፀደቀ መሆኑ Eና የሸያጭ ታክስ የተከፈለበት የሰነድ ማስረጃዎች መቅረባቸው ቤቱ ለ2ኛ መ/ሰጪ ተሸጧል ወይም ተዘዋውሯል ማለት Eንችላለን ወይ?∀ የሚል ጭብጥ ይዞ መዝገቡን መርምሯል። በውሣኔውም Aንድ የማይንቀሣቀስ ንብረት ባለሀበትነት በውል ወይም በኑዛዜ ለማስተላለፍ ምዝገባ ወሣኝ መሆኑን፣ ንብረቱ የሚተላለፈው በሽያጭ ከሆነም ሸያጩ ተከናውኖ በሚመለከተው የAስተዳደር ክፍል ርስት መመዝገቢያ ደብተር ተመዝግቦ ስሙ ተዘዋውሮ የምስክር ወረቀት ላሰጠው Eንደሚገባ፣ ይህም ሲሆን ሦስተኛ ወገን መብታቸውን በመንካቱ ንብረቱ Aላግባብ የሚተላለፍ ከሆነ ተቃውሞ በማንሣት መከራከር Eንደሚችሉ የፍ/ብ/ቁ. 1195(1)፣ 1185 Eና 2878 ጠቅሶ Aትቷል። በAጠቃላይ በዚህ ጉዳይ የሽያጭ ውሉ የመመዝገብና የማዛወር ስልጣን በተሰጠው Aካል ስመርስቱ ወደ 2ኛ መ/ሰጪ ባለመዛወሩ፣ ይህ ውል በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ላሆን Aይችልም በማለት የዞኑ ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር Aፈፃፀሙ በቤቱ ላይ ላቀጥል ይገባል ሲል ወስኗል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው የክልሉ ወ/ፍ/ቤት በ3A/5/98 ዓ.ም በመ/ቁ/ AA891 የሰጠውን ውሣኔ ለማስለወጥ የቀረበ ነው። Aመልካች ለዚህ ችሎት Aቤት ያሉት ቤቱን በመተከል ዞን ለፍትህ መምሪያ በፀደቀ ሕጋዊ የሽያጭ ውል መግዛቴ በማንኛውም ወገን ያልተስተባበለ ሆኖ ሣለ፣ስመርስቱ በAመልካች ስም ባለመዘዋወሩ በቻ በቤቱ ላይ መብት የለህም ተብዬ Aፈፃፀሙ Eንዲቀጥል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው በማለት ነው። ተጠሪም ለመልሣቸው የAንድ የማይንቀሣቀስ ንብረት ባለቤት መሆን የሚቻለው በመግዛት ብቻ ሣይሆን በፍ/ብ/ሕጉና በልሎች የማዘጋጃ ቤት ደንቦች መሰረት በርስት መዝገብ ተመዝገቦ የባለቤትነት የምስክር ወረቀት በመያዝ ላሆን ይገባል፤ ስለዚህም Aመልካች በቤቱ ላይ መብት ስለልላቸው Aቤቱታቸው ውድቅ ላደረግ ይገባል ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።Aመልካችም በጽሁፍ የመልስ መልሣቸውን Aቅርበው ቅሬታቸውን Aጠናክረዋል። ይህም ችሎት መዝገቡን በጥሞና መርምሯል። Eንደተመረመረውም በዚህ ጉዳይ መፍትሕ የሚሻው Aብይ ጭብጥ ክርክር የተነሣበትን ቤት Aመልካች የገዙት መሆኑና ውሉም ተመዝግቦና በቤቱ ማህደር ተያይዞ Eያለ፣ የባለቤትነት ስሙ በAመልካች ባለመዘዋወሩ ብቻ በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ላሆን Aይችልም በሚል Aፈፃፀሙ ቤቱ ላይ Aንዲቀጥል መደረጉ Aግባብ ነው ወይ?∀ የሚለው ነው።
No topics extracted.
የቤ/ጉ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ለውሣኔው መሰረት ያደረገው የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2878 የማይንቀሣቀሱ ንብረቶች ሽያጭ ውል ውሎችን ለማፅደቅ ስልጣን በተሰጠው Aካል ከፀደቁ በኋላ ንብረቱ በሚገኝበት ስፍራ በሚገኝ ማዘጋጃ ቤት ወይም የመሬት Aስተዳደር መስሪያ ቤት ርስት መዝገብ ተመዝግቦ ሲገኝ ሦስተኛ ወገኖች በንብረቱ ላይ ለሚጠይቁት መብት መቃወሚያ ላሆን Eንደሚችል ደንግጓል። በዚህ በተያዘው ጉዳይ፣ በAቶ ደስታ ሰርዳ Eና በAቶ Aምሣሉ ኤቢሣ መካከል በጥቅምት 17 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል በኀዳር 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመተከል ዞን ፍ/መምሪያ የፀደቀ ሲሆን የፍትህ መምሪያው የውሉን መጽደቅ Aረጋግጦ ለወንበራ ወረዳ መዛጋጃ ቤት የስም ዝውውሩን Eንዲፈጽምላቸው በኀዳር 1 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ መጠየቁን በዚሁም መሰረት የወረዳው ማዘጋጃ ቤት የቤት ሽያጭ ውሉን ከቤቱ ማኀደር ጋር ማያያዙ ታውቋል። ይህ በEንዲህ Eንዳለ ሻጩ በመታሰሩ Eና በማዘጋጃ ቤቱ የAሰራር ችግር ምክንያት ስመ ንብረቱ በAመልካች ስም ላዘዋወር Aልቻለም። በመሰረቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2878 የሽያጭ ውሉ በ3ኛ ወገን ላይ ውጤት Eንዲኖረው በተዋዋዮቹ ላይ ውላቸውን በመዝገቡ Eንዲፃፍ ከማድረግ የዘለለ ግድታ Aይጥልባቸውም።
ተዋዋዮች በሕግ በተጣለባቸው ግድታ መሰረት ውሉን በሕግ Aግባብ ሥልጣን በተሰጠው Aካል ዘንድ ፈጽመው Eንዲመዘገብ ካደረጉ በኋላ ቀሪ የሚሆነውን የስም ማዛወር ተግባር ላፈጽም የሚችለው የAስተዳደር መ/ቤቱ Eንጂ ተዋዋዮች ራሣቸው ላሆኑ Aይችሉም። በመሆኑም የስም ማዛወሩን ተግባር መ/ቤቱ Aልፈፀመም በሚል ተዋዋች ውሉን ለ3ኛ ወገን መቃወሚያ ላያደርጉት Aይችሉም መባሉ ተገቢ Aይደለም፣ ሕጉም Aይደግፈውም።
ው ሣ ኔ 1/ የቤ/ጉም/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በጥር 30 ቀን 1998 ዓ.ም በመ/ቁ.
AA791 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
2/ በቤ/ጉ/ብ/ክ/መ/የመተከል ዞን ከ/ፍ/ቤት በጥቅምት 15 ቀን 1998 ዓ.ም በመ/ቁ/ 01378 የሰጠውን ውሣኔ Aጽንተነዋል።
3/ Aፈፃፀሙ Aመልካች በገዛው ቤት ላይ ላቀጥል Aይገባም ብለናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ 358 359 የሰ/መ/ቁ. 25A31 ታህሳስ 1 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ Aልታየወርቅ ኃ/ማርያም - ጠበቃ AርAያ ተጠሪ፡- Aቶ ዓለማየሁ ገለቱ - ጠበቃ ጌታቸው Eንግዳ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍርድ ባለመብት የAሁን ተጠሪና በፍርድ ባለEዳው መካከል Aፈፃፀም ቀጥሎ የAሁን AAመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aፈጻጸሙን በመቃወም ያቀረቡት Aቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለተውም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ውድቅ በማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የክርክሩ ሂትም ባጭሩ ሲታይ የAሁን Aመልካች በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት ባቀረቡት Aቤቱታ Aፈጻጸም Eየቀጠለበት ያለው በወረዳ 25 ቀበል A1 ክልል የሚገኘውና በሟች Aቶ Aበራ ገብረስላሴ ስም የተመዘገበውን የቤ/ቁ. 65A የሆነውን ቤት ሰኔ 21 ቀን 1995 ዓ.ም. በተፃፈ ውል ከሟች ወራሾች ሕጋዊ ወኪል ከሆኑት ከፍርድ ባለEዳ ከወ/ሮ Aልማዝ ከበደ ላይ በብር 14A ሺህ በመግዛት ቤቱን ተጨማሪ ገንዘብ በማውጣት ያሻሻልኩት ሲሆን የፍርድ ባመብት ከቤቱ ሽያጭ ገንዘብ ላይ ድርሻቸውን መጠየቅ ሲችሉ Aመልካች የገዙት ቤት በሐራጅ Eንዲሸጥ ያቀረቡት ጥያቄ Aግባብነት ስለልለው የሐራጅ ሽያጩ ቀሪ Eንዲሆን ይታዘዝልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤትም የፍርድ ባለመብትን ክርክር ከተቀበለ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ Aመልካችና የፍርድ ባለEዳ ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል የፍርድ ባለመብት Eስካልተስማሙ ድረስ ከሽያጩ ገንዘብ ላይ ድርሻውን Eንዲቀበሉ የማይገደዱ ከመሆኑም በላይ Aመልካች በሐራጅ Eንዲሸጥ በተባለው ቤት ላይ ቀዳሚ መብት የልላቸው በመሆኑ Aቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት Aፈጻጸሙ Eንዲቀጥል ትEዛዝ ሰጥቷል።
ይግባኝ የቀረበለትም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ትEዛዝ Aጽንቶቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ለሰበር ያስቀርባል ብሎ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ Aመልካች ገና ከመነሻው Aቤቱታቸውን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.418 መሰረት ማቅረባቸው Aግባብነት ነበረውን? የሚለው ሆኖ ስለተገኘ ከዚሁ Aኳያ ተመርምሯል።
በዚህ ሰበር ችሎት ግራ ቀኙ ክርክር ሲያደርጉ ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነውና በወረዳ 25 ቀበል A1 ክልል የሚገኘው ቁጥር 65A የሆነው ቤት የፍርድ ባለመብት በነበሩት በAሁን ተጠሪና የፍርድ ባለEዳ በነበሩት በወ/ሮ Aልማዝ ከበደ መካከል ዋናው ክርክር ሲደረግ በዚሁ ቤት ላይ ፍርድ ያረፈበት መሆኑን ግራ ቀኙ ተጠይቀው Aረጋግጠዋል። ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ ፍርድ Aርፎበታል ከተባለ ደግሞ ይሄው ፍርድ ላሰረዝልኝ ይገባል የሚለው ወገን Aቤቱታ ማቅረብ ያለበት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት Eንጂ በ418 መሰረት ላሆን Aይችልም።
ምክንያቱም ሁለቱ የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች የተለያየ ዓላማና ውጤት ያላቸው ስለሆነ ነው።
360 361 በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aቤቱታ Aቅራቢ በዋናው ፍርድ ላይ ምንም ዓይነት ክርክር የልላውና Aፈጻጸም Eንዲቀጥል ትEዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት Aለኝ የሚል ወገን መሆን Aለበት።
በተያዘውም ጉዳይ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ የፍርድ ውሣኔ Eስከተሰጠ ድረስ ከላይ በተጠቀሰው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት Aመልካች ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት መቃወሚያ ማቅረብ ሲገባቸው ፍርድ ባረፈበት ንብረት ላይ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aቤቱታ ማቅረባቸው ከሥነ ሥርዓት ውጭ የቀረበ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሐል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ከሥነ-ሥርዓት ውጪ የቀረበውን Aቤቱታ ከመነሻው መቀበል ያልነበረበት ቢሆንም ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሰጠው ትEዛዝ ግን Aቤቱታውን ባለመቀበል ስለሆነ ከውጤት Aኳያ የሚነቀፍ ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11745 የካቲት 3A ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ Eንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46A67 ግንቦት 9 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ ከውጤት Aኳያ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
Aመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት Aቤቱታ ለማቅረብ Aይችሉም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።