No summary available.
መጋቢት 9 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- 1. ወ/ሮ መድኃኒት ኃይሉ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ - ነገረ ፈጅ ወይንሸት ቸርነት መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በAመልካቾች በኩል በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ተጠሪ ላከፍል Aይገባም በማለት በሥር ፍ/ቤቶች በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካቾች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ Aመልካቾች በAዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ከተከሳሽ ጋር በተደረገ የብድር ውል በAዳማ ከተማ ቀበል 11 ክልል በካርታ ቁጥር 7AA6/82 የተመዘገበውን ሆቴል መያዣ ሰጥተን ብር 295‚62A.00 /ሁለት መቶ ዘጠና Aምስት ሺህ ስድስት መቶ ሀያ ብር/ ተበድረናል። ከተከሣሽ የተበደርነውን ገንዘብ ሥራ በማጣታችን ምክንያት መክፈል ባለመቻላችን ተከሣሹ በዋስትና የያዘውን ንብረት Aስገምቶ በብር 1‚6A7‚6A7.00 /Aንድ ሚላዮን ስድስት መቶ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር/ በAዋጅ ቁጥር 97/9A መሰረት ለመሸጥ ጨረታ Aውጥቶ የሚገዛ ስለጠፋ ድጋሚ ጨረታ Aውጥቶ ያለAግባብ ከAዋጅ 334 335 ቁጥር 97/9A ውጪ መነሻ ግምቱን በጣም ዝቅ Aድርገ በብር 3AA‚AAA /ሶስት መቶ ሺህ/ ወስዶታል።
ሰለሆነም ተከሣሹ ልዩነቱን ብር 1‚3A7‚6A7.00 /Aንድ ሚላየን ሶስት መቶ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር/ ንብረቱን ከወሰደበት ቀን Aንስቶ ከሚታሰብ 9% /ዘጠኝ በመቶ/ ወለድ ጋር Eንዲከፍል ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሾች ክስና ማስረጃ ለተከሳሽ ደርሶ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ጨረታ ወጥቶ ገዢ ስላልቀረበ ድጋሚ ጨረታ ወጥቶ ከAንድ ልላ ተጫራች ጋር ተወዳድረን ሚያዝያ 19/1991 ዓ.ም. ተከሣሽ ጨረታውን Aሸንፎ በብር 3AA‚AAA /ሶስት መቶ ሺህ/ ሆቴሉን ገዝቷል። ተከሣሽ ሆቴሉን የገዛው በሕጋዊ መንገድ ሰለሆነ ክሱ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትን የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን ከቀረበው ማስረጃና ከሕጉ ጋር Aገናዝቦ መርምሮ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 43A/1/ ሥር Eንደተመለከተው የፍርድ ባለመብት የሆነ ወገን በሚሸጥ ንብረት በጨረታ መሳተፍ የሚችለው ፍ/ቤትን Aስፈቅዶ ሲሆን በዚሁ መሰረት ተከሣሽ ፍ/ቤትን Aስፈቅዶ በጨረታው መሳተፍ ሲገባው ሳያስፈቅድ በጨረታው የተሳተፈ ስለሆነ ተግባሩ ሕገወጥ ነው ካለ በኋላ ተከሣሽ የከሳሾችን ሆቴል በመጀመሪያ ጨረታ ብር 1‚6A7‚6A7.00 መገመቱንና ይህንኑ ሆቴልም በብር 3AA‚AAA.00 መግዛቱን ያመነ በመሆኑ በልዩነት በከሳሾች የደረሰውን ጉዳት ብር 1‚307‚6A7.00 /Aንድ ሚላየን ሶስት መቶ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር/ ተከሣሽ ላከፍል ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሽ በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራቀኙን Aከራክሮ በAዋጅ ቁጥር 97/9A Aንቀጽ 3 Eና 4 Eንደዚሁም በAዋጅ ቁጥር 216/92 Aንቀጽ 1 Eና 2 መሰረት ጨረታ ወጥቶ ገዢ ባለመገኘቱ ባንኩ ንብረቱን ከያዘ ወይም ከወሰደ በመጀመሪያው ጨረታ ላይ በተሰጠው ግምት ያስቀረዋል የሚል ሲሆን ይግባኝ ባይ ባንክ ግን ክርክር የተነሳበትን ሆቴል Eራሱ የያዘው ወይም ያስቀረው ሳይሆን በድጋሚ ጨረታ የሸጠው ስለሆነ በባለEዳው ላይ ጉዳት Aድርሷል ለማለት ስለማይቻል የሥር ፍ/ቤት ጉዳት ደርሷል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ስላልሆነ ይግባኝ ባይ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍል Aይገባም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የAሁን Aመልካቾችም የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ይግባኙ ተቀባይነት የለውም በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.
337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዟል።
ይህም ችሎት የቀረበለትን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ Aመልካቾች በክስ የጠየቁትን ገንዘብ ተጠሪ ላከፍል Aይገባም ተብሎ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ Aግባብነት Aለውን? የሚለው በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ Aኳያ Aቤቱታው ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
No topics extracted.
Aመልካቾች ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነውንና በAዳማ ከተማ የሚገኘውን የሆቴል ንግድ ድርጅት ለተጠሪ መያዣ በመስጠት ብር 296‚620.00 /ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ብር/ መበደራቸውን፣ ብድሩ ባለመከፈሉ ምክንያት በሀራጅ መነሻ ግምት ብር 1‚6A7‚67A.00 /Aንድ ሚላዮን ስድስት መቶ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ብር/ የመጀመሪያ ጨረታ ወጥቶ ገዢ በመጥፋቱ በድጋሜ 2ኛ ጨረታ ወጥቶ ተጠሪና ልላ Aንድ ተጫራች ቀርበው ተጠሪ በብር 3AA‚000.00 /ሶስት መቶ ሺህ/ የጨረታው Aሸናፊ ስለመሆኑ Eነዚህ ፍሬ ነገሮች ግራ ቀኙን Aላከራከሩም።
በባንክ መያዣ የተያዙ ንብረቶችን Aስመልክቶ በወጣው Aዋጅ ቁጥር 97/9A Aንቀጽ 3 መሰረት መያዣ ተቀባይ Eዳው በውሉ ላይ በተመለተው 336 337 ጊዜ ሳይከፈለው ቢቀር ከሰላሣ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ ለመያዣ ሰጭው /ለባለEዳው/ በመስጠት በመያዣ የያዘውን ንብረት መሸጥ Eንደሚችል የተመለከተ ሲሆን በመጀመሪያ ጨረታ ንብረቱ ሳይሸጥ ቢቀር Aዋጅ ቁጥር 97/9A ለማሻሻል በወጣው በAዋጅ ቁጥር 216/92 Aንቀጽ 2/1/ መሰረት ድጋሚ ጨረታ ወጥቶ ገዢ ካልቀረበ ለመጀመሪያው ጨረታ መነሻ በተሰጠው የዋጋ ግምት መሰረት Aበዳሪው ባንክ ንብረቱን ለመውሰድና የባለቤትነት መብቱም በስሙ Eንዲዛወርለት ማድረግ Eንደሚችል ተደንግጓል።
በልላ በኩልም ባንክ በመያዣ የያዘውን ንብረት በሐራጅ የመሸጥ ሥልጣን በሥራ ላይ በሚያውልበት ጊዜ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 394-449 ያሉትን ድንጋጌዎች EንደየAግባብነታቸው ተፈፃሚነት Eንደሚኖራቸው በተቀጠሰው Aዋጅ ቁጥር 97/9A Aንቀጽ 6 ላይ የተመለከተ ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 43A/1/ ላይም የፍርድ ባለመብት የሆነ ወገን በሐራጅ Eንዲሸጥ የተወሰነውን ሀብት ለመግዛት ፍ/ቤትን ማስፈቀድ Eንደሚጠበቅበት ተመልክቷል። ይሁንና የሐራጅ ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ከላይ የተጠቀሱትን የሥነ - ሥርዓት ድነጋጌዎች ባንክ በሥራ ላይ የሚያውላቸው ከጉዳዩ ጋር Aግባብነት በሚኖራቸው ጊዜ Eንደሆነ በAዋጁ ላይ ከመመልከቱም በላይ በAዋጅ ቁጥር 97/9A Aንቀጽ 3 Eና 4 መሰረት ባንኩ የመያዣ ንብረቱን ሲሸጥ ባለEዳውን በመወከል የሚያደርገው ሽያጭ ሆኖ Eንደሚቆጠር በAንቀጽ 5 ላይ የተመለከተ ስለሆነ ባEዳውን ሻጭ Eራሱን ደግሞ ገዢ ማድረግ ስለማይችል ተጠሪ ሽያጩ በAግባቡ ተከናውኗል በማለት ያቀረበው ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ Aልተገኘም።
ሲጠቃለልም ተጠሪ በመያዣ የያዘውን የሆቴል የንግድ ድርጅት ለመሸጥ የመጀመያውን ጨረታ Aውጥቶ ገዢ ሳይቀርብ በመቅረቱ ድጋሚ ጨረታ ሲያወጣም ገዢ ካልቀረበ ሕጉ በጣለበት ግድታ መሰረት በመጀመሪያው የጨረታ መነሻ ዋጋ ንብረቱን መረከብ ሲገባው Eራሱ በጨረታው መሳተፍም ሆነ Aሸናፊ ሆኖ መገኘቱ ከሕጉ ያፈነገጠ ሆኖ ተገኝቷል። ተጠሪ ንብረቱን የተረከበበት Aግባብ ከAዋጁ መንፈስ ውጭ ቢሆንም 2ኛ ጨረታ ወጥቶ ገዢ በመጥፋቱ ምክንያት ለመጀመሪያው ጨረታ መነሻ በተሰጠው የዋጋ ግምት መሰረት ንብረቱን Eንደተረከበው ላቆጠር የሚችል ስለሆነ ንብረቱን በተረከበበት የዋጋ ግምትና ለመጀመሪያው ጨረታ መነሻ በተሰጠው የዋጋ ግምት መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት መክፈል የሚገባው በመሆኑ በዚሁ መሰረት Eንዲከፈል የAዳማ ልዩ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ Aግባብነት ያለው ሆኖ ሳለ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትና የፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ተጠሪ ሽያጩን ያከናወነው በግባቡ ስለሆነ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍል Aይገባም በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
18631