No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ Aክስዮን ማሕበር Aልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1ኛ/ የባህር ዳር ልዩ ዞን Aስተዳደር Aልቀረቡም 2ኛ/ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለAደራ ቦርድ ነገረደጅ Aቶ Aዳነ መጋቡ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ የቀረበው Aመልካች የAማራ ብሕራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥር 4 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የካቲት 5 ቀን 1999 ዓ.ም ያቀረበውን የሰበር Aቤቱታ Aጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በAማራ ብሕራዊ ክልል የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ፍሬ ጉዳዩም Aንደኛ ተጠሪ የAማራ ብሕራዊ ክልል ባወጣው ደንብ መሰረት የ1988 ዓ.ም የቦታ ኪራይ ብር 497,943.54 /Aራት መቶ ዘጠና ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ Aርባ ሦስት ብር ከሀምሣ Aራት ሣንቲም/ Eንዲከፍል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ያልከፈለ በመሆኑ Eንዲከፍል ውሣኔ ይስጥልኝ በማለት በAመልካች ላይ ክስ Aቅርቧል። Aመልካችም ይህ Eዳ የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የመንግሥት የልማት ድርጅት Eንደነበርና ወደ ባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማሕበር ከመቀየሩ በፊት የነበረ ስለሆነ፣ ሁለተኛው ባለEዳ፣ ሦስተኛ ወገን ተከራካሪ፣ /ተከሣሽ/ ሆኖ ጣልቃ Eንዲገባ በጠየቁት መሰረት ፍ/ቤቱ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ Eንዲገባ ትEዛዝ ሰጥቷል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት Aንደኛ ተጠሪ ያቀረበውን ክስና Aመልካቹና ሁለተኛው ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ የቦታውን ዋና ግብር 454,511.99 /Aራት መቶ ሀምሣ Aራት ሺ Aምስት መቶ Aሥራ Aንድ ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሣንቲም/ Eንዲከፍል ወስኗል።
ሁለተኛው ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪ ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ ሁለተኛ ተጠሪ ብር 56,159.44 /ሀምሣ ስድስት ሺ Aንድ መቶ ሀምሣ ዘጠኝ ብር ከAርባ Aራት ሣንቲም/ ብቻ Eንዲከፍል ቀሪውን Eዳ Aመልካች Eንዲከፍል በማለት ወስኗል።
Aመልካች በክሱ ተከሳሽ የሆነው የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማሕበር የተመሰረተው 1992 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ፋብሪካው ወደ Aክስዮን ማሕበርነት ከመለወጡ በፊት የነበረው Eዳ Eኛን የሚመለከት ባለመሆኑና ሁለተኛው ተጠሪ ይህንን Eዳ የመክፈል ግድታ በAዋጅ ቁጥር 182/1992 የተጣለበት ሆኖ Eያለ Aክስዮን ማሕበሩ Eዳውን Eንዲከፍል የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ ስህተት ያለበትና Aክስዮን ማህበሩን ለኪሣራ የሚዳርግ በመሆኑ በሰበር ይታረምልን በማለት Aመልክቷል።
ሁለተኛው ተጠሪ በበኩሉ ወደ Aክስዮን ማሕበሩ የሚተላለፉና የማይተላለፉ Eዳዎችን የመወሰን ሥልጣን ያለው የIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መከፈል ያለበት Eዳ ነው በማለት ያሣወቀን 56,159.44 /ሃምሣ ስድስት ሺ Aንድ መቶ ሃምሣ ዘጠኝ ብር ከAርባ Aራት ሣንቲም/ በመሆኑ ከዚህ ውጭ ያለውን Eዳ Aመልካች መክፈል ይገባዋል የሚል ክርክር Aቅርቧል። Aንደኛ ተጠሪ በበኩሉ Eዳው መከፈል ያለበት Eዳ 318 319 መሆኑን ሁለተኛ ተጠሪና Aመልካች Eንዳልካዱ ገልፆ በሁለቱ መካከል በሚደረገው ክርክር የከተማው Aስተዳደር ማግኘት የሚባውን ክፍያ ሣያገኝ ጉዳዩ Eየተጓተተ በመሆኑ በAጭር ጊዜ ታይቶ Eዳውን ከነወለዱ Eንዲከፍሉ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና የAመልካችና ተጠሪዎች በሰበር ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነው Aመልካች ያለበት Eዳና Aጠቅላይ Aሴቱ Eና መንቀሳቀሻ ካፒታሉ ተለይቶ የባህርዳ ጨርቃጨቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማህበር ተብሎ በAዲስ መልክ በAክስዮን ማህበርነት ከመደራጀቱ በፊት ለAንደኛ ተጠሪ መክፈል የሚገባው የቦታ ግብር Eዳ የመክፈል ኃላፊነት Aለበት ወይስ የለበትም የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል። ከዚህ Aንፃር ብንመዝነው መንግሥት Aመልካች ድርጅት ወደ Aክስዮን ማህበር ከመቀየሩ በፊት የነበሩበትን Eዳዎች በኃላፊነት የሚረከብ Aንድ ተቋም ማቋቋም በማስፈለጉ ምክንያት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለ Aደራ ቦርድን ሥልጣንና ኃላፊነት Eንደገና በመወሰንና ሕግ ያወጣ መሆኑን ከAዋጅ ቁጥር 208/1992 መግቢያ ለመረዳት ይቻላል። የባለAደራ ቦርዱ መሰረታዊ ዓላማም የመንግሥት የልማት ድርጅት ወደግል ይዞታ በሚዛወርበት ወይም ወደ Aክስዮን ማህበር በሚለወጥበት ወይም ወደ ቀድሞ ባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ ወደ Aዲሱ ባለቤት ወደ Aክስዮን ማህበሩ ወይም ወደ ቀድሞ ባለቤቱ የማይተላለፉ ሂሣቦችን መሰብሰብ Eዳዎችን መረከብና ከዚሁ ጋር የተያያዙ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን መከታተል Eንደሆነ በAዋጅ ቁጥር 208/1992 Aንቀጽ 5 ንUስ Aንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ የባለAደራ ቦርዱ ወደ Aክስዮን ማህበርነት የተቀየሩ ወደ ግል የተዛወሩ ወይም ለቀድሞ ባለቤታቸው የተመለሱ የመንግሥት የልማት ድርጅት Eዳዎችን ለመንግሥት Eያቀረበ Eንዲከፈሉ የማድረግ ሥልጣንና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን Aዋጅ ቁጥር 208/1992 Aንቀጽ 6 ንUስ Aንቀጽ 1/ሐ/ ይደነግጋል። በዚህ መዝገብ የባህርዳር ከተማ Aስተዳደር የጠየቀው የመሬት ኪራይ የባህርዳር ጨርቀጨርቅ ፋብሪካ ወደ Aክስዮን ማህበርነት ከመቀየሩ ከAራት ዓመት በፊት የነበረና የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የመንግሥት የልማት ድርጅት በነበረበት 1988 ዓ.ም መክፈል የሚባው Eዳ ነው። Aሁን ያለው የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማህበር 1992 ዓ.ም ህጋዊ ሰውነት ያገኘ ድርጅት በመሆኑ ከጅምሩ በፈረሰውና ወደ Aክስዮን ማህበርነት በተቀየረው የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ስም ያቀረበውን ክስ በኃላፊነት ይዞ መከራከር የሚገባው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለAደራ ቦርድ Eንደሆነ ከAዋጅ ቁጥር 208/1992 Aንቀጽ 5 ንUስ Aንቀጽ 1 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ሁለተኛ ተጠሪ Eዳውን ላለመክፈል የሚያቀርበው ምክንያት የIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ Aላሳወቀኝም የሚል ነው። ሆኖም የመንግሥት የልማት ድርጅቱ ወደ Aክስዮን ማህበርነት ሲቀየር በፕራይቬታይዜበሽን ኤጀንሲ ያልታወቀና ውሣኔ ያልተሰጠበት Eዳ ሁሉ ወደ Aክስዮን ማህበሩ ይተላለፋል የሚል ግልጽ የህግ ድንጋጌ ካለመኖሩም በላይ የዚህ Aይነት የህግ Aተረጓጐም Aክስዮን ማህበሩን ለከፍተኛ ኪሣራ የሚዳርግና የባለAደራ ቦርዱ የተቋቋመበትን መሰረታዊ ዓላማ ጋር የሚቃረን ሆኖ Eናገኘዋለን። በመሆኑም Eዳው Aክስዮን ማህበሩ ከመቋቋሙ በፊት የነበረ Eስከሆነ ድረስ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በወቅቱ ያላወቀውና ውሣኔ ያልሰጠበት Eዳ በAክስዮን ማህበሩ መከፈል ይገባዋል በማለት የሰጠው የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ትርጉምና ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍርዱ ግልባጭ ይተላለፍ።
320 321 2. የAማራ ክልል የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 27 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል። የፍርዱ ግልባጭ ይተላለፍ።
ሁለተኛው ተጠሪ ብር 454,511.99 /Aራት መቶ ሀምሣ Aራት ሺ Aምስት መቶ Aሥራ Aንድ ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሣንቲም/ Eና የከፍተኛው ፍርደ ቤት ውሣኔ ከሰጠበት ከሐምል 27 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፐርሰንት /9%/ ህጋዊ ወለድ ለAንደኛው ተጠሪ ይክፈል ብለናል።
Aመልካችና ተጠሪዎች ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻሉ።
ይህ ፍርድ ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ Aፈጻጸም የሰበር መ/ቁ. 1A489 ሐምል 24 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር ተተኪ መሰረተ ልማት ሚ/ር ነገረ ፈጅ Aቶ ወ/ማርያም ሥዩም ቀረቡ መልስ ሰጭ፡- የቀድሞ ብሕራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ኃ/የተ/የግል ማህበር መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በግራ ቀኙ መካከል የነበረውን የAፈፃፀም ጉዳይ በሚመለከት የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 552A ህዳር 3A ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትEዛዝ Eና የፍ/ከፍተኛው ፍ/ቤትም በይግባኝ ተመልክቶ ይኸው ትEዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይታረምልን በማለት ነው።
ጉዳዩም ባጭሩ Eንደሚከተለው ነው።
የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር ብር 11,9A8, 734 /Aስራ Aንድ ሚላዮን ዘጠኝ መቶ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሣ Aራት ብር/ ከEነ ወለዱ ለመልስ ሰጭ ለብሕራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግል ማህበር Eንዲከፍል ህዳር 23 ቀን 1991 ዓ.ም የተሰጠውን ትEዛዝ መነሻ በማድረግ Aፈፃፀሙ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲታይ ቆይቷል።
ይኸው ፍ/ቤት ክፍያው Eንድት Eንደሚፈፀም ግራ ቀኙ በልሉበት ጉዳዩን ሲከታተል ከቆዩ በኋላ ህዳር 3A ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት ባለEዳ Eዳውን Eንዲከፍል የተለያየ ትEዛዝ ሲሰጥ ቢቆይም Eዳው Aልተከፈለም ። የፍርድ ባለEዳ የሆነው የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር በAዋጅ ቁጥር 256/94 ፈርሶ መብትና ግድታው ወደ መሰረተ ልማት ሚ/ር ተላልፏል። ተተኪው የመሰረተ ልማት ሚ/ር ባለበት ጉዳዩ በመታየት ላይ Eንዳለ በጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት በቁጥር ጠ/8A -ጠ4/A1/11 በ3/8/94 በተፃፈው ደብዳቤ መነሻነት የብሕራዊ መሐንዲሶች ሥራ ተቋራጭ ማህበርን የቀድሞ ባለንብረቶች ይረከቡት ዘንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩ ሲታይ የቆየ ቢሆንም ኮሚቴው ውጤታማ ይሆን ዘንድ የመሰረተ ልማት ሚ/ር ሥራውን መሥራት Aልቻለም ።
ስለዚህ Aስቀድሞ በተወሰነው መሰረት ፍ/ቤቱ Aፈፃፀሙን ከመቀጠል ውጭ Aማራጭ Aላገኘም የሚለውን ምክንያት ካሰፈረ በኋላ የIት/ያ ብሕራዊ ባንክ የመሰረተ ልማት ሚ/ር ካለው ሂሣብ ላይ ህዳር 23 ቀን 1999 ዓ.ም በተሰጠው ትEዛዝ መሰረት ቀንሶ ለፍርድ ባለመብት ለAሁን መልስ ሰጭ ይክፈል የሚል ትEዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ትEዛዝ ቅር በመሰኘት Aመልካች የይግባኝ Aቤቱታውን ለፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርቧል። የከፍተኛ ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ትEዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍ/ቤቶች ከላይ በተገለፀው Aኳሃን የሰጡት ዳኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል፤
ይታረምልን በማለት ነው የAቤቱታው ይዘትም ተጠቃሎ ሲታይ።
በAዋጅ ቁጥር 256/94 Aንቀጽ 26/1/ ድንጋጌ መሰረት የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር መብትና ግድታ ለመሰረተ ልማት ሚ/ር ይተላለፍለት Eንጂ ለEዳ መክፈያ በጀት Aልተመደበለትም። የAመልካች በጀት ለደምወዝና ለስራ ማስኬጃ ብቻ ሆኖ Eያለ በጀት ለEዳ መክፈያ Eንዲውል መደረጉ 324 325 Aግባብነት የለውም፤ የሥር ፍ/ቤት ተቀብሎትና Aምኖበት ለEዳው Aከፋፈል በኮሚቴ Aማካኝነት የንብረት ማስተላለፍ ተግባር Eንዲደረግ ታዞ በዚህም መሰረት ሥራው ቀጥሎ ከ80% በላይ ኮሚቴው ሥራውን ማከናወኑ Eየታወቀ የሥር ፍ/ቤት የAንድን ወገን Aቤቱታ ብቻ Aዳምጦ Eራሱ የሰጠውን ትEዛዝ Eንደይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሆኖ በመሻር Eዳው በመደበኛ በጀት Eንዲከፈል ትEዛዝ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያመለክታል የሚል ነው።
መልስ ሰጭም ይህንኑ ቅሬታ Aስመልክቶ ዝርዝር መልስ ሰጥቶበታል የመልሱም ፍሬ ቃል የሥር ፍ/ቤት ስለAፈፃፀሙ የሰጠው ዳኝነት የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚያዘው መሰረት መሆኑንና Eዳውንም በመጨረሻ መንግሥት የሚሸከመው መሆኑን Aግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ናቸው የሚላቸውን በመጥቀስ Aስፈላጊም ከሆነ ከመንግሥት ካዝና ወጪ ሆኖ ላከፈል Eንደሚገባ Aብራርቷል።
ይህ ሰበር ሰሚው ችሎትም በበጀት የሚተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤት የፍርድ ባለEዳ ሆኖ ሲገኝ ውሣኔውን ለማስፈፀም ለልላ ጉዳይ በበጀት የተያዘውን Eና የሰራተኛ ደመወዝን የሚጨምረውን ገንዘብ ከባንክ ወጭ ሆኖ Eንዲከፈል ማዘዝ ይችላል ወይስ Aይችልም የሚለውን መነሻ በማድረግ ነው ያከራከረው። ክርክሩ በሰበር ከመቅረቡ በፊትም ሆነ በኋላ ጉዳይ በÝራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ቀርቦ ግራ ቀኙ ሲደራደሩ Eንደነበር ለመረዳት ተችሐል።
ድርድሩ የተደረገውም በሰራተኛ ቅነሣ ጥያቄ Eዳውን Eረከባለሁ በማለት ቦርድ ኃላፊነት ላወስድ የሚገባው የመሆኑን Aግባብነት፣ በተገባው ቃል መሰረት የቦታ ርክክብ ላፈፀም ያለመቻሉን፡ Eንዲሁም ተረከቡ ያሉን መሣሪያዎች የተገመቱት ከ5 ዓመት በፊት በመሆኑ በዚያው ዋጋ ተረከቡ መባሉን ፤
የወደቁ መሣሪያዎች ተለይተው ከግምቱ ተቀናሽ መሆን የሚገባቸው መሆኑን፣ ክሱ ተሰልቶ በሚታውቀው ግምት Eና Eኛ በምንፈልገው ገንዘብ መካከል ያለውን ልዩነት ጊዜ ተሰጥቶን ልንከፍል የምንችልበት ሁኔታ ላመቻች ይገባል በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ሲሆን ድርድሩ ውጤት ሣያገኝ መቅረቱን መዝገቡ ያስረዳል።
ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በፊት የተጀመረው ድርድር Eልባት ያገኝ ዘንድ በፍትህ ሚ/ር ሰብሣቢነት የሚመራ ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑንና ይህም ኮሚቴ ሥራውን በመስከረም ወር 1999 ዓ.ም ጀምሮ Eስከ ሚያዚያ ወር 1999 ዓ.ም ድረስ ከመልስ ሰጭዎች ጋር ሲደራደር ከቆየ በኋላ ደርሰንበታል ባለው ስምምነት መነሻ ስለጉዳዩ በመንግሥት በኩል ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ የውሣኔ ሀሣብ ያቀረበ መሆኑን ግንቦት 3A ቀን 1999 ዓ.ም ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሐል።
ከዚህ በላይ Eንደተገለፀው በAመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል የተነሣውን የAፈፃፀም ጉዳይ የሥር የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት Eንደጀመረው ከጠቅላይ ሚ/ሩ በተፃፈው ደብዳቤ መሰረት Eልባት የሚያገኝ ከሆነ በሚል ይህ ሰበር ችሎትም የEራሱን ጥረት Aድርጓል ይሁን Eንጅ በተለያዩ ምክንያቶች ውጤት ሣያገኝ ቀርቷል ግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች Eንደየጉዳዩ Eየታየ በፍ/ቤቱ Aነሳሽነት በሚቀርብላቸው ጥያቄ መሰረት ጉዳያቸውን በስምምነት መጨረስ ካልቻሉ ሕግን ባገናዘበ ሁኔታ ዳኝነት ላያገኙ ይገባል ስለሆነም ይህ ችሎት ቀደም ሲል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ቀርቦ ላታይ ይገባል በማለት በምክንያትነት ከያዘው ነጥብ Aንፃር ጉዳዩን መርምሯል።
Eንደመረመርነውም የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መግባባት Aፈፃፀሙ ፍፃሜ Eንዲያገኝ ጥረት ቢያደርግም የፍርድ ባለEዳን የተካው የመሰረተ ልማት ሚ/ር የሚጠበቅበትን Aልሰጠም በሚል Eንደ 326 327 መጨረሻ Aማራጭ የIት/ብሕራዊ ባንክ ከመሰረተ ልማት የባንክ ሂሣብ ገንዘቡን ወጭ Aድርጎ Eንዲከፍል ትEዛዝ ሰጥቷል። ይህ ከባንክ ወጭ ሆኖ ለEዳ መክፈያ ይዋል የተባለው ገንዘብ የመ/ቤቱ መደበኛ በጀት መሆኑንም መልስ ሰጭ ክዶ Aልተከራከረም ። መደበኛ በጀት ለሰራተኛ ደመወዝ ፤ለመ/ቤቱ የEለት ተEለት ተግባር ማከናወኛ ሲባል የሚመደብ ገንዘብ Aንደመሆኑ ለተጠየቀው Eዳ ክፍያ ይዋል ቢባል የመ/ቤቱን የሥራ Eንቅስቃሴ መግታት ይሆናል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 4A4 ድንጋጌ ሥር በEዳ ምክንያት በAፈፃፀም ላያዙ Aይችሉም ተብለው የተዘረዘሩትን የንብረት ዓይነቶችና መጠን Aዳምረን ስናይ Eነዚህ ለባለEዳው ፍፁም Aስፈላጊ የሆኑና ለEለት ጉርሱ የሚውሉ በመሆናቸው ህልውናውን ለመጠበቅ ታስቦ የተሰጠ የሕግ ጥበቃ መሆኑን Eንረዳለን። Aንድ የመንግሥት መ/ቤትም ለህዝብ Aገልግሎት Eንዲሰጥ ታስቦ ከተዋቀረ ለመደበኛ ሥራው ሲባል የተመደበውን በጀት ለልላ ተግባር ማለትም ለEዳ ክፍያ Eንዲውል ከተደረገ በግለሰብ Aቋም Eንዳየነው ሁሉ የመ/ቤቱን ሕልውና የሚፈታተንና የህዝብንም ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 4A4ን በማመሳሰል ሥራ ላይ የማይውልበት ምክንያት Aላገኘንም።
ስለሆነም ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ ሆኖ በተያዘው ነጥብ መሰረት የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት Aፈፃፀሙ በመሰረተ ልማት ሚ/ር መደበኛ በጀት ላይ ተፈፃሚ Eንዲሆን፤ ከመደበኛ በጀት ወጭ ሆኖ Eንዲከፈል ሲል የሰጠው ትEዛዝ Aግባብ ሆኖ Aላገኘነውም።
በልላ በኩል ከዚህ ውጭ የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት ለAፈፃፀሙ ተስማሚ Eና ተገቢ ነው የሚለውን መንገድ ተከትሎ ፍርዱን ያስፈጽም ብለናል።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 552A ህዳር 3A ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ ቀሪ ሆኖ ልላ ተስማሚ Eና ተገቢ ነው የሚለውን መንገድ ተከትሎ ፍርዱን ያስፈጽም ብለናል።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 552A በኀዳር 30 ቀን 1995 ዓ.ም የተሰጠው ትEዛዝ Eና የከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/ቁ. 16478 ታህሣሥ 3A ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ ተሽሯል ግልባጩ ይድረሣቸው ።