No summary available.
ሐምል 12 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ Aቶ Aሰግድ ጋሻው Aቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aቶ ታፈሰ ይርጋ Aቶ ብርሃኑ Aመነው Aመልካቾች፡- 1. Aቶ ተክል ዋቅጅራ 2. Aቶ ጥላሁን ቦባስ ቀረቡ 3. Aቶ ሃቢብ መሐመድ መልስ ሰጭ፡- Aቶ ሾንጣ ጉቡ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የተወሰነ ኃላፊነት ያለው የግል ማህበር Aንድ Aባል Aገባለሁ ያለውን መዋጮ መቼና Eንድት ማግባት ያለበት መሆኑን የሚመለከት ነው።
Aመልካቾችና መልስ ሰጭዎች ጠቅላላ ግምቱ ብር 8AA,AA0 /ስምንት መቶ ሺህ ብር/ ካፒታል ያለው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሥርተዋል። የEያንዳንዳቸው መዋጮ ብር 2AA,AAA.AA /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ሲሆን የAሁን መልስ ሰጭ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ Aገባለሁ ካለው መዋጮ ውስጥ ብር 74,838.8A /ሰባ Aራት ሺ ስምንት መቶ ሰላሣ ስምንት ብር/ ሣያስገባ ማህበሩ ሥራውን ሲያንቀሣቅስ ከቆየ በኋላ ልሎች Aባላት ይህንኑ ላያስገባ የተስማማውን መዋጮ በገንዘብ ገቢ Eንዲያደርግ ሲጠይቁት መልስ ሰጭ ይህንኑ መዋጮ ማህበሩ ከሚያስገኘው ትርፍ ገቢ በድርሻዬ ከማገኘው Eከፍላለሁ Eንጂ Eንደ ጥያቄያችሁ ክፍያውን ለመፈፀም ግድታ Aልገባሁም በማለቱ ምክንያት ይህ ክርክር ላከሰት ችሐል።
ይህንኑ ክርክር ያስነሣውን መዋጮ ገቢ ያደርግ ዘንድ Aመልካቾች በጌዲO ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ክስ መሥርተው መልስ ሰጭም ከላይ የተጠቀሰውን መከራከሪያ በማቅረቡ ይኸው ፍ/ቤት ጉዩን ተመልክቶ የAሁን መልስ ሰጭ ቀሪ Aክሲዮን ድርሻውን /መዋጮውን/ በዚህ ጊዜ Aስገባለሁ ብሎ ግድታ Aልገባም ማስጠንቀቂያ የደረሰው መሆኑም Aልተረጋገጠም፣ ስለሆነም የሚከፍልበት ምክንያት የለም በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ የAሁን Aመልካቾች ቅር ተሰኝተው የይግባኝ Aቤቱታቸውን ለደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች ክለል ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረባቸው ግራ ቀኙ በጉዳዩ ላይ ክርክር Aድርገዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የAሁን መልስ ሰጭ Aስገባለሁ ካለው መዋጮ ብር 74,838.8A /ሰባ Aራት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሣ ስምንት ብር/ Aላስገባም (Aልከፈለም) ሆኖም ይህንኑ ቀሪ ክፍያ ለመፈፀም ውል Aድርጓል። ይህ ውልም ፈራሽ ነው Aልተባለም ስለዚህ መልስ ሰጭ ገንዘቡን ላከፍል ይገባል በማለት ዳኝነት ሰጥቶ ግራ ቀኙን Aሰናብቷል።
በዚህ ውሣኔ ባለመስማማት Eና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል የAሁን መልስ ሰጭ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር Aቤቱታ Aቅርቦ በሰበር ግራ ቀኙ ተከራክረዋል። ሰበር ሰሚው ችሎት ጉዳዩን መርምሮ Eንደሚከተለው ወስኗል።
በንግድ ሕግ ቁጥር 338/1/ Aክሲዮኖች በሚገዙበት ጊዜ Eጅግ ቢያንስ ከተፃፈባቸው ዋጋ Aንድ ሩብ ላከፈል Eንደሚገባ ወይም በሙሉ Eንደሚከፈል ተደንግጓል። ዋጋቸው በሙሉ Eስኪከፈል ድረስም Aክስዮኖቹ በማህበሩ ስም የሚቆዩ ናቸው ሆኖም ይህ ያልተከፈለው Aክሲዮን ማህበሩ በንግድ መዝገብ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ቢበዛ Eስከ Aምስት ዓመት ድረስ በየጊዜው መከፈል Eንዳለበት በዚሁ ሕግ Eና ድንጋጌ ንUስ ቁጥር 2 308 309 ተመልክቷል። በዚህ ሕጉ ባስቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያልተከፈለው የAክሲዮን ክፍያ ካልተፈፀመ ምን ውጤት Eንደሚያስከትል ደግሞ በንግድ ሕግ ቁጥር 342 ሥር ተደንግጓል። ስለሆነም ድርሻ የAክሲዮን ክፍያውን ገቢ Aለማድረጉ ከተረጋገጠ በንግድ ሕግ ቁጥር 338/1/ Eና 342 መሰረት
የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ይህ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ያመለክታሉ ያላቸውን ነጥቦች Aመልካች በመጥቀስ Eንዲታረምለት ነው።
መልስ ሰጭም በበኩሉ የሥር የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ግድፈት Aልተፈፀመበትም በማለት ተከራክሯል።
Eኛም ጉደዩን ተመልክተናል Eንደተመለከትነውም Aመልካቾችና መልስ ሰጭ ያቋቋሙት የንግድ ማህበር የተወሰነ ኃላፊነት ያለው የግል ማህበር ስለመሆኑና ክርክር ያስነሣውን የብር 74,838.8A መዋጮ መልስ ሰጭ ለዚሁ የንግድ ማህበር ገቢ ማድረግ በሚገባው ጊዜ ያላገባ ስለመሆኑ በክርክሩ ሂደት የተካዱ ነጥቦች Aይደሉም ። Eያንዳንዱ ማህበርተኛ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ማግባት የሚገባውን መዋጮ Aጠቃሎ መክፈል ያለበት መሆኑን ከንግድ ሕግ ቁ. 516 Eና 517 ይዘት መረዳት ይቻላል።
No topics extracted.
ይኸውም ማህበሩ ተቋቁሟል የሚባለው በማህበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ ዓይነት በተዘጋጀው ግልጽ በሆነ ጽሁፍ ላይ ማህበርተኞቹ ወይም ወኪሎቻቸው የፈረሙበት Eንደሆነ ነው። በዚህ መመሥረቻ ጽሑፍ ላይ ከሚገለፁት ነገሮች Aንዱ የማህበሩ ዋና ገንዘብ በሙሉ መግባቱን የመጠቀሱ ጉዳይ ነው። Eንዲሁም በንግድ ሕግ ቁጥር 121 ሥር የAክሲዮኖች ድርሻ መዝገብ ምን ምን ነገሮችን ማካተት Eንዳለበት ከተዘረዘሩት መካከል በንUስ ቁጥር 1(ለ) “Eያንዳንዱ ማህበርተኛ ማግባት ያለበትን የመዋጮዎች ግምት” የሚለው መዋጮው ከተቋቋመም በኋላ ወደ ፊት መግባት Eንደሚችል በሚገልጽ Aኳኋን የተፃፈ ቢሆንም "the value of all contributions made by the members" ከሚለው የEንግላዝኛ ግልባጭ ጋር Aጠቃለን ስናየው መዋጮ Aስቀድሞ መግባት ያለበት መሆኑን የሚያመለከት ነው። Eነዚህም ድንጋጌዎች ማህበርተኛው Aገባዋለሁ ያለውን መዋጮ ማህበሩ በተቋቋመበት ጊዜ Aጠቃሎ መክፈል ያለበት መሆኑን የሚያመለክቱ Eንጂ ስለ Aክሲዮን ማህበር በዚሁ ሕግ ቁ. 338/1/ Eንደተመለከተው ክፍያ ሣይፈፀምበት ላቆይ የሚችል መዋጮ ላኖር የሚይችል መሆኑን Aያሣዩም ማህበርተኞቹ ማህበሩን ሲያቋቁሙ በዚህ መሰረት መፈፀም ሲገባቸው Aላደረጉም ሆኖም ማህበርተኛው መዋጮውን ዘግይቶ Eንዲያስገባ በማድረግ ማህበሩን መሥርተው በተገኙ ጊዜ ማህበሩ ህልውና የለውም ማለት Aይደለም።
ይህንን Aስመልክቶም የቀረበ ክርክር የለም። ይህ በጊዜው ገቢ ያልሆነው መዋጮ መቼ Eና Eንድት መከፈል Eንዳለበት በመመስረቻ ጽሑፍ ላይ ባይገለጽም መልስ ሰጭው ያልከፈለውና ገቢ ማድረግ ያለበት መዋጮ መኖሩን Aምኖ Eንደሚከፍል መተማመኛ የሰጠ ለመሆኑ ተረጋግጧል።
የህንን መተማመኛ ከሰጠ በኋላ የAሁን መልስ ሰጭ የሚያቀርበው ክርክር ይህንን ገቢ ያላደረግሁትን መዋጮ ማህበሩ ከሚያኘው ትርፍ በAስገባሁት መዋጮ ልክ ከሚደርሰኝ ገቢ Eየተሰላ በየጊዜው ልከፍል ከሚገባ በቀር በAንድ ጊዜ የመክፈል ግድታ የለብኝም የሚል ነው። ሆኖም ከላይ 310 311 Eንደተመለተው የተወሰነ ኃላፊነት ያለው ማህበር መዋጮ መክፈል ያለበት ማህበሩ ሲቋቋም Eንጂ ተቋቁሞ ሥራውን ከጀመረ በኋላ ባለመሆኑና መልስ ሰጭም ያላገባውን መዋጮ Eከፍላለሁ በማለት Eራሱን ግድታ ውስጥ ያስገባ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ መተማመኛ የሰጠ በመሆኑ በሂደት ማህበሩ በሚያስገኘው ገቢ ልክፈል የሚለው መከራከሪያው ሕጋዊ መሰረት ያለው Aይደለም።
የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት መዋጮ ሣይከፈል ከተገኘ በባለድርሻው ስም ሣይሆን በማህበሩ ስም ተመዝግቦ ላቆይ Eንደሚችልና መከፈል በሚገባው Eጅግ ቢዘገይ በAምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልተከፈለ ምን ውጤት Eንደሚያስከትል በንግድ ሕግ ቁጥር 342 ተመልክቷል የሚለውን ምክንያት ይዞ መልስ ሰጭ ያላገባውን መዋጮ Eንዲከፍል ማስገደድ Aይቻልም በሚለው መደምደሚያው የጠ/ፍ/ቤቱን ውሣኔ ላሽር የቻለው በንግድ ሕግ ቁጥር 338 Eና 342 ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ነው ይሁን Eንጂ Eነዚህ ድንጋጌዎች የAክሲዮን ማህበርን የሚመለከቱ ናቸው። የAክስዮን ማህበርና የተወሰነ ኃላፊነት ያለው የግል ማህበር ሁለቱም የንግድ ማህበሮች ይሁኑ Eንጂ በAመሰራረታቸው በAለባቸው የኃላፊነት Aድማስ፣ በሚሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ገደብ ያለባቸው ስለመሆኑና Aለመሆኑ ወዘተ ስራ ልዩነት Aላቸው። ለAክስዮን ማህበር የሚሸጡት Aክሲዮኖች መቼ ገቢ Eንደሚሆኑና ለተወሰነ ኃላፊነት ያለው ማህበር ደግሞ መዋጮው መቼ መግባት Eንዳለበት በተለያዩ Aኳኋን በየሚመለከታቸው ክፍሎች ተደንግገዋል መዋጮ መቼ መግባት ያለበት መሆኑን ስለAክሲዮን ማህበር የሚደነግጉትን ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ማድረግ Eንደሚቻልም ተጠቅሶ Aልተገኘም። ይህ ሆኖ Eያለ የንግድ ሕግ ቁጥር 338 Eና 342 Aሁን ለተያዘው ጉዳይ Aግባብነት Eንዳላቸው ቆጥሮ የክልሉ ሰበር ሰሚው ችሎት ለውሣኔው መሰረት ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል።
ው ሣ ኔ
መልስ ሰጭ ለንግድ ማህበሩ ገቢ Aደርጋለሁ ሲል መተማመኛ የሰጠበትን ብር 74,838.8A /ሰባ Aራት ሺ ስምንት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከ8A%/ ገቢ ላያደርግ ይገባል፤ ይከፈል ብለናል።
የጌዲO ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. 22/92 በ24/3/95 የሰጠው ውሣኔ Eና የደቡ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት በይ/መ/ቁ. 5648 በ26/A4/97 የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 3694 በ29/4/96 የሰጠውን ውሣኔ ፀንቷል።