No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3428A ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ ግርማይ ደስታ - ጠበቃ ረዳI ባራኪ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ዓቃቤ ሕግ - ሚላዮን ተዘራ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 17 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔና የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 27 ቀን 2AAA ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት Aመልካች በመጠየቁ ነው። የክርክሩ መነሻ Aመልካች የተጨማሪ Eሴት ታክስ Aዋጅ ቁጥር 285/1994 ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል ፈጽሟል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ Aቅርቦበት፣ ፍርድ ቤቱን የግራ ቀኙን ክስና ማስረጃ ከሰማ በኋላ Aመልካች የAዋጅ ቁጥር 285/1994 Aንቀጽ 22ን Eና ልሎች ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፋተኛ ነው ብሎ፣ Aመልካች በAምስት ዓመት Eስራት Eንዲቀጣ ከወሰነ በኋላ፣ ቅጣቱን በሶስት ዓመት ገድቧል። ዓቃቤ ሕግ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት Aቅርቦ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት Aመልካች በልለበት ይግባኙን ከሰማ በኋላ፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቅጣቱን መገደቡ ልሎችን ላያስተምር የሚችል Aይደለም በማለት ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን የሶስት ዓመት የገደብ ውሣኔ በመሻር Aመልካች Aምስት ዓመት Eስራቱን Eንዲፈጽሙ በማለት ወስኗል።
Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት Aቅርበው፣ ችሎቱ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የሚያስለውጥ ምክንያት የለም በማለት Aጽንቶታል።
Aመልካች የሰበር Aቤቱታ ያቀረበው፣ ይህ ውሣኔ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት ነው። Aመልካች በጠበቃቸው በኩል ባቀረቡት ማመልከቻ በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፋተኛነት ውሣኔ የተጨማሪ Eሴት ታክስ Aዋጁን በAግባቡ ሳይገነዘቡና ሣይተረጉሙ በመሆኑ መሰረታዊ ስህተት Aለበት በማለት ዝርዝር ማመልከቻ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዓቃቤ ሕግም በኩል በሰበር ደረጃ ጥፋተኛነቱን ለማስለወጥ ያቀረቡት Aቤቱታ ተገቢ Aለመሆኑንና የቅጣት ገደቡ መነሣቱ ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለበት ስለሆነ በሰበር የሚታረም Aይደለም የሚል ክርክር Aቅርቧል። Aመልካች ከቅጣት ውሣኔ Aሰጣጥና ቅጣትን ስለመገደብ ከተቀመጡት የወንጀል ሕግ መርሆች Aንፃር ሲታይ ቅጣትን ለማስተማሪያነት ሣይሆን በመበቀያነቱ ለመጠቀም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ላታረም ይገባዋል በማለት የመልስ መልስ Aቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና በሰበር የተደረገው የሕግ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው፡-
በሰበር ደረጃ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት የጥፋተኛነት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት Aመልካች ያቀረቡት Aቤቱታ ተገቢ ነው ወይስ Aይደለም?
በሥር ፍርድ ቤቶች ቅጣቱን ለመገደብና ቅጣቱን ተፈፃሚ መሆን Aለበት በማለት የተለያየ ውሣኔ የሰጡበት የቅጣት ውሣኔን 292 293 ስለመገደብ የተደነገጉ ድንጋጌዎች በምን Aይነት ሁኔታ መተርጎምና ሥራ ላይ መዋል Aለባቸው የሚሉትን ነጥቦች መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ Aመልካች ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው የጥፋተኝነት ውሣኔ ቅር በመሰኘት በመጀመሪያ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ የነበረባቸው ሲሆን ይህንን ማድረጋቸውን የፍርድ ቤቱ መዝገብ Aያሣይም። በዚህ መዝገብ Aመልካች ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበውን ይግባኝ ሰምቶ በቅጣት ውሣኔው ላይ የተሰጠውን የሶስት ዓመት ገደብ በመሻሩ ነው። ስለሆነም Aመልካች በጥፋተኛነት ውሣኔው ላይ፣ የነበራቸውን ቅሬታ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ይግባኝ ወይም መስቀለኛ ይግባኝ በማቅረብ Eስከ ሰበር ድረስ በማምጣት መከራከር ነበረባቸው። Aመልካች ይህንን ሥርዓት ተከትለው፣ በጥፋተኝነት ውሳኔው ላይ ተፈጽሟል የሚሉትን የህግ ስህተት ባላቀረቡበት ሁኔታ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔውን መገደቡ ተገቢ Aይደለም ብሎ Aቃቤ ሕግ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ መነሻነት የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት Aድርገው የከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ Aይደለም በማለት የሰበር መከራከሪያ ነጥብ ማድረጋቸው የህግ ድጋፍ የልለውና ሥርዓቱን ጠብቆ ያልቀረበ በመሆኑ፣ Aልተቀበልነውም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ፣ ፍርድ ቤት በAንድ ሰው ላይ የቅጣት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የቅጣት ውሳኔውን ለመገደብ Eንደሚችልና የቅጣት ውሳኔው ላገደብላቸው የሚገባው ምን መሰረታዊ ሁኔታዎች ሲሟሉ Eንደሆነ በወንጀል ህጉ Aንቀጽ 192 ላይ መሰረታዊ መርሁ ተቀምጧል።
ከዚህ በተጨማሪ ቅጣት የወሰነው ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔውን ከመገደብ በህግ የሚከለከልበት ሁኔታ Eንዳለና ይኸም የህግ ክልከላ በወንጀል ህጉ Aንቀፅ 194 የተደነገገ መሆኑን ለመረዳት Eንችላለን። ከዚህ Aንፃር ስንመዝነው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን የAምስት ዓመት Eስራት ቅጣት በሶስት ዓመት መገደቡ በወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 194 ንUስ Aንቀጽ 2 የተደነገገውን የማይጥስና በሕጉ የቅጣት ውሣኔ Eንዳይገደብ የተደነገገውን ክልከላ ተላልፎ፣ የሰጠው Aይደለም።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የቅጣት ውሣኔውን ሲገድብ በወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 194 የተደነገገውን የሕግ ክልከላ Aልተላለፈም ካልን በሁለተኛ ደረጃ የሚነሣው ጥያቄ Aመልካች ቅጣቱ የተገደበለት በወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 192 የተቀመጡትን መሰረታዊ ሁኔታዎች የሚያሟላ ሆኖ በመገኘቱ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለው ነው። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጣቱን የገደበው Aመልካቹ ከዚህ በፊት በወንጀል ያልተቀጣ በመሆኑና ቅጣቱን ተፈፃሚ ከማድረግ ይልቅ ቅጣቱን መገደቡ የተሻለ ውጤት ይኖረዋል በማለት ነው። በEርግጥ የሥር ፍርድ ቤቶች በዚህ መንገድ Aይተው ባሣለፉት ቅጣትን የመገደብ ውሣኔ የይግባኝ ቅሬታ ላቀርብበት የሚችልና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ከወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 192 መርህ Aንፃር በመመዘን ላሽረው፣ ላያሻሽለው ወይም ላያፀናው የሚችል ነው። ከዚህ Aንፃር ካየነው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የAምስት ዓመቱ Eስራት ቅጣት በሶስት ዓመት Eንዲገደብ የሰጠውን ውሣኔ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መመርመሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም። ሆኖም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የቅጣት ውሣኔው በሶስት ዓመት ተገድቦ Eንዲቆይ የሰጠውን ትEዛዝ የሻረው፣ Aመልካቹ የቅጣት ገደብ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውንና በወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 192 የተቀመጠውን መሰረታዊ መርህ የሚያሟላ Aይደለም በማለት ሣይሆን በAመልካቹ ላይ የተወሰነው ቅጣት መገደቡ ልሎች ተመሣሣይ ወንጀል የመሰራት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለማስፈራራትና Aመልካችን በመቀጣጫነት በማሣየት ትምህርት ለመስጠት የማያስችል ነው በሚል ምክንያት Eንደሆነ በውሣኔው ተልጿል።
Aመልካቹ በወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 192 የተቀመጠውን መርህ የሚያሟላበት 294 295 ሁኔታ ጠቅላላውን የወንጀል ሕጉን መሰረታዊ ግብ መነሻ በማድረግ ቅጣቱ መገደብ የለበትም ከሚለው መደምደሚያ ላይ መድረሱ የወንጀል ቅጣት Aወሳሰንና Aፈፃፀም የወንጀል ሰሪውን ልዩና ግላዊ ሁኔታዎች ያገናዘቡ መሆን Aለበባቸው በማለት በወንጀል ሕጉ Aንቀጽ 41 የተቀመጠውን መሰረታዊ መርህ የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
ስለሆነም ቅጣትን መገደብን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ግምት ውስጥ በማስገባትና በሕግ የተደረገውን ክልከላ ሣይተላለፍ፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቅጣቱን በመገደብ የሰጠውን ትEዛዝ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመሻር የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት። ስለሆነም ይህ ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ Aመልካች ያልፈፀመው ቀሪው፣ የEስራት ቅጣት በሶስት ዓመት ላገደብለት ይገባል በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ት E ዛ ዝ
Aመልካች ያልፈፀመው ቀሪው የEስራት ጊዜ በሶስት ዓመት የሙከራ ጊዜ የተገደበለት መሆኑን Aውቆ፣ ከEስር Eንዲለቅቀው Aመልካች Eስሩን Eየፈፀመበት ላለው ማረሚያ ቤት ይፃፍ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣቱን Aፈፃፀም Aስመልክቶ፣ የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ይፃፍ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
No topics extracted.