No summary available.
የሰ/መ/ 31731 የካቲት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የOሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ - ተሾመ ግርማ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ዘሪሁን ታደሰ ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር Aቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ ተጠሪ Aስገድዶ የመድፈር ወንጀል ፈጽሞAል በሚል ቀረበውን ክስ መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነወ። ክርክሩ የተጀረው በOሮሚያ ብ/ክ/መ/ በምEራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ በተጠሪው ላይ ክስ የመሰረተው ተከሣሽ በወ/መ/ሕግ ቁ. 59A የተመለከተውን በመተላለፍ ወ/ሪት Aስማረች መርሳ የተባለችውን Aስገድዶ በመድፈር ክብረ ንጽሕናዋን /ድንግልናዋን/ ገስሷል በማለት ነው። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ተጠሪውን Aስቀርቦ የEምነት ክህደት ቃል ከሰማ በኋላ፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን የጽሑፍ Eና የሰው ማስረጃ ሰምቶAል። በመጨረሻም ዓቃቤ ሕግ Eንደ ክሱ Aላስረዳም የሚል ምክንያት በመስጠት ተጠሪ ተከላከል ላባል Aይገባም በማለት ብይን ሰጥቶAል። በዚህ ብይን ላይ ይግባኝ የቀረበላቸው የOሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት Eና የሰበር ችሎትም ብይኑ ጉድለት የለበትም ብለዋል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች ሐምል 6 ቀን 1999 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው ተጠሪው በተከሰሰበት ወንጀል መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ ይሰናበት የተባለበትን Aግባብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ብይን Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ክሱ የወንጀል Eንደመሆኑ ተከሣሹ /የAሁን ተጠሪ/ የEምነት ክህደት ቃሉን Eንዲሰጥ ከተጠየቀ በኋላ፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች /ማስረጃዎች/ ተሰምተዋል። ከመዝገቡ Eንዳየነው ዓቃቤ ሕግ ያሰማው ማስረጃ የግል ተበዳይን ጨምሮ Aምስት ምስክሮች Eና Aንድ የጽሁፍ ማስረጃን የሚጠቃልል ነው። የግል ተበዳይ በሰጠችው የምስክርነት ቃል ዓቃቤ ሕጉ በክሱ በተሰጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተጠሪ ቡና ታፈላ ከነበረችበት ክፍል ውሃ Aቀብይኝ ብሎ Eንደጠራት Eና Aስዋም ውሃ በጀሪካን ስትወስድለት በቤቱ /በራሱ ቤት/ በር ስር ቆሞ በመጠበቅ ይዞAት ወደ መኝታ ክፍሉ በመውሰድ ፖንትዋን /የውስጥ ሱሪዋን/ በግድ Aውልቆ Eንደደፈራት፣ Aስዋም ለጊዜው Eራስዋን ስታ Eንደነበር፣ ሰውነትዋ Eንደደማ፣ በመቀጠልም ጩኸት Eያሰማች 3ኛ Eና 4ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን፣ መጥራትዋን፣ ተጠሪም ቀስ Aድርጎ በማስኬድ ወደ ቤትዋ Eንዳስገባት በማረጋገጥ Eንደመሰከረች የከፍተኛው ፍ/ቤት በሰጠው ብይን ላይ በግልጽ ተመልክቶAል። በመቀጠል የተሰማችው 2ኛዋ የዓቃቤ ሕግ ምስክርም ተጠሪ የግል ተበዳይዋን ሲደፍር Aለማየትዋን በAንድ በኩል ብትገልጽም፤ በልላ በኩል ግን በዓቃቤ ሕግ ክስ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት የግል ተበዳይ ቡና ስታፈላላቸው ቆይታ ሁለተኛውን /ከAቦል ቀጥሎ ያለውን/ Aፍልታ ለማምጣት ወደኩሽና መውጣትዋን ከ3A /ሰላሣ/ ደቂቃ በኋላ ተጠሪ ድንግልናየን ወሰደብኝ Eያለች Eየጮኸች መምጣትዋን፣ ልብስዋን ወደ ላይ Aድርጋ ስታሳያትም ደም ማየትዋን፣ የግል ተበዳይን ይዛ ወደ ተጠሪው ቤት ስትሄድ ተጠሪ Eቤቱ ውስጥ ሆኖ ቆዩ ሰው Eየመጣ ነው ሲል መስማትዋትን በማረጋገጥ መስክራለች ተብሎ በብይኑ ተገልጸAል።
ልሎች 3ኛ Eና 4ኛ ተብለው የተመዘገቡት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች Eንደዚሁ ሰጡት የተባለው የምስክርነት ቃል Eንዳየነው በዓቃቤ ሕግ ክስ በተጠቀሰው ቀን Eና ሰዓት Aካባቢ በተጠሪው ቤት ተቀምጠው ሳለ የግል ተበዳይ የተጠሪን ቤት ማንኳኳትዋን፣ Eነሱም በሩን ከፍተው ወደ ውጪ ሲወጡ ተጠሪ Aስገድዶ ስለደፈረኝ ጠይቁልኝ ማለትዋን፣ Eነሱም Eንጠይቅልሻለን ብለው መልስ EንደሰጡAት መናገራቸውን /መመስከራቸውን/ የሚያመለክት ነው። በ5ኛ ምስክርነት የተመዘገበው ፖላስ ሲሆን፣ የመሰከረውም የግል ተበዳይ ተደፈረች በተባለበት ማግስት ከረፋዱ Aምስት ሰዓት ላይ መደፈርዋን በመግለጽ ማመልከትዋን /Aቤቱታ መቅረብዋን/ Eንደሚያውቅ፣ ተጠሪም የግል ተበዳይ ምን ብላ Aመለከተች ተብሎ ያኔ Eንደ ጠየቀው፣ ምስክሩ ምን ብላ Eንዳመለከተች ሲነግረውም ወደፊትም ክሱ የሚደርስበትን ደረጃ ትነግረኛለህ Eንዳለው በመግለጽ መመስከሩ ተመዝግቦAል።
በመጨረሻ ክሱን የሰማው ፍ/ቤት የተመለከተው ማስረጃ ከግምቢ ሆስፒታል የተሰጠውን የሃኪም ማረጋገጫ ነው። በዚሁ ማስረጃ የተገለጸው በግል ተበዳይ ላይ የክብረ ንጽሕና መድፈር ተግባር መፈጸሙን፣ ብልትዋ ወደላይ Aብጦ መገኘቱን፣ Eየደማም Eንደነበር፣ ሁኔታው የግል ተበዳይ ተገዳ መደፈርዋን ላያመለክት Eንደሚችል ነው።
No topics extracted.
Eንደምንመለከተው በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው ክስ Eና ማስረጃ ከላይ በዝርዝር የተገለጸው ሲሆን፣ ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ይህንኑ በግልጽ ከመዘገበ በኋላ፣ ዓቃቤ ሕግ Eንደ ክሱ Aላስረዳም የሚል ምክንያት በመስጠት ተጠሪን በነፃ ለቅቋል። በመሆኑም Eዚህ ላይ ላነሳ Eና በAግባቡ ላጤን የሚገባው ነጥብ ዓቃቤ ሕግ ክሱን ለማስረዳት ከዚህ የተለየ ምን Aይነት ማስረጃ Eንዲያቀርብ ይጠበቅበታል? የሚለው ነው። ቀደም ሲል Eንደተመለከተው ዓቃቤ ሕግ ክሱን የመሰረተው በወ/መ/ሕግ ቁ. 59A የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞAል በማለት ነው። ይህ ድንጋጌም ስንመለከተው “በንጽሕና ክብር ላይ ስለሚደረግ የኃይል ተግባር” የሚል ርEስ የተሰጠው ሲሆን፣ ይዘቱም በኃይል ወይም በብርቱ ማስፈራራት ወይም በማናቸውም Aመጣጥ ለመቃወም ከማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ከጣለው በኋላ ግብረ ስጋን በመሰለ ወይም ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ በሆነ በማናቸውም ሥራ ጾታው ልዩ የሆነውን ሰው ለመገናኘት የሚያስገድድ ሰው ሕግን Eንደተላለፈ ተቆጥሮ የሚቀጣ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
Eንግዲህ ዓቃቤ ሕግ Eንደ ክሱ AስረድቶAል ወይስ Aላስረዳም? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ያሰማውን ማስረጃ ከሕጉ ይዘት ጋር ማገናዘብ ይገባል።
በበኩላችን Eንደምናየው ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰው Eና የጽሑፍ ማስረጃዎች በዝርዝር ይዘታቸውም ሆነ በጊዜ Eና ሰዓት Aጠቃቀስ ረገድ Eርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ ናቸው። ሲጠቃለሉም በጊዜው ተፈጸመ የተባለው ድርጊት በሚገባ መፈጸሙን የሚያረጋግጡ ናቸው። Aንድ ክስን የሚሰማ ፍ/ቤት በክሱ Aከራካሪ የሆኑትን ነገሮች Eውነት መሆን Aለመሆን ወይም ሕያው መሆን Aለመሆን ማረጋገጥ የሚችለው በሚቀርብለት ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ስለመሆኑ የሚያከራክር Aይደለም። በEርግጥም የማስረጃውን ይዘት በመመርመር ክብደቱንና ቅለቱን የመመዘን ስልጣንም የፍ/ቤቱ ነው።
ይሁንና ማስረጃውን በግልጽ ከመዝገቡ Eና ይዘቱንም ምን Eንደሚመስል Eያየ ግን ማስረጃ Eንዳልቀረበ Aድርጎ ማለፍ ይችል ዘንድ ሕግ Aይፈቅድለትም። የAንድ Aከራካሪ ነገር Aውነት ወይም ሕያው መሆንና Aለመሆን የሚረጋገጠው በማስረጃ ነው የሚለውን መርህም መጣስ Aይችልም። በያዝነው ጉዳይ Eንደምናየው ዓቃቤ ሕግ ያሰማው ማስረጃ በሕጉ የተነገረው ወንጀል ስለመፈፀሙ በግልጽ የሚያረጋግጥ ነው። የሥር ፍ/ቤቶች ግን ይህን የመሰለውን ማስረጃ Eንዳላዩ Aድርገው Aልፈውታል።
በEኛ ግንዛቤ Eና Eምነት ይህ Aይነቱ Aካሄድ ሕግን በግልጽ የጣሰ ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕንም በEጅጉ የሚጎዳ ነው። ከዚህ የተነሣም Aቤቱታ 280 281 የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
Aቤቱታ የቀረበበት በOሮሚያ ብ/ክ/መ/በምEራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 8A6 ሰኔ 22 ቀን 97 ዓ.ም. ተሰጥቶ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት Eና የሰበር ችሎት በመ/ቁ. 328A6 ግንቦት 16 ቀን 98 ዓ.ም. Eና በሰበር መ/ቁ. 43754 ሚያዝያ 15 ቀን 99 ዓ.ም. በሰጡAቸው ትEዛዞች የፀናው ብይን በወ/መ/ሕግ ሥ/ሥ/ቁ. 195 መሰረት ተሽሮAል።
ተጠሪ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ማስረጃ የተከሰሰበት ወንጀል ስለመፈጸሙ የተመሰከረበት ስለሆነ ላከላከል ይገባል ብለናል። በመሆኑም ክሱን የሰማው የከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን በማንቀሳቀስ በዚህ ሰበር ችሎት ውሣኔ መሰረት ክርክሩን ሰምቶ ይወስን ብለን ወስነናል። ይፃፍ።
መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ