No summary available.
መጋቢት 16 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጐስ ወልዱ ወ/ት ሂሩት መለሰ Aቶ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ - ሙሉEመቤት ውባየሁ ተጠሪ፡- Aቶ ባንቲ ታኤራ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች በተጠሪ ላይ Aቅርቦት የነበረውን ክስ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 122(2) መሰረት ካነሳ በኋላ በድጋሚ ክስ ላያቀርብ Aይችልም በማለት ድጋሚ የቀረበውን ክስ የሥር ፍ/ቤቶች ሳይቀበሉት በመቅረታቸው ነው።
ይህ ችሎትም የቀበረውን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ የቀረበው የወንጀል ክስ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 122(2) መሰረት ለጊዜው ተቋርጧል ተብሎ ከታዘዘ በኋላ Aቃቤ ሕጉ ክሱን ለመቀጠል Aይችልም መባሉ ተጠሪ ባለበት ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው ሆኖ በማግኘቱ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
የክርክሩ ነጥብ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሥር ፍ/ቤቶች ክሱ ላቀጥል Aይችልም ያሉበት ምክንያት Aግባብነት Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
የወንጀል ክርክር በሚመራበት የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥ/ሥ/ቁ.
122(2) መሰረት Aንድ ክስ በከሳሽ (በዓቃቤ ሕግ) ጥያቄ Eንዲነሳ ከተደረገ በኋላ ክሱን ለወደፊት ለመቀጠል የሚከለክል Eንደማይሆን በዚሁ Aንቀጽ 272 273 በንUስ Aንቀጽ 5 ላይ ተመልክቷል። የወንጀል ሕግ መርህም የሚከተለው በወንጀል የተከሰሰ ሰው በተከሰሰበት ጉዳይ ጥፋተኛ ነው ከተባለ ወይንም በነጻ ከተለቀቀ በኋላ በዚያው ጉዳይ ዳግመኛ ክስ የማይቀርብበት መሆኑን በተመለከተ ነው።
ስለሆነም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት መሰረት ከሳሽ (ዓቃቤ ሕግ) ክስ ማንሳት Eንደሚችልና ያነሳውንም ክስ መቀጠል Eንደሚችል የተመለከተ በመሆኑ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተነሳው ክስ ላቀጥል Aይችልም በማለት የA/ህግን ጥያቄ ሳይቀበለው መቅረቱ Eንደዚሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 43170 በ27/3/97 ዓ.ም የሰጠው ብይን Eንደዚሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሕዳር 11 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸው ስለሆኑ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 195(2) መሰረት ተሽረዋል።
Aመልካች Aስቀድሞ ክስ ማንሳቱ በድጋሚ ክሱን ለመቀጠል የሥነ ሥርAት ሕጉ የሚፈቅድት ስለሆነ የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክሱን ተቀብሎ ግራ ቀኙን Aከራክሮ Eንዲወስን ተመልሶለታል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.