No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ ወ/ት ሂሩት መለሰ Aቶ ፀጋዬ Aስማማው Aቶ በላቸው Aንሺሶ Aቶ Aልማው ወል Aመልካች፡- የOሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- Aሣምነው ገ/መስቀል - Aልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የሰበር Aቤቱታ ላቀረብ የቻለው በOሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የምEራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በከሣሽ የAሁኑ Aመልካችና በተከሳሽ የAሁኑ ተጠሪ መካከል የነበረውን በግፍ ሰው የመግደል Eና በግፍ ሰው የመግደል ሙከራ የወንጀል ክርክር የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በወ/መ/ቁ. 258/94 ግንቦት 19 ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተጠሪን በግፍ ሰው የመግደል ወንጀል በቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበበት ድንጋጌ፣ በግፍ ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ደግሞ በዓቃቤ ሕግ በኩል የተጠቀሰበትን ድንጋጌ ዝቅ በማድረግ ተራ በሆነ የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል በሚያስጠይቅ ድንጋጌ ጥፋተኛ ከAደረገው በኋላ በEድሜ ልክ ጽኑ Eስራት Eንዲቀጣ የወሰነውን ውሣኔ የAሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርቦ ይኸው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ከAከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤት ተጠሪን ጥፋተኛ ያደረገባቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን ዝቅ በማድረግ ቅጣቱን በተመለከተም ተጠሪን የሚያርመው ተመጣጣኝ ቅጣት የ8/ስምንት/ ዓመት ጽኑ Eስራት ነው በማለት በመወሰኑ ይኸው ውሣኔ ተጠሪ ጥፋተኛ የተባለባቸው የሕግ Aንቀጾችም ሆኑ የቅጣት 254 255 Aወሣሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያሣያል በማለት የAሁኑ Aመልካች ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት Aቅርቦ ችሎቱ ግራ ቀኙን ከAከራከረ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሰጠው ውሣኔ ስህተት የለበትም በማለት ውሣኔውን በማጽናቱ ነው።
Aመልካች በቁጥር 05/I/A-11/1120 በቀን 20/04/98 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የተጠሪ Aድራጐት በስር ፍ/ቤት ጥፋተኛ በተባሉባቸው ድንጋጌዎች የሚሸፈን ሆኖ Eያለ ውሣኔ የተሰጠበት የሕግ Aንቀጽ መለወጡ Aግባብነት ስለልለው ተስተካክሎ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል። በዚህ የሰበር Aቤቱታ መነሻ ተጠሪ መልስ Eንዲሰጥበት ተደርጐም ሐምል 28 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሰበር Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ ላፀና ይገባል በማለት መልሱን ሰጥቷል።
ይህ ችሎትም ጉዳዩን ከበታች ፍ/ቤቶች የውሣኔ ግልባጭ Eና Aግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። Eንደመረመረውም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የምራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪን ጥፋተኛ ያደረገባቸውን የህግ Aንቀጾች የለወጠው በAግባቡ /በሕጉ ረገድ/ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላመረመር የሚገባው ሆኖ Aግኝቶታል።
ተጠሪ በወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በክሱ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ ሟች ባለቤቱን፤ ወ/ሮ ዝናሽ ለማ የተባለችውን ሕፃን ልጅ ወልዳ Aራስ ቤት በተኛችበት ስፍራ ማካሮቨ ሽጉጥ ተኩሶባት Aናቷ ላይ ሁለት ቦታ መቷት ለህልፈተ ህይወት ዳርጓታል፣ በወ/መ/ሕ/ቁ.
27/1/ Eና 522/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ደግሞ በ1ኛው ክስ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ ከሟች ዝናሽ ለማ ጋር Eንዳይጣላ ሰዎች ጣልቃ ገብተው ለማለያየት ላገላግሉ ሲሉ Eናንተ ነገ ምስክሮች ትሆኑብኛላችሁ Aይደል? በማለት ማካሮቭ ሽጉጡን በመተኮስ የግል ተበዳይ የሆኑትን 1ኛ/ ወ/ሪት Eስከዳር ጋሻውን በሁለት ጥይት ከፊቷ ላይ መቷት Aንዱ ጥይት ከAንገቷ በስተኋላ ሲወጣ Aንዱ ጥይት ደግሞ ከAንገቷ ስር በሰውነቷ ውስጥ የቀረ በመሆኑ፣ 2ኛ/ ወ/ሪት መና መሐመድ በምትባለው ላይም Aንድ ጥይት ተኩሶባት በመሸሽዋ ህይወቷ መትረፍ የቻለ መሆኑን በመግለጽ በግፍ ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈጽሟል የሚል ክስ በAመልካች በኩል ቀርቦበት ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍ/ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ የተጠሪን የመከላከያ ማስረጃ የAቃቤ ሕግን ማስረጃዎች Aያስተባብልም በሚል ምክንያት ውድቅ Aድርጐ ተጠሪን በወ/መ/ሕ/ቁ.
27/1/ሀ/፣ 522/1/ሀ/ Eና 523 ድንጋጌዎች ስር ጥፋተኛ Aድርጓል።
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት ግን በተጠሪ ላይ የተሰጠውን የጥፋተኛነት ውሣኔ ከተቀበለ በኋላ Aድራጐቶቹ የሚሸፈኑባቸው ድንጋጌዎች ግን የስር ፍ/ቤት የጠቀሣቸው Aለመሆናቸውን በመግለጽ Aግባብነት Aላቸው ወደAላቸው ድንጋጌዎች ለውጦ ተጠሪን ጥፋተኛ Aድርጓል። ይህ ችሎት ለሕግ Aንቀጾቹ መቀየር ዋነኛ ምክንያት Aድርጐ የያዘው ተጠሪ በወቅቱ በ1ኛ የA/ሕግ ምስክር ተሰድቧል የተባለው የስድብ ዓይነት ሲታይ ለወንጀል ድርጊቶቹ ቅድመ ዝግጅት Eና ማነሣሣት፣ የክፋትና የጭካኔ ስሜት በሚያሣይ ሁኔታ ሣይሆን በምስክር ድርጊት የተነሣ በንድት፣ ስሜት ውስጥ በመግባት Eራሱን መቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሁኖ ነው የሚለውን ነጥብ ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ የሰው ግድያ ወንጀል በወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1/ሀ/ መሰረት Aንድን ሰው የሚያስጠይቀው ድርጊቱ ሆነ ተብሎ Aስቀድሞ በማሰብና በመዘጋጀት ሲፈፀም ወይም በቁጥር 81 ወይም በቁጥር 83 የተመለከቱት Aክባጅ ሁኔታዎች በተገኙበት ሁኔታ የወንጀል Aድራጊው በተለይ ጨካኝ ወይም Aደገኛ መሆኑን ሲያመለክቱ ስለመሆኑ በተጠቃሹ Aንቀጽ ተደንግጓል። ከዚሁ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለውም ለወንጀሉ ማቋቋሚያ የተጠቀሱት ነጥቦች “… ወይም…” በሚል ቃል ተያይዘው የተዘረዘሩ 256 257 መሆናቸውንና ምክንያቶቹም ወንጀሉን ለማቋቋም በAንድነት ተጣምረው መገኘት ሣያስፈልጋቸው በራሣቸው ቁመው የወንጀሉ ማቋቋሚያ ላሆኑ የሚችሉ መሆኑን ነው። በመሆኑም ቅድመ ዝግጅት Eና የክፋትና የጭካኔ ስሜት ተጣምረው የመገኘት ሁኔታ የወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1/ሀ/ ድንጋጌ ብቸኛ የወንጀሉ መቋቋሚያ ነጥቦች Aይደሉም። ይልቁንም በድንጋጌው ስር የተመለከቱት የወንጀሉ ማቋቋሚያ ነጥቦች ለየራሣቸው መቆም የሚችሉ ናቸው።
በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ ባለቤቱን ለመግደል የ1ኛዋ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ስድብ Eንደምክንያት የማይወሰድ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ያመነበት ጉዳይ ሆኖ የምስክሯ Aድራጐት ግን የተጠሪን የክፋትና የጭካኔ ስሜት በሚያሣይ ሁኔታ Eራሱን በማዘጋጀትና በማነሣሣት ለመሆኑ Aያሣይም በሚል ተደምድሟል። ይሁን Eንጂ ይኸው ድምዳሜ ፍ/ቤቱ የምስክሯ Aድራጐት ባለቤትን ለመግደል ምክንያት ላሆን Aይችልም ብሎ ከተነሣበት ነጥብ ጋር የሚጋጭ ነው ከመባሉ በተጨማሪ የወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1/ሀ/ ስር የተመለከቱት የወንጀሉ ማቋቋሚያ ነጥቦች ለየራሣቸው ላቆሙ የሚችሉ መሆናቸውን ያላገናዘበ ነው። ሟች በወቅቱ ወልዳ የተኛች Aራስ ከመሆኗም በተጨማሪ በወቅቱ ያደረገችው ምንም Aራጐት የልለ ሆኖ ተጠሪ ለሕልፈት የዳረጋት ግንባሯ ላይ በሁለት ጥይት በመምታት መሆኑ ሲታይ የተጠሪን የጭካኔ Eና የክፋት ስሜት በግልጽ የሚያሣይ ነው። ድርጊቱ የተፈፀመው በውድቅት ልላት የጦር መሣሪያን በመጠቀም በወቅቱ Aራስ በመሆኗ ልዩ ድጋፍ በሚያስፈልጋትና Eንስት መሆኗ ሲታይም Aድራጐቱ በቁጥር 81(1)(ሐ) Eና (ሰ) ስር Eንደተመለከተው በወ/መ/ሕ/ቁ. 522(1)(ሀ) ስር የሚሸፈን መሆኑን የሚያሣይ ነው። ተጠሪ Aድራጐቱን የፈፀመው ማንነቱን ተቀብላ Aብራው በመኖር ሁለት ልጅ በወለደችለት ባለቤቱ ላይ መሆኑ ከወ/መ/ሕ/ቁ. 83 Aኳያ ሲታይ Aክባጅ ምክንያት መኖሩን የሚያሣይና በግፍ ሰው የመግደል Aድራጐትን የሚያቋቁም ነው። በ1ኛ የAቃቤ ሕግ ምስክር ተነገረ የተባለው ስድብ በማናቸውም መመዘኛ Aራስ የሆነችን የትዳር Aጋር በክፋትና በጨካኝነት መንፈስ ለሕልፈተ-ሕይወት ለመዳረግ የሚያስችል ምክንያት ነው ላባል Aይችልም። በመሆኑም ተጠሪ በባለቤቱ ላይ የፈጸመው ግድያ ከቁጥር 81(1)(ሐ Eና ሰ) Eና ከቁጥር 83 ድንጋጌ Aኳያ ሲታይም በግፍ መግደሉ ተረጋግጦ Eያለ ለዚህ Aድራጐት Aግባብ ተብሎ በወ/መ/ሕ/ቁ. 523 ስር ጥፋተኛ መባሉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል በ2ኛው ክስ ለተጠቀሰው Aድራጐት Aግብብነት Aለው የተባለው የወ/መ/ሕ/ቁ. 27/1/ Eና 524/ለ/ ሲታይ ከምስክሯ Aድራጐትና ከነባራዊው ሁኔታ Aኳያ ሲመዘን ባግባቡ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ Aልተገኘም።
በዚህም መሰረት ተጠሪ በባለቤቱ ላይ ለፈፀመው የግድያ ወንጀል ላጠየቅ የሚገባው በወ/መ/ሕ/ቁ. 522(1)(ሀ) ሲሆን በ2ኛው ክስ በተጠቀሱት የግል ተበዳዮች ላይ ለፈፀመው Aድራጐት ደግሞ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በተለወጠው ድንጋጌ መሰረት ሆኖ Aግኝተናል። ይህ የሚያስገነዝበው ደግሞ ተጠሪ በዚህ ችሎት ጥፋተኛ የተባለው የበታች ፍ/ቤቶች የጥፋተኛነት ውሣኔ የሰጡባቸው ድንጋጌዎች መሻሻላቸውን ነው።
Eንዲህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ ላቀጣ የሚገባው በዚህ ችሎት ጥፋተኛ በተባለባቸው ድንጋጌዎች መሰረት ነው። በAጥፊ ላይ ቅጣት የሚወሰነው ደግሞ በወ/መ/ሕ/ቁ. 86 ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው። ችሎቱም Eነዚህን ሁኔታዎችን ተመልክቷል፤
Aመዛዝኗልም። ተጠሪ የቤተሰብ Aስተዳዳሪ መሆኑ፣ ብዙም ባለመማሩ የEውቀት ማነስና የመንፈስ ልልነት ያለበት መሆኑ Eና የኋላ ታሪኩ ሲታይም መልካም የነበረ መሆኑ በቅጣት ማቅለያነት ላያዙለት የሚገቡ መሆኑን ከወ/መ/ሕ/ቁ. 86 Eና 79(1)(ሀ) ድንጋጌዎች ተገንዝበናል። Eነዚህን 258 259 ምክንያቶች መሰረት ስናደርግ ደግሞ ተጠሪ ጥፋተኛ የተባለበት የመጀመሪያው ክስ ድንጋጌ ያስቀጣው የነበረው Eድሜ ልኩን ሁኖ በወ/መ/ሕ/ቁ. 184/ለ/ መሰረት መጠኑ መቅለል ያለበት መሆኑን ተገንዘብናል።
ሲጠቃለልም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተጠሪ ባለቤቱን በመግደሉ ላጠየቅ የሚገባው ድንጋጌ ተራ የሰው ግድያ ወንጀል በሚያስጠይቅበት ማድረጉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የተጠሪ Aድራጐት በግፍ ሰው መግደል የሚሸፈንና የቅጣቱ መጠንም ላሻሻል የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ መሰረትም የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
11541