No summary available.
ጥቅምት 28 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጐስ ወልዱ Aቶ ተገኔ ጌታነህ Aቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aቶ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- የAማራ ብ/ክ/መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ Aቶ ደረጀ ኃይሉ ተጠሪ፡- Aስማማው Aራጌ - ከጠበቃ ወ/ሮ Aዜብ ፋንታሁን ጋር ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበው ተጠሪው በፈጸመው የወንጀል ድርጊት በሥር ፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለበት የወ/መ/ህ Aንቀጽ በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት መለወጡ Aግባብ Aይደለም ሲል Aመልካች ህዳር 14 ቀን 1998 ዓ.ም Aቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የሰበር ችሎትም መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የተጠቀሰውን የሕግ Aንቀጽ ለመቀየር ሕጋዊ ምክንያት የነበረው መሆን Aለመሆኑን ለማጣራት ግራ ቀኙን Aስቀርቦ Aከራክሯል።
ከሥር ፍ/ቤት ውሳኔ መረዳት Eንደተቻለው ለከፍተኛው ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ተጠሪ ሟችን /ሚስቱ የነበረችውን ገነት ገበዬን/ ጨካኝና ነውረኛ በሆነ Aኳኋን በመግደሉ በወ/መ/ህግ Aንቀጽ 522/1/ሀ/ Aመልካች መስሪያ ቤት ክስ Aቅርቦ የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ከተጠሪው የወንጀል Aፈጻጸም Aኳያ በተጠቀሰው የወንጀል ሕግ Aንቀጽ የጥፋተኛነት ውሳኔ ሰጥቶ በሃያ /20/ ዓመት ጽኑ Eሥራት Eንዲቀጣ ፈርዶበታል። በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት 250 251 ይግባኝ በማቅረቡ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የወንጀሉን Aፈጻጸም መነሻ ምክንያትና ሁኔታ በመዘርዘር ከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል በወ/መ/ህ Aንቀጽ 523 መሰረት ጥፋተኛ በማለት በዚሁ መሰረት በAሥራ ሦስት /13/ ዓመት ጽኑ Eሥራት Eንዲቀጣ ፍርድ ሰጥቷል። ይህ ፍርድ በመሰረቱ የሕግ ስሕተት Aለው ሲል Aመልካች ያቀረበው Aቤቱታ የተጠሪ የወንጀል Aፈጻጸም በወ/መ/ህ Aንቀጽ 522/1/ሀ/ ጥፋተኛ የሚያደርገው ሆኖ ሳለ ወደ 523 ለመለወጥ የሕግ መሰረት የለውም የሚል ነው።
ከዚሁ Aኳያ የሰበር ችሎቱ መዝገቡን መርምሯል። በከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ሐተታ Eንደተመለከተው ሐምል 16 ቀን 1994 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጠሪና ሟች መኖሪያ ቤት ውስጥ ሆነው ተጠሪ የመኖሪያ ቤታቸውን በር ከዘጋ በኋላ ሟችን በበር መቀርቀሪያ ግንባሯን መትቷት በወደቀችበት ቦታ ሁለት Eጆቿን በማሰር ብልቷ ውስጥ Eጁን በማስገባት ከባድ ጉዳት Eንዳደረሰባት Eና በዚሁ ምክንያት ሐምል 23 ቀን 1994 ዓ.ም ሕይወቷ Eንዳለፈ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል። ይህንን የወንጀል ድርጊት Aፈጻጸም ከቀረቡት ማስረጃዎች ጋር በማገናዘብ የድርጊቱ Aፈጻጸም የተጠሪን ጨካኝነት Eና ነውረኛነት ያረጋግጣል በማለት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ለመለወጥ የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ያስቀመጠው ምክንያት “የተጠሪው ድርጊት ዘግናኝ ቢሆንም ሟችን ለመግደል Aስቀድሞ ያሰበና የተዘጋጀ ለመሆኑ Aልተረጋገጠም” የሚል ነው። ይህንን የጠቅላይ ፍ/ቤቱን Aቋም ከወ/መ/ህግ Aንቀጽ 522 ይዘት Aንፃር መመርመር Aግባብነት ያለው ሆኖ Aግኝተነዋል።
በመሰረቱ በወንጀል ሕግ የሀሳብ ክፍል የሚረጋገጠው ከወንጀል ድርጊት Aፈጻጸም መሆኑ Aከራካሪ Aይደለም። በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠሪ የወንጀል Aፈጻጸም በወ/መ/ሕግ Aንቀጽ 522/1/ሀ/ ሥር በተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ Eንዲወድቅ ያደረገው ድንጋጌው “Aስቀድሞ ማሰብን” Eንደዋነኛ ምክንያት ወይም ብቸኛ ምክንያት የተመለከተ Aለመሆኑ ነው።
በዚህ የወንጀል ሕግ ድንጋጌ ከባድ የግፍ Aገዳደል ወንጀል መፈጸሙን ለማረጋገጥ ወይም ለማቋቋም የሚታዩት ሁኔታዎች በAማራጭ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች መሆናቸው Eንጂ Aንዱ ከልላው ጋር በተደራራቢነት Eና በጋራ የሚታዩ ጉዳዮች መሆናቸው Aልተመለከተም። በመሆኑም የተጠሪን የወንጀል ድርጊት Aፈጻጸም ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዳት Eንደተቻለው በመጀመሪያ በቀን የመኖሪያ ቤቱን በር በመዝጋት በሟች ጩኸት የAካባቢው ሰው ደርሶ Eንዳያስጥለው ማድረጉ፣ ሟች ራሷን Eንዳትከላከል በገመድ Eጇን ወደ ኋላ ማሰሩ፣ Eንዲሁም ሟችን በበር መቀርቀሪያ ግንባሯን መትቶ ከጣላት በኋላ ብልቷ ውስጥ Eጁን በመክተት Eጅግ ከፍተኛ ለሆነ ጉዳት መዳረጉ ሲታዩ ተጠሪው የድርጊቱ ውጤት ይህንን Eንዲያስከትል የፈለገ መሆኑንና Aስቀድሞ ማሰቡን የሚያመለክቱ ከመሆናቸውም በላይ በሚስቱ የመዋለጃ Aካል ላይ የዚህ Aይነት ድርጊት መፈጸሙ ነውረኛ Eና ጨካኝ መሆኑን በማያጠራጥር ሁኔታ የሚያመለክት ነው። ከላይ ለማመልከት Eንደተሞከረው የተጠሪ የሀሳብ ሁኔታ ከድርጊቱ በመነሳት የሚገመት መሆኑ Eንዳለ ሆኖ የድርጊቱ Aፈጻጸም በራሱ Eጅግ ጨካኝና ነውረኛ መሆኑን ያረጋግጣል። ከዚህም ባሻገር የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ውሳኔውን ለማሻሻል መሰረት ያደረገው ሁኔታ የተጠሪን “የስንፈተ ወሲብ” ችግር ሕብረተሰቡ ከሚያደርስበት ተፅኖ Aንፃር በማየት Eንደሆነ በውሳኔው ተመልክቷል።
No topics extracted.
ይህም ሁኔታ የተጠሪው የተፈጥሮ ችግር ቢኖር Eንኳ ጋብቻቸውን ከማፍረስ Aልፎ የሟችን ሕይወት ለማጥፋቱ Eንደተገቢ ምክንያት ተደርጐ መወሰዱ Aግባብነት የለውም። ባጠቃላይ የከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪን የወንጀል ድርጊት Aፈጻጸም በማስረጃ በማጣራት Aግባብነት ባለው የወንጀል ሕግ Aንቀጽ 522 /1/ ሀ ሥር የሰጠውን የጥፋተኛነት ውሳኔ Eና ቅጣት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቂ የሕግ ምክንያት ሳይኖረው መቀየሩ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ሆኖ ተገኝቷል።
የAማራ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በወ/መ/ቁ. 05312 ጥቅምት 6 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የደቡብ ጐንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር ወ/00320 በጥቅምት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔውን Eንዲያውቁት ይፃፍ።
የዞኑ ማረሚያ ቤቶች በዚህ ፍርድ መሰረት Eንዲያስፈጽሙ ይፃፍ።
መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ