No summary available.
ጥቅምት 5 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው Aመልካች ነሐሴ 18 ቀን 1997 ዓ.ም ፅፎ ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት ነው።
የጉዳዩ የሥር Aመጣጥ ተጠሪ የወ/መ/ሕ/ቁ. 522/1ሀ/ን በመተላለፍ መጋቢት 26 ቀን 1996 ዓ.ም ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ላይ በፖዌ ልዩ ወረዳ በዳንጉር ቀበል መክላከያ ካምÝ Aካባቢ ሰውን ለመግደል Aስቦና Aቅዶ ሟች ማስተዋል Aማርቸኩል የተባለችውን በEኔ ላይ ወንድ ደርባለች በሚል ምክንያት ቂም ይዞ በመነሳሳት በያዘው ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጭካኔበተሞላበት ሁኔታ በሶስት ጥይት ደብድቦ ገድሐል የሚል ክስ ቀርቦበት ድርጊቱ በማለስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ በተጠቀሰበት Aንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ በEድሜ ልክ ፅኑ Eስራት Eንዲቀጣ የመተከል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈርዷል። ተጠሪ በቅጣት ውሣኔው ላይ ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ Aቅርቦ ፍርድ ቤቱም በAብላጫ ድምፅ ቅጣቱን ወደ ሃያ Aመት ፅኑ Eስራት ዝቅ Aድርጐለታል የክልሉ ዓቃቤ ሕግም በዚሁ የቅጣት ውሣኔ ቅር ተሰኝቶ ይህን የሰበር Aቤቱታ Aቅርቧል።
246 247 ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የሰበር Aቤቱታውን መርምሮ ተጠሪን በማስቀረብ ግራ ቀኙን Aከራክሯል። ክርክሩንም Aግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርም[ል። ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ተጠሪ ድርጊቱን መፈፀሙን ያለመካዱን፣ ተጠሪ ድርጊቱን ቢያምንም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለትክክለኛ ፍትሕ Aሰጣጥ ዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎቹን Eንዲያቀርብ ማድረጉን Eና ተጠሪም Eንዲከላከል መብቱ ቢጠበቅለትም የመከላከያ ማስረጃ Eንደልለው መግለፁን Aስፍሮ በቀረበው የዓቃቤ ሕገ ማስረጃ መሰረት የጥፋተኝነት ውሣኔ ካሣለፈ በኋላ ዓቃቤ ሕግ ቅጣቱ በተጠሪው ላይ ከብዶ Eንዲወሰንበት በመጠየቅ፣ ተጠሪም በበኩሉ ቀደም ሲል ልላ ወንጀል Aለመፈፀሙን Eና ለ6 ዓመት በመከላከያ ሰራዊት Aባልነት ማገልገሉን በመግለፅ ግራ ቀኙ የየበኩላቸውን የቅጣት Aስተየየት ካቀረቡ በኋላ ፍርድ ቤቱ በAንድ በኩል ተጠሪ በመጥፎ Aመል በቂመኝነትና በወራዳነት፣ ፍፁም በሆነ ፈቃደኝነትና ከፍተኛ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ሟችን Aያ[[ጠ መግደሉ ጨካኝነቱን Eንደሚያመለክት ከግምት ውስጥ በማስገባት በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ማገልገሉና የቀድሞ ሪከርድ የልለበት መሆኑን መገንዘቡን ገልፆ ቅጣቱን ከማቅለል ይልቅ የወንጀል Aፈፃፀሙ ቅጣቱ Eንዲከብድ የሚያመዝን ሆኖ መገኘቱን በመግለፅ ተጠሪ በEድሜ ክል ፅኑ Eሥራት Eንዲቀጣ ወስኗል። ተጠሪም በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ባቀረበው ይግባኝ ወንጀሉን የፈፀመው የትዳር ጓደኛው የሆነችው ሟች በርሱ ላይ ልላ ወንድ መደረቧ ለወንጀል ያነሣሣው መሆኑን Eና በወቅቱም በስካር መንፈስ ራሱን ላቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ መሆኑን፣ በተጨማሪም የስካር መንፈሱ Eንደበረደለት በድርጊቱ ተፀፅቶ Eጁን ለፖላስ መስጠቱን ገልፆ ጠቀላይ ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ድርጊቱን በደም ፍላትና በስካር መንፈስ ለመፈፀሙ ያቀረባቸው ምክንያቶች ቅጣቱን ለማቅለል የሚያስችሉ ቢሆኑም ተጠሪ ድርጊቱን በዚህ መሰረት ለመፈፀሙ ማስረጃ ያለማቅረቡን በመግለፅ ክርክሩን ውድቅ Aድርጓል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ በመቀጠል 1. ተጠሪ ጥፋቱን Aምኖ ለመንግሥት Eጁን መስጠቱ 2. በልላ ማስረጃ ባይረጋገጥም ሟች ልላ ወንድ ደርባለች በማለት መጠርጠሩ ስሜቱን ላነካና መረበሽንም የሚያስከትልበት ሆኖ መታሰቡና 3. ተጠሪ Aስካሁን ባሉት ክርክሮች የወንጀል ድርጊቱን Aምኖ መፀፀቱን ስለሚያመለክት በወ/መ/ሕ/ቁ. 79/1/መ/ Eና /ሰ/ Eንዲሁም 184/መ/ መሰረት ከመነሻው Eድሜ ልክ በመፍረድ ቅጣቱን ወደ 20 Aመት ዝቅ Aድርጓል።
በመሆኑም በተጠሪ ላይ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰነው የEድሜ ልክ ፅኑ Eሥራት በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻሽሎ መወሰኑ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ቀጥሎ Eንመለከታለን።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጣትን ለማቅለል ከተጠቀመባቸው ሦስት ምክንያቶች ውስጥ ሁለቱ ማለትም ተጠሪ ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ Eጁን ለመንግሥት መስጠቱ መፀፀቱን ያመለክታል በማለት Eና Eስካሁን በተካሕዱት ክርክሮችም ተጠሪ ድርጊቱን Aምኖ ቅጣቱ ብቻ ይቀነስልኝ ማለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ ፀፀትን ያመለክታል በማለት የጠቀሳቸው ምክንያቶች ተቀባይነት ያላቸው ሆነው Aልተገኙም ለማለት Aልተቻልም።
No topics extracted.
ምክንያቱም በ1996 ዓ.ም በወጣው Aዲሱ የወንጀል ሕግ በAንቀጽ 82/1/መ/ ላይ ወንጀለኛው ወንጀሉን ካደረሰ በኋላ በEውነት የተፀፀተ መሆኑን ለማስረዳት ጥፋቱን በመገንዘብ ራሱን ለፍትሕ Aካላት ካቀረበ፣ በክስ ማመልከቻው የተገለፀውን የወንጀል ዝርዝር በሙሉ ካመነ ቅጣቱ Eንደሚቀልለት ተደንግጓል። ምንም Eንኳን ተጠሪ ድርጊቱን በፈፀመበት ወቅት ተፈፃሚው ሕግ የቀድሞው የ1949 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቢሆንም ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ ውሣኔ በተሰጠበት ሰኔ 13 ቀን 1997 ዓ.ም Aዲሱ የወንጀል ሕግ ከግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለ በመሆኑና በAዲሱ የወንጀል ሕግ Aንቀጽ 6 ሥር Aዲሱ ሕግ ከፀና በኋላ በሥራ ላይ ከነበረው /ከቀድሞው/ የወንጀል ሕግ ይልቅ Aዲሱ ሕግ ቅጣት 248 249 የሚያቀል ከሆነ በዚሁ ሕግ መሰረት ቅጣቱ Eንደሚቀል የተደነገገ በመሆኑ ተጠሪ ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ Eጁን ለመንግሥት መስጠቱና የቀረበበትንም ክስ ገና ከመነሻው ጀምሮ Aምኖ መገኘቱ የቅጣት ማቅለያ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሆኖ ተገኝቷል።
ስለዚህ ከላይ የተመለከቱት 3 ምክንያቶች ቅጣቱን ለማቅለል የሚያስችሉ በመሆናቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በAብላጫ ድምፅ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ይ/መ/ቁ. 647 ሰኔ 13 ቀን 1997 ዓ.ም በAብላጫ ድምፅ የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ውሳኔው መፅናቱን Eንዲያውቁት የውሣኔው ግልባጭ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለተጠሪ በየAድራሻቸው ይድረሳቸው።
መዘገቡ ተዘግቷል የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/