No summary available.
ሐምል 1 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የIትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ኃይሉ ተሰማ ተጠሪ፡- 1/ ወ/ሮ ለተብርሃን በየነ 2/ የAቶ ገብረኪዳን ገዳ ወራሾች Eነ ፋሲል ገ/ኪዳን - ጠበቃ ኃ/ማርያም Iቲቻ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በOሮሚያ ክልል የምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የሰበር Aቤታውም ላቀርብ የቻለው Aመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ተጠሪዎች ባቀረቡት የተከሳሽ ከሣሽነት ክስ መሰረት Aመልካች የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍል ይገባል ተብሎ በመወሰኑ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ Aመልካች በምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው ክስ ከሣሽ ንብረትነቱ የAቶ ደረጀ ጉደታ ለሆነ ተሽከርካሪ በደቡብ Aብይ ቅርንጫፍ Aጠቃላይ የመድን ዋስትና ሰጥቶ በEንቅስቃሴ ላይ Eንዳለ ንብረትነቱ በAቶ ገ/ኪዳን ገዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኪና በመገጨቱና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ለደረሰው Aጠቃላይ ውድመት ከሣሽ ተገቢውን ካሣ የከፈለ ሲሆን በደረሰው Aደጋ ጥፋተኛው የተከሣሽን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ግለሰብ Eንደሆነ በማስረጃ 238 239 ተረጋግጧል፣ ይሄው Aደጋውን ያደረሰው ተሽከርካሪ በIትዮጵያ መድን ድርጅት ሰሜን ምEራብ ዓቢይ ቅርንጫፍ የመድን ዋስትና ስለነበረው በዚሁ መሰረት በ3ኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት Eስከ ብር 1AA ሺህ ካሣ ለመክፈል ከሣሽ ኃላፊነት ስለነበረበት ይህንን ገንዘብ በቀጥታ ጠያቂ ለሆነው ለደቡብ ዓቢይ ቅርንጫፍ Eንዲከፍል ተደርጓል። ስለሆነም የተከሣሽ መኪና በልላ የ3ኛ ወገን መኪና ላይ ባደረሰው ጉዳት በዋስትና ከተገባው የ3ኛ ወገን ኃላፊነት ጣሪያ በላይ የሆነውን ብር 369,342.00 Eንዲከፍሉ ይወስንልኝ በማለት ጠይቋል።
ተከሣሽ Aቶ ገብረኪዳን ገዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ስለተባለ የሟች ሚስትና ወራሾች በክርክሩ Eንዲተኩ ተደርጎ በሰጡት መልስ Aደጋ Aደረሰ የተባለው የሰ/ቁ. 3-382A1 መኪና በከሣሹ የመድን ሽፋን የተሰጠው ስለሆነና ጉዳቱም የደረሰው በሁለቱም መኪናዎች ላይ በመሆኑ በዚሁ መሰረት በሁለቱም መኪናዎች ላይ ለደረሰው ጉዳት ካሣ መክፈል ስለሚገባው Eኛን መጠየቅ Aይችልም በማለት የተከራከሩ ሲሆን በልላ በኩልም የተከሣሾች መኪና በግጭቱ መውደሙ በከሣሽ የታመነ ስለሆነ የመኪናውን የዋጋ ግምት ብር 265 ሺህ የቅሪቱን ዋጋ Eና የተቋረጠ ገቢን ጨምሮ በድምሩ ብር 488 ሺህ ከሣሽ Eንዲከፍል ይወስንልን በማለት የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ Aቅርበዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ዋናውን ክስና የተከሣሽ ከሣሽነት ክሱን መርምሮ የIትዮጵያ መድን ድርጅት ለተጎጂውም ሆነ ለጉዳት Aድራሹ መኪና የመድን ሽፋን የሰጠ Eንደመሆኑ መጠን ከንግድ ሕግ ቁጥር 663 Eና 664 Aኳያ ለሁለቱም ካሣ የመክፈል ኃላፊነት ስላለበት ለተከሣሾች ካሣ የመክፈል ግድታ Aለበት ካለ በኋላ መጠኑን በተመለከተ ከሣሽ ብር 92 ሺህ ካሣ ለመክፈል መስማማቱን ከቀረበው ማስረጃ መረዳት የተቻለ ስለሆነና የመኪናውም ቅሪት ብር 25A ሺ Eንደሆነ ስለተረጋገጠ ይህንን ክፍያ ለመፈጸም ከሣሽ ፈቃደኛ የነበረ ቢሆንም ያልፈጸመ በመሆኑ በድምሩ ብር 342 ሺህ በመኪናው ላይ ለደረሰ ጉዳት ካሣ መክፈል ያለበት ስለሆነ የሟች ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ለተብርሃን በየነ ግማሹን ማግኘት ስለሚገባቸው ብር 171 ሺህ Eንዲከፈላቸው Eንደዚሁም የተቋረጠ ገቢን በተመለከተ ወ/ሮ ለተብርሃን በየነ መኪናው ተጠግኖ ሥራ ቢጀምር ፈቃደኛ መሆናቸውን በ6/2/96 ዓ.ም. ባቀረቡት ማስታወሻ ለከሣሽ ያረጋገጡ ቢሆንም በዚሁ መሰረት መኪናው ተጠግኖ ያልተሰጣቸው ስለሆነ መኪናውን ለመጠገን ያስፈልጋል ተብሎ የሚገመተው የ3 ወር ጊዜ ተቀንሶ ከ6/7/96 Eስከ 18/4/98 ዓ.ም. ላለው የ1 ዓመት ከ8 ወር ከ12 ቀናት የተቋረጠ ጥቅም ከሣሽ መክፈል ይገባዋል ካለ በኋላ መጠኑን በተመለከተም ወ/ሮ ለተብርሃን በየነ መኪናው በቀን ብር 7AA ገቢ ያስገኝ Eንደነበር በመግለጽ በዚሁ ተሰልቶ ካሣ Eንዲከፈላቸው የጠየቁትን በመቀበል በዚሁ ስልት መሰረት የወ/ሮ ለተብርሃን በየነ ድርሻ ብር 214,200 ስለሚሆን ይህንን የተቋረጠ ገቢና ከላይ የተጠቀሰውን የመኪና ጉዳት ካሣ ጨምሮ በድምሩ ብር 385,2AA.00 ከሣሽ ለወ/ሮ ለተብርሃን በየነ Eንዲከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በልላ በኩልም ከሣሽ ያቀረበውን ክስ በተመለከተም ከሣሽ ለወ/ሮ ለተብርሃንም ሆነ ለAቶ ገ/ኪዳን ገዳ ወራሾች ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይፈጽም ክሱን በAቶ ገ/ኪዳን ገዳ ወራሾችና በወ/ሮ ለተብርሃን በየነ ላይ ማቅረቡ በንግድ ሕግ ቁጥር 683/3/ መሰረት Aግባብነት የለውም ብሎ ሳይቀበለው ቀርቷል።
No topics extracted.
የሥር ከሣሽ የAሁን Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱ ይግባኙን መርምሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የልለው ነው በማለት Aጽንቶታል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎትም Aቤቱታውን መርምሮ Aመልካች በደንበኛው ላይ ለደረሰ ጉዳት የከፈለውን ገንዘብ ደንበኛውን ተክቶ የጉዳት Aድራሹን ቤተሰብ በን/ሕ/ቁ/ 240 241 683/3/ መጠየቅ Aይችልም መባሉ፣ በተጠሪዎች መኪና የዋጋ ግምትና በተጨማሪም የተቋረጠ ገቢ Aመልካች Eንዲከፍል መወሰኑ ለሰበር ቀርቦ ላጣራ Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የዚህን ችሎት ምላሽ የሚሹ የጉዳዩ ጭብጦች፡- Aመልካች ያቀረበው ክስ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው በAግባቡ ነው Aይደለም?
ለተጠሪ የመኪና ዋጋ ግምትና የተቋረጠ ገቢ Eንዲከፈል የተወሰነው በAግባቡ ነው Aይደለም? የሚሉ ናቸው።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ Aመልካች በምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ከላይ Eንደተመለከተው ንብረትነቱ የAቶ ደረጄ ጉደታ የሆነው ተሽከርካሪ በAቶ ገ/ኪዳን ገዳ ተሽከርካሪ ግጭት ደርሶበት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ከነተሳቢው ብር 783,512.50 ካሣ የተከፈለ ስለሆነና ከዚህ ገንዘብ ላይ የመኪናው ቅሪት የተሸጠበት ዋጋና Eንደዚሁም የተጠሪዎች መኪና በ3ኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ለተገባ የኃላፊነት Iንሹራንስ /liability insurance/ የተከፈለው ሲቀነስ በቀሪነት ብር 396,342.00 ስለሚፈለግ ይህንኑ ገንዘብ Eንዲከፍሉ ይወስንልኝ በማለት ነው። የምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በዚህ መልኩ የቀረበውን ክስ ሳይቀበለው የቀረው መድን ሰጭው በን/ሕ/ቁ. 683/3/ መሰረት በመድን ገቢው ሚስትና ልጆች ላይ የመዳረግ መብት ስለልለው ለደንበኛው የከፈለው ገንዘብ ይተካልኝ በማለት ጥያቄ ማቅረብ Aይችልም በሚል ነው።
የንግድ ሕግ ቁጥር 683 ስለ Iንሹራንስ ሰጭው በምትክነት መግባት /Substitution of insurer/ የሚመለከት ሲሆን በዚሁ መሰረትም Iንሹራንስ ሰጭው በከፈለው ካሳ መጠን ጉዳቱ Eንዲደርስ ባደረጉት 3ኛ ወገኖች ላይ ክስ ለማቅረብ Iንሹራንስ ለገባው ሰው በተከፈለው ገንዘብ መጠን ባሉት መብቶችና ክሶች Iንሹራንስ ሰጭው ምትክ ሆኖ Eንዲገባ በዚሁ Aንቀጽ በንUስ ቁጥር /1/ ሥር ተመልክቷል።
ይህ Eንዳለ ሆኖም ለክፋት የተደረገ ካልሆነ በስተቀር Iንሹራንስ ሰጭው በIንሹራንስ ገቢው ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ወኪሎች ሰራተኞች ወይም ከEርሱ ጋር ዘወትር Aብረው በሚኖሩት ሰዎች ላይ Iንሹራንስ ሰጭው የመዳረግ መብት Eንደልለው በዚሁ ድንጋጌ በንUስ Aንቀጽ /3/ ሥር ተመልክቷል። ይህም የAጠቃላይ መርሁ ልዩ ሁኔታ /Exception to the General Rule/ Eንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ከዚህም ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው Iንሹራንስ ሰጭው የመዳረግ መብት የሚኖረው በሕጉ ላይ የተዘረዘሩት ሰዎች የመድን ሽፋን በተሰጠው የመድን ገቢው ንብረት ላይ በክፋት ጉዳት Aድርሰው በሚገኙበት ጊዜ Eንደሆነ ነው። በተያዘው ጉዳይ ግን Aመልካች የመዳረግ መብቱን መሰረት በማድረግ በክስ የጠየቀው በተጠሪዎች መኪና ላይ ለደረሰው ጉዳት የተከፈለው ካሣ Eንዲተካለት ሳይሆን በተጠሪዎች መኪና ተገጭቶ ጉዳት የደረሰበትንና ካሣ የተከፈለበትን የAቶ ደረጀ ጉደታን መኪና በተመለከተ ስለሆነ ከላይ በተጠቀሰው የንግድ ሕግ ቁጥር 683/3/ መሰረትም የመዳረግ መብት የሚኖረው ይሆናል ማለት ነው። ሆኖም ግን የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በዚህ ጉዳይ Aመልካች የመዳረግ መብት የለውም በማለት ክሱን ሳይቀበል መቅረቱ Eንደዚሁም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ ለድንጋጌው የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል።
ወደ 2ኛው ጭብጥ ስናልፍም የመድን ሽፋን የተገባለት የተጠሪዎች መኪና ቅሪቱ ተገምቶ ብር 25A ሺህ Eንደሆነ Eንደዚሁም የጉዳት ካሣ ብር 92 ሺህ Eንደሆነና በድምሩ ብር 342 ሺህ Aመልካች ለተጠሪዎች መክፈል Eንደሚገባው በሥር ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ በማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ተጠሪዎች ባቀረቡት የተከሳሽ ከሣሽነት ክስ የዚህ ገንዘብ ግማሹ ብር 171 242 243 ሺህ ለወ/ሮ ለተብርሃን Eንዲከፈል መወሰኑ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ Aላገኘነውም።
በልላ በኩልም ተጠሪዎች Eንዲከፈላቸው የጠየቁትን የተቋረጠ ገቢ በተመለከተም Aመልካች የሚከራከረው ግራ ቀኛችን ባደረግነው ውል የተቋረጠ ገቢ Eንደማይከፈል ተስማምተናል በማለት ሲሆን ነገር ግን Aመልካች ጉዳት የደረሰበትን የተጠሪዎች መኪና ጠግኖ ለማስረከብ ስምምነቱን የገለጸ Eንደመሆኑ መጠን ከውሉ Aኳያ የተቋረጠ ጥቅም ለመክፈል የማይገደደው መኪናውን ለመጠገን Aስፈላጊ ለሆነው ጊዜ (ማስጠገኑ ለሚወስደው ጊዜ) ብቻ Eንጂ ከዚህ Aልፎ መኪናው ሳይጠገን ለቀረበት ጊዜ በሙሉ ላሆን Aይችልም። በዚሁ መሰረትም መኪናውን ለመጠገን ያስፈልጋል የተባለው የ3 ወር ጊዜ በAEምሮ ግምት ተቀባይነት ያለው ነው። በዚህ ጊዜ መኪናውን Aመልካች ጠግኖ ለተጠሪዎች ካላስረከበ ደግሞ ተጠግኖ ቢሆን ኖሮ ላያስገኝ ይችል የነበረውንና ነገር ግን ሳይከፈል የቀረውን የተቋረጠ ገቢ መክፈል ይኖርበታል ማለት ነው። መጠኑን በተመለከተም መኪናው በቀን ብር 7AA ገቢ ያስገባ Eንደነበር ተጠሪዎች ገልጸው በዚሁ ልክ ካሣ Eንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። ሆኖም ግን ጉዳት የደረሰበት መኪና ይህን ያሕል ገቢ ያስገባ Eንደነበር በማስረጃ Aላረጋገጡም።
ከውልም ሆነ ከውል ውጭ ባለ ግንኙነት የጉዳት ካሣ Eንዲከፈለው የሚጠይቅ ወገን የደረሰበትን ኪሣራ /Damages/ በማስረጃ ማረጋገጥ Eንደሚገባው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 179A/1/ Eና 2141 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ይሁንና ጉዳት መድረሱ Eስከተረጋገጠ ድረስ የነገሩን Aካባቢ ሁኔታ ግምት ውስጥ በመክተት የካሣ መጠኑን ዳኞች በርትE መወሰን Eንዲችሉ ሕጉ ሥልጣን የሰጣቸው Eንደመሆኑ መጠን በተያዘውም ጉዳይ የከፍተኛው ፍ/ቤት Aመልካች በክሥ የተጠቀውን የገንዘብ መጠን በበኩሉ Aስልቶ Eንዲከፈል ውሣኔ መስጠቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ Aላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
ስለሆነም Aመልካች በመዳረግ ከጠየቀው ብር 396,342 /ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ሶስት መቶ Aርባ ሁለት/ ላይ ግማሹን ብር 198,171 /Aንድ መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ Aንድ መቶ ሰባ Aንድ ብር/ ተጠሪ ወ/ሮ ለተብርሃን በየነ ላከፍሉ ይገባል ብለናል።
Aመልካች በድምሩ ብር 385,2AA.00 /ሦስት መቶ ሰማንያ Aምስት ሺህ ሁለት መቶ ብር/ ለተጠሪ ላከፍል ይገባል ተብሎ የተወሰነው የካሣ መጠን በAግባቡ ስለሆነ Aጽንተነዋል።
ግራ ቀኙ Aንዱ ከልላው የሚፈልገው ገንዘብ ሲቻቻል Aመልካች ብር 187,A29.00 /Aንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ ሀያ ዘጠኝ ብር/ ለተጠሪ መክፈል የሚገባው ስለሆነ ይህንኑ ገንዘብ Eንዲከፍል ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።