No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 247A4 ኀዳር 12 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጎስ ወልዱ Aቶ ተገኔ ጌታነህ Aቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aቶ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- የIትዮጵያ መድን ድርጅት-ጠበቃ Aቶ ኃይሉ ተሰማ-ቀረቡ ተጠሪ፡- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ A/ሕግ Aቶ ተመስገን መንግሥቴ ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር የመድን ዋስትና ውል ስለመኖር የሚመለከት ነው።
ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ክስ በAሰላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመሰረተው የAሁኑ Aመልካች ሲሆን የክሱ ይዘትም ባጭሩ የተጠሪ ንብረት የሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች የመድን ሽፋን Eንዲያገኙ ጥር 2 ቀን 1995 በደብዳቤ ቁጥር 2915/73/9 በጠየቀው መሰረት Aመልካች ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኋላ የሰልዳ ቁ. 4-28437 ቶዮታ ኮብራ የሆነው የተጠሪ መኪና E.ኤ.A. ከ13/3/93 ጀምሮ ለAንድ ዓመት የሚቆይ የመድን ሽፋን ውል በፖላሲ ቁጥር NK/1/MTPV/0727/03 ተሰጥቶት፣ ለዚህም Aገልግሎት Aረቦን ብር 11‚51A.00 /Aሥራ Aንድ ሺህ Aምስት መቶ Aሥር ብር/ ተጠሪ ባለመክፈሉ በፍርድ Eንዲወሰንበት ሲል ክስ ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤትም የተጠሪን የጽሑፍ Eና የቃል ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበውን የመድን ዋስትና ውል 228 229 Aለመኖር የተመለከተ ክርክር ከቀረበው የግራ ቀኝ ማስረጃ Aንፃር ከመረመረ በኋላ የመድን ዋስትና ውሉ ላይ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1727/1/ የተዋዋይ ወገኖች ፊርማ መኖር Eንዳለበት Eና ይህም በሁለት ምስክሮች መረጋገጥ ያለበት መሆኑን ሕጉ የሚያስገድድ ሆኖ Eያለ በAመልካች በኩል የቀረበው ማስረጃ ይህንን Eና ልሎች የሕጉን ድንጋጌዎች ስለማያሟላ በAመልካች Eና በተጠሪ መካከል ውል ተቋቁሟል ለማለት Eጅግ Aዳጋች ነው በማለት ክሱን ውድቅ Aድርጓል። ይህንን ውሣኔ መቃወም Aመልካች ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን የፍድራሉ ከፍተኛ ፍረድ ቤት ይግባኙ Aያስቀርብም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።
ለሰበር ችሎት የቀረበው Aቤቱታ ይህንን ውሣኔ የሚቃወም ሲሆን Aመልካች ያቀረባቸው የAቤቱታ ነጥቦች፣ የመድን ውል Aመሰራረት የሚረጋገጠው በንግድ ሕጉ በተደነገገው Eንጂ በፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ Aይደለም፣ ይህም ሲባል በጉዳዩ ላይ ልዩ ሕግ Eያለ የጠቅላላ ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት Aድርጎ የመድን ውል የለም መባሉ Aግባብ Aይደለም። Eንዲሁም የምስክሮች ፊርማ መኖር ወሳኝና Aንገብጋቢ መሆኑን የንግድ ሕጉ Aያመለክትም። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች የመድን ውል Aመሰራረትን በተመለከተ የወሰዱት Aቋም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ Eንዲታረም ሲል ጠይቋል።
የሰበር ችሎቱም መዝገቡን ከመረመረ በኋላ በAመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሰነድ ልውውጥ በሕግ የተደነገገውን የመድን ውል ፎርም Aያሟላም በሚል Aመልካች ያቀረበው ክስ ውድቅ የተደረገው በሕጉ Aግባብ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪን Aስቀርቦ Aከራክሯል።
የተጠሪ መ/ቤት ተወካይ የክልሉ ፍ/ቢሮ በAቤቱታው ላይ ሚያዝያ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ የመድን ውል በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ካልተፈረመና በምስክሮች ካልተረጋገጠ ሕጋዊ ውጤት Eንደልለው የፍ/ብ/ሕግ Aንቀጽ 1675 Eና የንግድ ሕግ Aንቀጽ 659/1/ ያስገነዝባል።
Aመልካች የመድን ውል Aለ በማለት ያቀረበው ማስረጃ የተጠሪ መ/ቤት ማኀተምና ፊርማ የልለው በመሆኑ Aመልካች ብቻውን ያዘጋጀው ውል ተጠሪን ስለማያስገድድ የመድን ውል ሳይኖር የመድን ውል ግድታ የለም በማለት በሥር ፍ/ቤት ያቀረበውን ክርክር Aጠናክሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ Eንዲፀና ጠይቋል።
Aመልካች ግንቦት 16 ቀን 1999 ዓ.ም. ባቀረበው የመልስ መልስ በተጠሪ የቀረበው የመድን ዋስትና ሽፋን ጥያቄ Eና በAመልካች የተሰጠው የመድን ውል ፖላሲ በጋራ ላታዩ ይገባል በማለት Aቤቱታውን Aጠናክሮ ተከራክሯል።
በዚህ ጉዳይ ምላሽ የሚያሻው የሕግ ነጥብ በAመልካች Eና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሰነድ ልውውጥ ስለ Iንሹራንስ ውል Aፃፃፍ ፎርም የተመለከተውን ድንጋጌ Aሟልቷልን? የሚለው ሆኖ Aግኝተነዋል።
ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት የሕጉን ይዘት ከመመርመራችን በፊት በፍሬ ጉዳይ ክርክሩ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ንብረትነታቸው የተጠሪ ለሆኑት ሁለት መኪኖች የመድን ሽፋን Eንዲሰጠው በተጠሪ መ/ቤት ማኀተም Eና በሚመለከተው ሁለት ፊርማ መጠየቁ Aመልካች ለAንደኛው መኪና የመድን ሽፋን ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኖ የመድን ውል ፖላሲ ለተጠሪ መስጠቱ ነው። Aከራካሪው ጉዳይ የEነዚህ ሁኔታዎች መኖር በራሱ የIንሹራንስ ውል በAመልካች Eና በተጠሪ መካከል መመሥረቱን ያረጋግጣልን? የሚለው ነው።
No topics extracted.
የመድን ውል ስለመኖሩ ለማስረዳት Aመልካች ያቀረበውን ማስረጃ ከፍተኛው ፍ/ቤት ሲመረምር መሰረት ያደረገው በፍ/ብ/ሕግ ስለውሎች Aጻጻፍ ፎርም የተመለከተውን ድንጋጌ ነው። በሥር ፍ/ቤት ተጠሪ Aጥብቆ የተከራከረው የውሎችን Aመሰራረት የሚመለከቱ የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌዎች ከመሆኑ የተነሣ ይመሰላል ከፍተኛው ፍ/ቤት ትኩረት የሰጠውና ለውሣኔው መሰረት ያደረገው የፍ/ብ/ሕግ Aንቀጽ 1719 Eና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች 230 231 ነው። Eነዚህ ድንጋጌዎች በጥቅሉ መሰረት ያደረጉት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1725/ለ/ Eና 1727/2/ መሰረት የIንሹራንስ ውሎች በጽሁፍ መደረግ Eንዳለባቸው በጽሁፍ የሚደረጉትም በምስክሮች ፊት መሆን Eንዳለበት ይህ ካልተፈፀመ ውሉ Eንደማይፀና የሚያስገነዝቡ ናቸው የሚለውን የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት መሆኑን ተገንዝበናል።
የIንሹራንስ ውል Aመሰራረት Eና የፍ/ብ/ሕግ Aንቀጽ 1725 Eና 1727 ድንጋጌዎች Aፈጻጸም ወሰን Eንዲሁም የንግድ ሕግ ስለ Iንሹራንስ ውሎች የተመለከተውን ድንጋጌ ቁጥር 657 Eና ተከታዮቹ በተመለከተ የሰበር ችሎት ከዚህ ቀደም በመዝገብ ቁጥር 23AA3 ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ Aሁን ከተያዘው ጉዳይ Eና ጭብጥ ጋር ተመሣሣይ ሆኖ ስላገኘነው ከዛው ውሣኔ Aንፃር መታየት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
በመሆኑም Aሁን በተያዘው ጉዳይ Aመልካች ለተጠሪ የሰጠው የመድን ሽፋን ለAንድ ዓመት በመሆኑ የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 23AA3 በወሰደው Aቋም መሰረት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1725 Eና 1727 ለዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት የለውም ብለናል። /የሰበር መ/ቁ. 23AA3 ይመለከቷል/ ስለዚህ ተጠሪ የመድን ሽፋን Eንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት Aመልካች ለAንድ ዓመት የሚቆይ የመድን ሽፋን በፖላሲው ፈርሞ የሰጠው መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ Eና የፖላሲው ይዘት በንግድ ሕግ ቁጥር 654‚ 657 Eና 658 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ይዘት ያሟላ መሆኑ በሥር ፍ/ቤት ያልተካደ በመሆኑና Eነዚህ Aንቀጾች በAመልካችና በተጠሪ መካከል ለAንድ ዓመት የቆየ የመድን ሽፋን መኖሩን ለማረጋገጥ በቂ ሆነው ሳለ የሥር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1725 Eና 1727ን መሰረት በማድረግ በሁለቱ መካከል የመድን ውል Aልተመሰረተም በማለት ተጠሪ የጠየቀውን Aረቦን Eንዳይከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
በAመልካች Eና በተጠሪ መካከል በፓላሲ ቁጥር NK/1/MTPV/07 27/03 በተሰጠው የመድን ፖላሲ ውል መሰረት ለAንድ ዓመት የቆየ የመድን ውል ተመስርቷል ብለናል።
የAሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 816 መጋቢት 19 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ Eና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 39792