No summary available.
ሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በAሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ ለሚጠቀምባቸው 10 ተሽከርካሪዎች በገባው የመድን ውል መሰረት መክፈል የሚገባውን ብር 55,068.56 የAረቦን ክፍያ ለመክፈል ፈቃደኛ ስላልሆነ Eንዲከፈል ይወሰንልን በማለት ጠይቋል።
የAመልካች ክስና ማስረጃ ለተጠሪ ደርሶ መልስ Eንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ተጠሪ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ በAግባቡ ደርሶት ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት Eንዲታይ ፍ/ቤቱ ትEዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የAመልካችን ክስና ማስረጃ መርምሮ በAመልካችና በተጠሪ መካከል በሕግ Aግባብ የተቋቋመ የመድን ውል Aለ ለማለት ስለማይቻል Aመልካች ያቀረበው ማስረጃ ድጋፍ የለውም በማለት ክሱን ሳይቀበለው ቀርቷል።
Aመልካች በዚህ ውሳኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ Aይደለም በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
224 225 የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎት Aቤቱታውን መርምሮ ያስቀርባል በማለት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ በግራ ቀኙ መካከል በሕግ Aግባብ የተቋቋመ የመድን ውል Aለ ወይስ የለም? የሚለው በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ Aኳያ ጉዳዩ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካች ክስ ያቀረበው ከተጠሪ ጋር ባደረግነው የመድን ውል መሰረት ላከፈለኝ ይገባኝ የነበረው የAረቦን ክፍያ ያልተከፈለኝ ስለሆነ ይከፈለኝ በማለት Eንደመሆኑ መጠን ጉዳዩ መታየት ያለበት የግራ ቀኙን ግንኙነት በተለይ ከሚገዛው የንግድ ሕጉ Aኳያ ነው።
ከዚህም Aንጻር ጉዳዩ ሲታይ የመድን ውል ሲመሰረት Eንደማንኛውም ውል የውል Aቀራረብና Aቀባበል /offer and acceptance/ ላኖር የሚገባ ሲሆን የውል Aቀራረብ /offer/ የሚከናወነው መድን ገቢው በመድን ሰጭው የሚዘጋጅን መግለጫ /proposal form/ ሲሞላና ይህንኑ መግለጫም ለመድን ሰጭው ሲያስረክብ ነው። በመድን ገቢው የቀረበው የውል Aቀራረብ ጥያቄ በመድን ሰጭው ተቀባይነት Aግኝቷል ለማለት የሚቻለው ደግሞ በተዘጋጀው ፖላሲ ላይ በሚፈርምበት ጊዜ /The issuance of policy/ Eንደሆነ፣ ከዚህ በኋላም በሁለቱ ወገኖች መካከል የመድን ውል የተቋቀመ መሆኑንና የትኛውም ወገን ላያቋርጠው Eንደማይችል ከንግድ ሕግ ቁጥር 651፣654 Eና 657 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ የተጠሪ መ/ቤት ለሚጠቀምባቸው ተሽከርካሪዎች የመድን ውል ለመግባት Eንደሚፈልግ በመግለጽ የመ/ቤቱን ማሕተም በማድረግና በኃላፊው Aማካኝነት በመፈረም ለመድን ሰጭው ለAመልካች መ/ቤት ደብዳቤ ጽፏል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በተጠሪ በኩል የውል Aቀራረብ /offer/ የተደረገ መሆኑን ነው። ከዚህ በኋላም Aመልካች በተዘጋጀው ፖላሲ ላይ መፈረሙ የተረጋጠ Eንደመሆኑ መጠን ከላይ ከተጠቀሱት የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች Aኳያ በመካከላቸው የመድን ውሉ የተደረገ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በEርግጥ በፍ/ብሄር ሕጉ በተለየ የAጻጻፍ ሥርAት መደረግ ከሚገባቸው ውሎች መካከል Aንዱ የIንሹራንስ ውል ሲሆን የዚህ ዓይነት ውሎችም በተዋዋይ ወገኖች መፈረም Eንዳለባቸውና በሁለት ምስክር ፊትም መረጋገጥ Eንዳለባቸው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ቁ.1725 Eና 1727 ላይ የተመለከተ ቢሆንም የግራ ቀኙን ግንኙነት በተለይ የሚገዛው ልዩ ሕግ የሆነው የንግድ ሕጉ ስለሆነና በጠቅላላ ሕግና በልዩ ሕግ መካከል Aለመጣጣም በሚኖርበት ጊዜ ልዩ ሕግ የበላይነት Eንደሚኖረው /The special prevails over the general/ ከሕግ Aተረጓጐም መርህ መገንዘብ የሚቻል Eንደመሆኑ በዚሁ መሰረትም መድን ሰጭው በሚያዘጋጀው ፖላሲ ላይ Eራሱ መፈረም Eንዳለበት በን/ሕ/ቁ. 657 ላይ ከመመልከቱ በስተቀር መድን ገቢው መፈረም Eንደሚገባው ያልተመለከተ በመሆኑ በውል ማቅረቢያ /offer/ ሰነዱ ላይ መድን ገቢው ከፈረመና በፖላሲው ላይ ደግሞ መድን ሰጭው ከፈረመ በሁለቱ መካከል የመድን ውል ስለመደረጉ በቂ Aስረጂ Eንደሆነ ከንግድ ሕጉ Aኳያ መገንዘብ ስለሚቻል በሁለቱ መካከል የመድን ውል Aልተቋቋመም ተብሎ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
የAሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 528 ታህሳስ 30 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ Eንደዚሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 31510 የካቲት 6 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል። ይፃፍ።
በAመልካችና በተጠሪ መካከል ከንግድ ሕጉ Aኳያ በAግባቡ የተቋቋመ የመድን ውል መኖሩ የተረጋገጠ ስለሆነና በክስ 226 227 በተጠየቀውም ገንዘብ ላይ ተጠሪ ክርክር ስለልው ይህንኑ በክስ የተጠየቀውን ብር 55,068.56 /Aምሳ Aምስት ሺህ ስልሳ ስምንት ብር ከሃምሳ ስድስት ሳንቲም/ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ 9% /ዘጠኝ በመቶ/ ወለድ ጋር ተጠሪ ለAመልካች ላከፍል ይገባል ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።