No summary available.
ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ Aመልካች፡- ወ/ሮ ዘነበወርቅ ወልዱ ፀጋ - ወኪል Eስክንድር ወልዱ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ በውርስ ንብረት ክፍፍል ላይ የተነሳውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሳሽ የነበረችው የAሁንዋ Aመልካች ስትሆን፣ በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተችው ይዘውት ከሚገኘው የውርስ ንብረት ላይ ድርሻዋን EንዲያካፍሉAት ነው። የውርስ ንብረት የተባሉት በAዲስ Aበባ Eና በደሴ ከተማ የሚገኙ ሁለት ቤቶች Eንደሆኑም ተገልፆAል። ክሱ የቀረበለት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ወደ ክሱ ስረ ነገር ከመግባቱ በፊት Aዲስ Aበባ ከተማ ይገኛል በተባለው ቤት ላይ የዳኝነት ስልጣን የለኝም፣ ማስተናገድ የምችለው ደሴ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን ቤት በሚመለከት የሚቀርበውን ክስ ነው በማለት መዝገቡን ዘግቶAል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የAማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤትም የግዛት ክልል ስልጣን የለኝም ተብሎ በሚሰጥ ትEዛዝ ላይ ይግባኝ ላቀርብ Aይችልም። የሚል ምክንያት በመስጠት ይግባኙን ሳያስተናግድ ቀርቶAል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
216 217 Eኛም Aመልካች ሕዳር 17 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። Aቤቱታው ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ የተወሰነው Aመልካች ለደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበችው የውርስ ንብረት ክፍፍልን የሚመለከተው ክስ በግዛት ክልል የዳኝነት ስልጣን ምክንያት Aይስተናገድም የመባሉን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህም መሰረት ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ትEዛዝ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር መገዝብ Eንደቻልነው Aመልካች Eና 2ኛ ተጠሪ የሟች Aቶ ወልዱ ፀጋ ልጆች ሲሆኑ፣ 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የሟቹ ሚስት ናቸው። ሟች ይኖሩ የነበሩት በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን Eንደሆነና የሞቱትም በዚሁ ቦታ ስለመሆኑ በክርክሩ ተመልክቶAል።
ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪዎች ሟች በኖሩበትና በሞቱበት በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን በደሴ ወረዳ ፍ/ቤት የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ማቅረባቸውን ከቀረበው ክርክር ተመልክተናል።
Eንደምናየው ጉዳዩ የውርስ ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ነው።
Aመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተችው የውርስ ሃብት ነው ከተባለው ንብረት ላይ ድርሻዋን ለማግኘት ነው። በAጠቃላይ ክርክሩ የፍትሐብሕር Eንደመሆኑ የሚመራው በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት ነው።
በግዛት ክልል ስለሚወሰን የዳኝነት ሥልጣን በተመለከተ በሥነ ሥርዓት ሕጉ Aንደኛ መጽሐፍ በምEራፍ 3 ስር ካሉት ድንጋጌዎች ውስጥ በቁጥር 23 የተመለከተውም ለጉዳዩ Aወሳሰን ተገቢነት ያለው ነው። ይህ ድንጋጌ በውርስ ምክንያት የሚቀርብ ክስ የሚታይበትን ቦታ የሚወሰን ነው። ክሱ መቅረብ ያለበት ወይም የሚቀርበው የውርሱ ክፍያ በተጀመረበት ቦታ ለሚገኘው ፍ/ቤት Eንደሆነም ያመለክታል። ሕጉ ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ የውርስ ሃብት የሆኑ ንብርቶች በተለያዩ ቦታዎች የመኖራቸውን ጉዳይ ግምት ውጥስ የሚገባ Aይደለም። Aቤቱታ የቀረበበት ትEዛዝ ከዚህ Aንጻር ሲታይም የሕግ መሰረት ያለው Aይደለም። ይልቁንም መሰረታዊ የሕግ ሥህተት ያለበት ሆኖ ነው ያገኘነው። ስለዚህም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በAማራ ብሕራዊ ክ/መ/ደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16355 ሰኔ 25 ቀን 99 ዓ.ም ተሰጥቶ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1070/99 መስከረም 27 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ትEዛዝ ይግባኝ Aይባልበትም የተባለው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮAል።
Aመልካች ያቀረበችው የውርስ ክፍፍል ክስ መታየት ያለበት በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ፍ/ቤት በመሆኑ ፍ/ቤቱ ክሱን በማስተናገድ በበኩሉ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ ይስጥበት ብለናል። ጉዳዩ ይመለስለት። ይፃፍ።
No topics extracted.
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።