No summary available.
ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጐስ ወልዱ Aቶ ታፈሰ ይርጋ Aቶ መድሕን ኪሮስ Aቶ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ ባዩሽ ደጀኔ - ከጠበቃ ዳኛቸው ተስፋዬ ጋር ቀረበች ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ ሃሳብ ከፋይ ጌራወርቅ ቀረበች።
ደረጀ ጌራወርቅ - Aልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ ኑዛዜን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ Eንደሚታየው ክርክሩ በተጀመረበት በድሬዳዋ ከተማ Aስተዳደር የመጀመያ ደረጃ ፍ/ቤት የAሁንዋ Aመልካች ሟች Aቶ ጌራወርቅ ህሩይ (ባለቤትዋ) Aድርገውት ያለፉት ኑዛዜ መሰረት ተደርጐ የወራሽነት ማስረጃ ይሰጣት ዘንድ በመጠየቅዋ ፍ/ቤቱም ጥያቄዋን በመቀጠል የኑዛዜ ወራሽነት በማለት ማስረጃውን ሰጥቶAት ነበር። በልላ በኩል ደግሞ የAሁኖቹ ተጠሪዎች ማስረጃው መሰጠት Aልነበረበትም በማለት መቃወሚያ በማቅረባቸው ፍ/ቤቱ ጉዳዮን በድጋሚ ያየ ሲሆን በመጨረሻም ሟች Aድርገውታል የተባለውን ኑዛዜ ከፊሉን በመሻር የተወሰነውን ክፍሉን ደግሞ በማጽደቅ ወስኖAል።
በዚህ ላይ ከAሁንዋ Aመልካች ይግባኝ የቀረበላቸው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶችም ውሳኔው ጉድለት የለውም ብለዋል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች ነሐሴ 4 ቀን 1999 ዓ.ም በጻፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ጉዳዩን ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ከላይ Eደተመለከተው ክርክሩ ላነሳ የቻለው ሟች Aደረገው የተባለው ኑዛዜ ፈራሽ ነው ይባል የሚል ክስ በመቅረቡ ሳይሆን (የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 973) ኑዛዜውን መሰረት በማድረግ የወራሽነት ማስረጃ (የምስክር ወረቀት) ይሰጠኝ (የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996(1)) በማለት Aመልካች ጥያቄ በማቅረብዋ ነው። በፍትሐብሕር ሕጉ በግልጽ Eንደተመለከተው ኑዛዜ ፈራሽ ነው ይባል በሚል የሚቀርበው ክስ የወራሽነት የምስክር ወረቀት Eንዲሰጥ ከሚቀርበው ጥያቄ (Aቤቱታ) የተለየ ነው። ጥያቄዎቹ የተለያዩ በመሆናቸውም የተለያየ ውጤት ነው ያላቸው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996(1) Eንደተደነገገው ወራሽነኝ የሚል ማንኛውም ሰው የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይሰጠው ዘንድ ለፍ/ቤት ላያመለክት ይችላል። ፍ/ቤቱም ጥያቄውን ከመቀበሉ በፊት ጠያቂው ማስረጃዎቹን ሁሉ Eንዲያቀርብ በማድረግ Eና Aስፈላጊ መስሎ የታየውን ዋስትና Eንዲሰጥ በማስገደድ ጭምር ዋስትናውን ካገኘ በኋላ የተጠየቀውን የምስክር ወረቀት ላሰጥ Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
996(2) ተመልክቶAል። በልላ በኩል ደግሞ ፍ/ቤቱ የAመልካቹን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ሰጥቶት የነበረውን የወራሽነት የምስክር ወረቀት ላሰርዘው Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 998(1) የተቀመጠው ድንጋጌ ያመለክታል። ከዚህ Eንግዲህ መገንዘብ Eንደሚቻለው የምስክር ወረቀቱ በጠያቂው Aቤቱታ መነሻነት የሚሰጥ ቢሆንም የተሰጠው ያለAግባብ ነው የሚል መቃወሚያ ላቀርብ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩንና መቃወሚያው ተገቢ ሆኖ ከተገኘም የምስክር ወረቀቱ የሚሰረዝ መሆኑን ነው።
ወደ ያዝነው ጉዳይ ስንመለስ የወራሽነት የምስክር ወረቀት Eንዲሰጥ ጥያቄ የቀረበለት ፍ/ቤት ጥያቄውን ተቀብሎ የምስክር ወረቀቱን ሰጥቶ Eንደነበር Eንመለከታለን። ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996(1) የተመለከተውን ድንጋጌ ተከትሎ የተፈጸመ በመሆኑ ትክክል ነው። ልላው ቀጥለን የምናየው ተጠሪዎች የተሰጠውን የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመቃወም መቅረባቸው ሲሆን ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን መሰረት በማድረግ ለምስክር ወረቀቱ መሰጠት መሰረት የሆነውን ኑዛዜ ይዘት Eና ሕጋዊነትን መርምሮAል።
በመጨረሻም ኑዛዜውን በከፊል በመሻር በከፊል ደግሞ AጽድቄAለሁ ብሎAል። በበኩላችን ትክክለኛ Aካሄድ ሆኖ ያላገኘነውም ይህንን ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ በሕጉ የተቀመጠውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ኑዛዜው ፈራሽ ነው Eንዲባል ክስ Aልቀረበለትም። የፍ/ቤቱ የዳኝነት ሥልጣን የተወሰነ በመሆኑ በሥልጣን ክልሉ ስር የሚወድቀውን የወራሽነት የምስክር ወረቀት Eንዲሰጥ ነው ጥያቄ የቀረበለት። ይህን ጥያቄ ተቀብሎ ሰጥቶት የነበረውን የምስክር ወረቀት ተጠሪዎች ካቀረቡለት መቃወሚያ Aንጻር ሲመዝነው ተገቢ Aልነበረም የሚል ድምዳሜ ከደረሰም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
998(1) በተደነገገው መሰረት መሰረዝ ነው የነበረበት። ከዚህ Aልፎ ኑዛዜው ፈራሽ ይባል የሚል ክስ በቀረበ ጊዜ ላደረግ Eንደሚችለው ሁሉ ኑዛዜውን በከፊል ሽሬAለሁ ማለቱ ትክክል Aይደለም። የሕግ መሰረትም የለውም።
No topics extracted.
ከሁሉ በላይ ደግሞ ፍ/ቤቱ ወደ ኑዛዜው ይዘት Eና ሕጋዊነት ሁኔታ ገብቶ ውሳኔ መስጠት የሚችልበት ሕጋዊ መንገድ Aልነበረውም Eንጂ ሕጋዊ መንገድ ነበረው ተብሎ ቢሆን ኖሮ Eንኳን የደረሰበት መደምደሚያ የኑዛዜን ፎርም Eና ማስረጃ ከሚመለከተው ሕግ Aንፃር ላታይ ፍጹም የተሳሳተ ነው።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ኑዛዜ በግልጽ የተደረገ ኑዛዜ Eንደሆነ በፍ/ቤቱ ውሳኔ ተመልክቶAል። በግልጽ የተደረገ ኑዛዜ ላያሟላቸው የሚገቡትን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 ስር የተመለከቱትን መስፈርቶች ያሟላ Eንደሆነም ፍ/ቤቱ ማረጋገጡን በውሳኔው ላይ AመልክቶAል። ይህን ሁሉ ካረጋገጠ በኋላ በከፊል ሽሬዋለሁ ያለው ሟች ንብረቱ ባልሆነው ንብረት ላይ ጭምር ተናዟል በማለት Eንደሆነ ከውሳኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
በሕጉ በግልጽ Eንደተመለከተው በግልጽ የተደረገው ኑዛዜ በሕጉ መሰረት Aልተደረገም ተብሎ ላነቀፍ የሚችለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 የተቀመጡትን መስፈርቶች ያላሟላ ሆኖ ሲገኝ ነው። የስር ፍ/ቤት ኑዛዜውን ለመንቀፍ ምክንያት ያደገው ነጥብ የኑዛዜውን ሕጋዊነት በተመለከተ Aግባብነት የለውም። ተናዛዡ የEሱ ባልሆነው ንብረት ጭምር ተናዟል የሚባል ቢሆን የንብረት ክርክር ሲቀርብ Eራሱን ችሎ የሚታይ ጉዳይ ነው። ፍ/ቤቱ ይህን ነጥብ በማድረግ የኑዛዜውን ሕጋዊነት (ፎርም) መንቀፍ ተገቢ Aይደለም የምንለውም በዚህ ምክንያት ነው። ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች የተጠሪዎችን መቃወሚያ መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለት ሆኖ Aግኝተነዋል።
Aቤቱታ የቀረበበት በድሬዳዋ ጊዜያዊ Aስተዳደር የድሬዳዋ ከተማ የመጀመያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ./97 የካቲት 30 ቀን 99 ዓ.ም ተሰጥቶ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመ.ቁ 106/99 ግንቦት 8 ቀን 99 ዓ.ም በተሰጠው ትEዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሮAል።
ቀደም ሲል ለAመልካች የተሰጠው የወራሽነት የምሰክር ወረቀት የሚሰረዝበት የሕግ ምከንያት የለም ብለናል።
214 215 3. ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።