No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ብርሃኑ Aመነው Aቶ መድሕን ኪሮስ Aቶ ዓላ መሐመድ Aቶ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Eማሆይ ወይንሸት Aድማሱ ተጠሪ፡- Eነ ወ/ሮ ክብነሽ ስዩም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን Aመጣጡም የAሁኑ ተጠሪዎች ታህሳስ 30 ቀን 99 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ሟች Aቶ ስዩም Aየለ በወረዳ 3 ቀበል 53 ቁጥሩ 143 የሆነውን ቤት Eኩል Eንድንካፈለው ለኛና ለተከሳሾች ተናዝዘውልናል። ስለቤቱ Aጠቃቀም ውርሱን በማጣራትና በመለየት ቤቱን Aስከምንከፋፈል በኪራይም ይሁን በኮንትራት የሚገኘውን ገቢ Eየተከፋፈልን Eንድቆይ ተስማምተናል። ሆኖም ተከሳሾች ቤቱን Aከራይተው ያገኙትን ገቢ ላያካፈሉን ፈቃደኞች ባለመሆናቸው በኪራይ ያገኙትን ገንዘብ Eንዲያካፍሉን። ቤቱም ተሽጦ Eንድንከፋፈል ይወሰንልን በማለት ክስ Aቅርበዋል።
የAሁን Aመልካቾች (የሥር ተከሳሾች) ደግሞ ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ ያደረግነው ስምምነት ኑዛዜውን የሚተካና ወሳኝነት ያለው Aይደለም ክርክር ያስነሳው ቤትም የምንኖርበት Eንጅ የሚከራይ Aይደለም።
ለተወሰነ ጊዜ ተከራይቶ በነበረበት ጊዜ የተገኘው ገቢም ብር 7560 ነው።
ከዚሁ ገንዘብ የቤት ባለቤትነት ደብተር ለማስወጣት ከፍለንበታል። ቀሪውን ገንዘብ ተሳስበን ለመክፈል ዝግጁነን። የቤቱን መከፋፈል ግን የሚደረገው206 በኑዛዜው መሰረት ከ1ኛ ተከሳሽ የህይወት ፍፃሜ በኋላ ነው። በመሆኑም ከሣሾች ያቀረቡት ክስ ኑዛዜውን መሰረት ያላደረገ መሆኑ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረና ማስረጃ ከተማ በኋላ ተከሳሾች ቤቱን በማከራየት ካገኙት ገቢ ውስጥ የከሳሾች ድርሻ የሆነውን ብር 1628.50 ለከሳሾች Eንዲከፍሉ። ቤቱም በሐራጅ ተሸጦ ለወራሾች Eንዲከፋፈል በማለት ወስነናል።
ከፍተኛው ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ መሰረት በማድረግ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤቱን ውሳኔ Aጽንቶታል።
Aመልካቾች የሰበር Aቤቱታው ያቀረቡት በሥር ፍ/ቤቶቹ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ቅሬታቸውም ሟች የተናዘዙት ክርክር ያስነሳውን ቤት 1ኛ ተጠሪ ከልሎቻችን ወራሾች ጋር በመሆን Eንዲገለገሉበት። ለልሎቻችን ወራሾች ላከፋፈል የሚችለው Eሳቸው ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ጊዜ መሆኑን ነው። 1ኛ Aመልካች በህይወት Eያለ ቤቱን መሸጥና መከፋፈል Aይቻልም። Eንደዚሁም ወራሾች በሙሉ ተሰብስበን 1ኛ Aመልካችም ጭምር ቤቱ ሳይከፋፈል ከሚያስገኘው ጥቅም Eኩል Eየተጠቀምን መቆየት Eንዳለብን የተስማማንና የተዋዋልን በመሆኑ ተጠሪዎች ቤቱን ለመካፈል ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትና የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ቤቱ በሐራጅ ተሽጦ ገንዘቡን ወራሾች Eንዲከፋፈሉት በማለት የሰጡት ውሳኔ የAውራሻችን ኑዛዜና ከዚያም በኋላ ወራሾች ያደረግነውን ውል ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ውሳኔው ላሻርልን ይገባል የሚል ነው።
የሰበር ችሎቱም Aቤቱታውን ከመረመረ በኋላ ክርክር የተነሳበት ቤት በAጠቃላይ በሐራጅ Eንዲሸጥ በማለት የተሰጠው ውሳኔ የሟችን የኑዛዜ ቃል የተከተለ መሆን Aለመሆኑን መመርመር Aስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው Aቤቱታው ያስቀርባል ሲል ትEዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪዎችም ሐምል 2 ቀን 99 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ 1ኛ Aመልካች በቤቱ ላይ የጋራ መብት የላቸውም። ከኑዛዜው በኋላ ጥር 8 ቀን 1987 ዓ.ም በተፃፈው የወራሾች የጋራ የስምምነት ውል 1ኛ Aመልካች ቤቱ የማይመለከታቸው መሆኑ ተወስኗል። ቤቱ የወራሾች የጋራ ንብረት በመሆኑ ተሽጦ Eንድንከፋፈለው Eንዲወሰንልን ክስ ማቅረባችን Aግባብ ነው። 2ኛ Eና 3ኛ Aመልካቾች በኑዛዜ ያገኘነውን ቤት ክርክር ካስነሳው ቤት ጋራ በሐራጅ Eዲሸጥ ተወሰነብን በማለት ያቀረቡት ክርክር በስር ፍ/ቤት ያላነሱት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የስር ፍ/ቤቶች ቤቱ በሐራጅ ተሽጦ ገንዘቡን ወራሾች Eንዲከፋፈሉት በማለት የሰጡት ውሳኔም Aንዳችም የሕግ ስህተት የለበትም። በመሆኑም ውሳኔው Eንዲፀናልን በማለት ተከራክረዋል።
Aመልካቾች ያቀረቡት የመልስ መልስ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
በበኩላችን ደግሞ 1ኛ Aመልካች በህይወት Eያሉ ወራሾቹ ክርክር ያስነሳውን ቤት በሐራጅ ተሽጦ ላከፋፈሉት ይገባል ወይስ Aይገባም?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም የወራሾቹ Aውራሽ የሆኑት ሟች Aቶ ስዩም Aየለ ነሐሴ 11 ቀን 1984 ዓ.ም በሰጡት ኑዛዜ ወ/ሮ ወይንሸት Aድማሱ ክርክር ባስነሳው ቤት ውስጥ ከልሎቹ ወራሾች ጋር Aብረው Eንዲኖሩ የፈቀዱና Eሳቸው በህይወት Eያሉም ቤቱን ሸጬ ድርሻዬን Eወስዳለሁ የሚል ካለ ያገዱት መሆኑን ተገንዝበናል። ተናዛዡ ወራሾችን ወይም በኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸውን ሰዎች ከሚደርሳቸው ሃብት ላይ በተለይ ለAንድ ወይም ለብዙ ሰዎች Aንድ Aገልግሎት Eንዲሰጡ ግድ Eንዲሆንባቸው በኑዛዜው ለመወሰን Eንደሚቻል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 920 ተደንግጓል። የAመልካቾችና የተጠሪዎች Aውራሽ የሆኑት Aቶ ስዩም Aየለ በኑዛዜያቸው ያስቀመጡት የ1ኛ Aመልካች ቤቱን የመጠቀም መብትም ወራሾች Eንዲፈጽሙት የሚያስገድዳቸው ነው። በኑዛዜው ግድታ 208 209 የተገባላቸው 1ኛ Aመልካችም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 922/1/ መሰረት የታዘዘላቸውን Eንዲፈጽሙላቸው ወራሾችን ለማስገደድ ይችላሉ።
No topics extracted.
ወራሾቹ ተሰብስበው በውርስ ስለተሰጣቸው ቤት Aጠቃቀም ለመወሰን ጥር 8 ቀን 1987 ዓ.ም የደረሱበት ስምምነትም የAውራሹን ኑዛዜ የሚያስቀይር ይዘት ስለልለው ተጠሪዎቹ ላቀረቡት ክስ በምክንያትነት ላጠቀስ የሚገባው Aይሆንም። 2ኛ Eና 3ኛ Aመልካቾች በኑዛዜ Aገኘነው ያሉትን ቤት በተመለከተ ደግሞ የAሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ ተለይቶ ክስ ያልቀረበበትና የሥር ፍ/ቤትም ይህን Aስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ ባለመኖሩ በግራ ቀኙ የተደገው ክርክር Aግባብነት የለውም።
በመሆኑም 1ኛ Aመልካች በኑዛዜ የተሰጣቸውን በህይወት ዘመናቸው ክርክር ያስነሳውን ቤት የመገልገል መብት ወራሾች ላያሳጡዋቸው የሚችሉበት ምክንያት ባለመኖሩ ተጠሪዎች የውርስ ንብረት የሆነው ቤት ተሽጦ ገንዘቡን ወራሾች Eንድንከፋፈለው በማለት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ቤቱ ተሽጦ ገንዘቡ ወራሾች Eንዲከፋፈሉት የሚለው ውሳኔም የ1ኛ Aመልካችን በቤቱ የመገልገል መብትና የወራሾቹን 1ኛ Aመልካች በህይወት Eያሉ ቤቱን ያለመሸጥ ግድታ የጣሰና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16509 ሰኔ 3 ቀን 97 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 41583 ሚያዝያ 16 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
Aቶ ስዩም Aየለ 1ኛ Aመልካች በቤቱ ውስጥ መኖር Eንዳይከለከሉ። Eሳቸው በህይወት Eያሉ ቤቱን ሸጬ ልካፈል ማለት Aይቻልም በማለት የተናዘዙ በመሆኑ በወረዳ 3 ቀበል 53 ክልል የሚገኘው ቁጥሩ 143 የሆነው ቤት Eማሆይ ወይንሸት Aድማሱ በህይወት Eያሉ መሸጥ የለበትም በማለት ወስነናል።ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ 210 211 የሰበር መ/ቁ/ 32414 ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጐስ ወልዱ Aቶ ታፈሰ ይርጋ Aቶ መድሕን ኪሮስ Aቶ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ ባዩሽ ደጀኔ - ከጠበቃ ዳኛቸው ተስፋዬ ጋር ቀረበች ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ ሃሳብ ከፋይ ጌራወርቅ ቀረበች።
ደረጀ ጌራወርቅ - Aልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ ኑዛዜን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ Eንደሚታየው ክርክሩ በተጀመረበት በድሬዳዋ ከተማ Aስተዳደር የመጀመያ ደረጃ ፍ/ቤት የAሁንዋ Aመልካች ሟች Aቶ ጌራወርቅ ህሩይ (ባለቤትዋ) Aድርገውት ያለፉት ኑዛዜ መሰረት ተደርጐ የወራሽነት ማስረጃ ይሰጣት ዘንድ በመጠየቅዋ ፍ/ቤቱም ጥያቄዋን በመቀጠል የኑዛዜ ወራሽነት በማለት ማስረጃውን ሰጥቶAት ነበር። በልላ በኩል ደግሞ የAሁኖቹ ተጠሪዎች ማስረጃው መሰጠት Aልነበረበትም በማለት መቃወሚያ በማቅረባቸው ፍ/ቤቱ ጉዳዮን በድጋሚ ያየ ሲሆን በመጨረሻም ሟች Aድርገውታል የተባለውን ኑዛዜ ከፊሉን በመሻር የተወሰነውን ክፍሉን ደግሞ በማጽደቅ ወስኖAል።
በዚህ ላይ ከAሁንዋ Aመልካች ይግባኝ የቀረበላቸው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶችም ውሳኔው ጉድለት የለውም ብለዋል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች ነሐሴ 4 ቀን 1999 ዓ.ም በጻፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ጉዳዩን ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ከላይ Eደተመለከተው ክርክሩ ላነሳ የቻለው ሟች Aደረገው የተባለው ኑዛዜ ፈራሽ ነው ይባል የሚል ክስ በመቅረቡ ሳይሆን (የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 973) ኑዛዜውን መሰረት በማድረግ የወራሽነት ማስረጃ (የምስክር ወረቀት) ይሰጠኝ (የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996(1)) በማለት Aመልካች ጥያቄ በማቅረብዋ ነው። በፍትሐብሕር ሕጉ በግልጽ Eንደተመለከተው ኑዛዜ ፈራሽ ነው ይባል በሚል የሚቀርበው ክስ የወራሽነት የምስክር ወረቀት Eንዲሰጥ ከሚቀርበው ጥያቄ (Aቤቱታ) የተለየ ነው። ጥያቄዎቹ የተለያዩ በመሆናቸውም የተለያየ ውጤት ነው ያላቸው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996(1) Eንደተደነገገው ወራሽነኝ የሚል ማንኛውም ሰው የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይሰጠው ዘንድ ለፍ/ቤት ላያመለክት ይችላል። ፍ/ቤቱም ጥያቄውን ከመቀበሉ በፊት ጠያቂው ማስረጃዎቹን ሁሉ Eንዲያቀርብ በማድረግ Eና Aስፈላጊ መስሎ የታየውን ዋስትና Eንዲሰጥ በማስገደድ ጭምር ዋስትናውን ካገኘ በኋላ የተጠየቀውን የምስክር ወረቀት ላሰጥ Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
996(2) ተመልክቶAል። በልላ በኩል ደግሞ ፍ/ቤቱ የAመልካቹን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ሰጥቶት የነበረውን የወራሽነት የምስክር ወረቀት ላሰርዘው Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 998(1) የተቀመጠው ድንጋጌ ያመለክታል። ከዚህ Eንግዲህ መገንዘብ Eንደሚቻለው የምስክር ወረቀቱ በጠያቂው Aቤቱታ መነሻነት የሚሰጥ ቢሆንም የተሰጠው ያለAግባብ ነው የሚል መቃወሚያ ላቀርብ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩንና መቃወሚያው ተገቢ ሆኖ ከተገኘም የምስክር ወረቀቱ የሚሰረዝ መሆኑን ነው።
ወደ ያዝነው ጉዳይ ስንመለስ የወራሽነት የምስክር ወረቀት Eንዲሰጥ ጥያቄ የቀረበለት ፍ/ቤት ጥያቄውን ተቀብሎ የምስክር ወረቀቱን ሰጥቶ Eንደነበር Eንመለከታለን። ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996(1) የተመለከተውን ድንጋጌ ተከትሎ የተፈጸመ በመሆኑ ትክክል ነው። ልላው ቀጥለን የምናየው ተጠሪዎች የተሰጠውን የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመቃወም መቅረባቸው ሲሆን ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን መሰረት በማድረግ ለምስክር ወረቀቱ መሰጠት መሰረት የሆነውን ኑዛዜ ይዘት Eና ሕጋዊነትን መርምሮAል።
በመጨረሻም ኑዛዜውን በከፊል በመሻር በከፊል ደግሞ AጽድቄAለሁ ብሎAል። በበኩላችን ትክክለኛ Aካሄድ ሆኖ ያላገኘነውም ይህንን ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ በሕጉ የተቀመጠውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ኑዛዜው ፈራሽ ነው Eንዲባል ክስ Aልቀረበለትም። የፍ/ቤቱ የዳኝነት ሥልጣን የተወሰነ በመሆኑ በሥልጣን ክልሉ ስር የሚወድቀውን የወራሽነት የምስክር ወረቀት Eንዲሰጥ ነው ጥያቄ የቀረበለት። ይህን ጥያቄ ተቀብሎ ሰጥቶት የነበረውን የምስክር ወረቀት ተጠሪዎች ካቀረቡለት መቃወሚያ Aንጻር ሲመዝነው ተገቢ Aልነበረም የሚል ድምዳሜ ከደረሰም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
998(1) በተደነገገው መሰረት መሰረዝ ነው የነበረበት። ከዚህ Aልፎ ኑዛዜው ፈራሽ ይባል የሚል ክስ በቀረበ ጊዜ ላደረግ Eንደሚችለው ሁሉ ኑዛዜውን በከፊል ሽሬAለሁ ማለቱ ትክክል Aይደለም። የሕግ መሰረትም የለውም።
ከሁሉ በላይ ደግሞ ፍ/ቤቱ ወደ ኑዛዜው ይዘት Eና ሕጋዊነት ሁኔታ ገብቶ ውሳኔ መስጠት የሚችልበት ሕጋዊ መንገድ Aልነበረውም Eንጂ ሕጋዊ መንገድ ነበረው ተብሎ ቢሆን ኖሮ Eንኳን የደረሰበት መደምደሚያ የኑዛዜን ፎርም Eና ማስረጃ ከሚመለከተው ሕግ Aንፃር ላታይ ፍጹም የተሳሳተ ነው።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ኑዛዜ በግልጽ የተደረገ ኑዛዜ Eንደሆነ በፍ/ቤቱ ውሳኔ ተመልክቶAል። በግልጽ የተደረገ ኑዛዜ ላያሟላቸው የሚገቡትን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 ስር የተመለከቱትን መስፈርቶች ያሟላ Eንደሆነም ፍ/ቤቱ ማረጋገጡን በውሳኔው ላይ AመልክቶAል። ይህን ሁሉ ካረጋገጠ በኋላ በከፊል ሽሬዋለሁ ያለው ሟች ንብረቱ ባልሆነው ንብረት ላይ ጭምር ተናዟል በማለት Eንደሆነ ከውሳኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
በሕጉ በግልጽ Eንደተመለከተው በግልጽ የተደረገው ኑዛዜ በሕጉ መሰረት Aልተደረገም ተብሎ ላነቀፍ የሚችለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 የተቀመጡትን መስፈርቶች ያላሟላ ሆኖ ሲገኝ ነው። የስር ፍ/ቤት ኑዛዜውን ለመንቀፍ ምክንያት ያደገው ነጥብ የኑዛዜውን ሕጋዊነት በተመለከተ Aግባብነት የለውም። ተናዛዡ የEሱ ባልሆነው ንብረት ጭምር ተናዟል የሚባል ቢሆን የንብረት ክርክር ሲቀርብ Eራሱን ችሎ የሚታይ ጉዳይ ነው። ፍ/ቤቱ ይህን ነጥብ በማድረግ የኑዛዜውን ሕጋዊነት (ፎርም) መንቀፍ ተገቢ Aይደለም የምንለውም በዚህ ምክንያት ነው። ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች የተጠሪዎችን መቃወሚያ መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለት ሆኖ Aግኝተነዋል።
Aቤቱታ የቀረበበት በድሬዳዋ ጊዜያዊ Aስተዳደር የድሬዳዋ ከተማ የመጀመያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ./97 የካቲት 30 ቀን 99 ዓ.ም ተሰጥቶ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመ.ቁ 106/99 ግንቦት 8 ቀን 99 ዓ.ም በተሰጠው ትEዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሮAል።
ቀደም ሲል ለAመልካች የተሰጠው የወራሽነት የምሰክር ወረቀት የሚሰረዝበት የሕግ ምከንያት የለም ብለናል።
214 215 3. ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።