No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካቾች፡- Eነ ወ/ሮ ፀሐይነሽ Aደም ሞግዚት ሐይሉ ሲሳይ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- የኮ/ል Eሸቱ ተስፋዬ ወራሾች ጠበቃ ወርቅዬ Aባይነህ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ ለሰበር የቀረበው Aመልካች የAማራ ክልል የደሴ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 83/90 መጋቢት 17 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍታብሕር ይግባኝ መዝገብ ጥቅምት 30 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍታብሕር ይግባኝ መዝገብ ቁጥር 255/1999 ጥር 22 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት የሰበር Aቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ Eናቴ ወ/ሮ Aበበች ጀግሬና Aክስቴ በየነች ጌቶ Aሁን በህይወት የሉም። Eናቴና Aክስቴ ከሟች Eናታቸው ወ/ሮ ጀማነሽ Aቡዬ በውርስ የተላለፈላቸውንና በደሴ መዝገበ ማርያም የስንድ ግብር Eየከፈሉ ይዘውት የቆዩትን በደሴ ከተማ ቀበል 05 ቁጥሩ 407 የሆነ ቤትና 668 ካሬ ሜትር ቦታ Aቶ በዛብህ ጐሽ Aላግባብ የያዘና በስሙ ያዛወረ ስለሆነ ከውርስ ንብረቱ የሚደርሰኝን ብር 6000 (ስድስት ሺህ ብር ) Eንዲከፍል 200 201 ይወሰንልኝ በማለት የወራሽነት ክስ በማቅረቡ ነው። Aመልካቾቹ በክሱ የተገለፀው ቤትና ቦታ የAቶ በዛብህ ጐሽ የግል ንብረት Eንደሆነና ይኸም በደሴ ማዘጋጃ ቤት Eንደተመዘገበ ገልፀው የተከራሩ ሲሆን ንብረቱ ያልተከፍፈለ የውርስ ንብረት ነው ቢባል Eንኳን የከሳሽ(ተጠሪ) ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። የደሴ ወረዳ ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በAመልካቾች በኩል የቀረበውን ክርክር Aልፈው ተጠሪ ያቀረበውን የሰው ማስረጃ መሰረት ንብረቱ የውርስ ንብረት ስለሆነ Aመልካቾች ለተጠሪ Eንዲያካፍሉ በማለት ውሣኔ ሰጥተዋል።
የክለሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የህግ ወይም የፍሬ ጉዳይ ስህተት የለበትም በማለት ትEዛዝ ሰጥቷል።
Aመልካቾች ይኸ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት በደሴ ከተማ ቀበል 05 ቁጥሩ 407 የሆነው መኖሪያ ቤት ጥንት ለመዝገበ ምህረት ማሪያም የስንድ ግብር ተገብሮበት ነበር በማለት ቤተክርስቲያን በፃፈው ቀላጤ መነሻ ለሰላሣ ሁለት ዓመት በስማቸው ያለውን ንብረት Aካፍሉ መባላችን መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት ንብረቱ በAመልካች ባለቤትና Aውራሾች በዛብሕ ጐሽ ስም ስለሆነ ተጠሪዎች ላጠየቁ ይችላሉ የሚለው ውሣኔ በሰበር ታይቶ Eንዲታረምላቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ንብረቱ በውርስ ከወ/ሮ ጀማነሽ Aቦዬ በውርስ የተላለፍ ነው። የተጠሪ Eናትና Aክስት ይኖሩ ነበር ተጠሪ Aውራሽ Eናታቸው 1989 ዓ.ም ሞተው በ1989 ዓ.ም የወራሸነት ጥያቄ ያቀረቡ ስለሆነ የይርጋ የጊዜ ገደብ Aልተላለፈም። ንብረቱ የሟች ወ/ሮ ጀማነሽ Aቦዬ ስለሆነና ለተጠሪ Eናትና Aክስት በውርስ የተላለፈ በመሆኑ ተጠሪ ድርሻ መጠየቃቸው ህጋዊ ነው የሚል መልስ Aቅርቧል። Aመልካቾች የሰበር Aቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ Aቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና በጽሑፍ ያደረጉት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎት የAመልካችንና የተጠሪን የቃል ክርክር ሰምቷል። ይህ ችሎት ግራ ቀኙ የAከራካሪውን ቤት ባለቤትነት Aስመልክቶ ያቀረቡት ክርክር ከመታየቱ በፊት የተጠሪ ክስ በይርጋ የጊዜ ገደብ ይታገዳል ወይስ Aይታገድም? የሚለውን ጭብጥ መመርመር Aስፈላጊ ሆኖ Aግኝቶታል።
ተጠሪ ለደሴ ወረዳ ፍርድ ቤት Aስቀርቦ ካሰማቸው Eና ፍርድ ቤቱ በውሣኔው ላይ የምስክርነት ቃላቸው ከመዘገበው Aንደኛ ምስክር ለመረዳት የሚቻለው የተጠሪ Eናት Eና Aክስት Aውራሽ ናቸው የተባሉት ወ/ሮ ጀማነሽ Aቡዬ የሞቱት በ1949 ዓ.ም ነው። ይህ ተጠሪ ባቀረበው ማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ከዚህ በኋላ የተጠሪ Eናት ወ/ሮ Aበበች ጀግሬና Aክስታቸው ወ/ሮ በየነች ጌቶ የEናታቸው የውርስ ንብረት Eንዲከፈልና ድርሻቸው በስማቸው Eንዲዞር ያቀረቡት ክስ የለም። ንብረቱንም በስማቸው Aላዞሩም። በተቃራኒው የAንደኛ Aመልካች ባለቤትና የሁለተኛና ሶስተኛ Aመልካቾች Aባት Aቶ በዛብህ ጐሽ የቤቱን ስመ ንብረት በስማቸው Aዛውረውና በደሴ ማዘጋጃ ቤት የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ Aስመዝግበው Eንደኖሩ ተረጋጋጧል። የወረዳው ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪው ክስ በፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000(2) የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚታገድ Aይደለም የሚል ብይን የሰጡት ንብረቱ ከዘር የወረደ ርስት ነው በሚል ምክንያት ነው። በEርግጥ የፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000 (2) “ሟች ከሞተበት ወይም ተከሳሹ በመብቱ ለመምራት ከቻለበት ቀን Aንስቶ Aስራ Aምስት ዓመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በስተቀር የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም Aስተያየት ቢሆንም ተቀባይነት Aያገኝም” በማለት ይደነግጋል።
No topics extracted.
ከዚህም ድንጋጌ የምንረዳው ሟች ከሞተ ከAስራ Aምስት Aመት በኋላ ወይም ተከሳሹ በመብቱ ላሰራበት ከቻለበት ቀን Aንስቶ ለምሣል ህፃን ልጅ ወራሽ ሲሆንና ሞግዚትና Aስተዳዳሪው መብቱን በAግባቡ ያልጠየቀለት ቢሆን Aካለ መጠን ከደረሰበትና በመብቱ ላሰራበት ከቻለበት ቀን Aንስቶ 202 203 በAስራ Aምስት Aመት ውስጥ ክስ ካላቀረበ ጉዳዩ በይርጋ Eንደሚታገድ በመርህ ደረጃ ይደነግጓል። ድንጋጌው ከላይ የተገለፀው የAስራ Aምስት ዓመት ጊዜ ሣያልፍ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ያላቀረበ ሰው ከAስራ Aምስት ዓመት በኋላ ክስ Eንዲያቀርብ የሚፈቅደው በAንድ ልዩ ሁኔታ ብቻ ነው።
ይኸውም ንብረቱ ከዘር የወረደ ርስት ሆኖ ሲገኝ በAስራ Aምስት Aመት የይርጋ ጊዜ የማይገደብ መሆኑን በልዩ ሁኔታ የደነገገ በመሆኑ ነው።
ስለሆነም ተጠሪ ክስ ማቅረብ የሚችሉት ክርክር የተነሣበት ንብረት ከዘር የወረደ ርስት ከሆነ ብቻ በመሆኑ ክርክር የተነሣበት “ከዘር የወረደ ርስት” ምን Aይነት ንብረትን ያጠቃልላል? በተለይም ከዘር የወረደ ርስት የሚባለው ቤትን ያጠቃልላል ወይ? የሚለውን ትርጉም መስጠት ያስፈልጋል።
ስለሆነም “ርስት” የሚለውን ቃል ስንመለከት “ቤተዘመድ የሆነ Eያረሰ የሚጠቀምበት ለተወላጅ በውርስ የሚተላለፍ መሬት” ማለት Eንደሆነ ከAማርኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም በፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000 (2) “ከዘር የወረደ ርስት” የሚለው Aገላለጽ፣ ለተወላጅ በውርስ የተላለፈ መሬትን ብቻ የሚመለከት Eንጂ ቤትንና ልሎች የማይንቀሣቀሱ ንብረቶችን የሚመለከት Aይደለም። መሬት የመንግስትና የህዝብ በመሆኑና Aሁን ባለው ህገመንግስታዊ ሥርዓት የመሬት ባለቤት የIትዮጵያ ብሕር በሕረሰቦችና ህዝቦች Eና መንግስት Eንደሆኑ በህገ መንግስቱ Aንቀጽ 40 በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ “ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በስተቀር” የሚለው የፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000 (2) ድንጋጌ በAሁኑ ሰዓት የተሻረና ተፈፃሚነት የልለው ነው።
ስለሆነም በAሁኑ ጊዜ ርስት የልለ በመሆኑ ሟች ከሞተበት ወይም ተከሳሹ በመብቱ ላሰራበት ከቻለበት ጊዜ ጀምሮ ከAስራ Aምስት ዓመት በኋላ የሚቀርብና በይርጋ የማይገደብ የወራሽነት ጥያቄ የለም። ስለሆነም የተጠሪ Eናትና Aክስት Aውራሻቸው ወ/ሮ ጀማነሽ Aቦዬ ከሞቱበት 1949 ዓ.ም ጀምሮ የወራሽነት ክስ ያላቀረቡ በመሆናቸው ይርጋው መቆጠር ያለበት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠር የተጠሪ Aውራሽ ወ/ሮ Aበበች ጀግሬም ሆኑ ተጠሪ Aውራሻቸው ከሞቱ ከሰላሣ ዘጠኝ Aመት በኋላ ተጠሪ የወራሽነት ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ በፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000 (2) በተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ ክሳቸው ቀሪ ይሆናል። የተጠሪ Eናት Eቤቱ ውስጥ መኖራቸው የውረሱን ንብረት የተካፈሉና በስማቸው ያደረጉት መሆኑን Aያረጋጋጥም። ስለሆነም የደሴ ወረዳ ፍርድ ቤትና የደቡብ ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ንብረቱ ከዘር የወረደ Eርስት ስለሆነ በይርጋ Aይታገድም በማለት የሰጡት ትርጓሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት። Eንደዚሁም ተጠሪው Aውራሹ የሆነችው ወላጅ Eናቱ የAናቷን የወ/ሮ ጀማነሽ Aቦዬን ውርስ ሳትጠይቅ ያሳለፈችው ረጅም ጊዜ በተጠሪው ላይ የሚቆጠርበት መሆኑን ሣያገናዝብ ተጠሪው የይርጋ የጊዜ ገደቡ ሣያልፍ ነው ክስ የቀረበው በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ ድጋፍ የልለው በመሆኑ Aልተቀበልነውም። የተጠሪ የወራሽነት ጥያቄ በፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000(2) መሰረት በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ Aመልካችና ተጠሪ የቤቱን ባለቤትነት Aስመልክቶ ያነሱትን ክርክር መመርመሩ Aስፈላጊ ሆኖ Aላገኘነውም። ስለሆነም ከላይ በተገለፀው መንገድ የፍታብሕር ህግ ቁጥር 1000(2) በተሣሣተ መንገድ በመተርጐም የወረዳውና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሣኔ የህግና የፍሬ ጉዳይ ስህተት የለበትም በማለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማጽደቅ የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍትሐብሄር ይግባኝ መዝገብ ቁጥር 255/1999 ጥር 22 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል። ይፃፍ።
የደቡብ ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍትሐብሄር ይግባኝ መዘገብ ጥቅምት 30 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የደሴ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 83/90 መጋቢት 17 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
ተጠሪ በAመልካቾች ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ የታገደ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ይህ ፍርድ በፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ