No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድኀን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ Aየለች Aልታዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ Aስናቀች Aየለ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ በሰበር የቀረበው የፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት Eና ህዳር 27 ቀን 1993 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍድራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 5436 ሚያዝያ 3 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሰኔ 19 ቀን 1998 ዓ.ም ባቀረበችው Aቤቱታ ስለጠየቀች ነው።
የክርክሩ መነሻ Aመልካች የሕፃን ዮናስ ወንድሙና የያሬድ ወንድሙ ወላጅ Eናት Eና ሞግዚት መሆኗን ገልፆ የሞግዚት Aድራጊዎች ወላጅ Aባት Aቶ ወንድሙ ገብረየስ መጋቢት 3 ቀን 1981 ዓ.ም በሞት ተለይተዋል።
ሟች Aቶ ወንድሙ ከተከሣሽ /ከተጠሪ/ ጋር በባልና ሚስትነት Eያሉ በAዲስ Aበባ ከተማ ወረዳ 19 ቀበል 56 ቁጥሩ 115 የሆነ መኖሪያ ቤት ሰርተዋል።
ስለዚህ የመኖሪያ ቤቱን ግምትና ቤቱን ለሱቅና ለሆቴል Eያከራየች የምታገኘው ገንዘብ ጭምር የሕፃኖቹ ወላጅ Aባት የጋራ ሀብት በመሆኑና የውርስ ሀብት ክፍል Eንድታካፍለኝ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ 196 197 Aቅርበዋል። ተጠሪ የውርስ ንብረት ክፍል ነው የተባለውን ሀብት Aስመልክቶ የተለያየ ክርክርና ማስረጃ ያቀረበች ሲሆን ወ/ሮ ጥሩወርቅ ወንድሙ የተባለች ሴት በበኩሐ የሟች ወንድሙ ገብረየስ ወራሽ Eና ልጅ ነኝ በማለት የወራሽነት ማስረጃዋን በማያያዝ በክርክሩ ጣልቃ ገብታለች።
ፍርድ ቤቱ ቤቱና ልሎች ንብረቶች ተገምተው Eንዲቀርቡለት ትEዛዝ ሰጥቶ የፍርድ Aፈፃፀም መምሪያ መሀዲስ የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ብር 19,823.47 /Aስራ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከAርባ ሰባት ሣንቲም/ ነው በማለት Aስተያየት Aቅርቧል። ከዚህ በኋላ የቤቱ ግማሽ ባለቤትነት የተጠሪ፣ የቤቱ ግማሽ ባለቤትነት ደግሞ የAመልካች ሞግዚት Aድራጊዎችና የወ/ሮ ጥሩወርቅ ወንድሙ መሆኑን ከዘረዘረ በኋላ ተጠሪና ወ/ሮ ጥሩወርቅ ወንድሙ፣ ለAመልካች ብር 5,551.21/Aምስት ሺ Aምስት መቶ ሃምሣ Aንድ ብር ከሃያ Aንድ ሣንቲም/ በመክፈል ቤቱን በጋራ Eንዲያስቀሩ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ በሀራጅ Eንዲሸጥ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት Aቅርባ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ Aጽንቷል።
Aመልካች ልጆቹን ማሣደጊያ ቤት የለኝም። ንብረቱ በAይነት መካፈል Eየተቻለ ተጠሪ ትጠቅልለው መባሉ ተገቢ Aይደለም፣ ንብረቱም መሸጥ ካለበት መሀዲሱ ባቀረበው ግምት ሣይሆን በሀራጅ መሆን ይገባዋል፣ የዳኝነት በጋራ ክፈሉ መባሉ ተገቢ Aይደለም፣ በAጠቃላይ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያመለከተች ሲሆን፤ ተጠሪ ደግሞ በበኩሐ ቤቱ Aመልካችና ተጠሪ ባሉበት በመሐንዲስ የተገመተ በመሆኑ Eና በAይነት ላከፈል የማይችል በመሆኑ፤ Aመልካች ያቀረበችው Aቤቱታ ሕጋዊ መሰረት የለውም የሚል መልስ የሰጠች ሲሆን Aመልካች የመልስ መልስ Aቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው የክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ሟች ወንድሙ ገብረየስ Eና ተጠሪ በባልና ሚስትነት ሲኖሩ በጋራ የሰሩት ቤትና የጋራ ንብረት መሆኑ Aልተካደም።
ሟች ወንድሙ የሞተ በመሆኑ Eሱ በቤቱ ላይ ያለው የጋራ ባለቤትነት መብት ለወራሾቹ ዮናስ ወንድሙ፣ ያሬድ ወንድሙና ጥሩወርቅ ወንድሙ በፍትሐብሕር ሕግ ቀጥር 826 ንUስ Aንቀጽ 2 መሰረት ይተላለፋል።
ስለሆነም የቤቱ የጋራ ባለንብረቶች የሟች ወንድሙ ገብረየስ ወራሾች Eና ተጠሪ ናቸው።
የማይንቀሣቀስ ንብረት የጋራ ባለቤት የሆኑ ሰዎች የማይንቀሣቀሰውን ንብረት በAይነት ለመከፋፈል የሚችሉ ከሆነ በAይነት መከፋፈል Eንደሚችሉ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1272 የተደነገገ ሲሆን ንብረቱ በAይነት መከፋፈል የማይቻል ሲሆን ደግሞ በሀራጅ ተሸጦ ገንዘቡን Eንደሚከፋፈሉ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1273 ተደንግጓል። ከዚህ Aንፃር ንብረቱ በAይነት ለመከፋፈል የሚችል ከሆነ የሟች ወራሾች Eና ተጠሪ ንብረቱን Eኩል መከፋፈልና የሟች ወራሾች ድርሻቸውን በስምምነት የሚከፋፈሉበት Eድል ላሰጣቸው ይገባል። ስለሆነም ቤቱ በAይነት ለመከፋፈል የሚቻል ሲሆን Aመልካችና ተጠሪ ቤቱን በAይነት Eንዲካፈሉ ትEዛዝ መስጠት ሲገባቸው Aላግባብ ያለፉት በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
No topics extracted.
ከላይ በተገለፀው መንገድ ቤቱ በAይነት ለመከፋፈል የሚችል ካልሆነ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1273 መሰረት ግልጽ ሀራጅ ወጥቶ መሸጥ ይገባዋል። ተጠሪም ሆነች Aመልካች የቤቱን ዋጋ በመክፈል የቅድሚያ ግዥ መብታቸው የሚጠበቀው ቤቱ በግልጽ ጨረታ ያወጣውን ከፍተኛ ዋጋ ገቢ ለማድረግ ዝግጁ ሆነው ሲገኙ Eንጅ መሀዲሱ ገምቶ ያቀረበውን ዋጋ ገቢ በማድረግ Aይደለም።
198 199 ስለሆነም Aመልካችና ተጠሪ ቤቱን በግልጽ ሀራጅ በሚያወጣው ዋጋ መሰረት ለማስቀረት የሚስማሙ ከሆነ በስምምነታቸው መሰረት መፈፀም Aለበት። Aመልካች Eና ተጠሪ የማይስማሙ ከሆነ ግን ቤቱ በግልጽ ሐራጅ ተሸጦ የሟች ወራሽ የሆኑት ሶስት ልጆች ግማሹን ለሶስት Eኩል Eንዲካፈሉ፣ ተጠሪ ደግሞ የቤቱን ግማሽ ዋጋ Eንድትወስድ መደረግ ይገባዋል። ከዚህ በተጨማሪ Aመልካች በፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ባቀረበችው ክስ መሰረት በክርክሩ ፊት ሆና Eያለ ከተጠሪ ጋር ዳኝነት በጋራ Eንድትከፍል የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የልለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህዳር 27 ቀን 1993 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 5436 ሚያዚያ 3 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
Aመልካችና ተጠሪ የሚቻል ከሆነ ቤቱንና ቦታውን በAይነት Eንዲከፋፈሉ ቤቱን በAይነት ለመከፋፈል የማይችሉ ከሆነ በግልጽ ጨረታ በሀራጅ ተሸጦ ግማሹን ተጠሪ Eንዲወስዱ፣ ግማሹን የሟች Aቶ ወንድሙ ወራሾች ለሶስት Eኩል Eንዲካፈሉ በማለት ወስነናል።
በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ወጭ ተጠሪ ብቻዋን መሸፈን Aለባት ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሣቸው ይቻቻሉ።
ይህ ፍርድ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰኔ 19 ቀን 2AAA ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ