No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ታፈሰ ይርጋ Aቶ መድሕን ኪሮስ Aቶ ዓላ መሐመድ Aቶ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ Aዳነች ወርዶፋ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- Eነ ወ/ሮ Aስናቀች ወርዶፋ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን Aመጣጡም የAሁንዋ Aመልካች ህዳር 10 ቀን 97 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ የውርስ Aጣሪው በ16/2/97 ዓ.ም ያቀረቡት ሪፖርት በAግባቡ የቀረበ Aይደለም።
Aጣሪው ላጸድቅ የማይገባውን የስጦታ ውል መነሻ በማድረግ ውሳኔ ሰጥተዋል። በውርስ Eዳነት መመዝገብ የማይገባውን Eዳ መዝግበዋል።
ያቀረብኳቸውን ማስረጃዎች በAግባቡ Aልመረመረም። ወራሾች ሳንስማማበት የውርስ ንብረት ለወራሾች Eንዲከፋፈል ወስነዋል። በመሆኑም የውርስ Aጣሪው ሪፖርት መጽደቅ የለበትም በማለት Aመልክተዋል።
ፍ/ቤቱም የውርስ Aጣሪው የሟች የኑዛዜና ያለኑዛዜ ወራሾች Eነማን Eንደሆኑ፣ የሟች የውርስ ሃብት ምን Eንደሆነ ከውርሱ ሐብት ላይ ላከፈል የሚገባውን Eዳ ምንነት Eና በኑዛዜ የተሰጠ ስጦታ ለተቀባዩ መክፈልን በተመለከተ የግራ ቀኙን Aቤቱታና ማስረጃ መርምረው ያቀረቡት ሪፖርት የሚነቀፍበት ምክንያት የለም። Aመልካች Aለኝ የሚሉት መብት ካላቸው ዳኝነት ከፍለው በክስ ከሚጠይቁ በስተቀር የውርስ Aጣሪውን ሪፖርት ባለማጽደቅ በዚህ መዝገብ ላጠይቁ የሚችሉበት ሁኔታ የለም በማለት Aቤቱታውን ባለመቀበል ሪፖርቱን Aጽድቆታል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ከAመልካች የቀረበለትን ይግባኝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል Aመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት Aቤቱታ ያቀረቡትም የስር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ትEዛዝ በመቃወም ነው። በAቤቱታው ውስጥ የተጠቀሱት ቅሬታዎችም የውርስ Aጣሪው የሟችን ሃብት በAግባቡ Aላጣሩም። በሕግ መፍረስ የሚገባውን የስጦታ ውል Aጽድቀዋል። የቆጠርኳቸውን ማስረጃዎች ባለመስማት መብቴን Aጣብበውብኛል። ያለAግባብ የውርስ ንብረቶችን ወራሾች Eንድንከፋፈል ወስነዋል። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የውርስ Aጣሪው ያቀረቡትን ሪፖርት Eንዳያጸድቅ፣ የውርስ ማጣራቱ ሥራ Eንደገና Eንዲካሄድ Eንዲያደርግልኝ ያቀረብኩትን ጥያቄ ባለመቀበል ሪፖርቱን ማጽደቁ በAግባቡ Aይደለም።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ትEዛዝ መሰረትዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ትEዛዙ ላሻርልኝ ይገባል የሚሉ ናቸው።
1ኛ ተጠሪ ሐምል 30 ቀን 99 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ የውርስ Aጣሪው በኑዛዜ ስጦታው ላይ ያሉትን ምስክሮች Aስቀርበው በመስማት የኑዛዜ ስጦታው የህግ ስህተት የልለበት መሆኑን Aጣርተው የAሁንዋ Aመልካችንና ልሎቹን ወራሾች በዝርዝር መዝግበው ባደረጉት ማጣራት መሰረት ሪፖርታቸውን ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ማቅረባቸው በAግባቡ ነው። የሥር ፍ/ቤቶቹ ሪፖርቱን ለማጽደቅ የሰጡት ትEዛዝም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም። በመሆኑም ትEዛዙ ላጸድቅልን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ ደግሞ ሐምል 30 ቀን 99 ዓ.ም ጽፈው በሰጡት መልስ ውርስ Aጣሪው የውርስ ንብረቱን በAግባቡ Aላጣሩም የ1ኛ ተጠሪን ቤት በውርስ ንብረት ውስጥ ማካተት ሲኖርባቸው በስጦታ ያገኙት ነው በማለት መወሰናቸው ተቀባይነት የለውም። Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፊት 192 193 ሟች ለEኔ የሰጡኝን ቁጥሩ 432 የሆነውን ቤት በውርስ ንብረት ውስጥ ያለማካተታቸው ግን በAግባቡ ነው። በመሆኑም የውርስ Aጣሪው ሪፖርት ባለበት ሁኔታ Eንዲፀድቅ መደረጉ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የውርስ ንብረት Aጣሪውን ሪፖርት ምንም ጉድለት Aላገኘሁበትም በማለት ያፀደቀው በAግባቡ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም የውርስ Aጣሪው ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ቁጥሩ 432 የሆነው ቤት Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፊት ሟች ወ/ሮ ደጊቱ ደንጓሬ ለወ/ሮ Aሰለፈች ወርዶፋ በስጦታ የሰጡዋቸው በመሆኑ የውርስ ሐብት Aይደለም በማለት ወስኛለሁ፣ ቁጥሩ 431 የሆነው ቤትም የወ/ሮ Aስናቀች ወርዶፋ የኑዛዜ ድርሻ ነው፣ Aመልካች ስጦታዎቹ ፈራሽ ናቸው በማለት ቢከራከሩም የሚፈርስበትን ምክንያት Aልገለፁም፣ ስጦታው Eንዲፈርስ በፍርድ ቤት ጠይቀው ያስፈረሱበትን የፍ/ቤት ውሳኔ Aላቀረቡም በማለት ያሰፈሩዋቸው ድምዳሜዎች ንብረቶቹን የማከፋፈል ዓይነት ሥራ ያከናወኑ መሆኑን Eንደሚጠቁሙ ለመረዳት ችለናል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 956 Eንደተደነገገው የAጣሪው ሥራ ሟቹ Aንድ ኑዛዜ ትቶ Eንደሆነ መፈለግና በመጨረሻው ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዎች Eነማን Eንደሆኑ ማረጋገጥ፣ የውርሱን ሃብት ማስተዳደር፣ መክፈያቸው የደረሰውን የውርስ Eዳዎች መክፈል Eና ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈልና የኑዛዜውን ቃል ለመፈፀም ማንኛቸውም ልሎች Aስፈላጊ ጥንቃቄዎች ማድረግ ነው። Eነዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በሚያከናውንበት ጊዜ ደግሞ በኑዛዜው የውርስ ንብረት መሆናቸው ተጠቅሶ የክፍፍል ስርAትም የተቀመጠላቸውና ወራሾች በሙሉ የተስማሙባቸው ንብረቶችና መክፈያቸው የደረሰው የውርስ Eዳዎች ሲኖሩ በወራሾቹ ስምምነት መሰረት ንብረቶቹን ላያከፋፍልና Eዳዎችንም ላከፍል ይችላል።
በኑዛዜው ላይ በተጠቀሱትና ባልተጠቀሱት ንብረቶች የውርስ ሃብት መሆን ያለመሆን ላይ ወራሾቹ ያልተስማሙና ክርክር ያነሱ ከሆነ ግን የAጣሪው ሥራና ሐላፊነት ወራሾች የተስማሙባቸውን ንብረቶች የውርስ ሃብት መሆናቸው መመዝገብ። ወራሾች ያልተስማሙባቸው ንብረቶችና Eዳዎች ካሉ ደግሞ ማስረጃ በመሰማት ማስረጃው ምን Eንደሚያስረዳ ሪፖርቱ ላይ በማስፈር Eንዲያጣራ ላዘዘው ፍ/ቤት ማቅረብ Eንጂ ንብረት Aጣሪው ይህ ንብረት የውርስ ሐብት Aይደለም የሚሉ ወራሾች ቢኖሩም ማስረጃ በመስማት የውርስ ሃብት መሆኑን ስለተገነዘብኩኝ ንብረቱ የውርስ ሃብት ነው በማለት ወስኛለሁ ወይም ደግሞ ማስረጃውን Eንደተመለከትኩት ንብረቱ የውርስ ሐብት ያለመሆኑን ስላረጋገጥኩኝ የውርስ ሐብት Aይደለም በማለት ወስኛለሁ ለማለት የሚያስችለው ሥልጣን የለውም።
በዚህ ጉዳይ የውርስ Aጣሪው ያደረጉትን የማጣራት ሥራ ስንመለከተው ወራሾቹ የውርስ ሐብት ናቸው በሚሉዋቸው ሁለቱም ቤቶች ላይ ገና ከጅምሩ Aንስቶ ያልተስማሙና ክርክር ያነሱ በመሆኑ Aጣሪው ማስረጃ መስማታቸው በAግባቡ ነው። ሁኖም Aጣሪው በወራሾች መካከል የተደረገው ክርክር ምን Eንደነበረ፣ የኑዛዜ ወራሾችና የሕግ ወራሾች Eነማን Eንደሆኑ፣ የግራ ቀኙ ማስረጃ ምን Eንደሚመልስ፣ Eንዲሁም ወራሾች የተማመኑባቸውና ያልተማመኑባቸው የውርስ ንብረቶችና Eዳዎቹ ምን ምን Eንደሆኑ በመዘርዘር ሪፖርት ማዘጋጀት ሲኖርባቸው ከዚህ Aልፈው ወራሾችን Aከራከረው ማስረጃ ከሰሙ በኋላ ክርክሩንና ማስረጃውን ከሕግ ጋር በማገናዘብ ይህ ንብረት የEገል Eንጂ የEገል Aይደለም በማለት መወሰናቸው ከተሰጣቸው የውርስ Aጣሪነት ሥልጣን በላይ በመሄድ መደበኛ ፍ/ቤት በሚያከናውነው የዳኝነት ሥራ ውስጥ መግባት መሆኑንና ይህም ተገቢ ያለመሆኑን ተገንዝበናል።
ውርስ Aጣሪው Aዘጋጅተው ያቀረቡት ሪፖርት ውሳኔም ጭምር ያዘለ በመሆኑ ሪፖርቱ በቀረበለት ፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መጽደቁ ደግሞ በAጣሪው 194 195 የተወሰነው ነገር በፍ/ቤት ተቀባይነት Aግኝቶ የፀደቀ ተደርጐ ስለሚወሰድ Aመልካች Aዲስ ክስ Aቅርበው የውርስ ድርሻቸውን ለማግኘት የሚያስችላቸውን መብት የሚያጣብብ ነው የሚሆነው። በመሆኑም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሪፖርቱን መርምሮ ያለበትን ጉድለት Eንዲስተካከል ማድረግ ሲገባው Eንዳለ ተቀብሎ ማጽደቁ ተገቢ ሆኖ Aልተገኘም።
ስለዚህ የውርስ ንብረት Aጣሪው ያቀረቡት ሪፖርት የAጣሪንና የመደበኛ ፍ/ቤትን ሥራ Aጠቃሎ የያዘ በመሆኑ ሪፖርቱ በAግባቡ የተዘጋጀ ባለመሆኑና የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሪፖርቱን ያፀደቀበትና የፍ/ከ/ፍ/ቤት ደግሞ የቀረበለትን ይግባኝ የሰረዘበት ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆነው ስለተገኙ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 04036 ጥር 5 ቀን 97 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37777 ሕዳር 21 ቀን 98 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የሥር ፍ/ቤት የውርስ ማጣራት ሪፖርቱን ያፀደቀው ከነጉድለቱ ጭምር በመሆኑ መጽደቅ Aልነበረበትም ብለናል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት Eንደገና Aጣሪ ሾሞ የውርስ ማጣራቱን ሥራ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 956 መሰረት Eንዲከናወን በማስደረግ ሪፖርቱ በAግባቡ የቀረበ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በሕጉ መሰረት Aስፈላጊውን Eንዲፈጽም በማለት ወስነናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን Eንዲችሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መለሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ
No topics extracted.