No summary available.
መ/ ሐምል 29 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጐስ ወልዱ ወ/ት ሂሩት መለሰ Aቶ መድህን ኪሮስ Aቶ በላቸው Aንሺሶ Aመልካች፡- ሜድሮክ Iትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር Aልቀረበም ተጠሪ፡- Aቶ በዛወርቅ ሺመላሽ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዳዩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የክርክሩን Aመጣጥ በተመለከተ የAሁን ተጠሪ የሥር ከሣሽ መጋቢት 18 ቀን 1993 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ ከግንቦት 24 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ Eስከ ጥቅምት 20 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ በሕግ Aገልግሎት ሃላፊነት ተቀጥሬ ያገለገልኩ ሲሆን በፍደራል ፍ/ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ Aሰጣጥን ምዝገባ Aዋጅ ቁጥር 199/92 መሰረት ለተከሳሹ Aገልግሎት ለመስጠት በመቸገሬ ምክንያት ተከሣሹ ሁኔታውን Eንዲያሻሽል ብጠይቅ ተከሣሹ የሥራ ውልን Aቋርጧል። የተከሳሹ ሥራ Aስኪያጅ በብር 5,000 /Aምስት ሺህ ብር/ ደመወዝና የመኪና Aበል (በተጨማሪነት) የቀጠሩኝ ቢሆንም ይህ ክፍያ ሣይከፈለኝ የቆየ በመሆኑ የ43 ወራት የAገልግሎት ቀሪ ክፍያ ብር 76,411፣ የመኪና ማካካሻ ክፍያ ብር 43,000፣ የትራንስፖርት Aበል ብር 21,500፣ E.ኤ.A. ህዳር 23 ቀን 1999 በተፃፈ ደብዳቤ የታመነ ብር 1,349.74፣ ዳላስ ሄጄ የተመለስኩበት የውሎ Aበል ብር 5,049፣ የAውሮፕላን ትኬት ክፍያ ብር 2,607፣ የ3 ወር ያልተከፈለ Aበል ብር 19,500፣ የ3 ዓመት ወለድ ብር 30,495፣ በድምሩ ብር 199,911.74 (Aንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ Aስራ Aንድ ብር ከሰባ Aራት ሳንቲም) Eንዲከፈለኝ ወደ ሥራም Eንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ክስ Aቅርበዋል።
ተከሳሽም ጥቅምት 14 ቀን 1994 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ የከሣሽ የክፍያ ጥያቄዎች በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ የታገዱ ናቸው፤ ላከፈላቸው የሚገባ ደመወዝ ላይ የተደረገ ስምምነት የለም፣ ደመወዛቸው ሲከፈላቸው Eንደቆየው ነው፣ ፈርመው ሲቀበሉት በነበረው ገንዘብ ላይ ክርክር መፍጠራቸው Aግባብ Aይደለም፤
ዳላስ ሄደው የተመለሱበት የውሎ Aበል ተከፍሐቸዋል፤ ብር 1,349.74 ላከፈላቸው Aይገባም፤ የAውሮፕላን ትኬቱን በተመለከተ ብር 2,607 ለመክፈል ፈቃደኛ ሆነን Eያለ ከሣሽ ጥያቄ ባለማቅረባቸው Eድሉ Aልፏቸዋል፤ ከሣሽ የሶስት ወር ደመወዝና Aበል ያሉት የመቼ Eንደሆነ ያልተገለፀ ከመሆኑም ልላ ከሣሽ Eስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ያለ የሚገባቸው ደመወዝና Aበል ተከፍሎAቸዋል፤ ከሣሽ የተሰናበቱት በAግባቡ ነው፤
የሚከፈላቸው ወለድም የለም በማለት ከተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ከሣሽ ያቀረቡት የAውሮፕላን ትኬት፣ የውሎ Aበልና የብር 1,349.74 ክፍያ መከፈል ከነበረበት ጊዜ Aንስቶ ክስ Eስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ሲሰላ Aንድ Aመት ያለፈበት Eንደመሆኑ ክፍያው በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ የታገደ ነው፤ የደመወዝ ጥያቄውም Eንደዚሁ ክስ ከቀረበበት ጊዜ Aንድ Aመት ወደኋላ በመቁጠር ሲታይ ጊዜ ያለፈበት በመሆኑ በAዋጅ Aንቀጽ 162(1) መሰረት በይርጋ ቀሪ መሆን የሚገባው ነው፤ በልላ በኩል ተከሣሽ ከሣሽን ከሥራ ያሰናበተበት ምክንያት Aቶ ዳንኤል ተገኑ ከፃፉት ሪፖርት በመነሳት Eንጂ ልላ ተከሣሽ Aልሰራም ያሉ ስለመሆናቸው የሚያሳይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ሥንብቱ ሕጋዊ Aይደለም። በመሆኑም የተከሣሽ ወደ ሥራ መመለስ ለሥራ ግንኙነቱ የማይመች ላሆን ስለሚችል ከሣሽ ለከሣሽ የሥራ ስንብት፣ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያና የስድስት ወር የካሣ ክፍያ በመክፈል ከሣሽን Eንዲያሰናብት፤ ከይርጋ የተረፈውን ክፍያ በተመለከተ የከሣሽ የደመወዝ ብር 5,000 ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩና ከሣሽ የጠየቁት የሶስት ወር ክፍያም የመቼ Eንደሆነ ተብራርቶ ስላልቀረበ የሶስት ወር ደመወዝ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም፤ ኃላፊዎቹ በመጻጻፍ ሒደት ላይ ስለነበሩ የከሣሽ ደመወዝ ብር 5,000 Eንዲሆንላቸው ተወስኖ ላሆን Eንደሚቻል ተገንዝበናል። ልዩነቱን የይርጋ ጊዜ ከሚጀምርበት መጋቢት 21 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ Eስከተሰናበቱበት ጥቅምት 20 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ ያለውን የስምንት ወር ልዩነት ተከሳሽ ለከሳሽ Eንዲከፍል በማለት ወስኗል።
የAሁን Aመልካች የፍ/መ/ደፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርቧል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በድርድር ላይ ያለ ደመወዝ Eንደተወሰነ ደመወዝ ተደርጐ ላወሰድ Aይችልም፣ የሰራተኛው ደመወዝ ብር 4,524 ነው። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት የሰራተኛው ደመወዝ ብር 5,000 ነው ያለው በAግባቡ Aይደለም።
ሰራተኛው Eስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ደመወዛቸውን ሲያገኙ የቆዩ በመሆናቸው የስምንት ወር የደመወዝ ልዩነት ይከፈላቸው ተብሎ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔም ተቀባይነት የለውም። የስንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያ ለሰራተኛው Eንዲከፈላቸው የተባለውም በAግባቡ Aይደለም። ስንብቱ ሕገወጥ በመሆኑ ድርጅቱ የስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ለሰራተኛው ላከፍላቸው Eንደሚገባ ግልጽ ቢሆንም ድርጅቱ ይህን ክፍያ መፈፀሙን በስንብት ደብዳቤው ስለገለፀና ሰራተኛውም ይህ ክፍያ Aልተከፈለኝም ብለው ስላልተከራከሩ ድጋሚ ላከፈላቸው Aይገባም በማለት ድርጅቱ በብር 4,524 የደመወዝ ሒሳብ Aስልቶ ካሣ ለሰራተኛው ይክፈል በማለት በፍ/መ/ደ/ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ውሳኔ በመቀጠልም Aመልካች የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለዚህ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት Aቤቱታውን Aቅርቧል። ቅሬታውም ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት የተቀጠሩበትን ሥራ Aልሰራም በማለታቸው ነው።
No topics extracted.
ተጠሪው ሥራውን Aልሰራም ያሉትም ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ ወይም ደግሞ የኩባንያው ሸሪክ (ባለAክሲዮን) Aድርጐ ካላስመዘገበኝ ሥራ መስራት Aልችልም። ከሰራሁ በወንጀል የሚያስጠይቀኝ በመሆኑ ሁኔታው ላመቻችልኝ ይገባል በማለት ነው። Eንዲህ የሚል ሐሳብ ስለማቅረባቸው ራሳቸው የፃፋት ደብዳቤ ያስረዳል። Aቶ ዳንኤል ተገኑ የፃፉት ደብዳቤም ተጠሪው Aልሰራም ማለታቸውን ያረጋግጣል። Eንደዚሁም Aቶ ዳንኤል ተገኑ በመከላከያ ምስክርነት ቆጥረናቸዋል። የሥር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የወሰኑትም የቀረቡትን ማስረጃዎችና የተደረገውን ክርክር ባለመገንዘብና በመከላከያ ምስክርነት የቆጠርናቸውን Aቶ ዳንኤል ተገኑን ምስክርነት ባለመሰማት ነው። በመሆኑም ተጠሪው የተቀጠሩበትን ሥራ Aልሰራም በማለታቸው በAዋጅ ቁ. 42/85 Aንቀጽ 26(1) Eና 28 መሰረት የተሰናበቱ ናቸው። ስንብቱ ሕጋዊ ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የAዋጁን ድንጋጌ የሚፃረር በመሆኑ ውሳኔቸው መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበትና ላታረም የሚገባው ነው የሚል ነው።
ተጠሪው ደግሞ በሰጡት መልስ የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ በመሆኑ Aመልካች ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ ነበረበት። ይህን Aልፎ ለሰበር ችሎት Aቤቱታ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም። ድርጅቱ የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ ሥራ Aልሰራም Aላልኩም ባለAክሲዮን Aድርጐ ካላስመዘገበኝ የምክር Aገልግሎት Aልሰጥምም Aላልኩም። Aመልካች Aልተሰማልኝም ያሉት ምስክር የሚያውቀውን በጽሑፍ ስለገለፀ ለምን ቀርቦ Aልመሰከረም Aይባልም።
ተፈጠረ ላልኩት ችግር መፍትሄ ሳይሰጥበት ድርጅቱ Eኔን ማሰናበቱ ተገቢ Aይደለም። የፍ/ከ/ፍ/ቤት ድርጅቱ ለችግሩ መፍትሄ ሳይፈለግ የተወሰደው የሥራ ስንብት Eርምጃ ሕገወጥ ነው በማለት የወሰነው በAግባቡ ነው።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለበትና በAግባቡ የተሰጠ በመሆኑ ላፀናልኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ግራ ቀኙ ያደረጉት የቃል ክርክርም በመቅረፀ ድምፅ ከተሞላው ካሴት ወደ ጽሑፍ ተመልሶ ጽሑፉ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። Aመልካች ያቀረበው የመልስ መልስም Eንደዚሁ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
በበኩላችን ደግሞ Aመልካች ኩባንያ ተጠሪውን ያሰናበታቸው በሕገወጥ መንገድ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ተጠሪው ሐምል 7 ቀን 1992 ዓ.ም ለAቶ ንጉሴ Aበራ በፃፉት ደብዳቤ Aዋጅ ቁጥር 199/92 በAንቀጽ 31 የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት የሚፈልግ ሰው ከፍትህ ሚኒሰቴር የጥብቅና ፈቃድ ማግኘት Eንዳለበት ደንግጓል፣ Eንደዚሁም የግል ድርጅት ወይም ኩባንያ ኃላፊ ወይም ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ የሆኑ ሰዎች የጥብቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት Eንደሚችሉ በAዋጁ Aንቀጽ 31(1) ሥር ተደንግጓል፣ Eኔ Eነዚህን መስፈርቶች ስለማላሟላ የጥብቅና Aገልግሎት ብሰጥ በሕጉ Eቀጣለሁ፣ የድርጅቱን ወይም የኩባንያውን ጥቅም ለማስጠበቅ በፍርድ ቤት መከራከር ሕጋዊ የውክልና ሥልጣን የተሰጠው ሰው፣ የኩባንያ ኃላፊ፣ ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ መሆንን ይጠይቃል።
ፍ/ሚኒሰቴር የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጠው የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ላልሆነ ሰው Eንጂ ለሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ Aይደለም። በመሆኑም መመርያችሁን Eጠብቃለሁ ማለታቸውን ተመልክተናል። የዚህ ደብዳቤ ይዘት ደግሞ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሆኜ መስራት ብቀጥል የጥብቅና ፈቃድ ስለማይሰጠኝ የጥብቅና ፈቃድ ማግኘት Aልችልም። ያለ የጥብቅና ፈቃድ ለመስራት የሚቻልበት ልላው Aማራጭ ደግሞ የኩባንያው ሐላፊ ባለAክሲዮን ሸሪክ በመሆን ቢሆንም Eኔ ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ ወይም ደግሞ የኩባንያው ኃላፊ ባለመሆኔ የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት Aልችልም።
ፈቃድ ሳይወጣልኝ ወይም ባለAክሲዮን ሆኜ ሳልመዘገብ የሕግ Aገልግሎት ለኩባንያው ብሰጥ በወንጀል የምቀጣ በመሆኑ መፍትሄ Eስከሚፈለግልኝ ጊዜ ድረስ የተቀጠርኩበትን ሥራ Aላከናውንም የሚል ነው።
ተጠሪው መጋቢት 18 ቀን 1993 ዓ.ም ባዘጋጁት የክስ ማመልከቻና ታህሳስ 17 ቀን 94 ዓ.ም ባቀረቡት የመልስ መልስ የጥብቅና Aገልግሎት ለመስጠት በቅድሚያ የጥብቅና ፈቃድ Eንደሚያሻ፣ ፈቃድ ሳይኖር Aገልግሎት መስጠት በወንጀል Eንደሚያስጠይቅ፣ ለግል ኩባንያም ቢሆን ያለ ጥብቅና ፈቃድ Aገልግሎት መስጠት የሚችሉት የድርጅት ሃላፊ ወይም ሸሪክ መሆን Eንደሚያስፈልግ የጠበቆች Aዋጅ ይደነግጋል፤ ላይሰንስ (የጥብቅና ፈቃድ) የማገኝበት መንገድ ሳይቀየስና ፈቃድ ሳይኖረኝ ብሰራ በወንጀል Eንደምቀጣ Eየታወቀ Aቶ ዳንኤል ተገኑ ሆራ ሆቴል በሚመለከት የሕግ Aገልግሎት Eንድሰጥ ማዘዛቸው Eኔን ለማስወንጀል ወይም ደግሞ የተመደበበትን ሥራ Aልሰራም ብሐል በማለት Eርምጃ ለማስወሰድ የታሰበ ነበር በማለት ያቀረቡት ክርክርም ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ ወይም ደግሞ የባለAክሱዮንነት ምዝገባ ካላደረገልኝ ሥራውን Aልሰራም ማለታቸውንና ሆራ ሆቴልን የተመለከተውን ሥራም ሳያከናውኑ መቅረታቸውን በማመን የተከራከሩ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው።
Aቶ ዳንኤል ተገኑ ሰኔ 7 ቀን 1993 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ Aቶ በዛወርቅ ሽመላሽ የሆራ ሆቴል ኮንትራትን በተመለከተ የሕግ Aስተያየት Eንዲሰጡ Eንደነግራቸው በተሰጠኝ መመሪያ መሰረት ብነግራቸውም Aዲሱ ሕግ Aይፈቅድልኝም በማለት የሕግ Aስተያየታቸውን ለመሰጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል በማለት የሰጡትን መግለጫ ተጠሪው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስና የመልስ መልስ ከጠቀሷቸው የመከራከሪያ ነጥቦች ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው ተጠሪው በኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ የማገኝበት ሁኔታ ካልተመቻቸልኝ Eና ፈቃዱን ካልያዝኩኝ በስተቀር ለድርጅቱ የሕግ Aገልግሎት Aልሰጥም በሚል Aቋማቸው መሰረት ሆራ ሆቴልን የሚመለከት የሕግ Aስተያየት ሳይሰጡ የቀሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሆኖ Aግኝተነዋል።
Eንደዚሁም ተጠሪው ነሐሴ 9 ቀን 1992 ዓ.ም ለAቶ ንጉሴ በፃፉት ደብዳቤ ሆራ ሆቴልን የሚመለከት የሕግ Aስተያየት Eንድሰጥ በAቶ Aልፍሬድ መመሪያ መሰጠቱን Aቶ ዳንኤል ነግሮኛል Eንዲህ ዓይነት የሕግ Aስተያየት (ምክር) መስጠት በAዲሱ Aዋጅ ላያስጠይቅ ይችላል Eያልኩኝ Eየወተወትኩኝ Eንደዚህ ዓይነት መመሪያ ለምን Eንደተሰጠ Aልገባኝም፣ Aሁንም ቢሆን በቅድሚያ የጥብቅና ፈቃድ የማገኝበት መንገድ Eንዲቀየስ Aሳስባለሁ ማለታቸው ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ስላላስወጣልኝ ሥራውን Aላከናውንም በማለት የሕግ Aገልግሎት ሳይሰጡ መቅረታቸውንና ለወደፊቱም ድርጅቱ ፈቃዱን ካላስወጣላቸው በስተቀር የተመደቡበትን የሕግ Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Eንደማያከናውኑ የሚያስረዳ ነው።
በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪው በስር ፍ/ቤቶች ባደረኩት ክርክር Aመልካች /የሥር ተከሳሽ/ ኩባንያው ለቀጠራቸው የሕግ ባለሞያዎች የጥብቅና ፈቃድ የማስወጣት ግድታ ያለበት መሆኑንና ይህን ግድታውን መወጣት ሲገባው ሳይወጣ የቀረ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ Aላቀረቡም።
ኩባንያው ይህ ዓይነቱ ግድታ ያለበት መሆኑን የሚደነግግ ሕግ Aለ ብለው Aልጠቀሱም Aልተከራከሩምም። ኩባንያው ሰዎችን በባለAክሲዮንነት የሚመዘግብ ከሆነም የኩባንያውን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በማድረግ ከሚጠይቁ በስተቀር ተጠሪው የሕግ Aገልግሎት Eንዲሰጡ ተብሎ በባለAክሱዮንነት ወይም በሸሪክነት ላመዘግባቸው የሚገደድበት ምክንያት የለም። ተጠሪም በፃፉት ደብዳቤ በምሳልነት ጠቀሱት Eንጂ ኩባንያው በባለAክሲዮንነት ወይም በሸሪክነት Eንዲመዘግባቸው በግልጽ የጠየቁ ባለመሆኑ ይህን ነጥብ Aመልካች በክርክሩ ውስጥ ማካተቱ ተገቢ Aይደለም።
186 187 ከዚህ በላይ በተዘረዘረው ሁኔታ ተጠሪው የጥብቅና ፈቃድ በኩባንያው Aማካኝነት ካልወጣልኝ በስተቀር የተመደብኩበትን የሕግ Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም በማለት ሥራ ማቆማቸው ራሳቸው ባደረጉት ክርክር ያመኑበትና ከግራ ቀኙ በቀረቡት የጽሑፍ ማስረጃዎች የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪው የተቀጠርኩበትን ሥራ Aልሰራም Aላልኩም በማለት ለሰበር Aቤቱታው በሰጡት መልስና በቃልም ባደረጉት ክርክር መግለፃቸው ተቀባይነት የለውም።
ልላው ቁምነገር ደግሞ ተጠሪው ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ የሕግ Aገልግሎት ሥራ Aልሰራም፣ ከሰራሁኝ በወንጀል Eቀጣለሁ የሚሉት ቀደም ብለው የወሰዱትን የጥብቅና ፈቃድ ሳይመልሱና የሕግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችም በውክልና የሕግ ባለሞያዎችን Eንዳያሰሩ በAዋጅ ባልተከለከለበት ጊዜ ነው። የጥብቅና ፈቃድ Eያላቸው በውክልናም መሥራት Eየቻሉ ለኩባንያው የሕግ Aገልግሎት ብሰጥ በወንጀል Eቀጣለሁ ማለታቸውም ግልጽ Aይደለም።
Aመልካች ለቀጠራቸው የሕግ ባለሞያዎች ከፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፈቃድ የማስወጣት ግድታ ሳይኖርበትና ተጠሪው ለAመልካች የጥብቅና ማለትም የሕግ Aገልግሎት ቢሰጡ በወንጀል የሚቀጡበት የሕግ ምከንያት በልለበት ጊዜ ተጠሪው ድርጅቱ የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ በስተቀር የተቀጠርኩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም የሚሉበትና Aመልካች ደግሞ ተጠሪው ምንም ሥራ ሳይሰሩ ሰራተኛዬ ናቸው በማለት ደሞዝ Eየከፈለ የሚቆይበት ምከንያት የለም።
ተጠሪው በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 13(2) ሥር የተደነገገው የAሰሪውን ትEዛዝ የመቀበል ግድታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ Aመልካች በAዋጁ Aንቀጽ 26(1) መሰረት ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ቅጥር ውሉን ለማቋረጥ ይችላል። Aመልካች የሥራ ውሉን በAዋጁ Aንቀጽ 26 Eና 28 መሰረት ማቋረጡና ተጠሪውን ማሰናበቱም በAግባቡ ነው።
በመሆኑም Aመልካች ተጠሪውን ከሥራ ያሰናበታቸውን የተቀጠሩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተጨባጭ የሥራ ትEዛዝን Aልቀበልም በማለታቸው ምክንያት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠና ተጠሪም ያመኑበት ሆኖ Eያለ የሥር ፍርድ ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪው ካሣ ይከፈል በማለት ውሳኔ መስጠታቸው Aግባብ ሆኖ Aላገኘነውም። ፍርድ ቤቶቹ የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረበላቸውን ማስረጃ በሚመለከት ውሳኔ መስጠት ሲገባቸው የቀረበላቸው ማስረጃ የሚያስረዳውን ቁምነገር በመተውና ተጠሪው በክርክራቸው ያመኑትን ከግምት ውሰጥ ባለማስገባት የተጠሪውን የግል ማህደር በማስቀረብ ተጠሪው የተቀጠሩበትን ሥራ ለማከናወን ፈቃደኛ Aለመሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከማሕደራቸው ስላላገኘን ለመስራት ፈቃደኛ ስላለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ የለም፣ ስንብቱ ሕገወጥ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪው ካሣ ይከፈል በማለት የሰጡት ውሳኔም የAዋጅ ቀጥር 42/85 ዓላማን የሳተና ለተጠሪው የማይገባቸውን መብት ያጐናፀፈ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/08459 ህዳር 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 43679 ሚያዝያ 17 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪው ከሥራ የተሰናበቱት ድርጅቱ /ኩባንያው/ የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ በስተቀር የተቀጠርኩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም በማለታቸውና በተጨባጭም ሆራ 188 189 ሆቴልን የተመለከተ የሕግ Aስተያየት Aልሰጥም በማለታቸው ምክንያት መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ስንብቱ ሕጋዊ ነው።
የሥራ ስንብት ክፍያ ላከፈላቸው Aይገባም በማለት ወስነናል።
ፍፃፍ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ፀ/መ ¨< ` e 190 191