No summary available.
ግንቦት 21 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች ፡- ወ/ሮ Aስካለ ማርያም ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ ተሾመ ካሣዬ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁኑ Aመልካች በመጋቢት 5 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ተከሳሽ በሱልልታ ሙሎ ወረዳ የማህበር Aባል ነኝ በማለት ድርሻዬ ነው ያሉትን ቦታ በብር 18,400 (Aስራ ስምንት ሺህ Aራት መቶ) ሸጠውልኝ የቦታውን ካርታ Aስረክበውኛል። ቦታውን Aጥሬ ለመስራት ስሞክር ግን ቦታው የተገኘው በሕገወጥ መንገድ ነው በማለት የመሬት Aስተዳደር ቦታውን ወርሶብኛል። በመሆኑም ተከሳሽ ገንዘቤን Eንዲመልስልኝ ይወስንልኝ የሚል ክስ Aቅርበዋል።
የAሁኑ ተጠሪ ልላ ቤት የገዛባቸው Aቶ ኤልያስ ደምሴ የተባሉት ተከሳሽ ደግሞ በሰጡት መልስ ይህ ክስ መቅረብ የሚገባው በቤት ሥራ ማህበሩ Eንጂ በEኔ ላይ Aይደለም። ከሣሽ ካርታውን የተቀበሉት ከማህበሩ Eጅ በመሆኑ ስለቦታው ሕጋዊነት መጠየቅ ያለባቸው ማህበሩ ነው። በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ከከሳሽ Aልተቀበልኩም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠና ማስረጃም ከሰማ በኋላ ተከሳሽ ገንዘቡን መቀበላቸውንና በውላቸው ደግሞ ቦታውን ለከሣሽ ካላስረከብኩኝ ገንዘቡን Eመልሳለሁ በማለት ግድታ መግባታቸውን በማስረጃ ስለተረጋገጠ በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ለከሳሽ ይክፈሉ ሲል ወስኗል።
በመቀጠልም ፍ/ቤቱ የAሁኑ ተጠሪ በተከሳሽ ስም የተመዘገበው ቤት የገዛሁት በመሆኑ Eግዱ ይነሳልኝ በማለት Aመልክተዋል። የAሁኑ Aመልካች ደግሞ በተከሳሽ ላይ ቀደም ብሎ የወሰዱት ገንዘቤን Eንዲመልሱልኝ ያስወሰንኩኝ በመሆኑና ቤቱም ተሸጦ ገንዘቤን የማስመልስበት የተከሳሹ ሃብት በመሆኑ Eግዱ መነሳት የለበትም በማለት ተቃውመዋል።
ፍ/ቤቱም Aቶ ተሾመ ካሣዬ ገዛሁት የሚሉትን ቤት የሽያጭ ውል ስልጣን ባለው Aካል ያልተመዘገበ በመሆኑ የሽያጭ ውሉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2878 መሰረት ውጤት የለውም። Eግዱ በቀረበው Aቤቱታ መልኩ ላነሳ የሚችልበት ምክንያት የለም በማለት ጥያቄውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
በዚህ የEግዱ ይነሳልኝ ጥያቄ መሰረት የAሁን ተጠሪ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርበው ፍ/ቤቱም ይግባኝ ባይ ቤቱን ከAቶ ኤልያስ ደምሴ መስከረም 19 ቀን 98 ዓ.ም በተፈፀመ የሽያጭ ውል ገዝተው ስም ለማዛወር በሒደት ላይ መሆኑን ገልጾ ነው ውልና ማስረጃ የEግድ ትEዛዙን የመዘገበው፤ ሽያጩ በክብር መዝገብ የተመዘገበው የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለመመዝገብ ስልጣን ባለው Aካል በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት Eግዱ Aይነሳም ማለቱ በAግባቡ Aይደለም በማለት Eግዱ Eንዲነሳ ሲል ውሣኔ ሰጥቷል።
የፍ/ጠ/ፍ/ቤትም ይግባኝ ቀርቦለት ይግባኙን መሰረት በማድረግ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የፍ/ከ/ፍ/ቤቱን ውሣኔ Aጽንቶታል።
Aመልካች ለዚህ ፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት Aቤቱታ ያቀረቡትም የፍ/ከ/ፍ/ቤትና የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጡትን ውሣኔ በመቃወም ነው። ቅሬታውም Aቶ ኤልያስ ደምሴ ገንዘቡን ከንብረታቸው Eንዲከፍሉኝ ተወስኖልኛል። Aቶ ተሾመ ካሣዬ ቤቱን ገዝቸዋለሁ ቢሉም የሽያጭ ውሉ ስልጣን ባለው Aካል Aልተመዘገበም። ከፍተኛ ፍ/ቤት የሽያጭ ውሉን ለማስመዝገብ ጥያቄ መቼ 174 175 Eንዳቀረበ ሳያጣራ ተመዝግቧል በማለት Eግዱን Á’d¨< በAግባቡ Aይደለም።
ጠ/ፍ/ቤቱም የከ/ፍ/ቤቱን ውሣኔ ማጽናቱ ተገቢ Aልነበረም። ሁለቱም ፍርድ ቤቶች በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2878 የተደነገገውን ሳያገናዝቡ የሰጡዋቸው ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው eKJ’< ተሽረው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ላፀናልኝ ይገባል የሚል ነው።
ተጠሪው ደግሞ በሰጡት መልስ የሽያጭ ውሉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2878 መሰረት Eስከተመዘገበ É[e ስም ያለመዛወር የሚያመጣው ለውጥ የለም። የሽያጭ ውሉ ከመዝገቡ ጋር ተያይ³DM። ቀደም ብሎ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ/ 16109 ሚያዝያ 12 ቀን 99 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ የሽያጭ ውK< ከመዝገቡ ጋር መያያዝ በቂ ነው ተብሐል። በመ/ቁ/ 21448 የተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1123 ለዚህ ጉዳይ Aግባብነት የለውም። የEግድ ትEዛዝ የተሰጠው የሽያጭ ውሉ ከተያያዘ በኋላ ነው። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለበት በመሆኑ ላፀናልኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በቤቱ ላይ የሰጠው የEግድ ትEዛዝ በተጠሪው Aመልካችነት ላነሳ ይችላል ወይስ Aይችልም?
No topics extracted.
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ኮልፍ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀበል 06 የሚገኘው የቤት ቁጥር Aዲስ የካርታ ቁጥሩ ኮ/ቁ/ 09/3/መ/00/180/ 6904/00 በሆነው ቤት ላይ የEግድ ትEዛዝ የሰጠው መጋቢት 29 ቀን 98 ዓ.ም ነው። ይህ የEግድ ትEዛዝ ደግሞ በኮልፍ ቀራንዮ መሬት Aስተዳደር ባለሥልጣን ተመዝግቧል። Eግዱ በተመዘገበበት ጊዜም ቤቱ በAቶ ኤልያስ ደምሴ ስም የተመዘገበ መሆኑን “ የሽያጭ ውK< ከማህደሩ ጋር የተያያዘ ቢሆንም የስም ማዞሩ ጉዳይ በሂደት ላይ ያለ መሆኑን የመሬት Aስተዳደር ባለስልጣኑ ገልጾAል።
ነገር ግን የመሬት Aስተዳደር ባለስልጣኑ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል ያለው የሽያጭ ውል መቼ ከመዝገቡ ጋር Eንደተያያዘ Aልገለፀም።
በማስረጃነት ቀርቦ ከፍ/ቤቱ መዝገብ ጋር ተያይዞ የሚገኘው” የሽያጭ ውል ጽሑፍም ስንመለከተው Eላዩ ላይ ክብ የውሎችና የክብር መዝገብ ማስረጃ ማህተም ከማረፉ በስተቀር ይህ ማህተም መቼ የውል ጽሑñ ላይ Eንደተደረገ Aይታወቅም። በሽያጭ ውሉ ጽሑፍ ላይም ይሁን ጀርባ ያረፈ Aራት ማEዘን ማህተም የለም። የሽያጭ ውሉ uክብር መዝገብ ውስጥ የተያያዘው መቼ Eንደሆነ ካልታወቀ ደግሞ የተያያዘው የEግድ ትEዛ²< ከመሰጠቱ በፊት ነው ለማለት ያስቸግራል።
በልላ በኩል ደግሞ የሽያጭ ውሉ የተያያዘው የEግድ ትEዛዙ ከመሰጠቱ በፊት ነው ከተባለም በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2878 የAንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ንብረቱ ባለበት Aገር በሚገኘው በማይንቀሳቀስ ሃብት መዝገብ ካልተፃፈ በቀር በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ውጤትን ላያስገኝ Aይችልም ተብሎ ከተደነገገው ጋር በማዛመድ ስንመለከተው የሽያጭ ውሉ በማይንቀሳቀስ ሃብት መዝገብ ከመፃፉ በፊት የሽያጭ ውሉ መኖር ያለመኖሩ Aስቀድሞ መረጋገጥ ይኖርበታል። ይህ በተጠሪውና በAቶ ኤልያስ ደምሴ መካከል ተደረገ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል ግን በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1723 በፍ/ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው Aካል ፊት የተሰራ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም።
በመሆኑም ተደረገ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል ጽሑፍ uማይንቀሳቀስ ሃብት መዝገብ የተፃፈው ሳይረጋገጥ በመሆኑ ውሉ በመልካች ላይ የሚያመጣው ለውጥ ወይም የሚያስገኘው ውጤት የለም።
በተጠሪው በመከራከርያነት የተጠቀሰው ቀደም ብሎ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ/ 16109 የሰጠውን ውሣኔ ስንመለከተውም ፍ/ቤቱ የውሉ ከማይንቀሳቀስ ሃብት መዝገብ ጋር መያያዝ በቂ ነው ያለው የሽያጭ ውሉ ግንቦት 9 ቀን 1987 ዓ.ም በውልና ማስረጃ ምዝገባ መምርያ Aዋዋይነት የተደረገ መሆኑን 176 177 በመመልከቱ ምክንያት በመሆኑ ጉዳዩ በዚI መዝገብ ከሚታየው ጉዳይ ጋር ተመሳሳይ ባለመሆኑ የተጠሪው ክርክር Aግባብነት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም።
የመሬት Aስተዳደር ባለስልጣን የሽያጭ ውሉን ለማዋዋል ስልጣን ባለው Aካል ተረጋግጦ የቀረበለትን የሽያጭ ውል ተቀብሎ ከማይንቀሳቀስ ሃብት መዝገብ ላይ ከማያያዝና ከመፃፍ በስተቀር የማዋዋልና የማረጋገጥ ስልጣን ስለልለው የፍድራል ከፍ/ፍ/ቤትና የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የመሬት Aስተዳደሩ ባለስልጣን የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሽያጭ ውል የመመዝገብ ስልጣን Aለው፤ የሽያጭ ውሉ በዚሁ ሁኔታ የተመዘገበ በመሆኑ Eግዱ መነሳት Aለበት በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው ነው።
በመሆኑም Aመልካች ቀደም ብለው ክርክር ባስነሰው ቤት ላይ የEግድ ትEዛዝ ያሰጡት ከAቶ ኤልያስ ደምሴ የሚፈልጉትን ገንዘብ ለማስመለስ በመሆኑና በዚሁ መሰረትም ያስወሰኑ ስለሆነ ቤቱን በሐራጅ በማሸጥ ገንዘባቸውን የማስመለስ መብታቸው የተጠበቀ ነው። ይህ መብታቸው ቀሪ ላሆን ይችል የነበረው የቤቱ ባለቤትነት ከAቶ ኤልያስ ደምሴ ወደ ተጠሪ ዞሮ ቢገኝ ነው። ይሁን Eንጂ ቤቱ በAቶ ኤልያስ ደምሴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በመሆኑና በማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ የተያያዘው የሽያጭ ውልም ስልጣን ባለው Aካል ያልተረጋገጠ በመሆኑ ቀደም ብሎ የተሰጠው Eግድ ተነስቶ የባለቤትነቱ ስም ወደ ተጠሪው Eንዲዛወር ማድረግ ተጠሪው ያለAግባብ Eንዲጠቀሙ Aመልካች ደግሞ በፍርድ ያገኙትን መብት ”Ç=ÁÖ< ¾T>ÁÅ`Ó በመሆኑ Eግዱ በተጠሪው Aመልካችነት የሚነሳበት የሕግ ምክንያት የለም። በዚሁ ምክንያትም የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና ላሻር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 29717 ሐምል 17 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 50420 መጋቢት 13 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለv†¨< በመሆ“†¨< በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተi[ªM::
በኮልፍ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀበል 06 የሚገኘው በካርታ ቁጥር ኮ/ቁ/09/3/ መ/00/180/6904/00 የተመዘገበው ቤት ላይ በመ/ቁ/ 32777 ፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው Eግድ በተጠሪው Aመልካችነት ላነሳ የሚችልበት ምክንያት የለም። Eግዱ ላነሳ የሚችለው Aመልካች ከAቶ ኤልያስ ደምሴ Eንዲከፈላቸው የተወሰነላቸው ብር 18,400 c=ከፈላቸው ወይም ደግሞ ቤቱን በሐራጅ ለመሸጥ Eንዲቻል Aመልካች Eግዱ Eንዲነሳ ሲጠይቁ ነው በማለት ተወስኗል። በዚሁ መሰረትም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 32777 ጥቅምት 22 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን Eንዲችሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ዙ/ ¾ Ö u q ‹ ð n É የሰበር መ/ ሐምል 29 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ሐጐስ ወልዱ ወ/ት ሂሩት መለሰ Aቶ መድህን ኪሮስ Aቶ በላቸው Aንሺሶ Aመልካች፡- ሜድሮክ Iትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር Aልቀረበም ተጠሪ፡- Aቶ በዛወርቅ ሺመላሽ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዳዩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የክርክሩን Aመጣጥ በተመለከተ የAሁን ተጠሪ የሥር ከሣሽ መጋቢት 18 ቀን 1993 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ ከግንቦት 24 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ Eስከ ጥቅምት 20 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ በሕግ Aገልግሎት ሃላፊነት ተቀጥሬ ያገለገልኩ ሲሆን በፍደራል ፍ/ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ Aሰጣጥን ምዝገባ Aዋጅ ቁጥር 199/92 መሰረት ለተከሳሹ Aገልግሎት ለመስጠት በመቸገሬ ምክንያት ተከሣሹ ሁኔታውን Eንዲያሻሽል ብጠይቅ ተከሣሹ የሥራ ውልን Aቋርጧል። የተከሳሹ ሥራ Aስኪያጅ በብር 5,000 /Aምስት ሺህ ብር/ ደመወዝና የመኪና Aበል (በተጨማሪነት) የቀጠሩኝ ቢሆንም ይህ ክፍያ ሣይከፈለኝ የቆየ በመሆኑ የ43 ወራት የAገልግሎት ቀሪ ክፍያ ብር 76,411፣ የመኪና ማካካሻ ክፍያ ብር 43,000፣ የትራንስፖርት Aበል ብር 21,500፣ E.ኤ.A. ህዳር 23 ቀን 1999 በተፃፈ ደብዳቤ የታመነ ብር 1,349.74፣ ዳላስ ሄጄ የተመለስኩበት የውሎ Aበል ብር 5,049፣ የAውሮፕላን ትኬት ክፍያ ብር 2,607፣ የ3 ወር ያልተከፈለ Aበል ብር 19,500፣ የ3 ዓመት ወለድ ብር 30,495፣ በድምሩ ብር 199,911.74 (Aንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ Aስራ Aንድ ብር ከሰባ Aራት ሳንቲም) Eንዲከፈለኝ ወደ ሥራም Eንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ክስ Aቅርበዋል።
ተከሳሽም ጥቅምት 14 ቀን 1994 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ የከሣሽ የክፍያ ጥያቄዎች በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ የታገዱ ናቸው፤ ላከፈላቸው የሚገባ ደመወዝ ላይ የተደረገ ስምምነት የለም፣ ደመወዛቸው ሲከፈላቸው Eንደቆየው ነው፣ ፈርመው ሲቀበሉት በነበረው ገንዘብ ላይ ክርክር መፍጠራቸው Aግባብ Aይደለም፤
ዳላስ ሄደው የተመለሱበት የውሎ Aበል ተከፍሐቸዋል፤ ብር 1,349.74 ላከፈላቸው Aይገባም፤ የAውሮፕላን ትኬቱን በተመለከተ ብር 2,607 ለመክፈል ፈቃደኛ ሆነን Eያለ ከሣሽ ጥያቄ ባለማቅረባቸው Eድሉ Aልፏቸዋል፤ ከሣሽ የሶስት ወር ደመወዝና Aበል ያሉት የመቼ Eንደሆነ ያልተገለፀ ከመሆኑም ልላ ከሣሽ Eስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ያለ የሚገባቸው ደመወዝና Aበል ተከፍሎAቸዋል፤ ከሣሽ የተሰናበቱት በAግባቡ ነው፤
የሚከፈላቸው ወለድም የለም በማለት ከተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ከሣሽ ያቀረቡት የAውሮፕላን ትኬት፣ የውሎ Aበልና የብር 1,349.74 ክፍያ መከፈል ከነበረበት ጊዜ Aንስቶ ክስ Eስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ሲሰላ Aንድ Aመት ያለፈበት Eንደመሆኑ ክፍያው በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ የታገደ ነው፤ የደመወዝ ጥያቄውም Eንደዚሁ ክስ ከቀረበበት ጊዜ Aንድ Aመት ወደኋላ በመቁጠር ሲታይ ጊዜ ያለፈበት በመሆኑ በAዋጅ Aንቀጽ 162(1) መሰረት በይርጋ ቀሪ መሆን የሚገባው ነው፤ በልላ በኩል ተከሣሽ ከሣሽን ከሥራ ያሰናበተበት ምክንያት Aቶ ዳንኤል ተገኑ ከፃፉት ሪፖርት በመነሳት Eንጂ ልላ ተከሣሽ Aልሰራም ያሉ ስለመሆናቸው የሚያሳይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ሥንብቱ ሕጋዊ Aይደለም። በመሆኑም የተከሣሽ ወደ ሥራ መመለስ ለሥራ ግንኙነቱ የማይመች ላሆን ስለሚችል ከሣሽ ለከሣሽ የሥራ ስንብት፣ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያና የስድስት ወር የካሣ ክፍያ በመክፈል ከሣሽን Eንዲያሰናብት፤ ከይርጋ የተረፈውን ክፍያ በተመለከተ የከሣሽ የደመወዝ ብር 5,000 ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩና ከሣሽ የጠየቁት የሶስት ወር ክፍያም የመቼ Eንደሆነ ተብራርቶ ስላልቀረበ የሶስት ወር ደመወዝ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም፤ ኃላፊዎቹ በመጻጻፍ ሒደት ላይ ስለነበሩ የከሣሽ ደመወዝ ብር 5,000 Eንዲሆንላቸው ተወስኖ ላሆን Eንደሚቻል ተገንዝበናል። ልዩነቱን የይርጋ ጊዜ ከሚጀምርበት መጋቢት 21 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ Eስከተሰናበቱበት ጥቅምት 20 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ ያለውን የስምንት ወር ልዩነት ተከሳሽ ለከሳሽ Eንዲከፍል በማለት ወስኗል።
የAሁን Aመልካች የፍ/መ/ደፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርቧል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በድርድር ላይ ያለ ደመወዝ Eንደተወሰነ ደመወዝ ተደርጐ ላወሰድ Aይችልም፣ የሰራተኛው ደመወዝ ብር 4,524 ነው። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት የሰራተኛው ደመወዝ ብር 5,000 ነው ያለው በAግባቡ Aይደለም።
ሰራተኛው Eስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ደመወዛቸውን ሲያገኙ የቆዩ በመሆናቸው የስምንት ወር የደመወዝ ልዩነት ይከፈላቸው ተብሎ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔም ተቀባይነት የለውም። የስንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያ ለሰራተኛው Eንዲከፈላቸው የተባለውም በAግባቡ Aይደለም። ስንብቱ ሕገወጥ በመሆኑ ድርጅቱ የስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ለሰራተኛው ላከፍላቸው Eንደሚገባ ግልጽ ቢሆንም ድርጅቱ ይህን ክፍያ መፈፀሙን በስንብት ደብዳቤው ስለገለፀና ሰራተኛውም ይህ ክፍያ Aልተከፈለኝም ብለው ስላልተከራከሩ ድጋሚ ላከፈላቸው Aይገባም በማለት ድርጅቱ በብር 4,524 የደመወዝ ሒሳብ Aስልቶ ካሣ ለሰራተኛው ይክፈል በማለት በፍ/መ/ደ/ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ውሳኔ በመቀጠልም Aመልካች የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለዚህ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት Aቤቱታውን Aቅርቧል። ቅሬታውም ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት የተቀጠሩበትን ሥራ Aልሰራም በማለታቸው ነው።
ተጠሪው ሥራውን Aልሰራም ያሉትም ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ ወይም ደግሞ የኩባንያው ሸሪክ (ባለAክሲዮን) Aድርጐ ካላስመዘገበኝ ሥራ መስራት Aልችልም። ከሰራሁ በወንጀል የሚያስጠይቀኝ በመሆኑ ሁኔታው ላመቻችልኝ ይገባል በማለት ነው። Eንዲህ የሚል ሐሳብ ስለማቅረባቸው ራሳቸው የፃፋት ደብዳቤ ያስረዳል። Aቶ ዳንኤል ተገኑ የፃፉት ደብዳቤም ተጠሪው Aልሰራም ማለታቸውን ያረጋግጣል። Eንደዚሁም Aቶ ዳንኤል ተገኑ በመከላከያ ምስክርነት ቆጥረናቸዋል። የሥር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የወሰኑትም የቀረቡትን ማስረጃዎችና የተደረገውን ክርክር ባለመገንዘብና በመከላከያ ምስክርነት የቆጠርናቸውን Aቶ ዳንኤል ተገኑን ምስክርነት ባለመሰማት ነው። በመሆኑም ተጠሪው የተቀጠሩበትን ሥራ Aልሰራም በማለታቸው በAዋጅ ቁ. 42/85 Aንቀጽ 26(1) Eና 28 መሰረት የተሰናበቱ ናቸው። ስንብቱ ሕጋዊ ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የAዋጁን ድንጋጌ የሚፃረር በመሆኑ ውሳኔቸው መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበትና ላታረም የሚገባው ነው የሚል ነው።
ተጠሪው ደግሞ በሰጡት መልስ የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ በመሆኑ Aመልካች ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ ነበረበት። ይህን Aልፎ ለሰበር ችሎት Aቤቱታ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም። ድርጅቱ የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ ሥራ Aልሰራም Aላልኩም ባለAክሲዮን Aድርጐ ካላስመዘገበኝ የምክር Aገልግሎት Aልሰጥምም Aላልኩም። Aመልካች Aልተሰማልኝም ያሉት ምስክር የሚያውቀውን በጽሑፍ ስለገለፀ ለምን ቀርቦ Aልመሰከረም Aይባልም።
ተፈጠረ ላልኩት ችግር መፍትሄ ሳይሰጥበት ድርጅቱ Eኔን ማሰናበቱ ተገቢ Aይደለም። የፍ/ከ/ፍ/ቤት ድርጅቱ ለችግሩ መፍትሄ ሳይፈለግ የተወሰደው የሥራ ስንብት Eርምጃ ሕገወጥ ነው በማለት የወሰነው በAግባቡ ነው።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለበትና በAግባቡ የተሰጠ በመሆኑ ላፀናልኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ግራ ቀኙ ያደረጉት የቃል ክርክርም በመቅረፀ ድምፅ ከተሞላው ካሴት ወደ ጽሑፍ ተመልሶ ጽሑፉ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። Aመልካች ያቀረበው የመልስ መልስም Eንደዚሁ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
በበኩላችን ደግሞ Aመልካች ኩባንያ ተጠሪውን ያሰናበታቸው በሕገወጥ መንገድ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ተጠሪው ሐምል 7 ቀን 1992 ዓ.ም ለAቶ ንጉሴ Aበራ በፃፉት ደብዳቤ Aዋጅ ቁጥር 199/92 በAንቀጽ 31 የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት የሚፈልግ ሰው ከፍትህ ሚኒሰቴር የጥብቅና ፈቃድ ማግኘት Eንዳለበት ደንግጓል፣ Eንደዚሁም የግል ድርጅት ወይም ኩባንያ ኃላፊ ወይም ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ የሆኑ ሰዎች የጥብቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት Eንደሚችሉ በAዋጁ Aንቀጽ 31(1) ሥር ተደንግጓል፣ Eኔ Eነዚህን መስፈርቶች ስለማላሟላ የጥብቅና Aገልግሎት ብሰጥ በሕጉ Eቀጣለሁ፣ የድርጅቱን ወይም የኩባንያውን ጥቅም ለማስጠበቅ በፍርድ ቤት መከራከር ሕጋዊ የውክልና ሥልጣን የተሰጠው ሰው፣ የኩባንያ ኃላፊ፣ ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ መሆንን ይጠይቃል።
ፍ/ሚኒሰቴር የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጠው የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ላልሆነ ሰው Eንጂ ለሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ Aይደለም። በመሆኑም መመርያችሁን Eጠብቃለሁ ማለታቸውን ተመልክተናል። የዚህ ደብዳቤ ይዘት ደግሞ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሆኜ መስራት ብቀጥል የጥብቅና ፈቃድ ስለማይሰጠኝ የጥብቅና ፈቃድ ማግኘት Aልችልም። ያለ የጥብቅና ፈቃድ ለመስራት የሚቻልበት ልላው Aማራጭ ደግሞ የኩባንያው ሐላፊ ባለAክሲዮን ሸሪክ በመሆን ቢሆንም Eኔ ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ ወይም ደግሞ የኩባንያው ኃላፊ ባለመሆኔ የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት Aልችልም።
ፈቃድ ሳይወጣልኝ ወይም ባለAክሲዮን ሆኜ ሳልመዘገብ የሕግ Aገልግሎት ለኩባንያው ብሰጥ በወንጀል የምቀጣ በመሆኑ መፍትሄ Eስከሚፈለግልኝ ጊዜ ድረስ የተቀጠርኩበትን ሥራ Aላከናውንም የሚል ነው።
ተጠሪው መጋቢት 18 ቀን 1993 ዓ.ም ባዘጋጁት የክስ ማመልከቻና ታህሳስ 17 ቀን 94 ዓ.ም ባቀረቡት የመልስ መልስ የጥብቅና Aገልግሎት ለመስጠት በቅድሚያ የጥብቅና ፈቃድ Eንደሚያሻ፣ ፈቃድ ሳይኖር Aገልግሎት መስጠት በወንጀል Eንደሚያስጠይቅ፣ ለግል ኩባንያም ቢሆን ያለ ጥብቅና ፈቃድ Aገልግሎት መስጠት የሚችሉት የድርጅት ሃላፊ ወይም ሸሪክ መሆን Eንደሚያስፈልግ የጠበቆች Aዋጅ ይደነግጋል፤ ላይሰንስ (የጥብቅና ፈቃድ) የማገኝበት መንገድ ሳይቀየስና ፈቃድ ሳይኖረኝ ብሰራ በወንጀል Eንደምቀጣ Eየታወቀ Aቶ ዳንኤል ተገኑ ሆራ ሆቴል በሚመለከት የሕግ Aገልግሎት Eንድሰጥ ማዘዛቸው Eኔን ለማስወንጀል ወይም ደግሞ የተመደበበትን ሥራ Aልሰራም ብሐል በማለት Eርምጃ ለማስወሰድ የታሰበ ነበር በማለት ያቀረቡት ክርክርም ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ ወይም ደግሞ የባለAክሱዮንነት ምዝገባ ካላደረገልኝ ሥራውን Aልሰራም ማለታቸውንና ሆራ ሆቴልን የተመለከተውን ሥራም ሳያከናውኑ መቅረታቸውን በማመን የተከራከሩ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው።
Aቶ ዳንኤል ተገኑ ሰኔ 7 ቀን 1993 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ Aቶ በዛወርቅ ሽመላሽ የሆራ ሆቴል ኮንትራትን በተመለከተ የሕግ Aስተያየት Eንዲሰጡ Eንደነግራቸው በተሰጠኝ መመሪያ መሰረት ብነግራቸውም Aዲሱ ሕግ Aይፈቅድልኝም በማለት የሕግ Aስተያየታቸውን ለመሰጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል በማለት የሰጡትን መግለጫ ተጠሪው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስና የመልስ መልስ ከጠቀሷቸው የመከራከሪያ ነጥቦች ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው ተጠሪው በኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ የማገኝበት ሁኔታ ካልተመቻቸልኝ Eና ፈቃዱን ካልያዝኩኝ በስተቀር ለድርጅቱ የሕግ Aገልግሎት Aልሰጥም በሚል Aቋማቸው መሰረት ሆራ ሆቴልን የሚመለከት የሕግ Aስተያየት ሳይሰጡ የቀሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሆኖ Aግኝተነዋል።
Eንደዚሁም ተጠሪው ነሐሴ 9 ቀን 1992 ዓ.ም ለAቶ ንጉሴ በፃፉት ደብዳቤ ሆራ ሆቴልን የሚመለከት የሕግ Aስተያየት Eንድሰጥ በAቶ Aልፍሬድ መመሪያ መሰጠቱን Aቶ ዳንኤል ነግሮኛል Eንዲህ ዓይነት የሕግ Aስተያየት (ምክር) መስጠት በAዲሱ Aዋጅ ላያስጠይቅ ይችላል Eያልኩኝ Eየወተወትኩኝ Eንደዚህ ዓይነት መመሪያ ለምን Eንደተሰጠ Aልገባኝም፣ Aሁንም ቢሆን በቅድሚያ የጥብቅና ፈቃድ የማገኝበት መንገድ Eንዲቀየስ Aሳስባለሁ ማለታቸው ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ስላላስወጣልኝ ሥራውን Aላከናውንም በማለት የሕግ Aገልግሎት ሳይሰጡ መቅረታቸውንና ለወደፊቱም ድርጅቱ ፈቃዱን ካላስወጣላቸው በስተቀር የተመደቡበትን የሕግ Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Eንደማያከናውኑ የሚያስረዳ ነው።
በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪው በስር ፍ/ቤቶች ባደረኩት ክርክር Aመልካች /የሥር ተከሳሽ/ ኩባንያው ለቀጠራቸው የሕግ ባለሞያዎች የጥብቅና ፈቃድ የማስወጣት ግድታ ያለበት መሆኑንና ይህን ግድታውን መወጣት ሲገባው ሳይወጣ የቀረ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ Aላቀረቡም።
ኩባንያው ይህ ዓይነቱ ግድታ ያለበት መሆኑን የሚደነግግ ሕግ Aለ ብለው Aልጠቀሱም Aልተከራከሩምም። ኩባንያው ሰዎችን በባለAክሲዮንነት የሚመዘግብ ከሆነም የኩባንያውን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በማድረግ ከሚጠይቁ በስተቀር ተጠሪው የሕግ Aገልግሎት Eንዲሰጡ ተብሎ በባለAክሱዮንነት ወይም በሸሪክነት ላመዘግባቸው የሚገደድበት ምክንያት የለም። ተጠሪም በፃፉት ደብዳቤ በምሳልነት ጠቀሱት Eንጂ ኩባንያው በባለAክሲዮንነት ወይም በሸሪክነት Eንዲመዘግባቸው በግልጽ የጠየቁ ባለመሆኑ ይህን ነጥብ Aመልካች በክርክሩ ውስጥ ማካተቱ ተገቢ Aይደለም።
186 187 ከዚህ በላይ በተዘረዘረው ሁኔታ ተጠሪው የጥብቅና ፈቃድ በኩባንያው Aማካኝነት ካልወጣልኝ በስተቀር የተመደብኩበትን የሕግ Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም በማለት ሥራ ማቆማቸው ራሳቸው ባደረጉት ክርክር ያመኑበትና ከግራ ቀኙ በቀረቡት የጽሑፍ ማስረጃዎች የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪው የተቀጠርኩበትን ሥራ Aልሰራም Aላልኩም በማለት ለሰበር Aቤቱታው በሰጡት መልስና በቃልም ባደረጉት ክርክር መግለፃቸው ተቀባይነት የለውም።
ልላው ቁምነገር ደግሞ ተጠሪው ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ የሕግ Aገልግሎት ሥራ Aልሰራም፣ ከሰራሁኝ በወንጀል Eቀጣለሁ የሚሉት ቀደም ብለው የወሰዱትን የጥብቅና ፈቃድ ሳይመልሱና የሕግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችም በውክልና የሕግ ባለሞያዎችን Eንዳያሰሩ በAዋጅ ባልተከለከለበት ጊዜ ነው። የጥብቅና ፈቃድ Eያላቸው በውክልናም መሥራት Eየቻሉ ለኩባንያው የሕግ Aገልግሎት ብሰጥ በወንጀል Eቀጣለሁ ማለታቸውም ግልጽ Aይደለም።
Aመልካች ለቀጠራቸው የሕግ ባለሞያዎች ከፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፈቃድ የማስወጣት ግድታ ሳይኖርበትና ተጠሪው ለAመልካች የጥብቅና ማለትም የሕግ Aገልግሎት ቢሰጡ በወንጀል የሚቀጡበት የሕግ ምከንያት በልለበት ጊዜ ተጠሪው ድርጅቱ የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ በስተቀር የተቀጠርኩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም የሚሉበትና Aመልካች ደግሞ ተጠሪው ምንም ሥራ ሳይሰሩ ሰራተኛዬ ናቸው በማለት ደሞዝ Eየከፈለ የሚቆይበት ምከንያት የለም።
ተጠሪው በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 13(2) ሥር የተደነገገው የAሰሪውን ትEዛዝ የመቀበል ግድታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ Aመልካች በAዋጁ Aንቀጽ 26(1) መሰረት ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ቅጥር ውሉን ለማቋረጥ ይችላል። Aመልካች የሥራ ውሉን በAዋጁ Aንቀጽ 26 Eና 28 መሰረት ማቋረጡና ተጠሪውን ማሰናበቱም በAግባቡ ነው።
በመሆኑም Aመልካች ተጠሪውን ከሥራ ያሰናበታቸውን የተቀጠሩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተጨባጭ የሥራ ትEዛዝን Aልቀበልም በማለታቸው ምክንያት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠና ተጠሪም ያመኑበት ሆኖ Eያለ የሥር ፍርድ ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪው ካሣ ይከፈል በማለት ውሳኔ መስጠታቸው Aግባብ ሆኖ Aላገኘነውም። ፍርድ ቤቶቹ የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረበላቸውን ማስረጃ በሚመለከት ውሳኔ መስጠት ሲገባቸው የቀረበላቸው ማስረጃ የሚያስረዳውን ቁምነገር በመተውና ተጠሪው በክርክራቸው ያመኑትን ከግምት ውሰጥ ባለማስገባት የተጠሪውን የግል ማህደር በማስቀረብ ተጠሪው የተቀጠሩበትን ሥራ ለማከናወን ፈቃደኛ Aለመሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከማሕደራቸው ስላላገኘን ለመስራት ፈቃደኛ ስላለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ የለም፣ ስንብቱ ሕገወጥ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪው ካሣ ይከፈል በማለት የሰጡት ውሳኔም የAዋጅ ቀጥር 42/85 ዓላማን የሳተና ለተጠሪው የማይገባቸውን መብት ያጐናፀፈ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/08459 ህዳር 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 43679 ሚያዝያ 17 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪው ከሥራ የተሰናበቱት ድርጅቱ /ኩባንያው/ የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ በስተቀር የተቀጠርኩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም በማለታቸውና በተጨባጭም ሆራ 188 189 ሆቴልን የተመለከተ የሕግ Aስተያየት Aልሰጥም በማለታቸው ምክንያት መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ስንብቱ ሕጋዊ ነው።
የሥራ ስንብት ክፍያ ላከፈላቸው Aይገባም በማለት ወስነናል።
ፍፃፍ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ፀ/መ ¨< ` e 190 191
ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ ታፈሰ ይርጋ Aቶ መድሕን ኪሮስ Aቶ ዓላ መሐመድ Aቶ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ Aዳነች ወርዶፋ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- Eነ ወ/ሮ Aስናቀች ወርዶፋ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን Aመጣጡም የAሁንዋ Aመልካች ህዳር 10 ቀን 97 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ የውርስ Aጣሪው በ16/2/97 ዓ.ም ያቀረቡት ሪፖርት በAግባቡ የቀረበ Aይደለም።
Aጣሪው ላጸድቅ የማይገባውን የስጦታ ውል መነሻ በማድረግ ውሳኔ ሰጥተዋል። በውርስ Eዳነት መመዝገብ የማይገባውን Eዳ መዝግበዋል።
ያቀረብኳቸውን ማስረጃዎች በAግባቡ Aልመረመረም። ወራሾች ሳንስማማበት የውርስ ንብረት ለወራሾች Eንዲከፋፈል ወስነዋል። በመሆኑም የውርስ Aጣሪው ሪፖርት መጽደቅ የለበትም በማለት Aመልክተዋል።
ፍ/ቤቱም የውርስ Aጣሪው የሟች የኑዛዜና ያለኑዛዜ ወራሾች Eነማን Eንደሆኑ፣ የሟች የውርስ ሃብት ምን Eንደሆነ ከውርሱ ሐብት ላይ ላከፈል የሚገባውን Eዳ ምንነት Eና በኑዛዜ የተሰጠ ስጦታ ለተቀባዩ መክፈልን በተመለከተ የግራ ቀኙን Aቤቱታና ማስረጃ መርምረው ያቀረቡት ሪፖርት የሚነቀፍበት ምክንያት የለም። Aመልካች Aለኝ የሚሉት መብት ካላቸው ዳኝነት ከፍለው በክስ ከሚጠይቁ በስተቀር የውርስ Aጣሪውን ሪፖርት ባለማጽደቅ በዚህ መዝገብ ላጠይቁ የሚችሉበት ሁኔታ የለም በማለት Aቤቱታውን ባለመቀበል ሪፖርቱን Aጽድቆታል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ከAመልካች የቀረበለትን ይግባኝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል Aመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት Aቤቱታ ያቀረቡትም የስር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ትEዛዝ በመቃወም ነው። በAቤቱታው ውስጥ የተጠቀሱት ቅሬታዎችም የውርስ Aጣሪው የሟችን ሃብት በAግባቡ Aላጣሩም። በሕግ መፍረስ የሚገባውን የስጦታ ውል Aጽድቀዋል። የቆጠርኳቸውን ማስረጃዎች ባለመስማት መብቴን Aጣብበውብኛል። ያለAግባብ የውርስ ንብረቶችን ወራሾች Eንድንከፋፈል ወስነዋል። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የውርስ Aጣሪው ያቀረቡትን ሪፖርት Eንዳያጸድቅ፣ የውርስ ማጣራቱ ሥራ Eንደገና Eንዲካሄድ Eንዲያደርግልኝ ያቀረብኩትን ጥያቄ ባለመቀበል ሪፖርቱን ማጽደቁ በAግባቡ Aይደለም።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ትEዛዝ መሰረትዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ትEዛዙ ላሻርልኝ ይገባል የሚሉ ናቸው።
1ኛ ተጠሪ ሐምል 30 ቀን 99 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ የውርስ Aጣሪው በኑዛዜ ስጦታው ላይ ያሉትን ምስክሮች Aስቀርበው በመስማት የኑዛዜ ስጦታው የህግ ስህተት የልለበት መሆኑን Aጣርተው የAሁንዋ Aመልካችንና ልሎቹን ወራሾች በዝርዝር መዝግበው ባደረጉት ማጣራት መሰረት ሪፖርታቸውን ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ማቅረባቸው በAግባቡ ነው። የሥር ፍ/ቤቶቹ ሪፖርቱን ለማጽደቅ የሰጡት ትEዛዝም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም። በመሆኑም ትEዛዙ ላጸድቅልን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ ደግሞ ሐምል 30 ቀን 99 ዓ.ም ጽፈው በሰጡት መልስ ውርስ Aጣሪው የውርስ ንብረቱን በAግባቡ Aላጣሩም የ1ኛ ተጠሪን ቤት በውርስ ንብረት ውስጥ ማካተት ሲኖርባቸው በስጦታ ያገኙት ነው በማለት መወሰናቸው ተቀባይነት የለውም። Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፊት 192 193