No summary available.
የካቲት 4 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ መሐመድ Iብራሂም ቀረቡ።
ተጠሪ፡- Aቶ ታይደር ማች - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች በAስረጂነት ያቀረቡት ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረት በውል Aዋዋይ ፊት ያልተደረገ ስለሆነ ክስ የቀረበበትን ቤት ለተጠሪ ላያስረክቡ ይገባል በማለት የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመስጠታቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ የAሁኑ ተጠሪ በመልካች ላይ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ በጋምቤላ ከተማ ወረዳ 1 ቀበል A3 ክልል በስሜ ተመዝግቦ ከሚገኘው ሁለት ክፍል ቆርቆሮ ቤት Aንዱን ተከሣሽ /የAሁን Aመልካች/ ይዞ ሰለሚገኝ Eንዲለቅ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀ ሲሆን ተከሳሽም በሰጠው መልስ ክስ የቀረበበትን ቤት ከከሣሽ ጋር በነበረን ውል መሰረት በEሱ Eጅ በነበረው ይዞታ ላይ ሁለት ክፍል ቤት ሰርቼ Aንዱን ክፍል ለEሱ ልላውን ክፍል ደግሞ ለEኔ Eንዲሆን የተስማማን ስለሆነ ክሱ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ ተከሣሽ ክስ የቀረበበት ቤት ባለመብት ስለመሆኑ ያረጋግጥልኛል በማለት ያቀረበው ውል ሥልጣን በተሰጠው መንግሥታዊ Aካል ያልፀደቀ ከመሆኑም በላይ ከሣሽ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ቤቱና ይዞታው የEራሱ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ስለሆነ ክስ የቀረበበትን ቤት ተከሣሽ ለከሣሽ ላያስረክብ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በተከሣሽ ይግባኝ ባይነት ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሣኔ Aጽንቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ በግራ ቀኙ መካከል መስከረም 1 ቀን 1988 ዓ.ም. ተደርጓል የተባለው ውል ሥልጣን ባለው Aካል የፀደቀ ስላልሆነ ግድታን ላፈጥር Aይችልም ተብሎ በሥር ፍ/ቤቶች ውሉ ተቀባይነት ሳያገኝ ¾መቅረቱ Aግባብነƒ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ በግራ ቀኙ መካከል ተደርጓል የተባለው ውል በሕግ Aግባብ የተደረገ ስላልሆነ ተቀባይነት የለውም ተብሎ በበታች ፍ/ቤቶች መወሰኑ Aግባብነት Aለውን? የሚለው በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ Aኳያ የሰበር Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከላይ Eንደተጠቀሰው የAሁን ተጠሪ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ዳኝነት የጠየቁት ተከሣሽ ቤቴን ያለAግባብ ይዞ ስለሚገኝ Eንዲመልስ ይወሰንልኝ በማለት ነው። ተከሣሽ የAሁን Aመልካችም ቤቱን ያለAግባብ Aለመያዛቸውን ገልጸው መስከረም 1 ቀን 1988 ዓ.ም. ከከሣሽ ጋር ባደረጉት ውል መነሻነት በከሳሽ ይዞታ ላይ ተከሣሽ ሁለት ክፍል ቤት Eንዲሰሩና Aንዱ ለከሳሽ ልላው ቤት ደግሞ ለተከሣሽ Eንዲሆን በተስማሙት መሰረት ሁለት ክፍል ቤቱን ሰርተው Aንዱ” ከሳሽ Eንደተረከቡና ሁለተኛውንና ክስ የቀረበበትን ቤት ደግሞ ተከሣሽ የተረከቡት መሆኑን ገልጸው ክሱ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሉ የጸና Aይደለም ያለው ውል ለማዋዋል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው Aካል ፊት የተደረገ ስላልሆነ ነው በማለት ነው።
በEርግጥ የማይንቀሳቀስ ንብረƒን በተመለከተ የሚደረጉ ውሎች ውል ለማዋዋል በሕግ ስልጣን በተሰጠው Aካል ፊት ካልተደረጉ ዋጋ ላኖራቸው Eንደማይችል ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 Eና 172A ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ ግራ ቀኙ መስከረም 1 ቀን 1988 ዓ.ም. ያደረጉት ውል ይዘት ሲታይ ውሉ በተደረገ ጊዜ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ያልነበረ በመሆኑ በዚህ ውል መነሻነት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ከAንዱ ወደ ልላው ተላልፏል የሚያስብል Aይደለም። ከስምምነታቸውም በግልጽ መገንዘብ የሚቻለው ይዞታው የከሳሽ በሆነ ቦታ ላይ ተከሣሽ ሁለት ክፍል ቤቶችን በመስራት Aንዱን ለከሳሽ በመስጠት ልላውን ቤት ደግሞ ለEራሳቸው ለመውሰድ መስማማታቸውን ስለሆነ ይህ ስምምነት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1723 É”ÒÑ@ የሚገዛ Aይሆንም። ይልቁንም የማይንቀሳቀስ ንብረት መሥራትና መሸጥን Aስመልክቶ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2876 ላይ Eንደተመለከተው Aንዱ ወገን ተዋዋይ ለልላው ወገን ተዋዋይ Aንድ ቤት Aንድ የቤት ክፍል ወይም ገና የሚሰራ ሕንፃ ለመስጠት ግድታ የሚገባበት ውል የAንድ ሕንፃ የሥራ ውል ከሚባል በስተቀር የሽያጭ ውል ላባል Eንደማይችል ስለተመለከተ የበታች ፍ/ቤቶች ጉዳዩን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 Aኳያ መመልከታቸው በAግባቡ ሆኖ Aልተገኘም።
No topics extracted.
በልላ በኩልም በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል የሕንፃ ሥራ ውል ነው ከተባለ የውሉን Aመሰራረት የሚገዛው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሥራ ውልን Aስመልክቶ በቁጥር 3A19 Eና 3A2A ላይ በተመለከተው መሰረት ሲሆን ከዚህ Aኳያም ውሉ የተለየ የAፃፃፍ ሥርዓትን ተከትሎ መደረግ የሚገባው ሳይሆን የሥራው መጀመሪያም ሆነ የዋጋ ክፍያ ውሉ በAግባቡ Eንደተመሰረተ የሚያረጋግጥ Eንደሆነ በቁጥር 3A2A/2/ ላይ የተደነገገ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል በሕግ Aግባብ የተቋቋመ ውል የለም በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የጋምቤላ ክልል ዞን ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. AA321 በጥር 15 ቀን 1999 ዓ.ም. Eንደዚሁም የጋምቤላ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. AA6A5 በሰኔ 22 ቀን 1997 ዓ.ም. uÓ^ k–< S"ŸM ¾}Å[Ñ ¨<M ¾c×D†¨< ¨<d’@−‹ ውል የለም በማለት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመv†¨< ስለሆ’< በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት }i[ªM::
በAመልካችና በተጠሪ መካከል በሕግ Aግባብ የተቋቋመ ውል ያለ ስለሆነ ውሉን Aስመልክቶ ባነሱት ክርክር ላይ የጋምቤላ ክልል ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የበኩሉን ውሣኔ Eንዲሰጥበት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 341 መሰረት ጉዳዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።