No summary available.
ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ ዓለምነሽ ወ/Aገኘሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ Aባተ ተፈሪ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በAማራ ብሄራዊ ክ/መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረብርሃን ወረዳ ከተማ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት የAፈጻጸም ክስ በደብረብረሃን ከተማ ቀበል 03 ክልል የሚገኘውና የቤ.ቁ. 167 የሆነውን ቤት የAፈጻጸም ተከሳሽ በብር 18,500 (Aስራ ስምንት ሺህ Aምስት መቶ) ሸጦልኝ ቤቱንም Aስረክቦኝ ነገር ግን ባለሐብትነቱን በስሜ ባለማዛወሩ ምክንያት በዚሁ ፍ/ቤት ክስ Aቅርቤበት ስም Eንዲያዛውር የተወሰነ ስለሆነ በዚሁ ውሳኔ መሰረት ይፈጸምልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የAፈጻጸም Aቤቱታውም ለAፈጻጸም ተከሳሽ የAሁን ተጠሪ ደርሶ በሰጡት መልስ ለAፈጻጸም ክርክሩ ምክንያት የሆነውና በሽያጭ የተላለፈው ቤት የEራሳቸው Eንዳልሆነ በመግለጽ ስም ማዛወር Aልችልም በማለት ተከራክረዋል።
የAፈጻጸም ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለትም የወረዳው ፍ/ቤት በሽያጭ ለAፈጻጸም ከሳሹ ተላልፏል የተባለው ቤት ባለሐብትነት በማን ስም ተመዝግቦ Eንደሚገኝ የሚመለከተውን Aካል ጠይቆ በAፈጻጸም ተከሳሽ ስም ሳይሆን በልላ ግለሰብ ስም ተመዝግቦ Eንደሚገኝ በመረጋገጡ የA ከሳሹ ስም ይዛወርልኝ በማለት ያቀረቡት የAፈጻጸም ማመልከቻ በAግባቡ ስላለሆነ ላፈጸም Aይችልም ብሎ በሽያጩ ጊዜ የAፈጻጸም ተከሳሹ የተቀበሉትን ብር 15,000(Aሰራ Aምስት ሺህ) ለAፈጻጸም ከሳሹ ላመልሱ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የAፈጻጸም ከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን Eስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ በፍርድ Aፈጻጸም ወቅት Aስቀድሞ የተሰጠው ውሳኔ መሻሩ ለሰበር ቀርቦ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ Aኳያ ተመርምሯል።
Aመልካች በደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ዳኝነት የጠየቁት ቤት ሸጦልኝ ርክክቡ የተከናወነ ቢሆንም ስም ያላዛወረልኝ ስለሆነ Eንዲያዛውር ይወሰንልኝ በማለት ሲሆን የወረዳው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ሻጩ ስም ላያዛውሩ ይገባል በማለት ውሳኔ መስጠቱን ከመዝገቡ ለመረዳት ችለናል።
በዚህ ውሳኔ መሰረት ይፈጸምልኝ በማለት የAፈጻጸም ከሳሽ/የAሁን Aመልካች/ የAፈጻጸም ማመልከቻ ሲያቀርቡ Aስቀድሞ ተከሳሹ ስም ላያዛውሩ ይገባል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ በይግባኝ Aስካልተሻረ ድረስ ትክክል Eንደሆነ የሚገመት በመሆኑ ይህንኑ ውሳኔ ከማስፈጸም በስተቀር ውሳኔውን በAፈጻጸም በመሻር ሻጩ የሽያጩን ገንዘብ ለገዢው ላመልስ ይገባል ተብሎ ውሳኔ መስጠቱ ሙግቱ የሚመራበትን የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የሚፃረር ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩልም ለAፈጻጸም ክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ባለቤትነቱ በAፈጻጸም ተከሳሹ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ሳይሆን በልላ 3ኛ ወገን ስም ተመዝግቦ ይግኛል ቢባል Eንኳን ዋናው ክርክር ሲደረግ ይህ 3ኛ ወገን የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.41 በሚፈቅደው መሰረት በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ መብቱን ማስጠበቅ የሚችል ከመሆኑም በላይ ዋናው ክርክር ሲደረግ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር የሚችልበት ሁኔታ ካልተፈጠረም በልለበት የተሰጠው ውሳኔ መብቱን የነካ ከሆነ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 በሚፈቅደው መሰረት በልለበት የተሰጠው ፍርድ Eንዲሰረዝለት ከሚጠይቅ በስተቀር ፍ/ቤቱ በEራሱ Aስተያየት ላመለከተው Aይችልም።
ስለሆነም ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚል 3ኛ ወገን ባልቀረበበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ በEራሱ Aስተያየት በሸያጭ ለAፈጻጸም ከሳሹ ተላልፏል የተባለው ቤት በ3ኛ ወገን ስም የተመዘገበ ስለሆነ Aፈጻጸሙ ላቀጥል Aይችልም በማለት የሸያጩ ገንዘብ ላመለስላቸው ይገባል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 05529/99 መጋቢት 12 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13181 ግንቦት 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ Eንደዚሁም የAማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 378/99 ግንቦት 30 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመv†¨< ስለሆ’< በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.348/1/ መሰረት }i[ªM::
No topics extracted.
የደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በውሳኔው መሰረት Eንዲያስፈጽም ጉዳዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻሉ
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።