No summary available.
ታህሳስ 8 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ብሕራዊ የIትዮጵያ Iንሹራንስ ኩባንያ ኮ/ል ደነቀው ተጠሪ፡- ዘላቂ ግብርና ተሐድሶ ኮሚሽን Aልቀረበም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በይግባኝ ተመልክቶ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ የAሁን ተጠሪ በAሁን Aመልካችና በሥር 1ኛ ተከሣሽ ላይ በምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ 1ኛ ተከሣሽ ልዩ ልዩ የቢሮ Eቃዎችን ለመግዛት በወጣው ጨረታ ተካፋይ በመሆን ብር 468‚54A.00 (Aራት መቶ ሺህ Aምስት መቶ Aርባ) የሚያወጡ ልዩ ልዩ Eቃዎችን በ12A ቀን ውስጥ ላያቀርብ ስምምነት ተፈራርሞና 2ኛ ተከሣሽ በቀረበው የሥራ Aፈፃፀም ዋስትና Aሸናፊ ሆኖ ሙሉ ክፍያ የተፈፀመለት ቢሆንም በውሉ መሰረት ጊዜውን ጠብቆ Aብዛኛውን Eቃ በጥራት Aሟልቶና Aስተካክሎ ያላቀረበ ስለሆነ በክስ የተጠየቀውን ተከሳሾች ባልተነጣጠለ ኃላፊነት Eንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቆ ተከሳሻች ቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ሙሉ መልስም በመስጠት ተከራክረዋል።
በተከሳሾች በኩል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የተነሳው ክርክርም በውሉ Aንቀጽ 8 መሰረት ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ላቀርብ የሚችለው ሐምል 12 ቀን 1991 ዓ.ም. በተፈረመው ውል Aንቀጽ መሰረት በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መካከል Aለመግባባት ቢከሰት ጉዳዩ ወደ Aስታራቂ ኮሚቴ ላመራ Eንደሚገባውና Aስታራቂ ኮሚቴውም ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ቅሬታ ቢኖር ሲሆን በቀጥታ ወደ ፍ/ቤት መሄድ ግን ውሉን የሚቃረን ስለሆነ ፍ/ቤት ላቀበለው Aይገባም የሚል ነው።
የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በዚህ ረገድ የቀረበውን መቃወሚያ መርምሮ ግራ ቀኙ ባቋቋሙት ውል Aንቀጽ 8 ላይ ተከሳሾች በጠቀሱት መልኩ ስምምነት የተደረገ ስለሆነና በሕግ Aግባብነት የተቋቋሙ ውሎች በተዋዋዮች ላይ Aሳሪ ስለሚሆኑ በዚህ ሁኔታ የቀረበው ክስ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 244/2/ረ/መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት ክሱን በብይን ውድቅ Aድርጓል።
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ መ/ሰጪዎች በይ/ባይ Aማካይነት በውሉ መሰረት በስምምነት ለመጨረስ በደረሰባቸው ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ መሰረት መቅረብ ሲገባቸው ያልቀረቡ በመሆኑና ይህ ከሆነ ደግሞ በውላቸው ላይ Aለመግባባት ከተከሰተ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በፊት በመከራከር ወይም በሚመርጧቸው Aስታራቂ ኮሚቴዎች ለመፍታት መስማማታቸው ብቻውን ይግባኝ ባዮችን ወደ ፍ/ቤት ጉዳዩን ከማቅረባቸው በፊት በስምምነታቸው መሰረት መጨረስ ነበረባቸው ተብሎ ጉዳያቸውን ወደ ፍ/ቤት የማቅረብ መብታቸው የሚነፈግበት ምክንያት የለም የሚል ትችት በውሣኔው ላይ Aስፍሮ የሥር ፍ/ቤት ብይን በመሻር የፍሬ ጉዳይ ክርክሩ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይታይ በማለት ጉዳዩን መልሷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበለትን Aቤቱታ መርምሮ ጉዳዩ በፍ/ቤት መታየት Aለበት ተብሎ በAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ላጣራ የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ ክርክሩ በፍ/ቤት ላታይ ይችላል? ወይንስ Aይችልም? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ ይዘን Aቤቱታውን መርምረናል።
በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው ውል ማንኛውም Aለመግባባት ቢፈጠር ጉዳዩን በስምምነት ለመፍታት ይህም ካልተቻለ በAስታራቂ Aማካኝነት ለመጨረስና ወደ ፍ/ቤት ለመሄድ የተስማሙት በEነዚህ Aማራጮች Aማካይነት ጥረት Aድርገው ያልተቻለ ከሆነ ነው። በዚህ መልኩ ስምምነት የተደረገ መሆኑም ግራ ቀኙን Aላከራከረም። ተጠሪ በዚህ የውል ቃል መሰረት ላለመግባባቱ Eልባት ለመስጠት በማሰብ ለAመልካቾች ማሳሰቢያ ቢላክላቸውም ያልቀረቡ ስለሆነ ክሱ በቀጥታ ለፍ/ቤት ላቀርብ Eንደቻለ በመጥቀስ ተከራክሯል።
ይሁንና የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ Eንዳሰፈረው በሕግ Aግባብ የተቋቋሙ ውሎች በተዋዋዮች ላይ ሕግ Eንደመሆናቸው መጠን ግራ ቀኙ በዚህ መልኩ ለመፈፀም ፈቃዳቸውን Eስከሰጡ ድረስ በዚህ የውል ቃል የማይገደዱበት ምክንያት ላኖር Aይችልም። ተጠሪ ጉዳዩን በውሉ መሰረት ለመጨረስ በማሰብ ለAመልካች ማሳሰቢያ ስለመላኩ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው ቢባል Eንኳን ማድረግ የሚጠበቅበት በውሉ መሰረት Aስታራቂ ሽማግልዎች ተሰይመው ጉዳዩ Eልባት Eንዲያገኝ ዳኝነት መጠየቅ Eንጂ በቀጥታ ክስ ማቅረቡ ውሉን የሚፃረር በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በውሉ ላይ ተመስርቶ ¡c<” በብይን ሳይቀበል መቅረቱ የሚነቀፍ Aልነበረም። ሆኖም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዚህ ዓይነት ስምምነት ቢኖርም ወደ ፍ/ቤት ከመቅረብ Aያግዳቸውም በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን መሻሩ በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው ውል Aለመግባባትን በAስታራቂ ወይም በዘመድ ዳኛ Aማካይነት ለመጨረስ ያደረጉት ስምምነት በፍ/ብሕር ሕግ ቁጥር 1765 የተፈቀደ ከመሆኑም በላይ ማንኛውም ውል uሕግ Aግባብ Eስከተቋቋመ ድረስ በተዋዋዮች ላይ ሕግ Eንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1731/1/ ላይ የተመለከተ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ ጉዳዩ በቀጥታ በፍ/ቤት መታየት ይችላል በማለት የሥር ፍ/ቤትን ብይን በመሻር የፍሬ ጉዳይ ክርክሩ Eንዲታይ ጉዳዩን ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለሱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ