No summary available.
በየካቲት 18 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ ሱልጣን Aባተማም Aላ መሐመድ Aመልካች፡- Aቶ በቀለ ደቦጭ - ጠበቃ መ/Aለቃ ሽፈራው Aመኑ ተጠሪዎች፡- 1/ ወ/ሮ Aዛለች ደሣለኝ 2/ ወ/ሮ Aምሣለ ኃይሉ 3/ ወ/ሮ Aስቴር ኃይሉ ቀረቡ 4/ Aቶ ጌድዮን ኃይሉ 5/ Aቶ ፍቅሩ ኃይሉ 6/ Aቶ በትሩ ኃይሉ 7/ ወ/ሮ መሰረት ኃይሉ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ክርክር የተጀመረው በO/ብ/ክ/መ/የጅማ ዞን ከ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪዎች ከሣሾች Aመልካቹ ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ። የAሁን ተጠሪዎች በጥቅምት 12 ቀን 1996 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ Aመልካቹ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና የተቀሩት ተጠሪዎች Aባት ከሆኑት ከሟች ግራዝማች ኃይሉ ወ/ፃድቅ በጥቅምት 22 ቀን 1986 ዓ.ም ባደጉት ውል ግምቱ 1,3AA,AAA.AA (Aንድ ሚላዮን ሦስት መቶ ሺህ) ብር የሆነው የEንጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካ ግማሽ በብር 65A,AAA.AA (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ገዝተው ከውሉ ገንዘብ ውስጥ ብር 16A,AAA.AA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) የከፈሉ ሲሆን የቀረው ብር 49A,AAA.AA (Aራት መቶ ዘጠና ሺህ) Eስከ Aሁን ድረስ ያልተከፈለ በመሆኑና Aመልካቹም የሽያጭ ስምምነቱ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የፋብሪካው ሰራ Aስኪያጅ ሆኖ Eየሰራ ያለ በመሆኑ ከፋብሪካው ላይ የሚፈለግ ልዩ ልዩ Eዳ ከፍሎ ከሆነ ተሣስበን ቀሪውን ገንዘብ ከወለዱ ጋር Eንዲከፈለን Eንዲሁም ፋብሪካውን ለወደፊት በጋራ Eንድንጠቀምበት Eንዲወሰንልን በማለት ፍ/ቤቱን ጠይቀዋል።
የAሁን Aመልካች ለተጠሪዎች ክስ በሰጠው መልስ ግማሽ ፋብሪካውን በብር 65A,AAA (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) መግዛቱ Eና ቀብድ ብር 16A,AAA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) መክፈሉን ሣየስተባብል ነገር ግን በውሉ መሰረት ቀሪውን ገንዘብ ብር 49A,000 (Aራት መቶ ዘጠና ሺህ) ለመክፈል የሚገደደው የመንግሥስትና የግለሰብ የተለያዩ Eዳዎች ተከፍለው ስመንብረቱ በስሙ ከተዛወረ በኋላ መሆኑን ሆኖም ፋብሪካው ቀድሞ በ1971 ዓ.ም የIትዮጵያ ልማት ባንክ በEዳ መያዣነት Eንደያዘው በAሁኑ ሰዓትም ባንኩ በፋብሪካው ላይ የቀዳሚነት መብት Aለኝ በሚል የወሰደው Eና በEጄ የማይገኝ በመሆኑ ክሱ የሕግ ድጋፍ የለውም ሲል መልስ ሰጥቷል። በልላ በኩል ደግሞ የAሁን Aመልካች የተከሣሽ ከሣሽ በመሆን በዚያው መዝገብ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ በየካቲት 5 ቀን 1996 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ Eና ባለቤታቸው በዋስትና የተያዘውን ፋብሪካ ከEዳና Eገዳ ነፃ የሆነ በማስመሰል የሸጡልኝ በመሆኑ ውሉ ፈርሶ የከፈልኩትን ቀብድ ብር 16A,AAA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1885/2/ መሰረት Eጥፍ Aድርገው ብር 32A, AAA (ሦስት መቶ ሃያ ሺህ) ከወጪና ኪሣራ ጋር Eንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ ሲል ፍ/ቤቱን ጠይቋል።
የሥር ከሣሾች ለተከሣሽ ከሣሽነት ክሱ በሰጡት መልስ በተከሣሽ ከሣሽነት የቀረበው ክርክር ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ ጉዳይ በመ/ቁ. 19/94 ውሣኔ ያገኘ በመሆኑ ድጋሚ ላቀርብ Aይችልም፣ ውሉ ተሰርዞ በቀብድ የተሰጠው ገንዘብ ይመለስ ቢባል Eንኳ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 181A/1/ Eና በቁጥር 140 141 1845 መሰረት ክሱ በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።
የጅማ ዞን ከ/ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን Aከራክሮ የከሣሾችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ የAሁን ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክስ በተመለከተ፣ ፋብሪካው በመያዣ የተያዘ በመሆኑ የAሁን Aመልካች (የሥር ተከሣሽ) Eንደፍላጎቱ ስሙን ማዛወር Aይችልም፣ ከሣሾቹ ከስምምነቱ በፊት በፋብሪካው ላይ ያለውን Eዳ በመክፈል ከEዳ ነፃ Aድርገው ስሙ ከተዛወረለት በኋላ ቀሪው ብር 49A,AAA(Aራት መቶ ዘጠና ሺህ) Eንደሚከፈል ውሉ በግልጽ Aስቀምጦ ሣለ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ውሉ ላፈፀም ይገባል ማለት Aስቸጋሪ ስለሚሆን የከሣሾቹ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፤ ያለ ሲሆን የተከሣሽ ከሣሹን ክስ በተመለከተ ደግሞ ተጠሪዎች በባንክ Aዳ የተያዘን ንብረት Aመልካቹን (የሥር ተከሣሽን) በማሳሳት ሸጠውለት ብር 16A,AAA(Aንድ መቶ ሰልሳ ሺህ) ወስደው ቀሪውን ብር 49A,AAA(Aራት መቶ ዘጠና ሺህ) ስመንብረት በተከሣሽ ስም ካዛወሩ በኋላ ለመውሰድ ያደረጉት ስምምነት ላፈፀም የማይቻል ስምምነት ሆኖ የተገኘ ስለሆነ ተጠሪዎች (የሥር ከሣሾች) ቅን ልቦና የልላቸው መሆኑን በመገንዘብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1885(2) መሰረት የወሰዱትን ብር 16A,AAA(Aንድ መቶ ሰልሳ ሺህ) Eጥፍ በማድረግ ብር 32A,000(ሦሰት መቶ ሃያ ሺህ) ከፍለው ውሉ Eንዲፈርስ ሲል ወስኗል።
No topics extracted.
የጅማ ዞን ከ/ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለO/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ግራ ቀኙን Aከራክሮ በሚያዝያ 26 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ የተጠሪዎችን መቃወሚያ ከግምት ውስጥ በማስገባት የAሁን Aመልካች (በስር መ/ሰጭ) ቁጥሩ 19/94 በሆነ ልላ መዝገብ በተጠሪዎቹ (በስር ይ/ባዮች) ላይ የዚህ ክርክር መነሻ በሆነው ውል መሰረት ስመንብረቱን በስሜ Eንዲያዛውሩልኝ፤ በዚህ ፋብሪካ ምክንያት ያወጣሁትን ወጭ Eና በድርጅቱ ላይ ያለውን Eዳ Eንዲከፍሉኝ ሲሉ ክስ Aቅርበው ተጠሪዎቹ በውሉ መሰረት የድርጅቱን ግማሽ ስመንብረት Eንዲያዛውሩ Eና ለድርጅቱ የወጣውን Eዳ ከተለያዩ ወጪዎች ጭምር ብር 215,46A.13(ሁለት መቶ Aሰራ Aምሰት ሺህ Aራት መቶ ሰልሳ ከAስራ ሦሰት) Eንዲከፍሉት ተወስኖ Eያለ Aመልካች ውል ይፍረስልኝ ብሎ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ በማቅረቡ ብቻ ውሉ Eንዲፈርስ ተብሎ መወሰኑ ትክክል ሆኖ Aልተገኘም፣ ተጠሪዎቹም ግድታቸውን Eንደስምምነቱ ሣይፈጽሙ ቀሪው ገንዘብ ላከፈለን ይገባል በማለት ያቀረቡት ቅሬታም ተቀባይነት የለውም ያለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የAሁን Aመልካች የፋብሪካው ስራ Aስኪያጅ ሆኖ በሰራበት ጊዜ ከፋብሪካው የሚገኘው ገቢ በማስረጃ ተጣርቶ ተጠሪዎቹ የድርጅቱ ገቢ ይከፈለን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ውሣኔ Eንዲያኝ በማለት መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 መሰረት ወደ ጅማ ዞን ከ/ፍ/ቤት መልሶታል።
የOሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ መዝገቡ በሰጠው ውሣኔ ቅር የተሰኙት የAሁን Aመልካች ለክልሉ ሰበር ችሎት Aቤቱታቸውን ቢያቀርቡም የO/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት Aቤታቸውን ሣይቀበለው ቀርቷል።
Aመልካች በመስከረም 12 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በስር ፍ/ቤት ውሉ ፈርሶ ተጠሪዎች Aመልካች የከፈሉትን ቀብድ Eጥፍ Aድርገው ይመልሱ ሲል የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ከድርጅቱ የተገኘውን ገቢ በተመለከተ Aጣርቶ የመሰለውን ይወስን ሲል መወሰኑ Eና የክልሉም ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ይህንን ውሣኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት Aቤቱታቸው ለዚህ ችሎት Aቅርበዋል። ይህም ችሎት የAመልካችን Aቤቱታ ተመልክቶ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውና Aመልካች የገዙት ፋብሪካ በEዳ በባንክ የተሸጠ በመሆኑ ስም ላዛወር ስለማይችል ውሉ ላፈርስ ይገባል ተብሎ ue` õ/u?ƒ 142 143 የ}ሰጠው ውሣኔ Eንዲሻር መወሰኑ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪን Aስቀርቦ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር Aድርገዋል።
ከመዝገቡ መረዳት Eንደተቻለው የO/ጠ/ፍ/ቤት የጅማ ዞን ከ/ፍ/ቤት ውሉ ፈርሶ ተጠሪዎቹ የተቀበሉትን ቀብድ Eጥፍ Aድርገው ይክፈሉ ሲል የሰጠውን ውሣኔ ለመሻር መሰረት ያደረገው Aመልካቹ ከዚህ ቀደም በመ/ቁ.
19/94 ተጠሪዎቹ የፋብሪካውን ስመንብረት ያዛውሩልኝ ለፋብሪካው Eዳ የተከፈለ ገንዘብ ይመለስልኝ ሲሉ ባቀረቡት ክስ በተጠሪዎች ላይ ያስወሰኑ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 መሰረት ዳግመኛ ክስ ላመሰርቱ Aይችሉም በሚል ነው። በመሰረቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 ተፈፃሚነቱ ቀድሞ በተወሰነው ክርክር የስረ ነገር Eና የተያዘው ጭብጥ Aንድ Aይነት በሆነ ጊዜ ነው።
በዚህ ጉዳይ ግን ምንም Eንኳ ቀድሞ በመ/ቁ. 19/94 የቀረበው ክርክር በፋብሪካ ሽያጭ ውሉ ዙሪያ የሚያጠነጥን ቢሆንU በክሱ የተጠየቀውም ዳኝነት ይሁን Aከራካሪ የነበረው ጭብጥ ከውሉ መፍረስና Aለመፍረስ ጋር የተገናኘ ባለመሆኑ Aመልካች ውል ይፍረስልኝ ሲሉ ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ ክርክር ነው ላባል የሚችል ሆኖ Aልተገኘም።
Aመልካቹ በተያዘው ጉዳይ ያቀረቡት ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ.ቁ. 5 ሥር የሚካተት Aይደለም ከተባለ ደግሞ የውሉን መፍረስ Aግባብነት መመርመሩ ተገቢ ይሆናል። የክርክሩ መነሻ በሆነው ውል የተሸጠው ፋብሪካ በAሁኑ ሰዓት ባንክ ለEዳው ማስፈፀሚያ ያዋለው መሆኑን ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ ከተደረጉት ክርክሮች Eና ከተሰጡት ውሣኔዎች ለመገንዘብ ተችሐል።
ይህ ከሆነ ደግሞ የውሉ ጉዳይ የሆነው ፋብሪካ በAመልካቹ ስም ላዛወርም ሆነ Aመልካች በውሉ ላይ ተመርኩዞ ላተላለፍለት የሚችል መብት Aይኖርም። በልላ Aነጋገር የዚህ ውል ጉዳይ የሆነው Eንደ ፍ/ብ/ሕ/ቁጥ` 1715 ድንጋጌ Aነጋገር ላፈፀም የማይችል ሆኖ ተገኝቷል። የውሉ ጉዳይ ላፈፀም የማይችል በሆነ ጊዜ ውሉ Eንደሚፈረስ ይኸው ድንጋጌ ይገልፃል።
Aንድ ውል ሲፈርስ ደግሞ ውጤቱ የሚሆነው ተዋዋዮቹን ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815 ይደነግጋል። ይህም ችሎት የጅማ ዞን ከ/ፍ/ቤት ውሉ ይፈርሣል ሲል የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ መሆኑን የተገነዘበ ሲሆን ከፍተኛ ፍ/ቤቱ Aመልካች የፈፀሙት ክፍያ ቀብድ በመሆኑ ተጠሪዎች Eጥፉን ይመለሱ ሲል የሰጠውን ውሣኔ ግን በውሉ ክፍያው ቀብድ መሆኑ ካለመገለፁ Aንፃር Aልተቀበለነውም። በመሆኑም ይህ ችሎት የፋብሪካ ሽያጭ ውሉ ይፈርሣል፣ ተጠሪዎቹም Aመልካች የከፈሉትን ብር 16A,AAA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) ላመልሱ ይገባል ሲል ወስኗል።
ው ሣ ኔ 1/ የO/ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ.22676 በሚያዝያ 26 ቀን 1998 ዓ.ም Aመልካች በውሣኔ ያለቀውን ክርክር በድጋሚ ማቅረብ Aይችልም ሲል ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 ላይ ተመርኩዞ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተሽሯል። ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።