No summary available.
ሚያዝያ 9 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ Eርቁ ጎዳ - ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ Aህመድ Aብዱልሐሚድ - ባለቤታቸው ቀርበዋል መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የሰፈረውን ፍርድ ሰጥተናል።
በፍ/ከ/ፍ/ቤት የAሁን ተጠሪ ከሣሽ የነበሩ ሲሆን በAሁን Aመልካችና Aሁን በክርክሩ ውስጥ በልሉት ልሎች ሁለት ሰዎች ላይ በጥቅምት 30 ቀን 1996 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ከ2ኛዋ ተከሣሽ ከወ/ሮ ወይንሸት ካሣሁን ጋር ሚያዝያ 7 ቀን 1988 ዓ.ም በተፃፈ ሰነድ የባህል ጋብቻ መሥርተን በሰኔ 3 ቀን 1992 ዓ.ም ጋብቻውን በAዲስ Aበባ ከተማ መስተዳድር ያስመዘገብን ሲሆን 1ኛው ተከሣሽ Aቶ ውሂብ ማዘንጊያ ከ2ኛዋ ተከሣሽ በተሰጠው የውክልና ስልጣን ስሙ በ2ኛዋ ተከሣሽ የሆነውን የጋራ ቤታችንን ያለ ከሣሽ Eውቅና ለ3ኛ ተከሣሽ (ለAሁን Aመልካች) በመጋቢት 5 ቀን 1994 ዓ.ም በተፈረመ ውል በብር 16A,AAA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) ሸጠው የገንዘቡን መጠን ዝቅ በማድረግ ቤቱ የተሸጠው በብር 23,AAA (ሃያ ሦስት ሺህ) መሆኑን የሚገልጽ ውል በመጋቢት 12 ቀን 1994 ዓ.ም በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበው ተፈራርመዋል። ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውሉ የተደረገው ከቅን ልቦና ውጪ በመሆኑ ውሉ ፈርሶ የባለቤትነት ስሙ በ2ኛዋ ተከሣሽ Eንዲመዘገብ ይደረግልኝ ሲሉ ፍ/ቤቱን ጠይቀዋል። 1ኛው ተከሣሽ ከ2ኛ ተከሣሽ በተሰጠኝ ውክልና መሰረት በፈፀምኩት ውል ልከሰስ Aይገባም የሚል መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ጉዳዩም ረገድ ከ3ኛው ተከሳሽ (የAሁን Aመልካች) ጋር በጋራ በሰጡት መልስ የቤት ሽያጭ ውሉ የተደረገው በብር 23,000 (ሃያ ሦስት ሺህ) Eንጂ በብር 16A,AAA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) የተደረገ ውል የለም። ጋብቻ መኖሩንም Aናውቅም፣ ቤቱ የተመዘገበው በ2ኛዋ ተከሣሽ ስም ከመሆኑ ባሻገር 2ኛ ተከሣሽ ትዳር Eንደልላቸው ከሚኖሩበት ቀበል ተረጋግጧል። በመሆኑም ከሣሽ(የAሁን ተጠሪ) ጉዳት ደርሶብኛል ካሉ 2ኛዋን ተከሣሽ ከሚጠይቁ በቀር በቅን ልቦና የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ላፈርስ Aይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የ1ኛውን ተከሣሽ ተቃውሞ በመቀበል ከክርክሩ ያሰናበታቸው ሲሆን የAሁን Aመልካች ውሉን በፈፀመበት ወቅት 2ኛዋ ተከሣሽ ትዳር Eንዳላት Eንደማያውቁ ክደው የተከራከሩት በተጠሪ ያልተስተባበለ በመሆኑ Aመልካች በቅን ልቦና በተዋዋሉት የቤት ሽያጭ ውል መሰረት በህጉ Aግባብ የባለቤትነት መብት ያገኙበትን ንብረት ላያጡ Aይገባም ሲል የተጠሪን ክስ ውድቅ Aድርጓል። የAሁን ተጠሪ የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2483A በህዳር 6 ቀን 1998 ዓ.ም ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ቅሬታቸውን ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት በይግኝ Aቅርበዋል።
ይግባኙ የቀረበለት የፍ/ጠ/ፍ/ቤትም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1266 Eና A/ቁ.
213/92 Aንቀጽ 68/ሀ/'ን ጠቅሶ በማይንቀሣቀስ የጋራ ንብረት ላይ ለመዋዋል የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት ያስፈልጋል፣ ማስረጃውን የሰጠው ቀበልም 2ኛዋ መ/ሰጭን በነዋሪነት ያስመዘገበ ከመሆኑም በላይ ስለጋብቻው መኖር Aለመኖር የማስረዳት ብቃት የለውም ከዚህ Eና ሁለት የተለያየ የሽያጭ ዋጋ ያላቸው ውሎች በተዋዋዮች ስምምነት ከመደረጋቸው Aንፃር የውሉ Aደራረግ ከመነሻው በተንኮል መሆኑን፣ በAጠቃላይ የውሉ Aደራረግ ለህላና ብቻ ሣይሆን ለህግም ተቃራኒ ነው ማለት ይቻላል በሚል ምክንያት ውሉ በA/ቁ. 213/92 Aንቀጽ 69/1/ መሰረት ላፈርስ ይገባል ሲል የከ/ፍ/ቤት ውሣኔን ሽሮታል። ይህ የሰበር Aቤቱታም የቀረበው የፍ/ጠ/ፍ/ቤት 136 137 በመ/ቁ. 22126 በግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው።
ይህም ችሎት የAመልካችን የሰበር Aቤቱታ ተመልክቶ የሽያጭ ውሉ Eንዲፈርስ የተወሰነው በAግባቡ ነው? ወይስ Aይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር በሚል ተጠሪን Aስቀርቦ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በመሰረቱ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ውሉን ለማፍረስ ምክንያት ያደረገው የቀበል ጽ/ቤት የጋብቻ መኖር Aለመኖርን የማስረዳት ብቃት የለውም፣ ጋብቻን የመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው Eና የጋብቻ የምስክር ወረቀት ከሚሰጠው Aካል ማስረጃ Aልተጠየቀም፣ ሁለት የተለያየ የሽያጭ ዋጋ ያላቸው ውሎች መደረጋቸው የውሉ Aደራረግ ከመሰረቱ የተንኮል መነሻ የነበረው ነው የሚል ነው። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ Aመልካቹ ቤቱን ሲገዙ ከቀበል ማስረጃ መጠየቃቸው የቀበል ጽ/ቤት የነዋሪዎችን Aሰፋፈርና የAኗኗር ሁኔታ በተመለከተ ከማንኛውም ተቋም በተሻለ መረጃዎችን ሰብስቦ የሚመዘግብ ከመሆኑ Aንፃር መረጃው Aግባብነት ያለው ነው። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ቀርበው በውልና ማስረጃ ካስፀደቁት ውል በተጨማሪ በብር 16A.AAA (Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ) የተደረገ ልላ ውል Aለ ያሉ ሲሆን፣ ነገር ግን ህጉም ሆነ ይህ ፍ/ቤት ከግንዛቤ የሚያስገባው ያልፀደቀውን Eና Aመልካች የካዱትን የመንደር ውል ሣይሆን በAዋዋይ የፀደቀውንና በብር 23,AAA (ሃያ ሦስት ሺህ) የተደረገውን የሽያጭ ውል ብቻ ነው። ከነዚህ ነጥቦች በመነሣት Aመልካች የቤቱ ባለቤትነት በወ/ሮ ወይንሸት ካሣሁን ስም መሆኑን፣ ወ/ሮ ወይንሸትም ትዳር የልላቸው መሆኑን በበቂ ሁኔታ Aረጋግጠው የፈፀሙት የሽያጭ ውል ለሕግና ለሞራል ለቅን ልቦናም ተቃራኒ ነው ላባል የሚችል ሆኖ Aለተገኘም። በመሆኑም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የAመልካችን የቅን ልቦና መከራከሪያ ወደጎን በመተው የሽያጭ ውሉ ይፈርሣል ሲል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1/ በወረዳ 16 ቀበል 11 የቤ.ቁ. A98 የሆነውን ቤት Aስመልክቶ መጋበት 12 ቀን 1994 ዓ.ም የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል Aይፈርስም ብለን ወስነናል።
2/ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22126 በግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ሙሉ በሙሉ ተሽሯል። ይፃፍ።
3/ የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2483A ህዳር 6 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
4/ ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል።
ይመለስ።