No summary available.
ታህሳስ 8 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- 1. Aቶ ፈቃዱ ድሬሎ 2. ወ/ሮ ዓይናለም በሻህ ጠበቃ ሙላት ፈለቀ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በAመልካቾችና በተጠሪዎች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ተሰርዞ ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ Eንዲመለሱ በሥር ፍ/ቤቶች በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካቾች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪዎች በAመልካቾች ላይ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በወረዳ 16 ቀበል A4 ክልል የቤት ቁጥር 898 የሆነውን ቤት በታህሳስ 1 ቀን 1977 ዓ.ም. በተፃፈ የሽያጭ ውል በብር 58‚000 /ሃምሣ ስምንት ሺህ/ ከሣሾች ለተከሣሾች ሸጠን ውሉ በተደረገ Eለት ብር 5A‚AAA /ሃምሣ ሺህ/ የተቀበልን ሲሆን ቀሪውን 8‚AAA /ስምንት ሺህ/ ደግሞ በ3A ቀን ውስጥ ቤቱን Aስረክበን Eንደሚከፈለን በተስማማነው መሰረት ቤቱን ያስረከብን ቢሆንም ቀሪው ገንዘብ ያልተከፈለ ስለሆነ ውሉ Eንዲፈርስና ወደነበርንበት Eንድንመለስ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ክሱና ማስረጃው ለተጠሪዎች ደርሶም በሰጡት መልስ የውሉን መደረግ Aምነው ውሉ በተፈረመ በ3A ቀን ውስጥ ከሳሾች የሸጡትን ቤት ከEዳና Eገዳ ነፃ Aድርገው ውል ክፍል ቀርበው መሸጣቸውን በማረጋገጥ ሲፈርሙ ቀሪው ብር 8,000 (ስምንት ሺ) Eንደሚከፈላቸው በውሉ ላይ የተስማማን ቢሆንም ይህንን ግድታ ካለመወጣታቸው በላይ በክስ ከተጠየቀው ገንዘብ ላይም ክስ ከመቅረቡ በፊት ብር 5,000 (Aምስ ሺ) ለከሳሾች የከፈለን ስለሆነ ውሉ ይፍረስል በማለት ያቀረቡት ክስ ከበቂ ኪሣራ ጋር ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ተከሳሾች በቀሪነት የሚፈለግባቸውን ገንዘብ Eስከ ታህሣሥ 3A ቀን 1977 ዓ.ም. ድረስ Aጠቃለው ለመክፈል በውል ግድታ ገብተው ክፍያውን Aለመፈጸማቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ግራ ቀኙ ያደረጉት ውል ፈርሶ ወደነበሩበት ላመለሱ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሾች በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበለትን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዳዩ ጭብጥ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ላሰረዝ ይገባል? ወይንስ Aይገባም? የሚለው በመሆኑ ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
ታህሣሥ 1 ቀን 1977 ዓ.ም. በተፃፈ ውል ግራ ቀኙ የቤት ሽያጭ ውል ማድረጋቸውንና ውሉ በተደረገ Eለት ሻጮች የAሁን ተጠሪዎች ብር 5A‚AAA /ሃምሳ ሺህ/ የተቀበሉ መሆኑ” ግራ ቀኙ ተማምነውበታል።
ተጠሪዎች ውሉ ይሰረዝልን በማለት በክስ የጠየቁት ቀሪው ብር 8,000 (ስምንት ሺህ) Aልተከፈለንም በሚል ምክንያት ነው። በውል Aፈፃፀም ሂደት ከተዋዋዮች Aንዱ የውሉን ግድታ ሳይፈጽም የቀረ Eንደሆነ ልላው ወገን Eንደሁኔታው ውሉ Eንዲፈጸምለት መጠየቅ Eንደሚችል ይህም ካልሆነ ውሉ Eንዲሰረዝ ጥያቄውን ማቅረብ Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1771 ላይ ተመልክቷል። የውል ይሰረዝልኝ ጥያቄ ለፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኞች ውሉ ላሰረዝ ይገባል በማለት ውሣኔ ከመስጠታቸው በፊት የተዋዋዮችን ጥቅምና ለቅን ልቦና የሚያስፈልገውን ነገር መሰረት ማድረግ Eንዳለባቸው' በውሉ ላይ ዓይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ተግባር /fundamental breach of contract/ ካልተፈጸመ በስተቀር ዳኞች ውል ይሰረዝ ማለት Eንደልለባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1784 Eና 1785 ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዳይ በቤት ሽያጭ ውሉ መሰረት ለተጠሪዎች መከፈል ከሚገባው ገንዘብ Aብዛኛውን Aመልካቾች Eንደከፈሉ ተረጋግጧል። ከዚህም ውሉ በAመዛኙ Eንደተፈጸመ መገንዘብ ይቻላል። ውሉ ባመዛኙ መፈጸሙ ከተረጋገጠ ደግሞ ዓይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ተግባር ተፈጽሟል ለማለት የማይቻል ከመሆኑም በላይ ከቅን ልቦና መለኪያ Aኳያም ሲታይ ተጠሪዎች በቀሪነት የሚፈለገውን Aነስተኛ ገንዘብ Eንዲከፈላቸው በመጠየቅ ውሉ ውጤት Eንዲኖረው ማድረግ Eየቻሉ Eንዲሰረዝ መጠየቃቸው ተቀባይነት ያለው ምክንያት Aይደለም። የሥር ፍ/ቤቶችም ቀሪው ገንዘብ ባለመከፈሉ ምክንያት የቀረበውን የውል ይሰረዝልኝ ክስ ተቀብለው ውሉ Eንዲሰረዝ መወሰናቸው የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የሰጠው ፍርድ Eንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
43A67 ግንቦት 9 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመv†¨< ስለሆ’< በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽ[ªል።
Aመልካቾች መሰረታዊ የሆነ የውል መጣስ ተግባር ያልፈጸሙ ስለሆነ ከተጠሪዎች ጋር ያደረጉት ውል ላሰረዝ Aይገባም ተብሎ ተወሰኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።