No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ Aመልካች፡- ሰላም የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማEከል ተጠሪ፡- መኮንን ሉል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው የAሁኑ Aመልካች ነው። በተጠሪው ላይ ክስ የመሰረተው ተጠሪ በሁለቱ መካከል በተደረገው የሽያጭ ውል መሰረት በግዢ ለተረከበው ወፍጮ መከፈል የሚገባውን ዋጋ ከነመቀጫው በጠቅላላው ብር 63‚A1A Eንዲከፍለው ነው። ተጠሪ ለቀረበበት ክስ መልስ በመስጠት ተከራክሮAል። ፍ/ቤቱም ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣ በሁለቱ መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል ተከሣሹ በውሉ መሰረት Aፍርሶታል /ቀሪ Aድርጎታል/። ከዚህ በኋላም ቀደም ሲል ተደርጎ በነበረው ውል Aይነት የሽያጭ ውሉ Aልታደሰም የሚሉትን ምክንያቶች በመስጠት በመልካች የቀረበውን ክስ ውድቅ AድርጎAል። ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፍ/ከ/ፍ/ቤትም የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቶAል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
ይህ የሰበር ችሎትም Aመልካች መጋቢት 18 ቀን 98 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶAል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aቤቱታ የቀረበበት” ውሣኔ የሽያጭ ውል ከሚገዛበት ሕግ Aንፃር በማየት Aግባብነቱን ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል Eንደተገለጸው የተከራካሪዎቹ ወገኖች ግንኙነት የተመሰረተው በEቃ ሽያጭ ውል ላይ ነው። በዚሀ ውል መሰረት Aመልካች ወፍጮዎችን ለተጠሪ ሸጦAል፣ ተጠሪም በውሉ መሰረት ወፍጮዎቹን ተረክቦ የነበረ ሲሆን፣ ዋጋቸውን ግን AልከፈKም። በልላ በኩል ደግሞ ወፍጮዎቹ በውሉ መሰረት ትክክለኛ ሆነው Aልተኙም ወይም ጉድለት ያለባቸው ናቸው በሚል ለAመልካች ያስታወቀበት ሁኔታ የለም። ገንዘቡን Eንዲከፍል በተጠየቀ ጊዜ /ሲከሰስ/ ያቀረበው መከራከሪያም ¾ወፍጮዎቹ” ትክክል Aለመሆን የሚመለከት Aይደለም። የሥር ፍ/ቤቶችም የAመልካችን ክስ ውድቅ ያደረጉት ውሉ Eንደፈረሰ በመቁጠር Eንጂ የሽያጭ ውል Aፈፃፀምን በተመለከተ የተደነገገውን ሕግ መሰረት በማድረግ Aይደለም።
Eንደምንመለከተው ጉዳዩ የEቃ ሽያጭ ውልን የሚመለከት Eንደመሆኑ የተከራካሪዎቹ ወገኖች መብትና ግድታ መታየት ያለበት “ስለ ልዩ ውሎች” በሚል በተደነገገው በፍትሐብሕር ሕጉ በAንቀጽ Aስራ Aምስት ሥር ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት ነው። Eነዚህ ድንጋጌዎች የhጩን ግድታ Eና ገዢውም Eቃውን Eንደተረከበ ላወስዳቸው የሚገቡ Eርምጃዎች ምን Eንደሆኑ ያመለክታሉ። ሻጩ በውሉ በተመለከተው መሰረት ትክክለኛውን Eቃ ለገዢው የማስረከብ ኃላፊነት Eንዳለበት በፍ/ብ/ሕግ ቁ 2287 Eና 2288 Eንደተደነገገው ሁሉ ገዢም Eቃው በውሉ መሰረት የተሟላ Aይደለም ወይም ጉድለት ያለበት ነው የሚል Eምነት ካለው በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማስታወቅ ግድታ Aለበት /የፍ/ብ/ሕግ ቁ 2291፣ 2292/።
ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ ተጠሪ በሽያጭ ውሉ መሰረት የተረከባቸው ወፍጮዎች ጉድለት ያለባቸው ናቸው በሚል Aመልካችን ያስታወቀበት ጊዜ 122 123 /ሁኔታ/ የለም። ጉድለትን መሰረት በማድረግም በAመልካች ላይ ክስ Aልመሰረተም ወይም የሽያጭ ውሉን ቀሪ Eንዲሆን Aላደረገም። በመሆኑም የሽያጭ ውሉ ፈርሶAል በማለት የስር ፍ/ቤቶች የደረሱበት መደምደሚያ ትክክል Aይደለም። ይህን መደምደሚያ መሰረት በማድረግ የተሰጠው ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
No topics extracted.
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
ግንቦት 28 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ Aይሸሹም ጋተው - ጠበቃ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- Eነ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ጠበቃ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ክርክሩ የተጀመረው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን Aመጣጡን በተመለከተም የAሁኑ Aመልካች ሐምል 25 ቀን 1994 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ የተከሳሾች Aውራሽ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ነሐሴ 24 ቀን 1985 ዓ.ም. በተፃፈ የቤት ሽያጭ ውል ስምምነት Aድርገን በወረዳ 12 ቀበል 11 የሚገኘው ቁጥሩ 14A8 የሆነውና በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኘውን የግል ቤታቸው በብር 15,AAA /Aስራ Aምስት ሺህ ብር/ ሸጠውልኝ ከዚሁ ሽያጭ ገንዘብ ብር 1A,AAA ተቀብለው ቀሪውን ብር 5AAA /Aምስት ሺህ ብር/ ስም ሲዞርልኝ ላቀበሉ ተስማምተው በEማኞች ፊት ፈርመዋል። በዚሁ መሰረትም ውሉ Eንዲፀድቅልን ለዞን 4 ወረዳ 12 ፍ/ቤት መዝገብ ከፍቼ የተከሳሾች Aውራሽ ከመሞታቸው በፊት መጥሪያ ደርሶAቸው ቤቱን የሸጡ በመሆኑ ስሙ በከሣሽ ስም ቢዞር ተቃውሞ Eንደልላቸው የወረዳው ፍ/ቤት ቀርበው Aመልክተዋል። ፍ/ቤቱም ተቃዋሚ ቢኖር Eንዲቀርብ በAዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ Eንዲወጣ Aዝዞ ተቃዋሚ ባለመቅረቡ መጋቢት 15 ቀን 1987 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ ውሉን Aጽድቆ የቤቱን ባለቤትነት ስም በከሣሽ ስም Eንዲዘዋወር ትEዛዝ ሰጥቶA በዚህ መሰረትም የሥራና ከተማ ልማት በስሜ ካርታ ሰርቶ ሰጥቶኛል።
ነገር ግን ሟች የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ቤቱን ሲሸጡልኝ ስለቤቱ ርክክብ ሣይፈፀም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ባለቤት የሆንኩለትን ቤት ተከሣሳሾች ያለAግባብ Eየተጠቀሙበት በመሆኑ መብቴን ጠብቄ ቤቱን Eንዲያስረክበኝ ክስ ካቀረብኩበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ተከሣሾች የተጠቀሙበት የቤት ኪራይ ሂሣብ ተምኜ የመካስ መብቴ ይጠበቅልኝ በማለት ክስ Aቅርበዋል።
ተከሣሾች ከሆኑት የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ወራሾች መካከል 2ኛ ተከሣሽ ወ/ሪት ክብርወርቅ ሞገስ Eና 5ኛ ተከሣሽ ወ/ሪት የምስራች ሞገስ ታህሣሥ 12 ቀን 88 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ በማቅረብ ክርክር የቀረበበት ቤት የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ Eና ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ በጋብቻ ያፈሩት ስለሆነ Eናታችን ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ ሳታውቅ የተደረገው የሽያጭ ውል በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም በማለት የተከራከሩ ሲሆን 1ኛ፣ 3ኛ Eና 4ኛ ተከሣሾች በተገቢው ሁኔታ ተጠርተው ያልቀረቡ ስለሆነ ክሱ በልሉበት Eንዲታይ ፍ/ቤቱ ታህሣሥ 23 ቀን 1993 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ብይን ሰጥቷል።
ጣልቃ ገብ Aመልካች ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ የተከሳሽ Eናት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
41/1/ መሰረት በክርክሩ ጣልቃ Eንዲገቡ ጠይቀው ፍ/ቤቱ ፈቅዶላቸው መጋቢት 3 ቀን 1993 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ ክስ የቀረበበት ቤት የጣልቃ ገብና የሟች የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ የጋራ ሀብት ስለሆነ ከሣሽና ሟች የተዋዋሉት የቤት ሽያጭ ውል ሕጋዊ ላሆን Aይችልም በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ካዳመጠ በኋላ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2266 ጀምሮ በተደነገጉት መሰረት የሽያጭ ውል ተፈፀመ የሚባለው ገዢው ገንዘብ በውሉ መሰረት ሲከፍልና የገዛውን ነገር ሲረከብ ሻጭም የሸጠውን ነገር ከደጋፊ ማስረጃዎች ጋር ለገዢው ሲያስረክብ ነው።
በዚህ ጉዳይ ከሣሽ የሆኑት Aቶ Aይሸሹም ጋተው ግን ከተከሣሾች Aውራሽ ገዛሁ ያሉትን ቤት Eንደውሉ Aፃፃፍ Aልተረከቡም። ባለመረከባቸውም ስም Eንዲዛወር ክስ Aቅርበው ውሉን በፍ/ቤት Aስመዝግበው ቤቱን Eንዲረከቡ Aሁን የተያዘው ክርክር ያስነሳውን መዝገብ ከፍተዋል። ከመረከብ ጥያቄያቸው በመረዳትም ነሐሴ 24 ቀን 1985 ዓ.ም የተደረገው ውልና በፍ/ቤት ተመዝግቦ ስም Eንዲዛወር ተወስኖ በስማቸው የባለቤትነት ማረጋገጫ ያገኙበት ምክንያት የሽያጩ ውል የተደረገው የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ ሳያውቁና ስምምነታቸውን ሳይገልፁ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ሃብቱንም በEጃቸው ከማድረጋቸውና ባለ ይዞታ ከመሆናቸው በፊት በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1196 ድንጋጌ መሰረት ውጤት የሚኖረው Aይደለም። በመሆኑም ተከሣሾች ቤቱን ለከሣሽ የማስረከብ ግድታ የለባቸውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ ተመልክቶ ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
Aመልካች የሰበር Aቤቱታ ያቀረቡት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን ቅሬታውም የቤቱ” ሽያጭ የሚቃወም ካለ በAዲስ ዘመን ጋዜጣ Eንዲቀርብ ማስታወቂያ ወጥቶ ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ ቀርበው Aልተቃወሙም። ¾ሽያጩን Ñ”²w ባለቤቴ ናቸው ከሚሉዋቸው የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ከሚካፈሉ በስተቀር በAግባቡ የተደረገውን የሽያጭ ውል ላያፈርሱ የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም። ሚስት ነኝ የሚሉት ተቃዋሚ ቤቱ በተሸጠበት ጊዜ ከባላቸው ተለይተው ወደናዝሬት በመሄድ ልላ ባል Aግብተው ይኖሩ ስለነበር በቤቱ Là ምንም መብት የላቸውም። ሽያጩ Ÿ}Å[Ñ 13 ዓመት ሆኖታል። ከAስራ ሶስት ዓመት በኋላ መጥተው የሽያጭ ውሉ Eንዲፈርስ በማለት ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት የለውም። የሽያጭ ውሉ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት የፀደቀና ማረጋገጫ የተሰጠበት ’¨<:: ሚስት መብት ነበራቸው የሚባሉም ከሆኑ የሽያጭ ውሉን የሚቃወም ካለ Eንዲቀርብ ተብሎ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎ ሳይቀርቡ ፍ/ቤቱ የሽያጭ ካጸደቀና ማረጋገጫ ከተሰጠበት በኋላ vk[u<ƒ ጥያቄ የሽያጭ ውሉን ላያፈርስ የሚችልበት ምክንያት ¾KU:: eKJ’U የሥር ፍ/ቤቶች የሽያጭ ውሉ ተፈፃሚነት የለውም ተከሳሾች ቤቱን ለገዢው Eንዲያስረክቡ Aይገደዱም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ Ãh`M˜ ቤቱንU Eንዲሰጡኝ Eንዲወሰንልኝ የሚል ነው።
ተጠሪዎች ደግሞ በሰጡት መልስ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ የሸጡት ቤት የግላቸው Aይደለም። የሽያጭ ውሉን በፍ/ቤት ያፀደቁትም በሐሰተኛ መንገድ ነው። የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ሚስት የሆንኩት መልስ ሰጭ መፃፍ ማንበብ ስለማልችል በAዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጣ የተባለውን ማስታወቂያ Aላየሁትም። ቀሪዎቻችንም ቤቱን ከAባታችን በውርስ ያገኘነው ነው። የሥር ፍ/ቤቶቹ የሽያጭ ውሉ ተቀባይነት የለውም’¤ ተከሣሾች ቤቱን ለከሣሽ ማስረከብ የለባቸውም በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት ስለልለበት ላፀድቅልን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ወራሾች ክርክር ያስነሳውን ቤት ለAመልካች የማያስረክቡበት ምክንያት Aለ ወይስ የለም? ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ የሽያጩን ውል በመቃወም ጣልቃ መግባት የነበረባቸው በመ/ቁ. 2643 ነው ወይስ በመ/ቁ. 561/86? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነው የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ወራሾች የሆኑት ተጠሪዎች የሚያቀርቡት መከራከሪያ ነጥብ ክርክር ያስነሳው ቤት የAባታችን የ5A Aለቃ ሞገስ ማሞና የEናታችን ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ በመሆኑና የተሸጠውም Eናታችን ሳታውቅና ስምምነቷን ሳትሰጥ ነው' ቤቱ የተሸጠው በAግባቡ Aይደለም። Eኛ ደግሞ የAባታችን ወራሾች በመሆናችን የቤቱ ግማሽ ይገባናል። በመሆኑም ቤቱን ለሥር ከሣሽ ለAሁኑ ተጠሪ ልናስረክብ Aይገባም የሚል ነው። ይህን የወራሾች ክርክር ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው የውርስ ንብረት ነው የሚሉት ቤት Aባታቸው የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ በሕይወት Eያሉ በ1985 ዓ.ም. ለAመልካች የሸጡትና የሽያጭ ውሉም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2877 መሰረት በጽሑፍ የተደረገና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረት ደግሞ የሽያጭ ውሉ በመጋቢት 15 ቀን 1987 ዓ.ም. በፍ/ቤት የተረጋገጠና የቤት ባለቤትነቱንም ለAመልካች Eንዲዛወርላቸው የተወሰነ በመሆኑ ይህ ቤት የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ሃብት መሆኑ በዚያን ጊዜ ያበቃለት ሆኗል። ቤቱ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ማለት የወራሾቹ Aባት የሆኑት ሰው ንብረት ካልሆነ ደግሞ ወራሾቹ ንብረትነት ጥያቄ የሚያነሱበት ምክንያት Aይኖርም። Eንደዚሁም ወራሾቹ ቤቱን ለAመልካች Aናስረክብም ለማለት የሚያስችላቸው መብት የልላቸው በመሆኑ ክርክራቸው ተቀባይነት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም። ቤቱ የተሸጠው የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ሚስት የሆነች Eናታችን ሳታውቅና ስምምነቷን ሳትሰጥበት በመሆኑ የሽያጭ ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት የሚያቀርቡትን ክርክር በተመለከተም ይህን ክርክር መነሻ በማድረግ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ ራሳቸው በመቃወም Aመልካችነት ጣልቃ ገብተው Eየተከራከሩ የሚገኙ በመሆኑ ክርክሩ በወራሾቹ የሚነሳበትና የሚቀጥልበት ምክንያት የለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ወራሾች ቤቱን ለAመልካች የማስረከብ ግድታ የKvቸውም በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ያለመሆኑን ለመረዳት ተችሐል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ደግሞ የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ቤቱን ነሐሴ 24 ቀን 1985 ዓ.ም. ለAመልካች መሸጣቸውንና የሽያጭ ውሉም በጽሑፍ መደረጉን' ይህን የሽያጭ ውል በመያዝ ገዢና ሻጭ ሽያጩን ለማስመዝገብና የባቤትነ~” ስም ለማዛወር ፍ/ቤት ዘንድ መቅረባቸውን' ፍ/ቤቱም ተቃዋሚ ካለ Eንዲቀርብ በAዲስ ዘመን ጋዜጣ Eንዲጣራ ካደረገ በኋላ የመጣ ተቃዋሚ ያለመኖሩን በማረጋገጥና የግራ ቀኙን ስምምነትንም በመረዳት ውሉ Eንዲፀድቅ' የባለቤትነት ስምም ከሻጭ ወደ ገዢ Eንዲዛወር በማለት መወሰኑን በመ/ቁ. 561/86 መጋቢት 15 ቀን 1987 ዓ.ም.
128 129 ከተሰጠው ውሣኔ ለመረዳት ችለናል። ወ/ሮ ፋናዬ Aየለ በወቅቱ በጋዜጣው ጥሪ መሰረት ወይም በልላ መንገድ ሰምተው' በሰሙበትና ባወቁበት ጊዜ መቃወሚያ በማቅረብና ጣልቃ በመግባት መከራከር የነበረባቸው የሽያጭ ውሉ በፀደቀበትና የቤ~ ባለቤትነት ስም ለገዢው Eንዲዛወር ተብሎ በተወሰነበት የመዝገብ ቁ 561/86 በተደረገው ክርክርና በተሰጠው ውሣኔ ላይ Eንጂ ቤቱን ያስረክቡን ተብሎ በቀረበው ክስ ጣልቃ ገብተው ላከራከሩ የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም። ምክንያቱም Aመልካች ቤቱን Aስረክቡኝ Eያሉ ያሉት በፀደቀው የሽያጭ ውልና ስም Eንዲዛወር ተብሎ በፍ/ቤት በልላ መዝገብ ተወስኖ ባደረ ጉዳይ በመሆኑ ቤቱን የተመለከተ መብት የሽያጭ ውሉ በፍርድ ቤት በፀደቀበትና የባለቤትነት መብት ለገዢው Eንዲዛወር ተብሎ በተወሰነበት ጊዜ የታየና ያለቀለት ጉዳይ በመሆኑ ተጠሪዋ ይህ ውሣኔ በተሰጠበት የመ/ቁ. 561/86 ጣልቃ ገብተው መከራከር ነበረባቸው።
ክሱ በፀደቀልኝ የሽያጭ ውልና ስም Eንዲዛወርልኝ በተወሰነልኝ መሰረት ቤቱን ያስረክቡኝ የሚል Eንጂ የሽያጭ ውሉ ይጽደቅልኝ የሚል ባለመሆኑ በፀደቀው የሽያጭ ውልና ስም Eንዲዛወር ተብሎ Aስቀድሞ በልላ መዝገብ በፍ/ቤት ተወስኖ ባደረው ጉዳይ ጣልቃ ገብተው የሽያጭ ውሉን በዛን ጊዜ ያልተቃወሙት Aመልካች በዚሁ ቤቱን ያስረክቡኝ በሚለው ክስ ላይ ጣልቃ መግባት Aይችሉም።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት በAመልካች ኋላ የቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ ግራ ቀኙን ባከራከረበት ጊዜ ጣልቃ ልግባ በማለት የAሁን ተጠሪ ሲያመለክቱ ጣልቃ መግባት ያለባቸው ቀደም ብሎ የሽያጭ ውሉ ይጽደቅልኝ የባለቤትነት ስምም Eንዲዛወርልኝ በማለት Aመልካች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግራ ቀኙን Aከራክሮ ልላው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሣኔ በሰጠበት የመ/ቁ. 561/86 Eንጂ ኋላ በቀረበው በዚሁ የቤት ያስረክቡኝ ክስ Aይደለም በማለት ጥያቄውን ውድቅ ላያደርገው ሲገባ ጣልቃ Eንዲገቡ በመፍቀድ Aከራክሮ በተመሳሳይ ደረጃ ላይ የነበረው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በሚሽር መልኩ የሽያጭ ውሉ በAግባቡ የተደረገ ባለመሆኑ ላፈርስ ይገባል፤ ተከሣሾች ቤቱን የማስረከብ ግድታ የለባቸውም በማለት የሰጠው” ውሣኔ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 Eና 41 ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው ውሣኔዉ ተገቢ ሆኖ Aላገኘነውም።
በመሆኑም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትና የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የተሰጠውን ውሣኔና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23795 የካቲት 1 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የቤት ሽያጭ ውሉ በፍ/ቤት የፀደቀና የቤ~ ባለቤትነት መብትም ወደ Aመልካች Eንዲዞር ተብሎ የተወሰነ በመሆኑ ቤቱ የውርስ ንብረት Aይደለም። የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ወራሾችም ቤቱን የመውረስ መብት የላቸውም። የ5A Aለቃ ሞገስ ጽጌ ሚስትም ጣልቃ በመግባት መከራከር የነበረባቸው የሽያጭ ውሉ በፀደቀበትና የባለቤትነት ስም ለገዢው /ለAመልካች/ Eንዲዛወር ተብሎ ውሣኔ በተሰጠበት ክርክር Eንጂ ቤቱን ለመረከብ በቀረበው ክስ መሆን የለበትም። ተጠሪዎች በወረዳ 12 ቀበል 11 የሚገኘው”“ ቁጥሩ 14A8 የሆነውን ቤት ለAመልካች በውሉ መሰረት Eንዲያስረክቡ በማለት ወስነናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ 131
ታህሳስ 8 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- 1. Aቶ ፈቃዱ ድሬሎ 2. ወ/ሮ ዓይናለም በሻህ ጠበቃ ሙላት ፈለቀ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በAመልካቾችና በተጠሪዎች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ተሰርዞ ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ Eንዲመለሱ በሥር ፍ/ቤቶች በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካቾች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪዎች በAመልካቾች ላይ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በወረዳ 16 ቀበል A4 ክልል የቤት ቁጥር 898 የሆነውን ቤት በታህሳስ 1 ቀን 1977 ዓ.ም. በተፃፈ የሽያጭ ውል በብር 58‚000 /ሃምሣ ስምንት ሺህ/ ከሣሾች ለተከሣሾች ሸጠን ውሉ በተደረገ Eለት ብር 5A‚AAA /ሃምሣ ሺህ/ የተቀበልን ሲሆን ቀሪውን 8‚AAA /ስምንት ሺህ/ ደግሞ በ3A ቀን ውስጥ ቤቱን Aስረክበን Eንደሚከፈለን በተስማማነው መሰረት ቤቱን ያስረከብን ቢሆንም ቀሪው ገንዘብ ያልተከፈለ ስለሆነ ውሉ Eንዲፈርስና ወደነበርንበት Eንድንመለስ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ክሱና ማስረጃው ለተጠሪዎች ደርሶም በሰጡት መልስ የውሉን መደረግ Aምነው ውሉ በተፈረመ በ3A ቀን ውስጥ ከሳሾች የሸጡትን ቤት ከEዳና Eገዳ ነፃ Aድርገው ውል ክፍል ቀርበው መሸጣቸውን በማረጋገጥ ሲፈርሙ ቀሪው ብር 8,000 (ስምንት ሺ) Eንደሚከፈላቸው በውሉ ላይ የተስማማን ቢሆንም ይህንን ግድታ ካለመወጣታቸው በላይ በክስ ከተጠየቀው ገንዘብ ላይም ክስ ከመቅረቡ በፊት ብር 5,000 (Aምስ ሺ) ለከሳሾች የከፈለን ስለሆነ ውሉ ይፍረስል በማለት ያቀረቡት ክስ ከበቂ ኪሣራ ጋር ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ተከሳሾች በቀሪነት የሚፈለግባቸውን ገንዘብ Eስከ ታህሣሥ 3A ቀን 1977 ዓ.ም. ድረስ Aጠቃለው ለመክፈል በውል ግድታ ገብተው ክፍያውን Aለመፈጸማቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ግራ ቀኙ ያደረጉት ውል ፈርሶ ወደነበሩበት ላመለሱ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሾች በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበለትን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዳዩ ጭብጥ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ላሰረዝ ይገባል? ወይንስ Aይገባም? የሚለው በመሆኑ ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
ታህሣሥ 1 ቀን 1977 ዓ.ም. በተፃፈ ውል ግራ ቀኙ የቤት ሽያጭ ውል ማድረጋቸውንና ውሉ በተደረገ Eለት ሻጮች የAሁን ተጠሪዎች ብር 5A‚AAA /ሃምሳ ሺህ/ የተቀበሉ መሆኑ” ግራ ቀኙ ተማምነውበታል።
ተጠሪዎች ውሉ ይሰረዝልን በማለት በክስ የጠየቁት ቀሪው ብር 8,000 (ስምንት ሺህ) Aልተከፈለንም በሚል ምክንያት ነው። በውል Aፈፃፀም ሂደት ከተዋዋዮች Aንዱ የውሉን ግድታ ሳይፈጽም የቀረ Eንደሆነ ልላው ወገን Eንደሁኔታው ውሉ Eንዲፈጸምለት መጠየቅ Eንደሚችል ይህም ካልሆነ ውሉ Eንዲሰረዝ ጥያቄውን ማቅረብ Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1771 ላይ ተመልክቷል። የውል ይሰረዝልኝ ጥያቄ ለፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኞች ውሉ ላሰረዝ ይገባል በማለት ውሣኔ ከመስጠታቸው በፊት የተዋዋዮችን ጥቅምና ለቅን ልቦና የሚያስፈልገውን ነገር መሰረት ማድረግ Eንዳለባቸው' በውሉ ላይ ዓይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ተግባር /fundamental breach of contract/ ካልተፈጸመ በስተቀር ዳኞች ውል ይሰረዝ ማለት Eንደልለባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1784 Eና 1785 ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዳይ በቤት ሽያጭ ውሉ መሰረት ለተጠሪዎች መከፈል ከሚገባው ገንዘብ Aብዛኛውን Aመልካቾች Eንደከፈሉ ተረጋግጧል። ከዚህም ውሉ በAመዛኙ Eንደተፈጸመ መገንዘብ ይቻላል። ውሉ ባመዛኙ መፈጸሙ ከተረጋገጠ ደግሞ ዓይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ተግባር ተፈጽሟል ለማለት የማይቻል ከመሆኑም በላይ ከቅን ልቦና መለኪያ Aኳያም ሲታይ ተጠሪዎች በቀሪነት የሚፈለገውን Aነስተኛ ገንዘብ Eንዲከፈላቸው በመጠየቅ ውሉ ውጤት Eንዲኖረው ማድረግ Eየቻሉ Eንዲሰረዝ መጠየቃቸው ተቀባይነት ያለው ምክንያት Aይደለም። የሥር ፍ/ቤቶችም ቀሪው ገንዘብ ባለመከፈሉ ምክንያት የቀረበውን የውል ይሰረዝልኝ ክስ ተቀብለው ውሉ Eንዲሰረዝ መወሰናቸው የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ፍርድ Eንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
43A67 ግንቦት 9 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመv†¨< ስለሆ’< በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽ[ªል።
Aመልካቾች መሰረታዊ የሆነ የውል መጣስ ተግባር ያልፈጸሙ ስለሆነ ከተጠሪዎች ጋር ያደረጉት ውል ላሰረዝ Aይገባም ተብሎ ተወሰኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።