No summary available.
የካቲት 18 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ሰንላይት Iንዱስትሪና ማከፋፈያ ኩባንያ - ነ/ፈጅ ብርሃኑ ወንደሰን ተጠሪ፡- Aቶ ካሣዬ ዘውድ - Aልቀረበም።
ለሰበር Aቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ የጀመረው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ነው። Aመልካች በሥር ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረ ሲሆን ለተጠሪ በሁለት የዱቤ ሰነዶች የውሃ ማሞቂያ መሸጡንና ተጠሪ ግን ለገዙት Eቃ ዋጋቸውን ስላልከፈሉ የEቃዎቹን ዋጋ ብር 44‚93A /Aርባ Aራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ/ ብር Eንዲከፍሉ ጠይቋል። ተጠሪም ክሱን ክደው ተከራክረዋል:: ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በከሣሽና በተከሣሽ መሀከል የተደረገ የሽያጭ ውል Aልቀረበም። የዱቤ ሰነዱ በፍ/ሕ/ቁ. 1685 መሰረት ተጠሪን Aያስገድዳቸውም። የሽያጭ ውል ተያይዞ ባለመቅረቡም ውሉ በከሣሽና በተከሣሽ መሀከል Aለ ለማለት Aይቻልም ሲል የAመልካችን ክስ ውድቅ Aድርጓል። Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍ/ከ/ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል ሰርዞታል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
Aቤቱታው በAጭሩ ሲጠቃለል ሽያጩ የተደረገው በዱቤ ሰነድ /Credit invoice/ ሆኖ ሣለ የዱቤ ሰነዱ ጋር የሽያጭ ውል Aልተያያዘም በማለት ፍ/ቤቱ ክሱን ውድቅ ማድረጉ ስህተት ነው የሚል ነው።
ይህ ችሎትም ከዱቤ ሰነዱ በተጨማሪ ልላ የሽያጭ ውል Aልቀረበም በማለት ክሱ ውድቅ መደረጉ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ቀርቦ Eንዲታይ Aድርጓል። ተጠሪም ቀርበው ለቀረበው ክስ ምንም ዓይነት ማስረጃ ስላልቀረበ ውሣኔው ስህተት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል። ችሎቱም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና Aግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ Eንደሚከተለው መርምሯል።
Aመልካች በሥር ፍ/ቤት ክስ የመሰረተው ተጠሪ በዱቤ ሽያጭ ¾ገዙትƒ ውሃ ማሞቂያ ዋጋ Eንዲከፍሉ ነው። Aንድ ግድታ Eንዲፈፀምለት የሚጠይቅ ሰው ለግድታው መኖር ማስረጃ ማቅረብ Eንዳለበት በፍ/ሕ/ቁ.
2AA1/1/ ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም Aመልካች ተጠሪው ውሃ ማሞቅያውን መግዛታቸውንና ገንዘብ የመክፈል ግድታ ያለባቸው መሆኑን ማስረዳት ይጠበቅበታል። Aንድ ግድታ መኖሩን ለማስረዳት ሕጉ የተለየ ማስረጃ Eንዲቀርብ ያዘዘ ካልሆነ በቀር ግድታ¨< መኖሩን በጽሑፍ በምስክር' በሕላና ግምት' በተከራካሪው ወገን Eምነት ወይም በመሐላ ማስረዳት Eንደሚቻል በፍ/ሕ/ቁ. 2AA2 ሥር ተመልክቷል። በተያዘው ጉዳይ Aመልካች Eንዲያስረዳ የሚጠበቅበት ተጠሪ በዱቤ የውሃ ማሞቂያ ገዝተው የተረከቡ መሆኑን ነው። የውሃ ማሞቂያ ሽያጭ ውል ደግሞ በተለየ ሁኔታ Eንዲደረግ ወይም ውK< ስለመደረጉ የተለየ ማስረጃ Eንዲቀርብ ሕጉ የማያስገድድ በመሆኑ Aመልካች ሽያጩ ለመከናወኑ ማንኛውንም ማስረጃ ማቅረብ ይችላል። በዚህም መሰረት Aመልካች ሽያጭ ለመደረጉ የዱቤ ሰነድ /Credit invoice/ Aቅርቧል። ይህ የዱቤ ሰነድ ግራ ቀኙ ተስማምተው Eስከፈረሙት ድረስ የዱቤ ሽያጭ መከናወኑን ለማስረዳት በቂ ነው። ሕጉ ይህ Aይነቱ ሽያጭ በጽሁፍ Eንዲሆን ስለማያዝም ከዱቤ ሰነዱ በተጨማሪ ልላ የጽሁፍ ውል Eንዲቀርብ የሚጠየቅበት ምክያት Aይኖርም። በSሆኑም የሥር ፍ/ቤት ከዱቤ ሽያጩ ጋር የጽሁፍ ውል ባለመያያዙ ሽያጭ 116 117 ተከናውኗል ማለት Aይቻልም ሲል የደረሰበት መደምደሚያ ስህተት መሆኑን ተገንዝበናል።
በልላ በኩል ግን Aመልካች ሽያጭ መከናወኑን ለማስረዳት vk[u¨< የዱቤ ሰነድ Là የፈረS<ƒ Aመልካችና ልላ Aብይ የተባሉ ግለሰብ Eንጂ ተጠሪ ›ÃÅK<U። በEርግጥ ተጠሪ ፈርመውበት ቢሆን ኖሮ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ ስለሚገኘው የስምምነት ቃልና በላዩ ላይ ስለተፃፈው ቀን በተፈራራሚዎቹ መካከል ሙሉ Eምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ይሆን ነበር /የፍ/ሕ/ቁ. 2AA5/1/ ይመለከቷል/:: በተያዘው ጉዳይ ግን ተጠሪ በሰነዱ ላይ ያልፈረሙ በመሆኑ በሰነዱ ላይ ሰለሰፈረው ጉዳይ ተስማምተዋል ወይም ግድታ ገብተዋል ለማለት Aይቻልም። በዚህ ችሎት በተደረገው የቃል ክርክር Aመልካች ሰነዱ ላይ የፈረሙት ግለሰብ የተጠሪ ወኪል ናቸው ይበM Eንጂ ይህ ክርክር ከስር ያልተነሣ Aዲስ ነገር በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
329/1/ መሰረት ተቀባይነት የለውም።
በመሆኑም Aመልካች ያቀረበው ሰነድ በAመልካችና በተጠሪ መሀከል የዱቤ ሽያጭ ውል መደረጉን Eና በዚህም ምክንያት ተጠሪ የEቃውን ዋጋ የመክፈል ግድታ ያለባቸው መሆኑ” Aያስረዳም። በዚህም ምክንያት ምንም Eንኳን የሥር ፍ/ቤት የAመልካችን ክስ ውድቅ ለማድረግ የሰጠው ምክንያት ስህተት ቢሆንም ክሱን ውድቅ ማድረጉ ግን በAግባቡ ሆኖ Aግኝተነዋል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መጋቢት 5 ቀን 1997 ዓ.ም በመ/ቁ. 11568 የሰጠው ውሣኔ Eና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 38828 ኀዳር 23 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀን}ªል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።